አንድ ተከሳሽ በጋዚጣ ጥሪ ተደርጎለት ክስ የቀረበበት ስለመሆኑ አውቋል የሚል ግምት ሉወሰድ የሚገባው ሐገር አቀፍ ስርጭት ባለው ጋዚጣ ጥሪ የተደረገለት መሆኑ በተረጋገጠ ጊዚ እንጂ በአንድ ክልል ብቻ ተደራሽ በሆነ ጋዚጣ ብቻ ጥሪ መደረጉን መጥሪያ እንደደረሰው ማረጋገጫ አድርጎ በመውሰድ እና መጥሪያ ደርሶታል የሚል ግምት በመውሰድ ጉዲዩን ተከሳሹ በላለበት አይቶ ውሳኔ መስጠት በሕገ-መንግስቱ ለተከሰሱ ሰዎች የተጠበቁላቸውን መሰረታዊ መብት የሚነካ ስለመሆኑ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 161፣199(ሀ) የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ
No summary available.
መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሾሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡- አቶ አማኑኤል ገ/ጊዮርግስ ተጠሪዎች፡- የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕግ መዛገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 07 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ምዔራባዊ ዜን የሽሬ እንዲስላሴ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. መጋቢት 05 ቀን 2011 ዓ.ም አመልካች በላለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ሉነሳ አይገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
ጉዲዩ በወንጀል ጉዲይ በላለሁበት ታይቶ የተሰጠ ውሳኔ ይነሳልኝ በሚል የቀረበን ክርክርን የሚመለከት ነው። የአሁን ተጠሪ አመልካች የአዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 4/5 ድንጋጌን በመተላለፍ ሕገወጥ ማንቀሳቀሻ በተጭበረበረ ሰነድ መስራት ወንጀል ፈጽሟል በማለት ያቀረባቸውን ስድስት ክሶች የተመለከተው በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ምዔራባዊ ዜን የሽሬ እንዲስላሴ ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ተፈልጎ በአድራሻው ሉገኝ ስላልቻለ በመቃልህ ጋዚጣ ጥሪ ተደርጎለት ስላልቀረበ በላለበት ጉዲዩን በማየት በተከሰሰበት የሕግ አንቀጽ ጥፊተኛ በማለት በ18 ዓመት ጽኑ እሥራት እንዱቀጣ ሲል ወስኗል።
አመልካች ውሳኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት ባቀረበው አቤቱታ በላለበት ታይቶ የተሰጠውን ውሳኔ ያወቀው በቀን 23/05/11 ዓ/ም በሕመም ምክንያት አዱስ አበባ በነበሩበት ጊዚ መሆኑን፤ በጊዚ ቀጠሮ ጊዚ ዋስ የሆኗቸው ግለሰብ በሽሬ ከተማ የሚገኙ ቢሆንም አመልካችን እንዱያቀርቡ ያልተጠየቁ መሆኑን፤
በላለበት ጉዲያቸው እንዱታይ የተደረገው ከትግራይ ክልል ውጪ ሽፊን በላለው በመቃልሕ ጋዚጣ መሆኑን በመግለጽ በላለበት ታይቶ የተሰጠው ፍርድ ተሰርዜ ጉዲያቸው ባለበት እንዱታይ አቤቱታ አቅርበዋል።
ፍ/ቤቱም ተጠሪ በጉዲዩ ላይ አስተያየት እንዱሰጥበት ካደረገ እና የአመልካችን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ምስክሮቹ አመልካች በሐምል ወር 2008 ዓ.ም ወደ አዱስ አበባ ሄድ የታከመ እና ኒሞኒያ የተገኘበት መሆኑን፤ በኋላም እስከ 2009 ዓ/ም ድረስ ቆይቶ ለስራ ወደ ደባይ የሄደ እና በ2010 ዓ.ም ወደ መቀላ ተመልሶ እስከ ሚያዛያ ወር ድረስ ይኖር እንደነበር አስረድተዋል፤ ይህንኑ የሚያሳይ የሕክምና ማስረጃም ቀርቧል፤ አመልካች መጀመሪያ ክስ ቀርቦበት በመደበኛ መጥሪያ እንዱቀርብ ፕሉስ በቀጠሮ እንዱቀርብ ያዖዖው መሆኑን ለፍ/ቤቱ በጻፈው ምላሽ አሳውቋል፤ አመልካች የክስ ቻርጅ ደርሶት በመጥሪያ ሳይቀርብ በመቅረቱ ፕሉስ በእስር እንዱያቀርበው ከታዖዖ ጠፍቶ እንደተሸሸገ መረዲት ይቻላል፤ የክፍለ አስተዲደር ጽ/ቤት አመልካች በአድራሻው እንደላለ የገለጸ በመሆኑ አመልካች በመቃልህ ጋዚጣ ጥሪ ተደርጎለታል፤ አመልካች ባስመዖገበው ቀበላ እንደላለ ተረጋግጦ ፍ/ቤቱ በምትክ መጥሪያ አጠራር ስርዓት አመልካችን በሚጠቅም መንገድ የጋዚጣ ጥሪ ያደረገለት እና ያልቀረበ በመሆኑ ፍ/ቤቱ የፈጸመው የስነ ስርዓት ስሕተት የለም በማለት የአመልካች አቤቱታው ውድቅ በማድረግ ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- የስር ከፍተኛው ፍ/ቤት ፕሉስ መጥሪያ ሰጥቸዋለሁ ብል ወረቀት ስለጻፈ መጥሪያ ደርሶሃል ቢልም ፕሉስ አልነገረኝም፤ አመልካች የፈረምኩበትንም ማስረጃ አላቀረበም፤ ፕሉስ ነግሬዋለሁ ብቻ ማለቱ እንደነገረኝ ማረጋገጫ አይደለም፤ በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 125 በግልጽ እንደተደነገገው ተከሳሽ በእስር እንዱቀርብ ትዔዙዛ የሚሰጠው ተከሳሹ ፍርድ ቤት እንዱቀርብ መጥሪያ እንደደረሰው ማረጋገጫ ከቀረበ በኋላ ነው፤ ፕሉስ በእስር እንዱያቀርበኝ በፍ/ቤት ሲታዖዛ በእስር እያቀረብኩት ነው ብል በቀን 3/01/2009 ምላሽ የሰጠ ቢሆንም ይህን ምላሽ የሰጠው አመልካችን ሳይዛ ነው፤ ፕሉስ የፍ/ቤቱን ትዔዙዛ ለአመልካች ነግሬአለሁ ባለበት ሰዓት አመልካች በሽሬም ከተማ ሆነ በትግራይ ክልል አልነበርኩም፤ አመልካች በወቅቱ አዱስ አበባ ውስጥ እንደነበርኩ ባቀረብኳቸው ማስረጃዎች ያስረዲሁ ቢሆንም የስር ከፍተኛው ፍ/ቤት ይህን ማስረጃ ሳይመዛን አልፍታል፤ በመሆኑም የስር ፍ/ቤት የአመልካች ማስረጃዎች በአግባቡ ሳይመዛን የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት መጥሪያ ለአሁን አመልካች በቀጥታ መድረሱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ፕሉስ አመልካች ወደ ፍ/ቤት እንዱቀርብ ነግሬዋለሁ በማለት ሪፕርት ማድረጉን መሰረት በማድረግ እና በጋዚጣ መጥሪያ መውጣቱን በቂ አድርጎ በላለበት የተሰጠው ውሳኔ ሉነሳ አይገባም በማለት የመወሰኑን አግባብነት ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 125 ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ፡- ፕሉስ ለፍ/ቤቱ በሰጠው ምላሽ አመልካች በቀጠሮው ቀን እንዱቀርብ የተነገረው መሆኑን ምላሽ ገልጿል፤ ፍ/ቤቱም አመልካች እንዱቀርብ መጥሪያ ደርሶት ስላልቀረበ ታስሮ እንዱቀርብ ትዔዙዛ ከሰጠ በኋላ የክፍለ አስተዲደር ጽ/ቤት አመልካች ባስመዖገበው አድራሻ እንደላለ በመግለጽ ምላሽ ልኳል፤ አመልካች በመቃልህ ጋዚጣ ጥሪ ተደርጎለት ላቀርብ ስላልቻለ ጉዲዩ በላለበት ታይቶ የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ተላልፍበታል፤ ፕሉስ የፍ/ቤቱን ትዔዙዛ ለአመልካች እንደነገረው ምላሽ የሰጠ በመሆኑ መልስ የላከ በመሆኑ አመልካች ከፍትሕ ራሱን ደብቆ ተሸሽጎ እንደነበር የሚያመለክት ነው፤ አመልካች በሕክምና ላይ እንደቆየ ለማሳየት ያቀረባቸው ማስረጃዎች ጉንፊን እና ኒሞንያ በሽታ እንዲለበት ከሚያሳዩ በቀር በጤና ጣቢያው ተኝቶ ታካሚ እንደነበር አያሳዩም፤ አመልካች በትግራይ ክልል ባለ ሆስፑታልች ሕክምና ማግኘት ይችል ነበር፤ የአመልካች ምስክሮች ዖመድቹ በመሆናቸው ገለልተኛ ምስክሮች አይደለም፤ የስር ፍ/ቤት መጥሪያ አደራረስን አስመልክቶ የፈጸመው የስነ ስርዓት ስሕተት ስለላለ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዖውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
አመልካች ካቀረበው አቤቱታ እና የስር ፍ/ቤት ለውሳኔው መሰረት ካደረጋቸው ነጥቦች አንጻር የዘህን ችልት ምላሽ የሚፈልገው የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ የስር ፍ/ቤት አመልካች በላለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ እንዱነሳለት እና ጉዲዩ ባለበት እንዱታይ ያቀረበውን አቤቱታ ፕሉስ የፍ/ቤቱን ትዔዙዛ ለአመልካች የነገረው መሆኑን አሳውቋል፤ የክፍለ አስተዲደር አመልካች ባስመዖገበው አድራሻ የላለ መሆኑን በመግለጽ ምላሽ ሰጥቷል፤ ፍ/ቤቱ አመልካችን በሚጠቅም መልኩ በምትክ መጥሪያ አደራረስ በመቃልህ ጋዚጣ እንዱጠራ አድርጎ አመልካች ባለመቅረቡ በላለበት እንዱታይ ማድረጉ የፈጸመው የስነስርዓት ስሕተት የለም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉ በአግባቡ ነዉ? ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
በመሰረቱ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 161 የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው አንድ ክስ ተከሳሽ በላለበት ነገሩ እንዱሰማ ፍ/ቤቱ ትዔዙዛ የሰጠ እንደሆነ የፍ/ቤቱ ትዔዙዛ ተከሳሹ የተከሰሰበት ወንጀል ዛርዛር፤ ነገሩ እንዱሰማ በተቀጠረበት ቀን ተከሳሹ ሳይቀርብ ቢቀር በላለበት የሚፈረድ መሆኑን የሚገልጽ የመጥሪያ ማስታወቂያ በጋዚጣ እንዱወጣ ወይም ለተከሳሹ የሚደርስ መስል ከታየዉ መጥሪያዉ የሚደርስበትን ላላ መንገድ ፍርድ ቤቱ ሉያዛ እንደሚችል በዘሁ ሕግ ቁጥር 162 ላይ በግልጽ ተመልክቷል። በዘህ ድንጋጌ መሰረት የሚደረግ የጋዚጣ ጥሪም ጉዲዩን አመልካች በላለበት ለማየት የሚያስችል ቅድመ ሁኔታ ነው። ይህን ሥርዓት ተከትልና በዘሁ ሕግ ቁጥር 163(3) መሰረት እንደ ማንኛዉም ደንበኛ ክስ ታይቶ ፍርድ የተሰጠ እንደሆነ በሕጉ ቁጥር 197 እስከ 202 በተመለከቱት ምክንያቶች ፍርደ ዉድቅ እንዱደረግ ተከሳሹ ማመልከቻ ማቅረብ እንደሚችል በቁጥር 164 ተመልክቷል። ተከሳሹ በላለበት የተሰጠው ፍርድ ውድቅ ተደርጎ ጉዲዩ እንደገና እንዱታይ ያቀረበው ማመልከቻ የሚፈቀደው እንዱቀርብ መጥሪያ ያልደረሰዉ እንደ ሆነ ወይም ራሱ ወይም ጠበቃዉ ከዐቅም በላይ በሆነ ኃይል ምክንያት መቅረብ አለመቻለን ያስረዲ እንደ ሆነ ነዉ በማለት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 199 ላይ ተደንግጓል።
በያዛነው ጉዲይ የስር ፍ/ቤት ፕሉስ የፍ/ቤቱን ትዔዙዛ ለአመልካች የነገረው መሆኑን ለፍ/ቤቱ ያሳወቀ መሆኑን እና የክፍለ አስተዲደር አመልካች ባስመዖገበው አድራሻ የላለ መሆኑን በመግለጽ ምላሽ የሰጠ መሆኑን በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ በግልጽ ሰፍሯል። በአመልካች ላይ የቀረበው ክስ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 161 ላይ በተመለከቱት ሁኔታዎች በላለበት የሚታይ ከመሆኑ አኳያ ፍ/ቤቱ በቀጣይነት አመልካች በጋዚጣ ጥሪ እንዱደረግለት ትዔዙዛ መስጠቱ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 162 አግባብ የተሰጠ በመሆኑ በዘህ ረገድ ፍ/ቤቱ የፈጸመው ስሕተት የለም። ሆኖም ፍ/ቤቱ ለተከሳሽ የጋዚጣ ጥሪ ያስተላለፈው በመቃልህ ጋዚጣ ከመሆኑ አኳያ ተከሳሹ በላለበት ታይቶ የተሰጠው ፍርድ እንዱነሳለት የሚያቀርበው ማመልከቻ ስለሚፈቀድባቸው ምክንያቶች አስመልክቶ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 199 (ሀ) ላይ ‛መጥሪያዉ ያልደረሰዉ እንደሆነ“ በማለት ከተቀመጠው መስፈርት እና የተከሰሱ ሰዎች በሕገመንግስቱ ከተጠበቁላቸው መሰረታዊ መብቶች ገር በማገናዖብ ምላሽ ሉሰጠው የሚገባ የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ ነው።
የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20/4 የተከሰሱ ሰዎች ጉዲያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ በችልት ተገኝተው የቀረበባቸውን ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረበባቸውን ምስክሮችን የመጠየቅ፣ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዱሁም ምስክሮቹ ቀርበዉ እንዱሰሙላቸው የመጠየቅ መብት አላቸው። ከዘህ ሕገ-መንግስታዊ ድንጋጌ ይዖት መገንዖብ የሚቻለዉ የወንጀል ጉዲዮች ተከሳሽ በተገኘበትና የመከላከል መብቱ በተጠበቀበት ሁኔታ ማካሄድ መርሁ ሲሆን ልዩ ሁኔታው ደግሞ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 161 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት አንድ ጉዲይ ተከሳሽ በላለበት ታይቶ በተወሰነ ጊዚ በመርሁ የተቀመጠዉን የተከሳሽን የመከራከር መብት ለማረጋገጥ ሲባል ፍርደ እንደገና ተነስቶ ጉዲዩ እንደገና የሚታይበት ስርዓት በቁጥር 197 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች የተቀመጠ በመሆኑ በተቻለ መጠን ተከሳሹ በእርግጠኝነት መጥሪያ ደርሶት በችልት የመገኘትና የመከራከር መብቱን አዉቆ መተዉ እስካልተረጋገጠ ድረስ ይህ መብቱ ሉነፈግ አይገባም። በመሆኑም በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 199 (ሀ) ላይ ‛መጥሪያዉ ያልደረሰዉ እንደሆነ“ በሚል የተቀመጠውን መስፈርት መሰረት በማድረግ ተከሳሹ በላለበት ታይቶ የተሰጠው ፍርድ እንዱነሳ ባመለከተ ጊዚ ከሳሽ የሆነው ዓቃቤሕግ ተከሳሹ የፍ/ቤቱን መጥሪያ ሰምቶ ያልቀረበ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ ያለበት ሲሆን ፍ/ቤቱም ይህንን የማረጋገጥ ሀላፉነት አለበት።
ስለሆነም ከላይ ከተገለጹት ድንጋጌዎች እና ምክንያቶች አንጻር የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 199(ሀ) ተከሳሹ በትክክል መጥሪያ ደርሶት የመከራከር መብቱን አዉቆ በመተዉ መቅረቱ አሻሚ ባልሆነ መልኩ ዐ/ሕግ በሚያቀርበዉ በቂ ማስረጃ ካልተረጋገጠ በቀር ማወቅ ነበረበት ወይም ሉያዉቅ ይችላል የሚል ግምት በመዉሰድ ተከሳሹ በላለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ጉዲዩ ባለበት እንዱታይ ያቀረበዉ ማመልከቻ ዉድቅ ላደረግ አይገባም።
በተያዖዉ ጉዲይ የስር ፍ/ቤት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ያደረገዉ አመልካች በአገር ዉስጥ አለመኖሩ ተረጋግጦ በምትክ መጥሪያ አጠራር ስርዓት በመቃልህ ጋዚጣ ጥሪ ተደርጎለት ያልቀረበ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ተከሳሽ በላለበት ጉዲዩን አይቶ መወሰኑ የፈጸመው የስነስርዓት ስሕተት የለም በሚል ነዉ።
ሆኖም አመልካች ጥሪ የተደረገለት በክልለ ብቻ ተደራሽ በሆነው መቃልህ ጋዚጣ እንጂ ሐገር አቀፍ ስርጭት ባለው ጋዚጣ አይደለም፤ ዓቃቤሕግ ባቀረበው ክርክርም ለአመልካች ጥሪ የተላለፈበት መቃልህ ጋዚጣ ሐገር ዓቀፍ ስርጭት ያለው ስለመሆኑ አላረጋገጠም፤ ይልቁንስ አመልካች ባቀረባቸው ማስረጃዎች በጤና ችግር ምክንያት ከክልለ ውጪ እንደነበር በኋላም በስራ ምክንያት ከኢትዮጲያ ውጪ እንደነበር አስረድቷል። አንድ ተከሳሽ በጋዚጣ ጥሪ ተደርጎለት ክስ የቀረበበት ስለመሆኑ አውቋል የሚል ግምት ሉወሰድ የሚገባው ሐገር አቀፍ ስርጭት ባለው ጋዚጣ ጥሪ የተደነገለት መሆኑ በተረጋገጠ ጊዚ እንጂ በክልለ ብቻ ተደራሽ በሆነው ጋዚጣ ብቻ ጥሪ መደረጉ ተከሳሹ ክስ እንደቀረበበት አውቋል የሚል ግምት የሚያስወስድ አይደለም።
በመሆኑም የስር ፍ/ቤት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 162 ተከሳሹ በላለበት ነገሩ እንዱሰማ ፍ/ቤቱ ትዔዙዛ ለመስጠት የሚችልበትን ቅድመ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ሐገራዊ ስርጭት በላለው መቃልህ ጋዚጣ ለአመልካች ጥሪ ማስተላለፈን ለአመልካች መጥሪያ እንደደረሰው ማረጋገጫ አድርጎ በመውሰድ እና መጥሪያ ደርሶታል የሚል ግምት በመውሰድ አመልካች በላለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ጉዲዩ ባለበት እንዱታይ ያቀረበውን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 199(ሀ) ድንጋጌ ይዖትና በሕገመንግስቱ ለተከሰሱ ሰዎች የተጠበቁላቸውን መሰረታዊ መብቶች ያላገናዖበ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ምዔራብ ዜን የሽሬ እንዲስላሴ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. መጋቢት 15 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና መጋቢት 19 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ እንዱሁም መጋቢት 05 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሸሯል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት የስር ፍ/ቤት አመልካች በላለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ጉዲዩ ባለበት እንዱታይ ያቀረበውን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ነው በማለት ክርክሩ አመልካች ባለበት ታይቶ ውሳኔ እንዱያገኝ በማለት ወስነናል።
የሽሬ እንዲስላሴ ከፍተኛ አመልካች ባለበት ክርክሩን ቀጥል ተገቢውን እንዱወስን በማለት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ
No topics extracted.