የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 ድንጋጌ እና የሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 881/2007 መሰረት ዓቃቤ ሕግ መደበኛውን የወንጀል ሕግ ወይም ወንጀል መፈጸሙን ለማስረዲት ልዩ መስፈርትን የማያስቀምጡ ልዩ ሕጎችን መሰረት በማድረግ ክስ ሲያቀርብ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 መሰረት የአንድ ተከሳሽን የሀሳብ ክፍል እንዱያረጋግጥ የተጣለበት የማስረዲት ሸክም ለሙስና ወንጀልች በተመሳሳይ ተፈጻሚ የማይሆን ስለመሆኑ እና በሙስና ወንጀልች አዋጅ በተደነገገው መሰረት ግዘፊዊ ፍሬነገር መፈጸሙ በተረጋገጠ ጊዚ ተከሳሹ በድንጋጌው የተመለከተውን ግዘፊዊ ፍሬነገር ለመፈጸም የነበረውን የሀሳብ ክፍል ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ እንዱያስተባብል የማስረዲት ሸክሙ ወደ ተከሳሹ የሚዙወር ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀጽ 23/2/፣የሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 881/2007አንቀጽ 3 ፣አንቀጽ 13/3 እና 13/1/ እነ አቶ መሐመድ ያዔቆብ ከድር አልይዖአ እና የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጸረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤሕግ
No summary available.
መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡-
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካቾች በጠበቆቻቸው አማካኝነት ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ.ም ተጽፍ በቀረበ የሰበር አቤቱታ በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የባላ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. አመልካቾች ያቀረብነውን መቃወሚያ በማለፍ የሰጠው ብይን፤ በዘሁ መዛገብ በቀን 10/01/2010 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና በቀን 11/01/2010 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤
ይህን ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. በቀን 21/09/2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት በመጠየቃቸው ነው።
ጉዲዩ የሙስና ወንጀልን በሚመለከት የቀረበ ክርክር ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የባላ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። የአሁን ተጠሪ በስር ፍ/ቤት አመልካቾችን ጨምሮ በ38 ተከሳሾች ላይ ክስ ያቀረበ ሲሆን የአሁን አመልካቾች እንደ ቅደም ተከተላቸው 1ኛ፤ 2ኛ፤
3ኛ፤ 4ኛ፤ 5ኛ፤ 6ኛ፤ 7ኛ፤ 8ኛ፤ 9ኛ፤ 12ኛ፤13ኛ፤14ኛ፤16ኛ፤19ኛ እና 21ኛ ተከሳሾች ነበሩ። የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች እና ለዘህ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ባላቀረቡ ቀሪ ተከሳሾች ላይ በስር ተከሳሾች ላይ በስር ፍ/ቤት ያቀረባቸው ክሶቸ 11 ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ስድስቱ ክሶች አመልካቾችን የሚመለከቱ ናቸው። ይዖታቸውም፡- 1ኛ ክስ፡- አመልካቾች እና የስር 10ኛ፤11ኛ፤15ኛ እና 20ኛ ተከሳሾች የሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9/3 ድንጋጌን በመተላለፍ የሮቤ ከተማ ማኔጅመንት፤ የሮቤ ከተማ መሬት አስተዲደር እና ማኔጅመንት ሆነው ሲሰሩ የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት ወይም በመንግስት እና በሕዛብ ጥቅም ላይ ጉዲት ለማድረስ አስበው አመልካቾች እና የስር 10ኛ፤11ኛ፤15ኛ ተከሳሾች በቀን 01/10/2007 ዓ.ም ቃለጉባኤ በመያዛ፤ የስር 10ኛ፤ 11ኛ እና 20ኛ ተከሳሾች እንዱሁም የአሁን 14ኛ እና 15ኛ አመልካቾች በያዘት ቃለጉባኤ መሬት የመንግስት እና የኢትዮጵያ ሕዛቦች ሐብት እና የማይሸጥ የማይለወጥ መሆኑን እያወቁ፤ የገጠር መሬት ወደ ከተማ መሬት ሲካለል በፋዳራል አዋጅ 455/97 ፤ 721/2004፤ በኦሮሚያ የመሬት አዋጅ ቁጥር 130/99፤
ደንብ ቁጥር 155/2005 እና መመሪያ ቁጥር 9/2005 መሰረት መፈጸም እንዲለበት እያወቁ ሕግ የሚፈቅድላቸው በማስመሰል በከተማ ስር የገባውን የገጠር መሬት 45% መሬት የገበሬ ነው፤ 55% መሬት ደግሞ የመንግስት ነው ተብል ተከፊፍል የቆየ እና ይህን መሬት ገበሬው በሽያጭ ሲያስተላልፍ የቆየ መሆኑን በያዘት ቃለጉባኤ ገልጸው እያለ ሕገወጥ ግንባታ እና የድሮ ይዜታ በማስመሰል ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም ስፊቱ 247,161 እና 997 ፔልት መሬት 76 ለሆኑ ገበሬዎች በመስጠት ለእነዘህ ገበሬዎች በሕጉ አግባብ ለእያንዲንዲቸው 500 ካ.ሜ መሬት ተስጥቷቸው ቢሆን ኖሮ ስፊቱ 894,970 እንዱሰጥ በማድረግ መንግስት ሉያገኝ የሚችለው ገቢ 199,277.70 ስላሳጡት ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
2ኛ ክስ፡- አመልካቾች እና የስር 10ኛ፤11ኛ፤15ኛ ተከሳሾች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13/3 በመተላለፍ በ1ኛው ክስ ውስጥ በተወሰነው ውሳኔ መሰረት ቁጥራቸው 308 ለሆኑ ሰዎች በድምሩ ስፊቱ 120,000 የሆነ መሬት እንዱሰጥ በመወሰን፤ 1ኛ እና 11ኛ ተከሳሾች፤ 14ኛ አመልካች እና የስር 36ኛ ተከሳሽ ደግሞ መሬት በወሰደ እና በከተማው አስተዲደር መካከል የተደረገውን ሕገወጥ ውል በማጽደቅ፤ 27ኛ፤ 28ኛ እና 29ኛ ተከሳሾች በሕገወጥ በተላለፈው በዘህ መሬት ላይ ካርታ በማዖጋጀት፤
የስር 10ኛ፤ 11ኛ፤ 23ኛ እና 36ኛ ተከሳሾች እና 13ኛ እና 14ኛ አመልካቾች ደግሞ በሕገወጥ መንገድ በተሰጠ መሬት ላይ የተዖጋጀን ካርታ በማጽደቅ፤16ኛ አመልካች እና 20ኛ፤ 24ኛ፤ 26ኛ፤ 28ኛ፤ 30ኛ፤
31ኛ፤ 38ኛ ተከሳሾች ሕገወጥ የሆነን ቅጽ በመሙላት፤ በአጠቃለይ ተከሳሾች በጋራ በመሆን ሕዛብና መንግስት እኩል ሉጠቀሙበት የሚገባውን ይዜታ ሕግ እና መመሪያ በመተላለፍ ስፊቱ 65,755 የሆነ መሬት ለግለሰቦች እንዱሰጥ በማድረግ መንግስት ሉያገኝ የሚገባውን ገቢ 14,624,569.75 አሳጥተዋል የሚል ነው።
3ኛ ክስ፡- 17ኛ እና 18ኛ ተከሳሾች የአዋጁን አንቀጽ 9/1/ለ ድንጋጌ በመተላለፍ በ1ኛው ክስ በቀን 01/07/07 እና 03/09/07 በያዘት ቃለጉባኤ ሕገወጥ የመሬት አሰጣጡን ስራ ላይ የማዋል ድርጊት በመገምገም ሕገወጥ ስራው እንዱቀጥል አድርገዋል የሚል ነው።
4ኛው ክስ፡- 1ኛ እና 8ኛ አመልካቾች እንዱሁም 10ኛ፤17ኛ እና 18ኛ ተከሳሾች የኦሮሚያ ከተማ መሬቶችን በሉዛ ለማስተዲደር የወጣውን ደንብ ቁጥር 155/2005 አንቀጽ 59/1 ድንጋጌን በመተላለፍ በ3ኛ ክስ የተገለጸውን ቃለጉባኤ በመያዛ ሕገወጥ የሆነውን 45/55 ተብል የሚታወቀውን አሰራር በስራ ላይ እንዱውል አድርገዋል የሚል ነው።
5ኛ ክስ፡- 10ኛ፤ 11ኛ፤ ፤20ኛ ተከሳሾች፤ 14ኛ እና 15ኛ አመልካቾች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9/3 ድንጋጌን በመተላለፍ የሮቤ ከተማ አስተዲደር እና ማኔጅመንት ኮሚቴዎች በመሆን እና 17ኛው ተከሳሽ የገቢዎች የባለስልጣን ሀላፉ በመሆን የሙስና ወንጀልችን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9/3 በመተላለፍ 10ኛ፤11ኛ፤20ኛ ተከሳሾች እና 14ኛ እና 15ኛ አመልካቾች በቀን 14/09/2007 በያዘት ቃለጉባኤ ገበሬዎች ከድርሻቸው መሬት ላይ የሸጡትን ይዜታ የድሮ ይዜታ በማስመሰል ክፍያ እንዱፈጸምበት በመወሰን ለገቢዎች ባለስልጣን በመላክ፤ 17ኛው ተከሳሽ በተለያዩ ጊዚዎች ሲይዝቸው በነበሩት ቃለ ጉባኤዎች በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን እያወቀና እያየ ይህ ክፍያ እንዱፈጸም አድርጓል የሚል ነው።
6ኛ ክስ፡- 1ኛ እና 15ኛ አመልካቾች 10ኛ፤ 11ኛ እና ከ22ኛ እስከ 25ኛ ያለ ተከሳሾች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 32/1/ሀ እና የሙስና ወንጀልችን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13/1/ሐን በመተላለፍ 15ኛ አመልካች እና ከ22ኛ እስክ 25ኛ ያለት ተከሳሾች ሕገወጥ በሆነ መንገድ የአጣሪ ኮሚቴ ሆነው በመመረጥ መመሪያው እንደሚከለክላቸው እያወቁ እንደ ሕጋዊ ኮሚቴ እራሳቸውን በመቁጠር በሮቤ ከተማ መሬት ማኔጅመንት ኤጀንሲ በሚጣራ የመኖሪያ ቤት ክምችት በቀን 11/01/07 ቁጥሩ 1076/k13/2007 በሆነ እና ለባላ ዜን መሬት ማኔጅመንት እና ልማት ኤጀንሲ በተጻፈ ደብዲቤ 530 ሰዎች ብቻ ተጣርተው የተላከ ሆኖ ሳለ 56 ሰዎችን በመጨመር እና ላልች ሰዎችን በመቀነስ አጣርተው ልከዋል የሚል ነው።
የአሁን 4ኛ፤5ኛ፤8ኛ፤10ኛ አመልካቾች በአዱስ ዖመን ጋዚጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ስላልቀረቡ ጉዲያቸው በላለበት የታየ መሆኑን መዛገቡ ያመለክታል፤ 1ኛ፤ 2ኛ፤ 3ኛ፤ 6ኛ፤7ኛ ፤9ኛ ፤11ኛ ፤12ኛ፤13ኛ ፤14ኛ እና 15ኛ አመልካቾች ችልት ቀርበው ክሱ ተነቦላቸው አንዱረደት ከተደረገ በኋላ መቃወሚያ አቅርበው በብይን ውድቅ ተደርጓል። የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁም ድርጊቱን አልፈጸምንም በማለት ክደው በመከራከራቸው ፍ/ቤቱ የዓቃቤ ሕግን ማስረጃዎች ሰምቷል።
ፍ/ቤቱ የዓቃቤሕግ ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል እና ዓቃቤሕግ ከክሱ ጋር አያይዜ ያቀረባቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ያለት ክሶች ተከሳሾች 45/55 የተባለን አሰራር በስራ ላይ እንዱውል መወሰናቸውን እና በስራ ላይ ከማዋላቸው ጋር የሚያያዛ ነው።
በዘህ አሰራር መሬት ተሰጥቷቸዋል የተባለት ሰዎች በተለያዩ ክሶች የተገለጹ ቢሆንም በተያዖው ቃለ ጉባኤ የተጣሩ ሰዎች እራሳቸው ናቸው፤ ይህም በአንድ በሕግ በተጠበቀ መብት ላይ የተፈጸመን ወንጀል ከግብ ለማድረስ ተቀላቅለው የተፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶቸ መሆናቸውን የሚሳይ ነው፤ በልላ በኩል ድርጊቶቹ ሲያይዋቸው የነበሩትን ችግሮቸ ለመቅረፍ የተደረጉ በመሆኑ ከሙስና ወንጀልችን አዋጅ ስልጣንን አላግባብ ከመጠቀም ድንጋጌ ጋር የሚያያዛ ሳይሆን የመንግስት ስራን በማያመች መንገድ ከመስራት ጋር የሚያያዘ ናቸው፤ ስለዘህ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ባለት ክሶች በተደራራቢ ወንጀል ተከላከለ ሉባለ አይገባም፤ በዘሁ መሰረት ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያለት ክሶች እንደ አንድ ክስ ታይተው አመልካቾች እና 10ኛ፤11ኛ እና 20ኛ ተከሳሾች የወንጀለ ድርጊት በስራ ላይ እንዱውል የተወሰነውን ቃለ ጉባኤ በመያዙቸው እና በማጽደቅ እንዱሁም 10ኛ፤ 11ኛ፤20ኛ ተከሳሾች እና 13ኛ እና 14ኛ አመልካቾች በስራ ላይ በማዋል ውልችን እና የተለያዩ ሰነድችን በማዖጋጀት እና በማጽደቅ መሳተፊቸው የተረጋገጠባቸው በመሆኑ በአዋጁ 881/2007 አንቀጽ 13/3 ስር እንዱከላከለ በማለት ብይን የሰጠ ሲሆን፤ 6ኛ ክስን በተመለከተ ደግሞ የቀረበው ማስረጃ 15ኛ አመልካች እና ከ22ኛ እስከ 24ኛ ያለት ተከሳሾች የቴክኒክ ኮሚቴ በመሆን ሁለት ጊዚ የማጣራት ስራ ሰርተው ለከፍተኛው ኮሚቴ ያቀረቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፤ ይህ ኮሚቴ የመሬት ክምችትን ለማስመለስ በወጣው መመሪያ ቁጥር 12/2007 አንቀጽ 8/1 መሰረት መቋቋም ካለበት መስሪያ ቤቶቸ በሙለ አልተቋቋመም፤ ይህም ይህን ኮሚቴ ያቋቋመው የቤቱ ከፍተኛ ኮሚቴ የመንግስትን ስራ አመቺ ባልሆነ መንገድ መምራቱን የሚያሳይ ስለሆነ 1ኛ አመልካች እና 10ኛ እና 11ኛ ተከሳሾች በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13/1/ሐ ስር እንዱከላከለ፤ ከ15ኛ አመልካች እና ከ22ኛ እስከ 24ኛ ያለት ተከሳሾችን ደግሞ አጣርተው ለበላይ ኮሚቴ ማቅረባቸው ብቻውን እራሱን ችል እንደ ወንጀል ድርጊት የሚወሰድ አይደለም በማለት ዓቃቤሕግ ያቀረበባቸውን ክስ እና ማስረጃ መካላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዱሰናበቱ ሲል ብይን ሰጥቷል።
በዘሁ መሰረት 1ኛ አመልካች በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 142/3 መሰረት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ክሱን ለመከላከል ያስችለናል ያለትን የመከላከያ ምስክሮችን አቅርበዋል አሰምተዋል የሰነድ ማስረጃም አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም የግራቀኙን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ከ1ኛ እስከ 13ኛ ያለት አመልካቾች እና 15ኛ ተከሳሽ ከ1998 እስከ 2001 ዓ.ም በስራ ላይ የነበረውን እና ፍጻሜ ሳያገኝ የቀረውን 45/55 የተባለ ሕገወጥ አሰራር በ21/09/2007 በሮቤ ከተማ አስተዲደር ከንቲባ ጽ/ቤት በያዘት ቃለ ጉባኤ በሕገወጥ መንገድ ለሰዎች ተላልፍ የነበረን መሬት ማስረጃ እንዱሰጥበት ማስደረጋቸው በቀረበው የሰነድ ማስረጃ በግልጽ ተረጋግጧል፤ 10ኛ፤ 11ኛ፤ 20 ተከሳሾች እና 14ኛ እና 15ኛ አመልካቾች በተመሳሳይ ቀን በ21/09/2007 በሮቤ ከተማ መሬት ልማት እና ማኔጅመንት ጽ/ቤት በተያያዖ ቃለ ጉባኤ ይህ በሕገወጥ መንገድ የተሰጠ የመሬት ይዜታ በከንቲባው ጽ/ቤት በተያዖ ቃለ ጉባኤ አቅጣጫ በተመሳሳይ መንገድ መፍትሄ እንዱያገኝ ማድረጋቸው ተረጋግጧል፤ ተከሳሾች ቀርበው የተከራከሩት ድርጊታችን ሕጋዊ ነው በማለት እንጂ ድርጊቱን አልፈጸምንም በማለት አልተከላከለም፤ ድርጊቱ የተፈጸመበት ዓላማ 45/55 የተባለው ሙለ በሙለ በሕገመንግስቱ እና በሕጉ መሰረት ወደ ኋላ ተመልሶ መፍትሄ የሚሰጠው ከሆነ በተለይም በመንግስት ላይ የፕለቲካል ኢኮኖሚ ፈተና ላሆን እንደሚችል መገንዖብ ይቻላል፤
በከተማ አስተዲደሩ ስሕተት ምክንያት ከገበሬው መሬት የገዘ ሰዎች እና አብዙኛው ገበሬ በዘህ መሬት ላይ ከ2005 ዓ.ም በፉት ግንባታ የገነባበት እና መሬቱን ያለማው በመሆኑ ይህንን ማሕበረሰብ የመንግስት መዋቅር በፈጠረው ስሕተት ምክንያት ማፈናቀል እና የሚገባቸውን የካሳ ክፍያ መክፈል ከፍተኛ ፈተና ነው፤ በመሆኑም የአመልካቾች ድርጊት ወንጀል ቢሆንም አመልካቾች ይህን ወንጀል የፈጸሙበት ዓላማ ከፍተኛ ሉያስብለው የሚችል አይደለም፤ ከአመልካቾች ስልጣን ጋር በተያያዖም ሁለም አመልካቾች የከተማ አስተዲደሩ አመራሮች ቢሆኑም ከተማዋ የዜን ከተማ ያልሆነች እና ተጠሪነቷም ለዜን የነበረ ስለሆነ ስልጣናቸው በሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 433/97 አንቀጽ 2/5 ድንጋጌ መሰረት ከፍተኛ ነው ልባል የሚችል አይደለም፤ በመሆኑም ወንጀለን ከሚያከብደት ምክንያቶቸ መካከል የደረሰው ጉዲት ከፍተኛ መሆኑ ብቻ ነው በማለት አመልካቾችን እና 10ኛ፤ 11ኛ፤
15ኛ 20ኛ ተከሳሾችን የተከሰሱበትን የሕግ አንቀጽ በመለወጥ በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13/2 መሰረት የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል።
6ኛን ክስን በሚመለከት የቴክኒክ ኮሚቴው በመመሪያ ቁጥር 12/2007 መሰረት መቋቋም ካለባቸው ተቋሟት ተወካይ ተሟልቶ ያልተቋቋም መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ የቴክኒክ ኮሚቴውን ያቋቋመው አካል የመንግስትን ስራ አመቺ ባልሆነ መንገድ በመምራት የሚጠየቅ ይሆናል፤ የቴክኒክ ኮሚቴው አባላት መመረጣቸውን በቀን 10/06/2007 ዓ.ም የጻፈው 2ኛ አመልካች አልተከሰሰም፤ 1ኛ አመልካች በሕጉ አግባብ ባልተመረጠ በዘህ ኮሚቴ የቀረበውን ቃለጉባኤ በማጽደቅ በ30/07/07 በበላይ ኮሚቴው የተያዖን ቃለ ጉባኤ የመራው እና በሸኚ ደብዲቤ ለዜን የላከው 1ኛ አመልካች መሆኑ ተረጋግጧል፤ 10ኛ እና 11ኛ ተከሳሾች ይህንን ቃለ ጉባኤ መያዙቸው እና ይህ በሕገወጥ መንገድ የተመረጠው ኮሚቴ ያቀረበው ውጤት እንዱጸድቅ ማድረጋቸው ተረጋግጧል፤ የ1ኛ አመልካች መከላከያ ማስረጃዎች ይህ ኮሚቴ በሕጉ አግባብ ባለመመረጡ የተፈጠረ ችግር ስለላለ ድርጊቱ ሕገወጥ አይደለም በማለት የመሰከሩ ቢሆንም በዘህ ማጣራት ውስጥ የአጣሪ ኮሚቴው ስላልተከሰሰ እንጂ ፔልትን የመዛለል ችግሮች የተፈጠሩ መሆናቸው በዓቃቤሕግ 7ኛ ክስ እና ከቀረበው የሰነድ ማስረጃ መረዲት የሚቻል በመሆኑ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32/1/ሀ እና በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13/1/ሐ ስር ጥፊተኞች ናቸው በማለት የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል።፡ በመቀጠልም ቅጣቱን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማስላት 1ኛ አመልካች በስምንት ዓመት ጽኑ እስራት እና በብር 20,000፤ 2ኛ፤3ኛ፤6ኛ፤7ኛ፤9ኛ እና ከ11ኛ-15ኛ ያለት አመልካቾች በስድስት ዓመት ጽኑ እስራት እና በብር 15,000 ፤ 4ኛ፤5ኛ፤8ኛ፤10ኛ በሰባት ዓመት ጽኑ እስራት እና በብር 16,000 የገንዖብ መቀጮ እንዱቀጡ ሲል ወስኗል።
አመልካቾች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም አቤቱታቸው ተቀባይነት አላገኘም። አመልካቾች በመቀጠል ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበዋል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡትን የጥፊተኝነት ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት ያጸና ሲሆን በቅጣት ረገድ ግን ቅጣቱን አሻሽል 1ኛ አመልካች በአምስት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እሥራት እና በብር 7,000 የገንዖብ መቀጮ ከ2ኛ እስከ 15ኛ ያለት አመልካቾች ደግሞ በአምስት ዓመት ጽኑ እሥራት እና በብር 5,000 የገንዖብ መቀጮ እንዱቀጡ ሲል ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- የአመልካቾች ድርጊት ወንጀል ነው ተብል በሕግ አልተደነገገም፤ አከራካሪው መሬት በመንግስት ፈቃድ በከተማ ነዋሪዎች እጅ የገባው በ1998 ዓ.ም ሲሆን ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2001 ዓ.ም ድረስ ግንባታ ገንብተውበታል፤ አመልካቾች በ2007 ዓ.ም በሃላፉነት ስንመደብ ይዜታው ባድ ቦታ አልነበረም፤ መንግስት ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በገባው ውል መሰረት ነዋሪዎቹ ክፍያ ከፍለው ደረሰኝ ይዖው ነበር፤ አመልካቾች በያዛነው ቃለጉባኤ የወሰነው ከ1998 ዓ.ም እስከ 2001 ዓ.ም ድረስ ለክሱ መነሻ የሆነው መሬት ባለይዜታ የሆኑ ነዋሪዎች የሉዛ አዋጅ ከመታወጁ በፉት በመሬቱ ላይ ግንባታ ፈጽመው አልምተው እየተገለገለበት ለሚገኙት ነዋሪዎች ብቻ መንግስት በውል በገባው ግዳታ መሰረት በሕጉ አግባብ የይዜታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዱሰጣቸው ነው፤ የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ስራው በአስቸኳይ እንዱሰራ ያዖዖ በመሆኑ ድርጊቱ እንደ ወንጀል ሉቆጠር አይገባም፤
አመልካቾች ባድ መሬት ሰጥተዋል የሚል ክስ አልቀረብንም፤ አመልካቾች ከ2004 ዓ.ም በኋላ በተያዖ ይዜታ ላይ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ እንዱሰጥ ያስተላለፍነው ውሳኔ ሳይኖር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት መመሪያ አመልካቾችን አይመለከትም ማለቱ አግባብ አይደለም፤ የስር ፍ/ቤት 3ኛ፤ 4ኛ፤ 5ኛ እና 16ኛ ተከሳሾች በሕዛባዊ ድርጅት ስር የሚመደበው የኦህዳድ ተሿሚዎች በመሆናቸው አዋጁም በእነሱም ላይ ተፈጻሚነት አለው ማለቱ አግባብ አይደለም፤
አመልካቾች ክሱን እንድትከላከለ በማለት የተሰጠው ብይንም ሆነ ክሱን ተከላክለን ሳለ አልተከላከላችሁም በማለት የተሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ አግባብ አይደለም፤
በ21/09/2007 በተፈረመ ቃለ ጉባኤ የፈጸምነው ድርጊት ወንጀል ተብል ባልተከሰስንበት ይህን ቃለጉባኤ መነሻ በማድረግ ጥፊተኛ መባላችን አግባብ አይደለም፤ ወንጀለን ለማቋቋም የሚያስችለ ፍሬነገሮች አልተሟለም፤ በቅጣትም ረገድም የዓቃቤሕግን ማክበጃ በመቀበል እና አመልካቾች ያቀረብነውን ማቅለያዎችን ውድቅ በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ 45/55 በሚል ይዜታቸው ለልማት ለተወሰደባቸው ሰዎች ማካካሻነት በ1998 ዓ.ም የተሰጠ እና ሕጋዊ እንዱሆንላቸው ገበሬዎቹ መንግስትን ጠይቀው በዘህ መነሻነት መስመር ለማስያዛ አመልካቾች በስራ በሃላፉነት በቃለ-ጉባኤ የወሰኑት ውሳኔ ሕገወጥ ነው በሚል ጥፊተኛ የመባላቸውን አግባብነት ከተከሰሱበት የሕግ ድንጋጌ አንጻር ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ፡- አመልካቾች መሬት ከአርሶ አደር ሲነጠቅ አግባብ ባለው ሕግ መሰረት ካሳ መክፈል እና በሕግ አግባብ የተፈቀደለትን መሬት መስጠት ሲገባቸው ይህን አለማድረጋቸው፤
ከአርሶ አደሩ በሕገወጥ መንገድ 3ኛ ወገኖች ከገበሬው የገዘትን መሬት ለመንግስት ገቢ ሳያደርግ ሽያጭ ማካሄዲቸው፤ ከአርሶ አደሩ መሬት የገዘትን ሰዎች ነባር ይዜታ ወይም የድሮ ይዜታ በማለት ማስተናገዲቸው፤ የክልለን የመሬት ሕግ መመሪያ በመጣስ በክሱ የተመለከተውን ድርጊት መፈጸማቸው የመንግስትን ስራ በማያመች አኳሃን መምራት ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 881/2007 መከሰሳቸው እና ጥፊተኛ መባላቸው ተገቢ ነው፤ በ45/55 መሬት በእጃቸው የገባው አርሶ አደሮች በድሮ ይዜታ ስር መውሰድ ሲገባቸው በሉዛ ስር እንዱገባ መደረጉ፤ ከአርሶአደሮች በፉት መሬት በሕገወጥ መንገድ የገዘና በከተማው አስተዲደር እውቅና ተሰጥቶአቸው ማስረጃ የተሰጣቸው በሕገወጥ ይዜታ እና ውዛፍ ስር የሚካተቱ አይደለም፤ ከጠቅላይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተላለፈው መመሪያ የሚመለከተው ከ2004 ዓ.ም በፉት የነበረውን ሕገወጥ ይዜታና ውዛፍ እንጂ አመልካቾች የፈጸሙትን ድርጊት የማይመለከት በመሆኑ የስር ፍ/ቤት በአመልካቾች ላይ ያስተላለፈው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚለው ነው። አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
በአመልካቾች ላይ የቀረቡት ክሶች የመንግስትን ስራ በማያመች አኳሃን መምራትን የሚመለከቱ ናቸው።
የመንግስትን ስራ በማያመች አኳሃን መምራት ደግሞ የሙስና ወንጀል ነው። የሙስና ወንጀል በልዩ ሕግ የተደነገገ ሲሆን ሕጉ ከወጣለት ዓላማ አንጻር በአዋጁ ወንጀል ናቸው ተብለው የተደነገጉት ድንጋጌዎች ወንጀል መሆናቸውን ለማሳየት የራሱ የሆነ መስፈርት በልዩ ሕጉ የተቀመጠለት ከመሆኑ አኳያ የስር ፍ/ቤቶች አመልካቾች ክሱን እንዱከላከለ ብይን መስጠታቸው፤ አመልካቾች መካላከያ ማስረጃ ካሰሙ በኋላም በዓቃቤሕግ ማስረጃ የተረጋገጠባቸውን ፍሬነገሮች አላስረደም በማለት በአመልካቾች ላይ የጥፊተኝነት ውሳኔ እና የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፊቸው ከሙስና ወንጀልች አዋጅ፤
ከመደበኛው የወንጀል ሕግ እና ከወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ሕጉ እንዱሁም የተከሰሱ ሰዎች በሕገመንግስቱ ከተጠበቁላቸው መሰረታዊ መብቶች ጋር በማገናዖብ በጥንቃቄ ላታይ የሚገባው ነው።
በመሆኑም በዘህ ችልት ምላሽ ሉሰጠው የሚገባው የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ፡-
የስር ፍ/ቤት አመልካቾች የቀረበባቸውን ክስ እንዱከላከለ ብይን መስጠቱ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም?
የስር ፍ/ቤት አመልካቾች የቀረበባቸውን ክስ እንዱከላከለ ብይን መስጠቱ ተገቢ ነው ከተባለ አመልካቾች ባቀረቡት መከላከያ የቀረበባቸውን ክስ ተከላክለዋል? ወይስ አልተከላከለም?
የሚለት ናቸው።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡በአመልካቾች ላይ የቀረቡት ክሶች የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራትን የሚመለከቱ ናቸው።
ዓቃቤሕግ አመልካቾች በክሱ የተገለጸውን ድርጊት ስለመፈጸማቸው ለማስረዲት የሰው ምስክሮችን እና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል። የስር ፍ/ቤት አመልካቾች የቀረበባቸውን ክስ እንዱከላከለ ብይን መስጠቱ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? ለሚለው ነጥብ ምላሽ ከመስጠታችን በፉት ከመነሻውም ቢሆን ዓቃቤሕግ አመልካቾች በክሱ የተመለከተውን ድርጊት ፈጽመዋል ለማለት ማስረዲት የሚጠበቅበት ምንድነው? የሚለው መሰረታዊ ነጥብ ምላሽ ማግኘት አለበት።
የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀለን የሚያቋቁሙለት ሕጋዊ፤ ግዘፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬነገሮቸ በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ነው በማለት ይደነግጋል።
ከዘህ ድንጋጌ ይዖት መገንዖብ የሚቻለው ዓቃቤሕግ መደበኛውን የወንጀል ሕግ ወይም ወንጀል መፈጸሙን ለማስረዲት ልዩ መስፈርትን የማያስቀምጡ ልዩ ሕጎችን መሰረት በማድረግ ክስ ሲያቀርብ ተከሳሹ ወንጀል ለመስራት የነበረውን የሀሳብ ክፍል የማስረዲት ሸክም ያለበት መሆኑን እና ይህን ካላስረዲ በቀር ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ እንዱከላከል ብይን መስጠት የማይቻል መሆኑን ነው።
በልላ በኩል የሙስና ወንጀልች በፈጣን ሁኔታ የመቀያየር ባሕርይ ስላላቸው አጠቃላይ ወንጀልችን በሚደነግገው የወንጀል ሕግ ውስጥ እንዱካተቱ ከማድረግ ይልቅ ራሱን በቻለ አዋጅ እንዱደነገጉ ተመራጭ ሆኖ በመገኘቱ በሐገራችን የሙስና ወንጀልች አዋጅ በልዩ ሕግ ወጥቶ የተለያየ ማሻሻያ ሲደረግበት ቆይቷል። ይህንኑ መሰረት በማድረግም የሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 881/2007 ወጥቶ ስራ ላይ ውሎል።
የሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 3 ተቃራኒ ማስረጃ ካልቀረበ በቀር የሙስና ወንጀልቹ የተፈጸሙት የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም ላላውን ሰው ለመጉዲት መሆኑ በተደነገገ ጊዚ በድንጋጌው የተመለከተው ግዘፊዊ ፍሬነገር መፈጸሙ ከተረጋገጠ ድርጊቱ የተፈጸመው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራስ ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት ወይም የሶስተኛ ወገንን መብት ወይም ጥቅም ለራስ ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት ወይም የሶስተኛ ወገንን መብት ወይም ጥቅም ለመጉዲት እንደሆነ ይገመታል በማለት ይደነግጋል። ይህም የሙስና ወንጀል በሙስና ወንጀል አድራጊው እና በወንጀለ በሚጠቀመው ሰው መካከል ስምምነት የሚፈጸም በመሆኑ ዓቃቤሕግ ወንጀለ መፈጸሙን በበቂ ሁኔታ የማስረዲት ሸክም ከባድ የሚያደርግበት በመሆኑ ክሱ የቀረበው ያለአግባብ ነው የሚለው ወገን የዓቃቤሕግ ክስ ትክክል አለመሆኑን ያስረዲ ዖንድ የማስረዲት ሸክሙ ይዙወርበታል። ይህም ዓቃቤሕግ ክስ ሲመሰርት በላልች ወንጀልች ላይ ከተጣለበት በመደበኛነት ከሚታወቀው የማስረዲት ሸክም ወጣ ያለ ልዩ ሁኔታ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ከላይ ከተመለከቱት የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23/2 ድንጋጌ እና የሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 3 ድንጋጌ ጣምራ ንባብ መገንዖብ የሚቻለው ዓቃቤ ሕግ መደበኛውን የወንጀል ሕግ ወይም ወንጀል መፈጸሙን ለማስረዲት ልዩ መስፈርትን የማያስቀምጡ ልዩ ሕጎችን መሰረት በማድረግ ክስ ሲያቀርብ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23/2 መሰረት የተከሳሹን የሀሳብ ክፍል እንዱያረጋግጥ የተጣለበት የማስረዲት ሸክም ለሙስና ወንጀልች በተመሳሳይ ተፈጻሚ የማይሆን መሆኑን፤ ይልቁንም በሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 3 በተደነገገው መሰረት በድንጋጌው የተመለከተው ግዘፊዊ ፍሬነገር መፈጸሙ ከተረጋገጠ ተከሳሹ በድንጋጌው የተመለከተውን ግዘፊዊ ፍሬነገር ለመፈጸም የነበረውን የሀሳብ ክፍል ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ እንዱያስተባብለው የማስረዲት ሸክሙ ወደ ተከሳሹ የሚዙወር መሆኑን ነው። ስለሆነም ዓቃቤሕግ ማስረዲት የሚጠበቅበት በድንጋጌው የተመለከተው ግዘፊዊ ፍሬነገር መፈጸሙን ብቻ እንጂ ተከሳሹ ወንጀል ለመፈጸም የነበረውን የሃሳብ ክፍል አለመሆኑን እና የተከሳሹን የሀሳብ ክፍል አላስረዲህም ተብል ተከሳሹን መከላከል ሳያስፈልገው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141 መሰረት ነጻ ሉያወጣው የሚችል አይደለም።
ከላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ዓቃቤሕግ በሕጉ አግባብ የተጣለበትን አመልካቾች በተከሰሱበት ድንጋጌ ላይ የተመለከተውን ግዘፊዊ ፍሬነገር መፈጸሙን አስረድቷል? ወይስ አላስረዲም?
ለሚለው ነጥብ ምላሽ ለመስጠት በስር ፍ/ቤት የተሰሙትን የዓቃቤሕግ ማስረጃዎች ይዖት መመልከት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
1ኛ የዓቃቤሕግ ምስክር ለፍ/ቤቱ የሰጡት የምስክርነት ቃል ይዖት ፡ከላልች ሰዎች ጋር በመሆን ጉዲዩን ያጣሩ መሆኑን፤ የሮቤ ከተማ ማስተር ፔላን የሮቤ ዘሪያ ቀበላ እና ሆራ ቦቃን የሚያቅፍ መሆኑን፤ በከተማው ማስተር ፔላን ስር ያለ ቢሆንም በሲናና ወረዲ እና በሮቤ ከተማ መካከል ርክክብ ያልተፈጸመ በመሆኑ የከተማው አስተዲደር በመሬቱ ላይ ማዖዛ አይችልም በማለት የመለሱ መሆኑን፤ ባክልግ ለማስመለስ የተቋቋሙ ኮሚቴዎችን እና ቃለጉባኤ ያዩ ቢሆንም ሰው ሲፈርም ያላዩ መሆኑን፤ በቴክኒክ ኮሚቴ ውስጥ የተቋቋሙት አዋጁ የማይፈቅድላቸው መሆናቸውን፤ በአንድ ኮሚቴ የተደረገው ማጣራት 530 ሰዎች ሲሆኑ ሁለተኛው ኮሚቴ ደግሞ 56 ሰዎችን ጨምሮ ያቀረበ መሆኑን፤ 45/55 የሚለው አሰራር ገበሬው ካለው መሬት 45% የሚወስድ ሲሆን 55% ለመንግስት የሚገባ መሆኑን፤ በ21/09/2007 ዓ.ም የተጻፈን ቃለጉባኤ መነሻ በማድረግ የከተማ አስተዲደር በገንዖብ ሉከፈል የሚችል ክፍያ ስለላለው እንዱፈቀድልን በማለት የኦሮሚያ መሬት ልማት እና ማኔጅመንትን እና ዜኑን በደብዲቤ የጠየቁ መሆኑን፤ ለደብዲቤዎቹ የተሰጠ ምላሽ ማግኘት ያልቻለ መሆኑን፤ 45/55 የሚባል አሰራር በሕግ የላለ መሆኑን፤ ካሳ የሚከፈልበት መንገድ በሕጉ የተቀመጠ ቢሆንም በሕጉ መሰረት ያልተከፈለ መሆኑን፤ በገበሬው መሬት ላይ በከተማው አስተዲደር እና በሲናና ወረዲ መካከል ርክክብ ያልተደረገ መሆኑን፤ 45/55 የተባለው አሰራር በሮቤ ከተማ እና በሲናና ወረዲ መካከል ሲስፊፊ የነበረው ከ1998ዓ.ም እስከ 2001 ዓ.ም መሆኑን፤ ከሲናና ወረዲ ወደ ሮቤ ከተማ በገባ መሬት የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት የተሰሩ መሆኑን፤ ገበሬው በ45/55 ከተሰጠው መሬት ለግለሰብ አስተላልፍ አብዙኛው እጅ ከ2007 ዓ.ም በፉት ግንባታ የተገነባበት መሆኑን፤ መንግስት በወሰደው 55% መሬት ላይ ማስረጃ አለመመርመራቸውን፤ በ2004 ዓ.ም እና በ2005 ዓ.ም በገበሬው እና በከተማው አስተዲደሩ መካከል ክርክር ተነስቶ የነበረ መሆኑን፤ 45/55 የተባለው አሰራር የሕዛብን ጥያቄ እንመልሳለን በሚል የተሰራ ቢሆንም መንግስት የሕዛብን ጥያቄ የሚመልስበት መመሪያ ያለው መሆኑን፤ 45/55 የተባለው አሰራር ሲጀመር አመልካቾች በከተማው አስተዲደር በሀላፉነት ላይ ያልነበሩ መሆኑን በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው።
2ኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ለፍ/ቤቱ የሰጠው የምስክርነት ቃል ይዖት ፡በአብዙኛው 1ኛ ምስክር ከሰጡት የምስክርነት ቃል ጋር ተመሳሳይ ይዖት ያለውን ምስክርነት የሰጡ ሲሆን በከንቲባው የሚመራው ኮሚቴ 530 ሰዎች በባክልግ መሬት ማግኘት የሚገባቸው መሆኑን ያጣራ መሆኑን፤ 2ኛው ኮሚቴ 56 ሰዎችን ጨምሮ ያጣራ መሆኑን፤ 32 ሰዎች መሬት ተሰጥቷቸዋል የተባለውን በሚመለከት ማስረጃ የላላቸው መሆኑን፤ በቃለ ጉባኤ ላይ 45/55 የተባለው አሰራር በተመለከተ ገበሬው የ45% ድርሻውን ለግለሰቦች ማስተላለፍ ይችላል በማለት የተገለጸ ቢሆንም በምን አግባብ እንዱሚያስተላልፍ የማያውቁ መሆኑን፤ አመልካቾች 45/55 በስራ ላይ እንዱውል እንዱፈቀድላቸው ላቀረቡት ጥያቄ የተሰጠ መልስ ያላዩ መሆኑን፤ 79 ለሆኑ ገበሬዎች በ45/55 መሬታቸው የተሰጣቸው መሆኑን በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው።
3ኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ለፍ/ቤቱ የሰጠው የምስክርነት ቃል ይዖት ፡ከ76 ገበሬዎች ጋር በተያያዖ የቀረበው ማስረጃ በከተማው ድንበር ያለ ገበሬዎች ቤተሰቦች ስፊት፤
መሬቱ አገልግልቱ እና ደረጃው ምን እንደሆነ የሚገልጽ ነገር የላለው መሆኑን፤ ገላጭ ነገር ባለማግኘታቸው ምክንያት በደንብ 155/2005 መሰረት ከ200 ካ.ሜትር በላይ ያለው ገበሬ በኪራይ ስርዓት፤ ከዘህ በላይ ከሆነ 500 ካ.ሜ ለባለይዜታው ተሰጥቶ ከዘህ የቀረው ደግሞ የመንግስት መሬት ስለሚሆን መንግስት ከዘህ መሬት ሉያገኝ የሚገባው ገቢ ነው በማለት ያሰለ መሆኑን፤ የሮቤ ከተማ የከተማው ኤጀንሲ ከተዖጋጀ በኋላ 3ኛ ደረጃ የነበረች መሆኑን ከሐምል ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ ወደ 2ኛ ለደረጃ ያደገች መሆኑን፤ መሬቱ በመመሪያው መሰረት ቢተላለፍ ኖሮ 1ኛ ደረጃ ወይም 2ኛ ደረጃ በማለት ለይተው በዜኑ ኮሚቴ በተያዖው ቃለ ጉባኤ ላይ ተንተርሰው የሰሩ መሆኑን፤ የሮቤን ከተማ ስታንዲርድ ትልቁን በ 200 ካ.ሜ ወስደን በደንብ ቁጥር 155/2005 መሰረት የመሬቱ ይዜታ ባለቤት ለሆነው ገበሬው 500 ካ.ሜ ይጸድቅለታል፤ ከ500 ካ.ሜ በላይ የሆነው ይወሰድበታል፤ 105 ካ.ሜ ከሆነ ተመዛግቦ ይቀመጣል፤ በዘህ መሰረት መንግስት ማግኘት ይገባው የነበረውን ገንዖብ አስልተው ያስቀመጡ መሆኑን በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው።
4ኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ለፍ/ቤቱ የሰጠው የምስክርነት ቃል ይዖት ፡የሮቤ ከተማ መሬት ማኔጅመንት የመዛገብ ቤት አግልግልት አቀናጅ መሆናቸውን፤ በኦሮሚያ ጸረ ሙስና ኮሚሽን 311 ሰዎችን በሚመለከት እንዱያጣሩ ተጠይቀው 47 ሰዎችን ማግኘት ያልቻለ መሆኑን፤ 47ቱ ሰዎች ስራ በነበረበት ጊዚ ደረሰኝ ቆርጠው መዛገብ ያስከፈቱ መሆኑን፤ ውል ሳይሞለ የቀሩ ብዘ ሰዎች የነበሩ መሆኑን፤ ውል ተሞልቶላቸው ባለስልጣኑ ሳይፈርምበት የቀረባቸው ሰዎችም የነበሩ መሆኑን፤ 47ቱ ሰዎች መሬት አላቸው ተብል የመጣላቸው ቢሆንም በመዛገብ ውስጥ ግን የላለ መሆኑን፤ የተለያዩ ሰዎች እየመጡ ለመስተናገድ ይጠይቁ የነበረ እና ስራው ይቁም ስለተባለ ልናስተናግዲችሁ አንችልም እያለ ይመልስዋቸው የነበረ መሆኑን፤ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ብቻ ደረሰኝ የቆረጡ መሆኑን፤ 47ቱ ሰዎች ደረሰኝ ያላቸው ከመሆን ውጪ ለይተው የማያውቋቸው መሆኑን በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው።
ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች ይዖት፡- ዓቃቤ ሕግ ክሱን ለማስረዲት በርካታ የሰነድ ማስረጃዎችን ያቀረበ ሲሆን ዋነኞቹ አመልካቾች 45/55 የተባለ አሰራር እንዱፈቀድላቸው የያዝቸው ቃለጉባኤዎች እና ቃለ ጉባኤዎችን መሰረት በማድረግ ለበላይ አካል የጻፎቸው ደብዲቤዎች፤ በ45/55 ከገበሬዎች ተወስዶል የተባለው መሬት የገበሬው ድርሻ ነው የተባለው 45% በውለ መሰረት ያልተላለፈ መሆኑን፤ በሰነድ ማስረጃ መሰረት የ76ቱ ገበሬዎች መሬት እንደሆነ የባክልግ አጣሪ ኮሚቴው ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤት በሙለ ያልተቋቋመ መሆኑን፤ በቴክኒክ ኮሚቴው ሁለት ጊዚ የተጣራው ልዩነት ያለው መሆኑን የሚያሳይ ሪፕርት፤ ከከተማው መስፊፊት ጋር ተያይዜ በሮቤ ከተማ ስር የታቀፈት የገጠር ቀበላዎች ላይ በሲናና ወረዲ እና በሮቤ ከተማ አስተዲደር መካከል ርክክብ አለመከናወኑን የሚያሳይ ደብዲቤ ለመሬት ክምችት ከተመዖገቡት 642 ሰዎች መሃከል 530 ሰዎች መሬት እንዱያገኙ መደረጉን፤ 98 ሰዎች ማግኘት የላለባቸው መሆኑን መረጋገጡን እና በዘህ ረገድ እየተሰራ ያለው ስራ ያልተጠናቀቀ መሆኑን የሚያሳይ ቃለጉባኤ፤ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የተደረጉ ውልች ናቸው።
ከላይ በዛርዛር እንደተመለከተው የዓቃቤ ሕግ የሰው ምስክሮች ለፍ/ቤቱ ከሰጡት የምስክርነት ቃል እና ዓቃቤሕግ ካቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች ይዖት መገንዖብ የሚቻለው ዓቃቤሕግ ባቀረበው ማስረጃ አመልካቾች በተከሰሱበት የሙስና ሕግ ድንጋጌ ላይ የተመለከተው ግዘፊዊ ፍሬነገር መፈጸሙን ያረጋገጠ መሆኑን ነው። ዓቃቤ ሕግ መደበኛውን የወንጀል ሕግ ወይም ወንጀል መፈጸሙን ለማስረዲት ልዩ መስፈርትን የማያስቀምጡ ልዩ ሕጎችን መሰረት በማድረግ ክስ ሲያቀርብ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23/2 መሰረት የተከሳሹን የሀሳብ ክፍል እንዱያረጋግጥ የተጣለበት የማስረዲት ሸክም ለሙስና ወንጀልች በተመሳሳይ ተፈጻሚ የማይሆን እና በሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 3 በተደነገገው መሰረት በድንጋጌው የተመለከተው ግዘፊዊ ፍሬነገር መፈጸሙ ከተረጋገጠ ተከሳሹ በድንጋጌው የተመለከተውን ግዘፊዊ ፍሬነገር ለመፈጸም የነበረውን የሀሳብ ክፍል ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ እንዱያስተባብለው የማስረዲት ሸክሙ ወደ ተከሳሹ የሚዙወር በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያለት ክሶች እንደ አንድ ክስ ታይተው አመልካቾች የወንጀለ ድርጊት በስራ ላይ እንዱውል የተወሰነውን ቃለ ጉባኤ በመያዙቸው እና በማጽደቃቸው በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13/3 ስር እንዱከላከለ፤ 1ኛ አመልካች ደግሞ ስድስተኛውንም ክስ በተጨማሪ እንዱከላከል በማለት ብይን መስጠቱ የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡የስር ፍ/ቤት አመልካቾች የቀረበባቸውን ክስ እንዱከላከለ ብይን መስጠቱ በአግባቡ ነው ከተባለ አመልካቾች ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ የቀረበባቸውን ክስ ተከላክለዋል? ወይስ አልተከላከለም?
የሚለው ሁለተኛው መሰረታዊ ጭብጥ አመልካቾች በስር ፍ/ቤት ካቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ አንጻር በአግባቡ ታይቶ ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው ነው። ስለሆነም አመልካቾቸ በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ይዖት በቅድሚያ መመልከት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
1ኛ አመልካች በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 142/3 መሰረት ለፍ/ቤቱ የሰጠው ቃል ይዖት፡አመልካቾች የመጡት በ2007 ዓ.ም መሆኑን፤ የከተማው አስተዲደር ለገበሬው ይዜታ ካሳ ለመክፈል የገንዖብ ችግር ስለነበረበት 45/55 የተባለው አሰራር ከ1998 እስከ 2000 ዓ.ም ባለው ጊዚ ውስጥ የተጀመረ መሆኑን፤፤ 55% የገበሬውን መሬት መንግስት ወስድ ያለማው መሆኑን፤ 45% ደግሞ ለ3ኛ ወገን የተላለፈ መሆኑን፤ ወደኋላ ያለው 10 ዓመት ግንባታ ተገንብቶበት የለማ በመሆኑ፤ የሰብልን ካሳ ለመክፈል መሬቱ 10 ዓመት እዲሪ የነበረ በመሆኑ፤ የንብረት ካሳ ለመክፈል ንብረቱ በከተማ አስተዲደር ተወስድ የራሱ መሆን የነበረበት በመሆኑን ምክንያት በአዋጅ 455/97 መሰረት ተፈጻሚ ያልተደረገ መሆኑን፤ የከተማ አስተዲደሩ እስከ ክልል መንግስት ድረስ ጥያቄ ሲያቀርብ የነበረ መሆኑን፤ ከክልለ እና ከከተማው አስተዲደር ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዲዩ ሲታይ የነበረ መሆኑን ፤ መንግስት ባክልግ የነበረበት በመሆኑ አዋጅ ቁጥር 721/2007 በስራ ላይ ለማዋል የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ በመጠየቅ የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮም ጉዲዩ ለመጨረሻ ጊዚ መልስ እንዱያገኝ በጻፈው ደብዲቤ ፍቃድ የተሰጠ መሆኑን፤
በቀን 18/05/2007 ከጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ለክልለ ፔሬዛደንት ጽ/ቤት በቀጥታ በተጻፈ ደብዲቤ ላይ ሁለት መሰረታዊ ነጥቦችን የያዖ ሲሆን እነኚህም 1ኛ ደረሰኝ ያላቸው ባክልግ ደረሰኝ ቆርጠው መሬት ሳይገኙ የቀሩ ተስተናግደው ምላሽ እንዱሰጣቸው፤ 2ኛ መሬት ይዖው ቤት የሰሩት ሰዎች ሙለ ሰነድ ሳይኖራቸው የቀሩት ለመጨረሻ ጊዚ እንዱስተናገደ የሚል መሆኑን፤ በዘህ ደብዲቤ ላይ በመመሰረት የፔሬዛደንት ጽ/ቤት ለክልለ ኢንደስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ እና ለክልለ መሬት ኤጀንሲ በቀን 05/06/2007 ዓ.ም በጻፈው ደብዲቤ የተጠቀሱትን ጉዲዮች ለማስተናገድ እንዱችለ በማለት የጻፈ መሆኑን፤ ይህን ለማስፈጸምም ሁለቱ ቢሮዎቸ እቅድ በማውጣት በየደረጃው ላለ ኦረንቴሽን በመስጠት ወደ ስራ እንዱገባ አቅጣጫ የተቀመጠ መሆኑን፤ የክልለን ሕግ እና መመሪያ መሰረት በማድረግ በባክልግ በሕገወጥ ግንባታ እና ነባር ይዜታ ላይ መልስ እንዱሰጡ የተደረገ መሆኑን፤ ለገበሬው በካሳ የተሰጠው 45% ከከተማ መስተዲድሩ ጋር የፈጸሙት ውል በእጃቸው የነበረ በመሆኑ በመግለጽ ቃለን መስጠቱን የሚያሳይ ነው።
1ኛ መካላከያ ምሰክር የሰጡት የምስክርነት ቃል ይዖት፡በ1998 ዓ.ም በሮቤ ከተማ አባገዲ አዲራሽ ሰብስበው ከተማዋ ዜን ስለሆነች ልትለቁ ይገባል ያሎቸው መሆኑን፤ መሬቱን አንለቅም ሲለ ልማትን ማደናቀፍ አትችለም መንግስት እንዱሁም ሉወስድባችሁ ስለሚችል ካሳችሁን 45/55 እናደርግላችኋለን ያሎቸው መሆኑን፤ ካርኒ ሳይቆረጥላቸው በመቅረቱ ከ2005 እስከ 2006 አቤቱታ ሲያቀርቡ የነበረ መሆኑን፤ መፍትሄ እንዱሰጣቸው በየጊዚው ለነበሩ የክልለ ፔሬዛደንቶች በተለያየ ጊዚ አቤቱታ ሲያቀርቡ የነበረ መሆኑን፤ ሀላፉዎቹም እናንተ ጥፊት አልፈጸማችሁም ጥፊት የፈጸሙት እራሳችን እዙ ያስቀመጥናቸው ሰራተኞቸ ናቸው ከባክልግ ጋር አንድ ላይ ተደምሮ እንዱስተካከልላችሁ እናደርጋለን ያሎቸው መሆኑን፤ በ1998 ዓ.ም ተሸንሽኖ የነበረን መሬት እና ቤት የተሰራበትን ዜረው እያሳዩ አጣርተው ለይተው ካርኒ ይቆረጥላቸው የሚል ድምጽ የተሰማ መሆኑን፤ ከዘህ በኋላ በአዲራሽ ሰብስበው ሉዛ የቆረጡባቸው መሆኑን ፤ አመልካቾችም በ1998 ዓ.ም የተመሩትን ሰዎች ወደ ኋላ ተመልሰው በ2007 ዓ.ም ሉዛ ያስከፈሎቸው መሆኑን ፤ ወደ ሉዛ በመለሷቸው ጊዚ 45/55 የተባለው ይዜታ ሁለም ቤት የነበረበት መሆኑን፤ ለመንግስት የሰጡት መሬት የተለያየ ተቋማት ተሰርቶበት ሙለ ለሙለ ለመንግስት ጥቅም የዋለ መሆኑን በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው።
2ኛ መከላከያ ምስክር የሰጡት የምስክርነት ቃል ይዖት 45/55 የተባለውን አሰራር በተመለከተ ከ1ኛ ምስክር ጋር ተመሳሳይ ይዖት ያለው ምስክርነት የሰጡ ሲሆን በተጨማሪም አብዙኛው ሰው በወቅቱ የግብርና ስራ አቁሞ ስለነበረ ቀለብ ያልነበረው መሆኑን፤
ሕዛቡ ለሰባት ስምንት ዓመታት እርሻ አቁሞ የራሱን መሬት እየገዙ የነበረ መሆኑን፤ የራሳችንን መሬት ሰጥተናችሁ መልሰን እንገዙለን ሲል የነበረ መሆኑን፤ አመልካቾች ወደ ሉዛ ስርዓት ይገባል 45/55 በሚለው ስርዓት አይፈጸምም ብለዋቸው የነበረ መሆኑን፤ በአመልካቾች የተሸነሸነ መሬት የላለ መሆኑን፤ አመልካቾች በሉዛ ክፍያ ያስከፈለበት ዓላማ የሕዛብን ችግር ለመፍታት መሆኑን፤ መሬት ወደ ከተማ ሲመለስ የመሬት ንጥቂያ በዛቶ የነበረ እና ግለሰቦች የተለያየ ማስረጃዎች አሰርተው በሰዎች ላይ ክርክር እያቀረቡ የነበረ መሆኑን፤ ዋስትናችን ምንድነው? በምን እንከላከላለን? በከተማ ድንበር ውስጥ አስገብታችሁ እንዲናዛ ከልክላችሁናል ውል ሞልተናል ይህንን ውል ማፍረስ አንችልም የሚለ ነጥቦችን አንስተው በእጃቸው ላይ ያለው ይዜታ እንዱጸድቅላቸው የጠየቁ መሆኑን፤ 45/55 ን እንደዲታ ተጠቅመው ውል የፈጸሙላቸው መሆኑን በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው።
3ኛ መከላከያ ምስክር የሰጡት የምስክርነት ቃል ይዖት በአጭሩ፡- 45/55 የተባለውን አሰራር በተመለከተ ከ1ኛ እና 2ኛ ምስክር ከሰጡት ቃል ጋር ተመሳሳይ ይዖት ያለው ምስክርነት የሰጡ ሲሆን በተጨማሪም ከላይ ካለት ጋር ተመሳሳይ በሆነ 45/55 ውል በፈረሙበት እለት ለላላ ሰው ያስተላለፈ መሆኑን፤ በይዜታው ላይ .ቤት የተገነባበት መሆኑን፤ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ካርኒ መቁረጥ ቆሟል በማለት የከለከሎቸው መሆኑን፤ መሬቱ በተወሰደባቸው ጊዚ አመልካቾች ያልነበሩ መሆኑን፤ አመልካቾች ከመምጣታቸው በፉት የፈጸሙት ውል እያለ አንፈጽምም በማለት በሉዛ ያስከፈሎቸው መሆኑን፤ በበፉቱ ውል እንዱፈጸምላቸው ሲጠየቁ መመሪያ ይከለክለናል ያሎቸው መሆኑን በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው።
4ኛ መከላከያ ምስክር የሰጡት የምስክርነት ቃል ይዖት፡- በወቅቱ የከተማው አስተዲደር ለገበሬው ካሳ ለመክፈል ገቢ ያልነበረው መሆኑን፤ ገበሬው የራሱን ግንባታ ሲገነባበት ላላውን ደግሞ አሳልፍ ለሰው ሲሰጥ የነበረ መሆኑን፤ መሬት የመስጠት ጉዲይ ከቀን 16/09/2001 ዓ.ም ጀምሮ በወቅቱ በነበሩት የክልለ ፔሬዛደንት በነበሩት የቆመ መሆኑን፤ ምስክሩ መሬት መስጠት ከቆመ ከአንድ ወር በኋላ ከንቲባ የሆኑ መሆኑን፤ ገበሬው በተለያየ ጊዚ እየቀረበ በመሬታቸው ላይ ማሕተም ተመቶበት ከንቲባ እና የማዖጋጃ ቤቱ ባለሙያ የፈረመበትን ውል ይዜ በመምጣት ካርኒ ቆርጣችሁ ባለይዜታችንን አረጋግጡልን በማለት ጥያቄ ሲያቀርብ የነበረ መሆኑን፤
ከገበሬው ላይ መሬትን በስጦታም ሆነ በሽያጭ የወሰደትም ተመሳሳይ ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበረ መሆኑን፤ ገበሬው መልስ ሉያገኝ ስላልቻለ እስከ ክልል አስተዲደር ድረስ በመሄድ ሲጠይቅ የነበረ መሆኑን፤ በ2007 ዓ.ም ምርጫ ሲቃረብ ጥያቄውን ለመመለስ መንግስት ባስተላለፈው መመሪያ በመንተራስ አመልካቾች የገበሬዎቹን ጥያቄ የመለሱ መሆኑን፤ አመልካቾች ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2001 ዓ.ም በተሰራው ስራ ውስጥ ድርሻ የላላቸው መሆኑን፤ የነባር ይዜታው ባለቤት ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ የድሮ ይዜታ የመንግስት ክፍያን ከፍል ባለይዜታነቱ እንዱረጋገጥ የተደረገ መሆኑን፤ ከገበሬው ላይ ተላልፍለት መሬት ያገኘ ሰው ደግሞ የሉዛ መነሻ ዋጋ ክፍያን ከፍል ባለይዜታነቱ እንዱረጋገጥ የተደረገ መሆኑን በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው።
5ኛ ምስክር የሰጡት የምስክርነት ቃል ይዖት፡ምስክሩ የማዖጋጃ ቤቱ ስራ አስኪያጅ የነበሩ መሆኑን፤ ተንጠልጥለው የቆዩ ጉዲዮችን በሚመለከት የሚፈጸሙበትን ሁኔታ ስልጠና የወሰደ መሆኑን፤ በጠቅላይ ሚንስቴር እና በክልል ደረጃ የተጻፈ ደብዲቤዎች ስለነበሩ 45/55 በዘህ ሉስተናገድ የሚችል መሆኑን፤ በ1997 እና በ1998 አካባቢ የከተማዋ ገቢ ከ 4,000,000 የማይበልጥ የነበረ በመሆኑ ለ10 ዓመት ወደ ኋላ ተመልሰው ካሳ መክፈል የማይቻል መሆኑ፤ መንግስት መሬት መስጠትን አግድ ገበሬዎች የራሳቸውን ድርሻ መሬት ሲወስደ የነበረ መሆኑን፤ መንግስትም የራሱን ድርሻ ወስድ ሲያለማበት የቆየ መሆኑን፤ እስከ 500 ካ.ሜ ካርኒ ሲቆረጥበት የቆየ መሆኑን ፤ በወቅቱ የእገላ ቤተሰብ ነኝ በማለት ደረሰኝ ይቆረጥልኝ በማለት አቤቱታ ሲያቀርቡ ካርኒ በመቁረጥ ይስተናገደ የነበረ መሆኑን፤ ከሚፈቀደው ስታንዲርድ በላይ የጸደቀ የላለ መሆኑን፤ ገበሬው ወደ ከተማ አስተዲደሩ እንዱሁም ወደ ክልለ አስተዲደር በመሄድ ሃላፉዎች ያነጋገረ መሆኑን፤ የሕዛቡ ቅሬታ በመብዙቱ በአባገዲ አዲራሽ ሰብስበው አናግረዋቸው የደንብ ስለወጣ በአጭር ጊዚ ውስጥ መፍትሄ ይሰጣችኋል ያሎቸው መሆኑን፤ ለአመራሩም ኦረንቴሽን የተሰጠ መሆኑን፤
አመልካቾች ሳይጠናቀቅ ተንጠልጥል የቆየን ነገር ሕጋዊ መስመር አስይዖው ከማጠናቀቅ ውጪ 45/55ን በአዱስ መልክ የሰሩት ነገር የላለ መሆኑን፤ 45/55 የተባለው አሰራር በዜንም በክልልም እንደጥሩ ምሳላ ተወስድ የነበረ መሆኑን፤ ገበሬው በራሱ ድርሻ ላይ ማስረጃ ያለው መሆኑን፤ ገበሬው ወደ ኋላ ተመልሶ በሉዛ እንዱከፍል ስለተደረገ የተጎዲው ገበሬው እንጂ በመንግስት ላይ የደረሰ ጉዲት የላለ መሆኑን፤ ከከተማ አስተዲደር ጋር ውል የላላቸው ሰዎቸ ሕጋዊ ያልተደረጉ መሆኑን፤ ግንባታ የፈጸሙ እና ከገበሬው ውጪ ያለ ሰዎቸ ደግሞ በሉዛ ስርዓት ባለቤትነታቸው የተረጋገጠ መሆኑን፤
ከገበሬው ጋር የተለያዩ ውልች ሲደረጉ የነበረ መሆኑን፤ መንግስት 55% መብት እንዲለው ሁለ ገበሬውም በ45% ላይ ሉያዛበት መብት ያለው መሆኑን በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው።
6ኛ መከላከያ ምስክር የሰጡት የምስክርነት ቃል ይዖት፡- .45/55 የተባለውን አሰራር በተመለከተ ላልች ምስክሮች ከሰጡት የምስክርነት ቃል ጋር በተመሳሳይ የመሰከሩ ሲሆን በተጨማሪም መንግስት በ2007 ዓ.ም በሉዛ መሸጋገሪያ ጊዚ ተይዖው የነበሩ መሬቶች በሉዛ መመሪያ ተጠቃለው እንዱስተናገደ፤ በድሮ ይዜታ እና በሕገወጥ ግንባታ መካከል ተንጠልጥል የነበረ ይዜታ መፍትሓ እንዱያገኝ አቅጣጫ ያስቀመጠ መሆኑን፤ አስቀድሞ መሬቱ የገበሬው የራሱ የእርሻ መሬት ስለሆነ ገበሬው መሬቱን መኖሪያ ቤት ለማድረግ፤ በስጦታ ለማስተላለፍ መብት አለው፤
አመልካቾች በ2007 ዓ.ም 45/55 ን በማስቀጠል ለገበሬው ካሳ ሳይከፍለ የወሰደት መሬት የላለ መሆኑን፤ አመልካቾች በ2007 ዓ.ም የሰሩት ነገር መሬቱ አስቀድሞ ስለተሰጠ ማስረጃ ብቻ መስጠት እንጂ መሬት ያልሰጡ መሆኑን፤ መጀመሪያ ከከተማ አስተዲደሩ ጋር በተደረገ ውል በተሰጠ መሬት ላይ መሟላት ያለበት መስፈርት በሙለ መሟላቱን አረጋግጠው ሳይት ፔላን እና ማስረጃ የሰጡ መሆኑን በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው። አመልካቾች በተጨማሪም በምስክሮቻቸው የተገለጸውን የምስክርነት ቃል የሚደግፍ የሰነድ ማስረጃ አቅርበዋል።
እንግዱህ ከላይ በተገለጸው መሰረት አመልካቾች ደርጊቱን ለመፈጸም የቻለበትን ምክንያት ካስረደ አመልካቾች ባቀረቡት መከላከያ ማስረጃ የመንግስትን ስራ በማያመች አኳሃን መርታችኋል በማለት እንዱከላከለ በተሰጠው ብይን መሰረት ተከላክለዋል ወይስ አልተከላከለም ለማለት አመልካቾቸ በመከላከያ ማስረጃዎቻቸው እንዱያስተባብለት የሚጠበቀው ምንድነው? የሚለው ለጉዲዩ አወሳሰን መሰረታዊ ነጥብ ነው። በተያዖው መሰረታዊ ጭብጥ ላይ ምላሽ ለመስጠት ከላይ በመጀመሪያው ጭብጥ ላይ የገለጽነውን የማስረዲት ሸክም ወደ አመልካቾች የተላለፈበትን ምክንያት በድጋሚ መመልከት አስፈላጊ ነው።
አመልካቾች እንዱከላከለ በማለት ብይን የተሰጠባቸው የአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13/3 እና 13/1/ሐ ድንጋጌ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ስልጣንን ወይም ሀላፉነትን ተጠቅሞ የመንግስትን ስራ በማያመች አኳሃን መምራት ወንጀል ነው። ዓቃቤሕግ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23/2 መሰረት የተከሳሹን የሀሳብ ክፍል እንዱያረጋግጥ የተጣለበት የማስረዲት ሸክም ለሙስና ወንጀልች በተመሳሳይ ተፈጻሚ የማይሆን እና በሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 3 በተደነገገው መሰረት በድንጋጌው የተመለከተው ግዘፊዊ ፍሬነገር መፈጸሙ በተረጋገጠ ጊዚ ተከሳሹ በድንጋጌው የተመለከተውን ግዘፊዊ ፍሬነገር ለመፈጸም የነበረውን የሀሳብ ክፍል ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ እንዱያስተባብለው የማስረዲት ሸክሙ ወደ ተከሳሹ ይዜራል። ይህም ማለት አመልካቾች ድርጊቱን የፈጸሙት የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም ላላውን ሰው ለመጉዲት ነው በማለት አስቀድሞ ተይዜባቸው የነበረውን የሕግ ግምት ስራውን የመሩት የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም ላላውን ሰው ለመጉዲት አለመሆኑን እና ስራውን በሚያመች አኳኋን የመሩ መሆኑን ሉያሳይ የሚችል ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ ማስተባበል ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው።
ከላይ እንደተገለጸው በሙስና ወንጀልች ግዘፊዊ ፍሬነገሩ መፈጸሙ በተረጋገጠ ጊዚ ተከሳሹ በድንጋጌው የተመለከተውን ግዘፊዊ ፍሬነገር መፈጸሙን የሕግ ግምት የሚያዛበት መሆኑ፤ ተከሳሹም ይህን አስቀድሞ የተያዖበትን የሕግ ግምት ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ ሉያስተባብለው የሚችል በመሆኑ ፍ/ቤቶች ይህንኑ መሰረት በማድረግ ውሳኔ በሚሰጡበት ጊዚ ተገቢውን ሚዙን የጠበቀ ውሳኔ መስጠት ይጠበቅባቸዋል። ይህም በአንድ በኩል የሙስና ወንጀልች አዋጅ የሕዛብ እና የመንግስትን ጥቅም ለማስጠበቅ የወጣ በመሆኑ ወንጀለን ፈጽመዋል ተብለው ክስ የቀረበባቸው ሰዎች ወንጀለን የፈጸሙ መሆኑ በተረጋገጠባቸው ጊዚ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት ያለባቸው በመሆኑ፤ በልላ በኩል ደግሞ የተከሰሱ ሰዎች የመሰማት መብታቸው ተጠብቆ በቀረበባቸው ክስ ጥፊተኛ መሆናቸው በማስረጃ እስካልተረጋገጠ ድረስ ጥፊተኛ ሆኖ ያለመቆጠር መብት ያላቸው መሆኑ ነው።
ይህንኑ መሰረት በማድረግ ጉዲዩን እንደተመለከትነው አንድ ሰው የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም ላላውን ሰው ለመጉዲት ሲል ስራን በማያመች አኳኋን መርቷል ለማለት ስራውን በሚያመቸ አኳሃን ለመምራት የሚያስችል ሕግ እና የተዖረጋ ስርዓት መኖሩ እና ተከሳሹ ይህንኑ ሕግ እና ስርዓት ተላልፍ ስራውን በማያመች አኳኋን የመራ መሆኑ ሉረጋገጥበት ይገባል።
በያዛነው ጉዲይ 45/55 የተባለው አሰራር ከ1998 እስከ 2001 ዓ.ም ባለው ጊዚ ውስጥ የተጀመረ መሆኑን፤ አመልካቾች ወደ ሀላፉነት የመጡት በ2007 ዓ.ም መሆኑ፤ የከተማው አስተዲደር ለገበሬው ይዜታ ካሳ ለመክፈል የገንዖብ ችግር ስለነበረበት 45/55 የተባለው አሰራር የተጀመረ መሆኑን፤ በዘሁ መሰረት 45% ገበሬው በካሳ መልክ እንዱወስደው 55% የገበሬውን መሬት ደግሞ መንግስት እንዱወስድ የተደረገ መሆኑን፤ መንግስት በወሰደው 55% ድርሻው ላይ የተለያዩ ተቋማትን በመገንባት ያለማው መሆኑን፤ ገበሬው ደግሞ ድርሻው በሆነው 45% ከፉለን ራሱ የወሰደ ከፉለን ደግሞ ለ3ኛ ወገን ያስተላለፈ መሆኑን፤ ገበሬው ከከተማው አስተዲደር ጋር ውል ፈጽሞ የነበረ መሆኑን፤ ወደኋላ ያለው 10 ዓመት በመሬቱ ላይ ግንባታ ተገንብቶበት የለማ በመሆኑ፤ የሰብልን ካሳ ለመክፈል መሬቱ 10 ዓመት እዲሪ የነበረ በመሆኑ ምክንያት በአዋጅ 455/97 መሰረት ተፈጻሚ ያልተደረገ መሆኑን፤
የከተማ አስተዲደሩ እስከ ክልል መንግሰት ድረስ ጥያቄ ሲያቀርብ የነበረ መሆኑን፤ ከክልለ እና ከከተማው አስተዲደር ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዲዩ ሲታይ የነበረ መሆኑን ፤ መንግስት ምላሽ ያልሰጠበት ባክልግ የነበረበት መሆኑ፤ ገበሬው ተደራጅቶ በተለያየ ጊዚ ለነበሩ የክልለ ፔሬዛደንቶች ጥያቄ ሲያቀርብ የነበረ መሆኑን፤ ሀላፉዎቹም እናንተ ጥፊት አልፈጸማችሁም ጥፊት የፈጸሙት እራሳችን እዙ ያስቀመጥናቸው ሰራተኞቸ ናቸው ከባክ ልግ ጋር አንድ ላይ ተደምሮ እንዱስተካከልላችሁ እናደርጋለን ያሎቸው መሆኑን፤ ገበሬው አስቀድሞ በነበረው አሰራር መሰረት ካርኒ እንዱቀረጥለት ሲጠይቅ አመልካቾች ይህንኑ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልነበሩ መሆኑን፤ የገበሬው ጥያቄ ገፍቶ እስከ ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ድረስ የደረሰ መሆኑን፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮም ጉዲዩ ለመጨረሻ ጊዚ መልስ እንዱያገኝ በጻፈው ደብዲቤ ደረሰኝ ያላቸው ባክልግ ደረሰኝ ቆርጠው መሬት ሳያገኙ የቀሩ ተስተናግደው ምላሽ እንዱሰጣቸው፤ መሬት ይዖው ቤት የሰሩት ሰዎች ሙለ ሰነድ ሳይኖራቸው የቀሩት ለመጨረሻ ጊዚ እንዱስተናገደ የሚል መሆኑን፤ ይህንኑ መሰረት በማድረግ የክልለ ፔሬዛደንት በጻፈው ደብዲቤ የተጠቀሱትን ጉዲዮች ለማስተናገድ እንዱችለ በማለት የጻፈ መሆኑን፤ አመልካቾች ሳይጠናቀቅ ተንጠልጥል የቆየን ነገር ሕጋዊ መስመር አስይዖው ከማጠናቀቅ ውጪ 45/55 የተባለውን አሰራር በአዱስ መልክ ያልሰሩ መሆኑን፤ ገበሬው በራሱ ድርሻ ላይ ማስረጃ ያለው መሆኑን፤ ከከተማ አስተዲደር ጋር ውል የላላቸው ሰዎቸ ሕጋዊ ያልተደረጉ መሆኑን፤ ግንባታ የፈጸሙ እና ከገበሬው ውጪ ያለ ሰዎቸ ደግሞ በሉዛ ስርዓት ባለቤትነታቸው የተረጋገጠ መሆኑን፤ አመልካቾች በ2007 ዓ.ም የሰሩት ስራ መሬቱ አስቀድሞ ስለተሰጠ ማስረጃ ብቻ መስጠት እንጂ መሬት ያልሰጡ መሆኑን፤
መጀመሪያ ከከተማ አስተዲደሩ ጋር በተደረገ ውል በተሰጠ መሬት ላይ መሟላት ያለበት መስፈርት በሙለ መሟላቱን ተረጋግጦ ማስረጃ የተሰጠ መሆኑን አመልካቾች ካቀረቡት መከላከያ ማስረጃ ይዖት መገንዖብ ይቻላል።
ገበሬው ተገቢ የሆነ ካሳ ሳይከፈለው ከእርሻ መሬቱ ያለመፈናቀል መብት እንዲለው በሕገመንግስቱም ሆነ በክልለ የመሬት ሕግ የተደነገገ ቢሆንም ገበሬው ከይዜታው ላይ እንዱነሳ በተደረገ ጊዚ ከተማዋ ካሳ ለመክፈል የሚያስችል የገንዖብ አቅም ያልነበራት መሆኑ፤ 45/55 የተባለው አሰራር በሕግ ያልተደነገገ ቢሆንም በወቅቱ የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ሲባል በወቅቱ በነበሩ ሀላፉዎች ሲተገበር የነበረ መሆኑ፤ ይህንኑ ተከትል መሬቱ ከፉለ በገበሬው እጅ ከፉለ ደግሞ ለተለያዩ ግለሰቦች የተላለፈ መሆኑን፤ በከተማው አስተዲደር ስሕተት ምክንያት ከገበሬው መሬት የገዘ ሰዎች እና አብዙኛው ገበሬ በዘህ መሬት ላይ ከ2005 ዓ.ም በፉት ግንባታ የገነባበት እና መሬቱን ያለማው በመሆኑ ሕብረተሰቡን ለማፈናቀል እና የሚገባውን የካሳ ክፍያ ለመክፈል ከፍተኛ ማሕበራዊ ቀውስ የሚፈጥር እና መንግስታዊ ኢኮኖሚውም ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያመጣ መሆኑን፤ ከጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤትም ሆነ ከክልለ ፔሬዛደንት ለጉዲዩ መፍትሓ እንዱሰጥ በደብዲቤ የተገለጸ በመሆኑ፤ አመልካቾች ውሳኔ ሳይሰጥባቸው ተከማችተው ያለ ጉዲዮችን ለመፍታት የነደፈትና የተገበሯቸው አሰራሮች መሆናቸውን በግራ ቀኙ የቀረቡት ማስረጃዎች የተረጋገጠ ሲሆን ይህ ደግሞ ሆነ ብለው ወይም በቸልተኝነት አንደን አካል ለመጥቀም ወይም ለመጉዲት ከመነጨ ሀሳብ የተፈጸመ ተግባር ስለመሆኑ አስቀድሞ ተወስድ የነበረውን የህግ ግምት ጥያቄ ላይ የሚጥል ነው። አመልካቾች በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ መሰረት አድርገው የሰጧቸው ውሳኔያቸው ምንም ይሁን ምን የነበረውን ክፍተት በተገቢው አግባብ ለመድፈን የተፈጸመ መሆኑን የሚያስገነዛብ በመሆኑ ስራውን የሰሩት የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም ላላውን ሰው ለመጉዲት ነው የሚያስብል ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች በአመልካቾች ላይ ያስተላለፈት የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ነው በማለት በአብላጫ ድምጽ ወስነናል። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የባላ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካቾችን በሚመለከት በመ. በቀን 10/01/2010 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝት ውሳኔ እና በቀን 11/01/2010 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በቀን 04/04/2010 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ፤ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. በቀን 21/09/2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሽሯል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት አመልካቾች ከቀረበባቸው ክስ በነጻ እንዱሰናበቱ ተወስኗል።
ትዔዛዛ የሚመለከተው ማረሚያ ቤት የስር ፍ/ቤቶቸ በአመልካቾች ላይ አስተላልፈውት የነበረው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ተሽሮ አመልካቾች በነጻ እንዱሰናበቱ የተወሰነ መሆኑን አውቆ አመልካቾችን በዙሬው እለት ከእስር እንዱፈጹ ታዝል። ይጻፍ።
የፍ/ቤቱ ሬጅስትራር የዘህን ውሳኔ ግልባጭ ለሚመለከተው ማረሚያ ቤት በአስቸኳይ እንዱልክ ታዝል።
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዖግቷል።
ፊ/ዖ የልዩነት ሃሳብ ስማችን በአራተኛ እና አምስተኛ መስመር ላይ የተጠቀሰው ዳኞች አብላጫው ድምጽ አመልካቾችን ከወንጀል ተጠያቂነት ነፃ ለማለት በጠቀሰው ምክንያት እና በደረሰበት ድምዲሜ ያልተስማማን በመሆኑ የልዩነት ሀሳባችንን በሚከተለው መልኩ አስፍረናል።
ከቀረበው ክስ መረዲት እንደሚቻለው አመልካቾች መጀመሪያ የተከሰሱት በተሰጣቸው የመንግሰት የስራ ኃላፉነት ላይ ሆነው የቀረበላቸውን ጥያቄ በተመለከተ በክሱ ዛርዛር የተጠቀሱን የፋዳራል እና የክልል አዋጅ ደንብ እና መመሪያን መሰረት አድርገው ምላሽ መስጠት ሲገባቸው ይህንን ወደ ጎን በማለት የማይገባቸውን ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም በልላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የተሰጣቸውን ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም በህግ ያልተመለከተን እና 45% 55% የሚባል አሰራርን በመዖርጋት በህዛብ እና መንግስት ጥቅም ላይ ጉዲት አድርሰዋል በሚል ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካቾች ቃለ ጉባኤ ይዖው ስራ ላይ ያዋለት 45% 55% የተባለው አሰራር የህግ መሰረት የላለው መሆኑን ማረጋገጡን ሆኖም ድርጊታቸው ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ሳይሆን የህግ መሰረት የላለውን አሰራር በመዖርጋት የመንግስት ስራ በማያመች‹ መንገድ መምራት ወንጀልን ነው በሚል ክስ የቀረበበትን አንቀጽ ቀይሮ እንዱከላከለ አዝል።
አመልካቾች በመከላከያ ማስረጃቸው 45% 55% የተባለው አሰራር እነርሱ ወደ ኃላፉነት ከመምጣታቸው በፉት የነበረ መሆኑን ከመግለጽ ባለፈ አሰራሩ የህግ ማዔቀፍ ያለው ስለመሆኑ ያቀረቡት ክርክርም ሆነ ከዘህ አኳያ ያረጋገጡት ነገር የለም። ቀድሞ የነበረ ብልሹ አሰራር በቃለ ጉባኤ እውቅና ሰጥቶ ማስቀጠል ደግሞ የወንጀል ክስ መከላከያ ላሆን የሚችልበት የህግ አግባብ የለም።
አብላጫው ድምፅ አመልካቾችን ጥፊተኛ ከተባለበት ወንጀል በነፃ ለመልቀቅ በምክንያትነት የጠቀሰው አመልካቾች የመንግስትን ስራ በማያመች መንገድ መርተዋል በሚል ጥፊተኛ ለማለት ቀድሞ ‹‹የሚያመች አሰራር ሉኖር ይገባል›› የሚል ነው። ሆኖም የቀረበው ክስ በራሱ አመልካቾች የሰሩት ስራ ሉመራ እና ምላሽ ሉያገኝ ይገባ የነበረው በክሱ ዛርዛር ውስጥ የተጠቀሱትን የፋዳራል እና የክልል ህግጋት መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ ተገልጿል። ከዘህ በላይ ምን አይነት አሰራር እንደተፈለገ ግልጽ አይደለም። አመልካቾችም ቢሆኑ በቃለ ጉባኤ ያስቀጠለት ብልሹ አሰራር ከእነርሱ በፉትም የነበረ መሆኑን ከመግለጽ ባለፈ ለጉዲዩ አግባብነት አላቸው የተባለት የህግ ማዔቀፍች መፍትሄ ለመስጠት አላስቻለንም የሚል መከራከሪያ አላቀረቡም። ከዘህ አንፃር መከራከሪያ ቀርቦ ቢሆን እንኳን ህግ ክፍተት በህግ አግባብ ስልጣን ባለው አካል ስራን በሚያሳልጥ መልኩ እንዱታረም ከሚደረግ በቀር ‹‹ህጉ አላሰራኝም›› በሚል ሽፊን ህግ በቃለ ጉባኤ ተተክቶ የሚሰራበት አግባብ የለም።
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች አመልካቾች ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን ህግ ወደ ጎን ትተው የህግ መሰረት የላለውን አሰራር ስራ ላይ በማዋል የመንግስትን ስራ በማያመች መንገድ መርተዋል በማለት የሰጡት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በማስረጃ የተረጋገጠን ፍሬ ነገር መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ሉሻር አይገባውም በሚል ከስራ ባልደረቦቻችን በሀሳብ ተለይተናል።
No topics extracted.