የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ አንቀፅ 63 እና 67 በተከሳሾች ላይ ስላላቸው የደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዛቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓ/ሕግ እና አሸብር ዲጌታ ሄል
No summary available.
ጥቅምት 19 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ሃይለ ነጋሽ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንዶለም አመልካች፡- የደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዛቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓ/ሕግ የቀረበ የለም።
ተጠሪዎች፡- አሸብር ዲጌታ ሄል(42 ሰዎች) መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች ነሐሴ 06 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ሐምል 30 ቀን 2011 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ተጠሪዎች በዋስ ሆነው ጉዲያቸውን እንዱከታተለ በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለቱ ነው።
ጉዲዩ በወንጀል ጉዲይ የተከሰሰን ሰው ዋስትና በሚመለከት የቀረበ ክርክር ነው። የአሁን አመልካች በተጠሪዎች ላይ በስር ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ይዖት በአጭሩ ተጠሪዎች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 32/1/ሀ፤ 35 እና 239 ድንጋጌን በመተላለፍ ሕዲር 20 ቀን 2011 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 3፡30 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት በደቡብ ክልል በቀድሞ ጋሞ ጎፊ ዜን በሳውላ ከተማ አዱሱን የዜን ምስረታ ማብሰሪያ እና ቀደም ሲል ከተለያዩ አመራር እና ከአካባቢ ማሕበረሰብ ጋር የተፈጠረውን ቅሬታ ለመፍታት እንዱሁም በአካባቢው ሰላም እና ቀጣይ ልማት ዘሪያ ውይይት ለማድረግ የክልለ ዳ.ኢ.ህ.ዳን ጽ/ቤት ባስቀመጠው አቅጣጫ እና በተያዖው ፔሮግራም መሰረት በሳውል ከተማ ሚልንየም አዲራሽ በተዖጋጀው ስብሰባ የተለያዩ የፋዳራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የፒርላማ አባላት፣ የክልል ቢሮ ሀላፉዎች የዜን አመራሮች እንዱሁም የተለያዩ ምሁራን እና ግለሰቦች ተጋብዖው በተጠቀሰው ቀን በስብሰባ ቦታ ሁለም ተሰብሳቢዎች በተገኙበት፣ እኛ ባልተገኘንበት ስብሰባ አይደረግም፤
ከተሳታፉ ባለስልጣናት የምንፈልጋቸው ሰዎች አለ በማለት ከጸጥታ ሀይል ቁጥጥር ውጪ በመሆን ወደ ስብሰባ አዲራሽ በመግባት ስብሰባውን በመበተን ተሳታፉዎችን ከስብሰባ አዲራሽ እንዱወጡ አድርገዋል፤ የተሸከርካሪ እንቅስቃሴ እንዲይደረግ መንገድ ዖግተዋል፤ በጸጥታ ሀይልች ላይ ድንጋይ በመወርወር መከላከል እንዲያደርጉ በማድረግ መኪኖችን ሰበረዋል፣ ሱቆችን ሰብረው ዖርፈዋል፤ ንግድ ቤቶች እና የመንግስት መስሪያቤቶች እንዱዖጉ አድርገዋል፤የተፈጠረው ሁከት እና ብጥብጥ የከፊ ውጤት እንዲያስከትል ሲባል በጸጥታ ሀይልች በተወሰደው እርምጃ የሁለት ሰዎች ሕይወት እንዱያልፍ በአምስት ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዲት እንዱደርስ ምክንያት ስለሆኑ በሕብረት በፈጸሙት ሕገመንግስታዊ ስልጣንን ማሰናከል ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
ተከሳሾች ክሱ ከተነበበላቸው በኋላ የተከሰሱበት የሕግ አንቀጽ ከአስራ አምስት አመት በማይበልጥ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ እና የሰው ሕይወት ያለፈው በጸጥታ ሀይልች በተወሰደው እርምጃ በመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63(1)መሰረት የዋስትና መብታቸውን የሚያስከለክል ምክንያት የላለ መሆኑን፤ ምናልባት ፤ ቋሚ አድራሻ ያላቸው እና የቤተሰብ ሀላፉዎች በመሆናቸው ጥቂቶቹ ደግሞ ተማሪዎች በመሆናቸው፤ ምስክሮች ታባብላላችሁ እንዲይባለ ምስክሮች የፕሉስ አባላት በመሆናቸው እና ከመካከላቸው በዋስትና የተለቀቁ ሰዎች መኖራቸው የተከሰሱበት ሕግ ዋስትና የማያስከልከል መሆኑ አመላካች መሆኑን በመግለጽ በዋስ ሆነው እንዱከራሩ ጠይቀዋል።
የአሁን አመልካች ተጠሪዎች ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ በሰጠው አስተያያት ተጠሪዎች የተከሰሱበት የህግ አንቀጽ እስከ አስራ አምስት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ እና በተከሳሾች ቀጥታ ድርጊት ባይሆንም የሁለት ሰዎች ሕይወት ያለፈበት ጉዲይ ስለሆነ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63(1) መሰረት ሉከለከለ ይገባል፤ ፍ/ቤቱ ይህንን በበቂ ምክንያት የሚያልፈው ቢሆን ተከሳሾች ቢለቀቀለ ቀጠሮ አክብረው ሉቀርቡ የማይችለ በመሆኑ፤ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ተቋሙን ሲረብሹ የነበሩ እና በጊዚ ቀጠሮም ፍ/ቤት ሲመላለሱ የሳውላ ከተማ ፕሉሶች ላይ ሲዛቱ ስለነበር በዋስትና ቢለቀቁ ላላ ወንጀል ሉፈጽሙ ስለሚችለ እና ምስክሮች ላይ ተጽእኖ ሉያደርሱ ስለሚችለ የተከሳሾች የዋስትና መብት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 (ሀ)(ለ)እና(ሐ) መሰረት ሉከለከል ይገባል በማለት መልስ ሰጥተዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የተጠሪዎችን የዋስትና ጥያቄ እና አመልካች በጉዲዩ ላይ የሰጠውን አስተያየት ከመረመረ በኋላ ተጠሪዎች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 239 ድንጋጌ የተከሰሱ ሲሆን የፈጠሩት ሁከት እና ብጥብጥ የከፊ ውጤት እንዲያስከትል በጸጥታ ሀይልች በተወሰደው እርምጃ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፍ መንስኤ መሆኑን የሚያሳይ እና ድንጋጌው እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ሉያስቀጣ የሚችል በመሆኑ ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63(1 )መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።
ተጠሪዎች ይህንን ብይን በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል። ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ተጠሪዎች የተከሰሱበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 239 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ 15 ዓመት ሉቀጡ እንደሚችለ መገንዖብ ይቻላል፤ ወንጀል የተፈጸመበት ሰው የሞተ እንደሆነ ከሚለው የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63/1 መመዖኛ ሲታይ በተጠሪዎች በተፈጸመው ሁከት እና ብጥብጥ የከፊ ውጤት እንዲይመጣ ለማስቆም በጸጥታ ሀይልች በተወሰደ እርምጃ የሁለት ሰዎች ሕይወት ያለፈ በመሆኑ ተጠሪዎች በሕይወት ማለፍ ቀጥተኛ በሆነ የግድያ ወንጀል ተጠያቂ አይደለም፤ በሞቱት ሰዎች ላይ ሀላፉነት የላለባቸው እና ተጠያቂነታቸው የሕገመንግስታዊ ስልጣንን ተግባራዊነት ማሰናካል ከሆነ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63/1 በተጠሪዎች ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረው አይደለም፤ ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 አኳያ በተጠሪዎች ላይ ላላ የዋስትና መከላከያ ምክንያት በዓ/ሀግ እስካልቀረበ ድረስ የተከሰሱበት ክስ የዋስትና መብት ይከለክላል መባለ አግባብ አይደለም በማለት ተጠሪዎች እያንዲንዲቸው ለብር 20,000 የዋስትና ግዳታ በመግባት ጉዲያቸውን በውጪ ሆነው እንዱከታተለ ሲል ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም ተጠሪዎች በፈጸሙት የሕገመንግስታዊ ስርዓት ተግባራዊነት ማሰናከል ወንጀል ለማስቆም ሲባል በጸጥታ ሀይልች በተወሰደው እርምጃ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፎል፤ ተጠሪዎች ራሳቸው በቀጥታ ሟቾችን ባይገድለም ተጠሪዎች ሁከት እና ብጥብጥ ባይፈጥሩ ኖሮ የሰው ሕይወት አያልፍም ነበር፤ ተጠሪዎች በፈጸሙት ድርጊት ምክንያት የሰው ሕይወት ያለፈ በመሆኑ በወ/ሕ/ቁ 24/1 መሰረት በምክንያት እና ውጤት መካከል ግንኙነት አለ፤ ተጠሪዎች አስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት ሉያስቀጣ በሚችል ወንጀል የተከሰሱ በመሆናቸው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63/1 መሰረት የዋስትና መብታቸው ሉከለከል ይገባል፤ ይህ ቢታለፍ እንኳን አመልካች በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67/(ሀ)(ለ)(ሐ) መሰረት ተገቢ ምክንያት በመስጠት የተከሳሾች የዋስትና መብት ሉነፈግ ይገባል በማለት መቃወሚያ አቅርቦ ሳለ የስር ፍ/ቤት አይቶ መወሰን ሲገባው ማለፈ አግባብ አይደለም፤ ተጠሪዎች በዋስትና ቢለቀቁ በአካባቢያቸው በከፍተኛ ሁኔታ ሰላም እና መረጋጋትን ወደ ማይመለስ ቀውስ ውሥጥ ሉያስገቡ የሚችለ የተደረጃ ቡድን በመሆናቸው የስር ፍ/ቤት ወሳኔ ተሸሮ ማረሚያ ሆነው ጉዲያቸውን ሉከታተለ ይገባል የሚል ነው። አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልት ላታይ እንደሚገባው ስለታመነበት ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ፣ ለዘህ ሰበር ችልት ያስቀርባል ሲባል ከተያዖው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምረነዋል። እንደመረመርነው በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዖው ነጥብ፤አመልካች በስር ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪዎች የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ በመቃወም የተከራከረው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 እና 63 መሰረት በማድረግ ሲሆን ፍ/ቤቱ አንቀጽ 63ን መሰረት በማድረግ የተጠሪዎችን አቤቱታ ውድቅ ያደረገ ሲሆን ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63 በተከሳሾች ላይ ተፈጻሚነት የለውም በተጠቃሹ ሕግ አንቀጽ 67 መሰረት ምክንያት እስካልቀረበ ድረስ የተከሰሱበት ድንጋጌ የዋስትና መብት አያስከለክልም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር የወሰነበትን አግባብነት ከተጠቀሱት የስነ-ስርዓት ድንጋጌዎች እና ከመሰረታዊ የክርክር አመራር ሥነ-ሥርዓት ጋር በማገናዖብ ለመጣራት በሚል ነው።
በመሰረቱ የዋስትና መብት በሕገ መንግስት ጥበቃ ከተደረጉት የተያዘ ሰዎች መሰረታዊ መብቶች አንደ ነው። የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 19/6/ ስር የተያዘ ሰዎች በዋስትና የመፈታት መብት ያላቸው መሆኑን በመርህ ደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን ይህ በሕገ መንግሥቱ የተከበረው መሰረታዊ መብት ሉነፈግ፣ ሉገደብ ወይም በቂ የሆነ የዋሰትና መረጋገጫ እንዱቀርብ የሚደረገውም አግባብነት ባላቸው ላልች ዛርዛር ሕጎች መሰረት በልዩ ሁኔታ ስለመሆኑ ይኸው የሕገ መንግስቱ ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል። በመሆኑም የዋስትና መብት መሰረታዊ የሆነ ሕገ መንግስትዊ መብት ቢሆንም ፍጹም መብት ሳይሆን በሕጉ አግባብ ሉነፈግ የሚችል ነው። ስለሆነም የዋስትናው ጥያቄ ተቀባይነት አለው ወይም የለውም የሚለው ላይ ውሳኔ የሚሰጠው ፍርድ ቤት እንደመሆኑ መጠን በዘህ ረገድ አግባብነት ያለውን ልዩ ሕግ መሰረት አድርጎ ጉዲዩን ሉመዛነውና ተገቢውን ውሳኔ ሉልሰጥ እንደሚገባ ግልጽ ነው።
በያዛነው ጉዲይ በስር ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪዎች የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ የተደረገው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63 ‛ን“ መሰረት በማድረግ የተጠሪዎችን አቤቱታ ውድቅ ያደረገ ሲሆን ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63 በተከሳሾች ላይ ተፈጻሚነት የለውም በተጠቃሹ ሕግ አንቀጽ 67 መሰረት ምክንያት እስካልቀረበ ድረስ የተከሰሱበት ድንጋጌ የዋስትና መብት አያስከለክልም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር ውሳኔ ሰጥቷል።በስር ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪዎች ፈጽመውታል የተባለው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 239 ድንጋጌን በመተላለፍ የሕገመንግስታዊ ሥልጣንን ተግባራዊነት ማሰናከል ወንጀል ምክንያት በተፈጠረው ሁከት እና ብጥብጥ የከፊ ውጤት እንዲይመጣ ለማስቆም ሲባል በጸጥታ ሀይልች በተወሰደው እርምጃ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፈ የሚመለከት ነው።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአመልካች አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ተጠሪዎች ዋስትና መብት እንዱከበርላቸው ውሳኔ የሰጠው የቀረበው ክስ የዋስትና መብት የማያስከለክል በመሆኑና በተፈጠረው ሁከት እና ብጥብጥ የከፊ ውጤት እንዲይመጣ ለማስቆም ሲባል በጸጥታ ሀይልች በተወሰደው እርምጃ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፈ ተጠሪዎችን ቀጥተኛ በሆነ የግድያ ወንጀል የማያስጠይቃቸው በመሆኑ የወ/መ//ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63/1 በተጠሪዎች ላይ ተፈጻሚነት የለውም በማለት ነው።
በመሰረቱ ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63/1 ይዖት ለመረዲት እንደሚቻለው ማንኛውም የተያዖ ሰው የተከሰሰበት ወንጀል የሞት ቅጣትን ወይም አሥራ አምሥት ዓመት ወይም በላይ በሆነ ጽኑ እስራት የማያስቀጣው ከሆነና ወንጀል የተፈጸመበት ሰው በደረሰበት ጉዲት የማይሞት የሆነ እንደሆነ ፍ/ቤቱ የዋስትና ወረቀት አስፈርሞ ለመልቀቅ ይችላል በማለት ይደነግጋል ። ከድንጋጌው ይዖት መገንዖብ የሚቻለው ተከሳሹ የተከሰሰበት የሕግ አንቀጽ በሞት ወይም ከ15 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ እና ጉዲት የደረሰበት ሰው የሞተ እንደሆነ በዋስትና መልቀቅ የማይቻል መሆኑን ፤ሆኖም ተከሳሹ የተከሰሰበት የሕግ አንቀጽ በሞት ወይም ከ15 ዓመት እና በላይ የማያስቀጣ እና ጉዲት የደረሰበት ሰው ያልሞተ እንደሆነ ተከሳሹን በዋስትና መልቀቅ የሚቻል መሆኑን ነው።
በያዛነው ጉዲይ ተጠሪዎች የተከሰሰበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 239 ድንጋጌን በመተላለፍ ሆኖ ድንጋጌው እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት የሚያስቀጣ ቢሆንም በተጠሪዎች ተግባር የሞተ ሰው ስላለ እና ሞቱ የተባለት ሁለት ሰዎች በልላ አካል በተወሰደ እርምጃ መሞታቸው የተረጋገጠ መሆኑ በዘሁ ጉዲይም በተጠሪዎች ላይ ክስ ያልቀረበና በዓ/ህግ በኩል ያልተገለፀ በመሆኑ፣ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 63/1 የተመለከቱት ተከሳሹ የተከሰሰበት የሕግ አንቀጽ በሞት ወይም ከ15 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ እና ጉዲት የደረሰበት ሰው የሞተ እንደሆነ የሚለት ቅድመ ሁኔታዎች አልተሟለም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63/1 ላይ የተመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎች አልተሟለም በማለት ከድምዲሜ ላይ መድረሱ በአግባቡ ነው ብለናል። በተመሳሳይ ጉዲዮች ላይ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2 መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሰጠው የህግ ትርጉም ለዘህ ጉዲይ ተፈፃሚነት እንዲለው ተመልክተናል።
አመልካች የተከሳሾች የዋስትና መብት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 (ሀ)(ለ)እና(ሐ) መሰረት ሉከለከል ይገባል በማለት ያቀረበው ክርክር በተመለከተ ጉዲዩ በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ላይ ክርክር ያልቀረበበት መሆኑ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ዋና መዛገብ በማስቀረብ ያረጋገጥን በመሆኑ ፍርድቤቱ ‛በወ/መ/ሥ/ሥ/ግ/ቁ 67 መሰረት የዋስትና መከልከያ ምክንያት እስካልቀረበ ድረስ‛ በማለት የገለፀው ሲታይ አመልካች በስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ባልተከራከረበት ጉዲይ የተጠሪዎች የዋስትና መብት ለመከልከል የቀረበ አዱስ ክርክር በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም ስለሆነም የስር ፍ/ቤቱ የተጠሪዎችን የዋስትና መብት እንዱከበርላቸው እና ተጠሪዎች በዋስ ሆነው ጉዲያቸውን እንዱከታተለ በማለት የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው ብለናል።
በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 19/6/ እና በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 63 እና 67 መሰረት በማድረግ የሰጠው ብይን ሕጉ የሰጠውን ሥልጣን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር በህግ አተረጓጏምና አተገባበር ረገድ መሰረታዊ ሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዘህም መሰረት በአብላጫ ድምፅ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
1/ በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 30/11/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የተሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 75/2/ መሰረት ፀንቷል።
2 / ነሃሴ 10 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችልት በተሰጠ የእግድ ትእዙዛ ተጠሪዎች በነበሩበት ማረምያ ቤትሆነው ጉዲያቸው እንዱከታተለ ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል።ለሚመለከተው አካል ይፃፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል።ወደመዛገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
ቤ/ፍ የማይነበብ የአራት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.