ዓቃቤ ሕግ የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሰረት ያልቀረበ ሆኖ ሲገኝ ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት በራሱ አነሳሽነት ክሱ በህጉ አግባብ ተሻሽል እንዱቀርብ ማድረግ ያለበት ስለመሆኑ እና ዓቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽል እንዱቀርብ ሳይደረግ በሕጉ አግባብ ተዖጋጅቶ ያልቀረበው ክስ የተከሳሹን የመከላከል መብት የሚያጣብብ በመሆኑ ተከሳሹ በሕግ አግባብ ተዖጋጅቶ ባልቀረበው ክስ ጥፊተኛ ልባል የማይገባ ስለመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ቁጥር 118 እና 119/1/
No summary available.
የሰ.መ.
ጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች:- አየለ ሀፋቦ ተጠሪዎች፡- የደቡብ ክልል ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕግ መዛገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች ሕዲር 06 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዛቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የደና ወረዲ ፍ/ቤት በመ. ግንቦት 06 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤ የሀድያ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ጥር 05 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ፤ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለቱ ነው።
ጉዲዩ ወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዛቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ደና ወረዲ ፍ/ቤት ነው። በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ፤ ላልች አራት ግለሰቦች ደግሞ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተከሳሾች ነበሩ። የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች እና በላልች ተከሳሾች ላይ በስር ፍ/ቤት ካቀረባቸው ክሶች ውስጥ አመልካችን የሚመለከተው 1ኛ እና 3ኛ ክስ ሲሆን ይዖታቸውም፡- 1ኛ ክስ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 32/1/ሀ፤60/ለ እና 462/2/ሀ በመተላለፍ ጥር 17 ቀን 2010 ዓ.ም ጌምቤራ ቀበላ ተብል በሚጠራው ቦታ ደሪል ኒሪም የተባለ ግለሰብ በፍ/ቤት መያዣ ትዔዙዛ ለመያዛ የሄደት የፕሉስ አባላት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ካዋለት በኋላ አመልካች እነዘህ ፕሉሶች ያለእኔ ዔውቅና የመጡ ስለሆነ ተጠርጣሪውን መያዛ እና መውሰድ አይችለም በማለት ፕሉሶቹን ተባብረው በመያዛ እና በመምታት እስረኛውን አስመልጠዋል የሚል ሲሆን፡- 3ኛ ክስ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 32/1/ሀ፤ 60/ለ እና 441 ድንጋጌን በመተላለፍ በ1ኛ ክስ ለፈጸመው ድርጊት የክፍለን ፕሉሶች በሀይል እና በማስገደድ ስራቸውን እንዲይሰሩ በማድረጋቸው በፈጸሙት የመንግስት ስራ በሀይል ድርጊት ማሰናከል ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት የደና ወረዲ ፍ/ቤት አመልካችን እና የስር ተከሳሾችን ጥፊተኛ ሆነው ስላገኛቸው በተከሰሱበት የሕግ አንቀጽ ጥፊተኛ ብሎቸዋል። ቅጣቱንም በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 መሰረት በማስላት ለ1ኛ ክስ ድርጊቱ የተፈጸመው በቡድን እና በጸጥታ አስከባሪ አካላት ላይ በመሆኑ የጽኑ እሥራት አማራጭ ተወስዶል በማለት፤ የወንጀል ደረጃውን መካከለኛ በማለት በእርከን 15 ላይ በማሳረፍ፤ ምንም እንኳን አመልካች ያነሳሳ ቢሆንም በቀጥታ የፕሉሱን አካል ያልያዖ በመሆኑ መነሻ ቅጣት ሁለት ዓመት ከአስር ወር በመያዛ፤ ለ3ኛ ክስ የወንጀለን ደረጃ መካከለኛ በማለት በእርከን 6 ላይ በማሳረፍ አንድ ዓመት እስራት የተወሰደ ቢሆንም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 184/ለ መሰረት አንድ ጽኑ እስራት እና አንድ ቀላል እሥራት ተደራርበው በተፈጸሙ ጊዚ ቀላል እስራት ታጥፍ መደመር ያለበት በመሆኑ ቀላል እስራቱን ወደ ስድስት ወር ጽኑ እስራት በመቀየር በድምሩ ሶስት ዓመት ከአራት ወር በመያዛ በእርከን 17 ላይ በማሳረፍ፤ በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ባለመቀበል እና ለአመልካች ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን በመያዛ ቅጣቱን አቅል በእርከን 15 ላይ በማሳረፍ አመልካች በሁለት ዓመት ከአስራ አንድ ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ሲል ወስኗል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለሀዱያ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም። አመልካች በመቀጠል ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቧል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካች ክሱን አላስተባበለም በማለት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 462/2 እና 441/2 ድንጋጌ ጥፊተኛ ብልታል። ቅጣትን በተመለከተ ደግሞ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 462/2/ሀ የአመልካች ድርጊት አፈጻጸም በጠለፊ የተጠረጠረን ግለሰብ ለማስመለጥ በሕግ አስከባሪ አካላት ላይ በቡድን የተፈጸመ ወንጀል በመሆኑ በከባድ ሉቀጣ ይገባል በማለት የወንጀለን ደረጃ መካከለኛ በማለት መነሻ ቅጣት ሁለት ዓመት ከስድስት ወር በመያዛ፤ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 441/2 የወንጀል ደረጃውን መካከለኛ በማለት መነሻ ቅጣት ሁለት ዓመት በመያዛ፤ አመልካች ጥፊተኛ ለተባለበት ሕግ የተያዘትን መነሻ ቅጣቶች በመደመር አራት ዓመት ከስድስት ወር መነሻ ቅጣት በመያዛ እና በእርከን 19 ላይ በማሳረፍ፤ አመልካች የተያዖለት ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያት በመያዛ ቅጣቱን አቅል በእርከን 17 ላይ በማሳረፍ በሶስት ዓመት ከሶስት ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ሲል ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- ዓቃቤሕግ ባቀረባቸው ምስክሮች አመልካች ወንጀል የፈጸምኩ ስለመሆኔ አላስረዲም፤
የወረዲው ፍ/ቤት አመልካች የቀረበብኝን ክስ እንድከላከል ብይን የሰጠ ቢሆንም ባቀረብኩት መከላከያ ማስረጃ የአቃቤሕግን ክስ አስተባብዬ ሳለ ጥፊተኛ መባላ አግባብ አይደለም፤ የስር ፍ/ቤት የአመልካችን መከላከያ ማስረጃ ውድቅ ያደረገበትን ምክንያት በውሳኔው ላይ አልገለጸም፤ አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረብኩት አቤቱታ የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔው አግባብ አይደለም የሚል ሆኖ ሳለ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠውን የጥፊተኝነት ውሳኔ ካጸና በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ባልተጠየቀ ዲኝነት የቅጣት ውሳኔውን አምስት ዓመት ከሁለት ወር ብል በመያዛ ከፍ በማድረግ ቀንሶ እንዲሻሻለ በማድረግ የሶስት ዓመት ከሶስት ወር እሥራት እንድቀጣ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት አመልካች በሁለት ዓመት ከአስራ አንድ ወር እስራት እንዱቀጣ በሰጠው ውሳኔ አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ባቀረበው አቤቱታ መነሻነት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች በስር ፍ/ቤት ከተወሰነበት ቅጣት በላይ በሦስት ዓመት ከሦስት ወር እንዱቀጣ በማለት የመወሰኑን አግባብነት ከወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 195 ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ተጠሪ መጥሪያ ተልኮለት ስላልቀረበ በጽሐፍ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም የአመልካችን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ምክንያት ከሆነው ውሳኔ፤ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ፡-
የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በስር ፍ/ቤት አቅርቦት የነበረው 3ኛ ክስ አቀራረብ በወንጀል ስነስርዓት ሕጉ ስለክስ አቀራረብ በተቀመጡት ድንጋጌዎች አግባብ የቀረበ ነው? ወይስ አይደለም?
በየደረጃው ያለት የክልለ ፍ/ቤቶች በአመልካች ላይ ቀርቦ የነበረውን 3ኛ ክስን አስመልክቶ የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለትን ጭብጦች በመያዛ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረነዋል።
የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች እና በስር ተከሳሾች ላይ አቅርቦት የነበረው 3ኛ ክስ ይዖት ተከሳሾች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 32/1/ሀ፤ 60/ለ እና 441 ድንጋጌን በመተላለፍ በ1ኛ ክስ ለፈጸመው ድርጊት የክፍለን ፕሉሶች በሀይል እና በማስገደድ ስራቸውን እንዲይሰሩ በማድረጋቸው በፈጸሙት የመንግስት ስራ በሀይል ድርጊት ማሰናከል ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው።
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 441፡- ማንም ሰው፡ሀ/ አንድ የመንግስት ሰራተኛ የስራ ግዳታው የሆነውን ተግባር እንዲያከናውን በዙቻ፤ በማስገደድ ወይም በሀይል ድርጊት ያሰናከለ ወይም ይህን ግዳታውን እንዱያከናውን ወይም ማድረግ የላለበትን እንዱያደርግ ያስገደደ እንደሆነ፤ ወይም ለ/ የመንግስት ሰራተኛን ወይም በስራው የሚረዲውን ሰው የደበደበ ወይም የሀይል ወይም የማስገደድ ድርጊት ወይም ማናቸውንም ላላ የማስገደድ ድርጊት የፈጸመ እንደሆነ፤
ከሶስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል በማለት ይደነግጋል።
ከድንጋጌዎቹ ይዖት መገንዖብ የሚቻለው በድንጋጌው ንዐስ (ሀ) እና (ለ) ላይ የተቀመጡት የወንጀል ማቋቋሚያ መስፈርቶች ራሳቸውን ችለው የተቀመጡ መስፈርቶች መሆናቸውን ነው።
የአሁን ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ባቀረበው 3ኛ ክስ ተከሳሾች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 441 በመተላለፍ የመንግስት ስራ በሀይል ድርጊት ማሰናከል ወንጀል ፈጽመዋል ከማለት በቀር ተከሳሾች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 441 ላይ በተለያየ ንዐስ ቁጥር ላይ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች ውስጥ የትኛውን የንዐስ ቁጥር ድንጋጌ እንደተላለፈ በክሱ ላይ ለይቶ አላመለከተም።
ጉዲዩ የቀረበለት የወረዲው ፍ/ቤትም አመልካችን በ3ኛ ክስ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 441 መሰረት ጥፊተኛ ከማለት በቀር አመልካች ጥፊተኛ የተባለበትን የድንጋጌውን ንዐስ ቁጥር ለይቶ አላመለከተም፤
በአመልካች አቤቱታ አቅራቢነት ጉዲዩን በሰበር የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም 3ኛን ክስ በሚመለከት አመልካችን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 441/2 ጥፊተኛ ሲለው ይህን ያደረገበትን ምክንያት አልገለጸም።
በመሰረቱ ከሳሽ የሆነው ዓቃቤሕግ የሚቀርበው የወንጀል ክስ ማመልከቻ በምን አኳኃን መቅረብ እንዲለበት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 111 እና 112 ላይ በዛርዛር ተመልክቷል። ከድንጋጌዎቹ ይዖት መገንዖብ የሚቻለው ዓቃቤሕግ በሚያቀርበው ክስ ላይ በዛርዛር እንዱገልጽ ከሚጠበቅበት መሰረታዊ ፍሬነገሮች ዉስጥ ተከሳሹ ተላልፍታል የተባለው የወንጀል ሕግ ድንጋጌ እና ተከሳሹ የፈጸመዉ የወንጀል ተግባር በመሰረታዊነት ሉጠቀሱ የሚገባቸው ናቸው። ክሱ በዘህ አግባብ ተዖጋጅቶ እስካልቀረበ ጊዚ ድረስ ተከሳሽ የሆነው ወገን ክሱን በአግባቡ ሉረዲ እና ክሱን ሉከላከል አይችልም።
ይህም በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች በሕገመንግስቱ የተጠበቀላቸውን የቀረበባቸውን ክስ የመረዲት እና የመከላከል መሰረታዊ መብት የሚጻረር ነው።
ፍ/ቤቱም ዓቃቤሕጉ ያቀረበው የክስ አቤቱታ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት ያልቀረበ ሆኖ ባገኘው ጊዚ በራሱ አነሳሽነት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ቁጥር 118 እና 119/1 ላይ በተገለጸው አግባብ ክሱ ተሻሽል እንዱቀርብ ማድረግ ይኖርበታል። ዓቃቤሕግ ክሱን አሻሽል እንዱቀርብ እስካልተደረገ ጊዚ ድረስ በሕጉ አግባብ ተዖጋጅቶ ያልቀረበው ክስ የተከሳሹን የመከላከል መብት የሚያጣብብ በመሆኑ ተከሳሹ በሕግ አግባብ ተዖጋጅቶ ባልቀረበው ክስ ጥፊተኛ ልባል አይገባም።
በያዛነው ጉዲይ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ 3ኛውን ክስ በተመለከተ ተከሳሾች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 441 በመተላለፍ የመንግስት ስራ በሀይል ድርጊት ማሰናከል ወንጀል ፈጽመዋል ከማለት በቀር ተከሳሾች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 441 ላይ በተለያየ ንዐስ ቁጥር ላይ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች ውስጥ የትኛውን የንዐስ ቁጥር ድንጋጌ እንደተላለፈ በክሱ ላይ ለይቶ አላመለከተም። ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 3ኛ ክስ የተለያዩ ንዐስ አንቀጾች ያለት እና በንዐስ አንቀጾቹ ላይ የተቀመጡት የወንጀል ማቋቋሚያ መስፈርቶች ራሳቸውን ችለው የተቀመጡ መስፈርቶች በመሆናቸው አመልካች ተላልፍታል የተባለው ንዐስ አንቀጽ ተለይቶ በክስ አቤቱታው ላይ እስካልተገለጸ ጊዚ ድረስ አመልካች የቀረበበትን ክስ በአግባቡ ሉረዲ አይችልም። ዓቃቤሕግ ክሱን አሻሽል እንዱቀርብ እስካልተደረገ ጊዚ ድረስ በሕጉ አግባብ ተዖጋጅቶ ያልቀረበው ክስ የተከሳሹን የመከላከል መብት የሚያጣብብ በመሆኑ ተከሳሹ በሕግ አግባብ ተዖጋጅቶ ባልቀረበው ክስ መነሻነት ጥፊተኛ ልባል አይገባም።
በመሆኑም ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ተጠሪ ያቀረበው ክስ በሕጉ መሰረት የቀረበ አለመሆኑን ሲረዲው ክሱ እንዱሻሻል ትዔዙዛ መስጠት ሲገባው አመልካች በተከሰሰበት ሕግ ከተቀመጡት ንዐስ አንቀጾች ውስጥ አመልካች የተላለፈውን የሕግ ድንጋጌ ሳይለይ በደፈናው አመልካችን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 441 መሰረት ጥፊተኛ ማለቱ፤ ጉዲዩን በሰበር የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ይሕንኑ ሳያርም እና ምንም ዓይነት ምክንያት ሳይሰጥ አመልካችን በ3ኛው ክስ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 441/2 ጥፊተኛ በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል ዓቃቤሕግ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ በሕጉ አግባብ የቀረበ እና አመልካች በክሱ ላይ የተመለከተውን ድርጊት ስለመፈጸሙ ተረጋግጦበት ክሱን ያልተከላከለ በመሆኑ አመልካች 1ኛውን ክስ በሚመለከት ያቀረበውን ቅሬታ አልተቀበልነውም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች በአመልካች ላይ 3ኛ ክስን በተመለከተ ያስተላለፈትን የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በመሻር 1ኛ ክስን በሚመለከት ብቻ ቅጣቱን እንደሚከተለው አስልተናል።
በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች በ1ኛ ክስ ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 462/2/ሀ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 462/2/ሀ የወንጀለ ደረጃ መካከለኛ በማለት መነሻ ቅጣት ሁለት ዓመት ከስድስት ወር የተያዖለት በመሆኑ ይህ መነሻ በእርከን 12 ላይ የሚያርፍ ነው፤ በአመልካች ላይ ተቀባይነት ያገኘ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት የለም፤ አመልካች በስር ፍ/ቤት ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያት የተያዖለት በመሆኑ ቅጣቱ ሲቀል በእርከን 10 ላይ ያርፊል፤ በእርከን 10 ያለው ፍቅደ ስልጣን ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ነው።
በዘህ እርከን ስር አመልካችን ያርማል ላልቹንም ያስጠነቅቃል ብለን ያመንበትን አመልካች በአንድ ዓመት ከዖጠኝ ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጣ በማለት ወስነናል። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዛቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የደና ወረዲ ፍ/ቤት በመ. ግንቦት 06 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤ የሀድያ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ጥር 05 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ፤ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሻሽሎል ።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት አመልካች ከ3ኛ ክስ በነጻ ተሰናብቷል።
አመልካች ከ3ኛ ክስ በነጻ የተሰናበተ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት የቅጣት ውሳኔ ተሻሽል በአንድ ዓመት ከዖጠኝ ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጣ በማለት ወስነናል።
ትዔዙዛ
የሚመለከተው ማረሚያ ቤት በአመልካች ላይ በስር ፍ/ቤቶች ተላልፍ የነበረው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ተሻሽል አመልካች በአንድ ዓመት ከዖጠኝ ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጣ የተወሰነ መሆኑን አውቆ በተሻሻለው ውሳኔ መሰረት እንዱያስፈጽም ታዝል።
በደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዛቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዱያ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት የመ. የሆነው መዛገብ በመጣበት አኳሃን ወደ መጣበት ይመለስ።
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዖግቷል። ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።