አንድ ሰው በፈጸመው ወንጀል ምክንያት በማረሚያ ቤት በመሆኑ በሕፃናት ልጆቹ ላይ የሚደርሰውን ቁሳዊም ሆነ ኅሉናዊ ጫና ለማስቀረት ሲባል እንዱሁም ሕጻናቱ የወላጆቻቸውን እንክብካቤ እና ድጋፍ አግኝተው እንዱያድጉ ለማድረግ ሲባል፤ ፍ/ቤቶችም የሕጻናት ደኅንነት በቅድሚያ የማረጋገጥ ሕገመንግስታዊ ግዳታ ያለባቸው በመሆኑ በወንጀለኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት በመገደብ ህፃናቱ ተገቢውን የወላጅ እንክብካቤ እንዱያገኙ ለማድረግ ያስችል ዖንድ በወንጀል ህጉ ቅጣት ለማገድ የተቀመጡትን ሁኔታዎች በማረጋገጥ የተወሰነውን ቅጣት እንዲይፈጸም ማገድ የሚገባ ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 36/2፤የወንጀል ህግ አንቀጽ 192፣194፤የዓለም አቀፈ የህፃናት መብቶ፤ች ስምምነት የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ቁጥር 44/25 እንደ ኤሮፒውያን አቆጣጠር 1989 የወጣው አንቀጽ 7 (1)፤ የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 18
No summary available.
ሕዲር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- መዓዙ አሸናፉ ሰለሞን አረዲ እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ገብርኤል ፒራቶሪ አንቶንዮ ተጠሪ፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መዛገቡ ለምርመራ ለ23/4/2012 ዓ.ም የተቀጠረ ሲሆን ከቀጠሮ በፉት ቀርቦ ሉመረመር የቻለው የአመልካች ጠበቃ ህዲር 09 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው አቤቱታ አመልካች በከፍተኛ የደም ግፉት ህመም በመሰቃየት ላይ የሚገኝ እና ባለቤቱም የካንሰር ህመም ታማሚ በመሆኗ ምክንያት ህጻናት ልጆቻቸው በችግር ውስጥ የሚገኙ መሆኑን በመግለጽ ጉዲዩ ታይቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በዋስ እንዱቆዩ እንዱፈቀድለት በመጠየቁ ነው። በዘህ ምክንያት ለምርመራ የተያዖው ቀነ ቀጠሮ ተሰብሮ ጉዲዩ ተመርምሮ ቀጥል ያለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ለዘህ ሰበርችልት ላቀርብ የቻለው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወንጀል መዛገብ በቀን 20/02/2011 ዓ.ም በሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ፣እንዱሁም በ 10/03/2011 ዓ.ም በሰጠው የቅጣት ውሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወንጀል መዛገብ ቁጥር166293 ሚያዘያ 25 ቀን 2011 በቀን 5/10/2010 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት አመልካች እንዱታረምላቸው ግንቦት 12 ቀን 2011 ዓ.ም የተጻፈ አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የነገሩ አመጣጥ የወንጀል ጉዲይን የሚመለከት ነው።የአሁን ተጠሪ ግንቦት 28 ቀን 2009 ዓ.ም ያቀረበው የክስ ይዖትም፡-የሥር ተከሳሽ/የአሁን አመልካች/ ኢትዮጵያዊያን ዚጎችን ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ የሚያስችል ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ሳይኖረው ወ/ሮ እመቤት ይልማ ገ/የሱስ የተባለችውን የግል ተበዲይ ወደውጭ ሀገር ደባይ እንደሚልካት በመግለጽ ከምትኖርበት አዱስ አበባ ከተማ ንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዲ 12 ነዋሪ የሆነችውን ፒስፕርት፣ሁለት ጉርድ ፍቶግራፍ እና የህክምና የምርመራ ውጤት እንደሚያስፈልጋት በመግለጽ ስምንት ሺህ ብር እንደሚያስፈልግ በመነጋገር ሂደቱን ካስጨረሰ በኃላ ህዲርወር 2008 ዓ.ም ስልክ በመደወል ቪዙሽ መጥቷል ታህሳስ 3 ቀን 2008 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡.00 ሰዓት ወደ ደባይ በራራ ስለምታደርግ አየር መንገድ መገኘት እንዲለባት ከገለጸላት በኃላ የግል ተበዲይም አሁን አልተዖጋጀሁም፣ለአንድ ሳምንት አራዛምልኝ በማለት በጠየቀችው መሰረት አራዛሞላት የበረራው ቀን ሳይደርስ ቀደም ብላ የግል ተበዲይ ከ2ኛ እና ከ3ኛ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችጋር በመሆን ወደተከሳሽ የባለቤቱ እህት ሜሮን ኃይለ መኖሪያ ቤት ቀኑን በትክክል በማያስታውሱበት ታህሳስ ወር 2008 ዓ.ም በመሄድ የመላኪያውን ገንዖብ በመስጠት የአየር ቲኬትና ቪዙ ተቀብ ለው ከተመለሱ በኃላ በታህሳስ 10 ቀን 2008 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ቦላ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በኩል ወደ ደባይ ሀገር እንድት ሄድ ካደረገ በኃላ ደባይ ሀገር አሰሪዋ የግል ተበዲይ ጭንቅላቷ ላይ በብረትድስት በመምታት የፈነከተቻት ና ያቆሰለቻት፣ሁለት እጅዋን በቢላዋ የወጋቻት ና እንዱቆስል ያደረገች በመሆኑ፣እንዱሁም የሰራችበትን የአራት ወር ደሞዛዋንም ያልከፈለቻት ና ከፍተኛ ስቃይ እና ጉዲት እንዱ ደርስባት ያደረገው በመሆኑ በፈጸመው በህገወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊን ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወንጀል ተከሷል የሚልነው።
የአሁን አመልካች ፍርድ ቤት ቀርቦ የእምነት ክህደት ሲጠየቅ የወንጅል ድርጊቱን አልፈጸምኩም፣ ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት አስመዛግቧል። ዐቃቤ ህግ የሰው ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል። ፍርድ ቤቱም ተከሳሽን እንዱከላከል ብይን ሰጥቶ መከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል።
ጉዲዩን የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ና ማስረጃዎችን መርምሮ ተከሳሽ በበኩለ በጣቢያ የሰጠሁትን የእምነት ቃል ተገድጄ የሰጡት በመሆኑ ፍርድቤቱ እንዱያይልኝ ያለውን በሚመለከት ቃለን ተገድ የሰጠው ለመሆኑ በማስረጃ አስደግፍ ያላቀረበ በመሆኑ ና በእለቱ በቦታው አልነበረም የሚለው መከራከሪያ ዐቃቤ ህግ ካቀረቡት ማስረጃዎች ጋር ሲመዖን ተከሳሽ በዐቃቤ ህግ የቀረበበትን ክስ በመከላከያ ማስረጃ ተከላክሎል የሚያስብል በቂ ምክንያት ያላገኘን በመሆኑ አልተከላከለም ብለን ፈርደናል። ስለዘህ ተከሳሽ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 598 (2) ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በህገ ወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊያንን ለሥራ ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀል በመፈጸሙ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 149(1) መሰረት ጥፊተኛ ነው ሲል ወስኗል። ቅጣትን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ የግራቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብሎል። ዐቃቤ ህግ ያቀረበ የቅጣት ማቅለያ የለም። ተከሳሽ የወንጀል ሪከርድ የላለ መሆኑን፣የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆኑን፣በተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት እና ማሕበራዊ ተሳትፍ ያበረከተውን፣እንዱሁም በቤተክርስቲያን ያገለገለበትን አራት የቅጣት ማቅለያዎችን ፍርድ ቤቱ ተቀብሎል።ፍርድ ቤቱ የእሥራት መነሻ እርከን 22 ይዝል።ከዘህ ላይ አራት የቅጣት ማቅለያን በመቀነስ እርከን 18 ላይ እንዱያርፍ ካደረገ በኃላ ተከሳሽ በ3 ዓመት ከ7 ወር /ሶስት ዓመት ከሰባት ወር/ ጽኑ እሥራት እናብር 500. 00 /አምስት መቶብር/ ሉቀጣ ይገባል በማለት በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 149 (5) መሰረት የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁን አመልካች በጥፊተኝነትም ሆነ በቅጣት ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቧል።የይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኙን ተቀብል ግራቀኙን ካከራከራቸው በኃላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የሚያስለውጥ በቂ ና አሳማኝ የሆነ የፍሬነገርም ሆነ የህግ ስህተት የላለ ሆኖ ስላገኘነው በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነሥርዓት ቁጥር 195 (2) (ለ) (2) መሰረት አጽንተናል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የጥፊተኝነት እንዱሁም የቅጣት ውሳኔውን በመቃወም ነው።የአመልካች ጠበቃ ግንቦት 12 ቀን 2011 ዓ.ም የተጻፈ ዛርዛር የቅሬታ ነጥቦችን አቅርቧል።ይዖቱም በአጭሩ የተጠሪ ምስክሮች ቃል እርሰ በእርሱ የሚጋጭ ነው፣አመልካች ባቀረባቸው ማስረጃ በሚገባ ተከላክሎል፡በተጠሪ በኩል ተጠቅሶ የቀረበው ክስ የወንጀል ህግ ቁጥር 598 (2) ድንጋጌን በመተላለፍ የወንጀል ድርጊት ፈጽሟል የሚል ሆኖ በግል ተበዲይ ላይ የደረሰው የአካል ጉዲት ስለመድረሱ የቀረበ የህክምና ማስረጃ የለም፣ክስ በቀረበበት ፍርድ ቤትም በግል ተበዲይ ላይ የደረሰው ጉዲት ተመርምሮ እንዱቀርብ አመልካች ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱም ያለአግባብ ሳይቀበል ቀርቷል።በግል ተበዲይ ላይ የደረሰው ጉዲት በማስረጃ ባልተጠራበት ይህ ድንጋጌ ተጠቅሶ ክሰ መቅረቡ የፍትህ መጓደል አምጥቷል።በግል ተበዲይ ላይ የአካል ጉዲት አለመድረሱ ቢረጋገጥ በአመልካች ላይ የሚጠቀሰው የአንቀጹ ንዐስ አንቀጽ 2 መሆኑ ቀርቶ ንዐስ አንቀጽ 1 ይሆን ነበር።በዘህ ምክንያት በአመልካች ላይ የተጣለው ቅጣት ይቀንስ ነበር ማለት ነው።ስለሆነም የግል ተበዲይ የአካል ጉዲት ደርሶባታል የሚያስብል የማያጠራጥር ማስረጃ በዐቃቤ ህግ በኩል ስላልቀረበ በአመልካች ላይ ተፈጻሚ መሆን የሚገባው ድንጋጌ አንቀጽ 598 (1) ሆኖ፣ቅጣቱ በዘህ አንቀጽ መሰረት ታሳቢ ሉደርግ ይገበዋል ካለ በኃላ የሚጠይቀው ዲኝነት በማለት 1ኛ/ የሥር ችልቶች የሰጡት የጥፊተኝነት ውሳኔ ውድቅ ተደርጎ አመልካች በነፃ ይሰናበትልን ዖንድ እና እናመለክታለን። 2ኛ/ የሰበር ሰሚ ችልቱ የጥፊተኝነት ውሳኔውን የሚያፀናው ከሆነ ተፈጻሚ የሚሆነው አንቀጽ ግን 598 (1) ነው ካለ በኋላ፣በሥር ፍርድ ቤት ታሳቢ የተደረጉትን 4 (አራት) የቅጣት ማቅለያዎች ግምት ውስጥ አስገብቶ ውሳኔውን ይቀንስልን ዖንድ እናመልክታለን የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ የሥር ፍርድ ቤት የግል ተበዲይ የደረሰባት ጉዲት ስለመኖሩ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የአሁኑ አመልካችን በወንጀል ህግ ቁጥር 598 (2) ሥር ጥፊተኛ በማለት የወሰነበት አግባብነት ከወንጀል ህግ ቁጥር 598 (1) አንጻር መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በቀን 3/2/2012 ዓ.ም የተጻፈ ዛርዛር መልስ ሰጥቷል።የመልሱ ይዖትም በአጭሩ ዐቃቤ ህግ ባቀረባቸው ማስረጃዎች የግል ተበዲይ በአመልካች ወደ ውጭ አገር የተላከች መሆኑን፣ከተላከች በኃላም የሰብአዊ መብት ጥሰት እና የአካል ጉዲት እንደደረሰባት አስረድቷል።
በአመልካች በኩል የቀረቡት የመከላከያ ማስረጃዎች ይህን ያስተባበለ አይደለም። አመልካች ከቀረቡት ማስረጃዎች አንጻር በወንጀል ህግ አንቀጽ 598 (2) ጥፊተኛ መባለ አግባብ ነው። ስለሆነም ሰበር ሰሚ ችልቱ የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ አግባብ ነው በማለት እንዱያፀናልን የሚል ነው።
የአመልካች ጠበቃም ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም በሰጠው የመልስ መልስ በግል ተበዲይዋ ላይ ደረሰ የተባለው የአካል ጉዲት ምሆነ ላላ የሰብአዊ መብት ጥሰት የግል ተበዲይዋ ከሰጠችው ምስክርነት ቃል በስተቀር በልላ በምንም ዓይነት ማስረጃ አልተረጋገጠም።የግል ተበዲይዋ የምትሰጠው ቃል ደግሞ ብቻውን ተወስድ አመልካችን በ ንዐስ ቁጥር 2 ሥርተጠያቂ ሉያደርገው አይችልም።ላላው ቢቀር በግል ተበዲይዋ ላይ የአካል ጉዲት የደረሰ መሆን አለመሆኑ በህክምና ማስረጃ ሉረጋገጥ እየቻለ የሥር ፍርድ ቤት የህክምና ምርመራ ላደረግ አይገባም በማለት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል ብቻ መሰረት በማድረግ ውሳኔ መስጠቱ አግባብነት የለውም።በመሆኑም የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የሰጡት ቃል ዐቃቤ ህግ የወንጀል ህግ ቁጥር 598 (2) 'ን' መሰረት በማድረግ የመሰረተውን ክስ የሚደግፍ ባለመሆኑ አመልካች ልጠየቅ የሚገባው በወንጀል ህግ ቁጥር 598 (1) ሥር ነው። ስለዘህ ችልቱ ይህንን ተገንዛቦልን አመልካችን ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በአንቀጽ 598(1) ሥር ነው እንዱባልልን እናመለክታለን በማለት ተከራክሯል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት ከላይ እንደ ተገለጸው ሲሆን ጉዲዩን የሰበር አጣሪው ከያዖው ጭብጥ አንጻር መርምረናል። የፍሬ ነገር ክርክርን መሰረት በማድረግ ከማስረጃ ጋር ተያይዜ የጥፊተኝነት ውሳኔው ተገቢ አይደለም ተብል የቀረበውን የአመልካችን ቅሬታ የሰበር አጣሪው በጭብጥነት አልያዖውም። ይህ ችልትም ይህ ተገቢ እንደሆነ ያምናል። ነገር ግን የሰበር አጣሪው የያዖውን የህግ መከራከሪያ ነጥብን በተመለከተ በሥር ፍርድ ቤት እና በዘህ ችልት የተነሳውን ክርክር እንዱሁም ተያይዜ የቀረበውን ውሳኔ እና አግባብነት ያለውን ህግ መሰረት በማድረግ ተመልክተናል።
የወንጀል ህግ አንቀጽ 598 (1) ማንም ሰው ፈቃድ ሳይኖረው ወይም በማናቸውም ላላ ህገ ወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊ ዚጋን ለሥራ ወደ ውጭ አገር የላከ እንደሆነ፣ከአምስት ዓመት እስከ አሥር ዓመት ሉደርስ በሚችል ጽኑ እሥራት ና ከሃያ አምስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል ሲል ይደነግጋል።በዘህ ድንጋጌ መሰረት ፈቃድ ሳይኖር ወይም በህገወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊ ዚጋን ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወንጀል ሆኖ ተደንግጓል። በወንጀል ህግ አንቀጽ 598 (2) በዘህ ድርጊት ምክንያት የተላከችው ኢትዮጵያዊት በሰብአዊ መብቷ፣በህይወትዋ ወይም በአካልዋ ላይ ጉዲት የደረሰባት እንደሆ ነቅጣቱ ከአምስት ዓመት እስከ ሃያ ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ና ከሃምሳ ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ ይሆናል በሚል ተደንግጓል። ይህ ድንጋጌ ወደ ውጭ አገር የተላከችው ኢትዮጵያዊት በሰብአዊ መብቷ፣በአካል ደኅንትዋ ወይም በህይወትዋ ላይ የሚደርሰውን ጉዲት ታሳቢ በማድረግ ቅጣቱን ከፍ አድርጎ አስቀምጧል። የወንጀል ህግ ቁጥር 598 ንዐስ ቁጥር 1 እና 2 የሚለየው በተላከችው ኢትዮጵያዊት ላይ በደረሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣በህይወት ወይም በአካል ላይ የደረሰውን ጉዲት መሰረት በማድረግ ነው።
በያዛነው ጉዲይ የአሁን አመልካች የግል ተበዲይ ወ/ሮ እመቤት ይልማ ገ/የሱስ የተባለችውን ወደ ደባይ ከላካት በኃላ የግል ተበዲይ አሰሪዋ ጭንቅላቷ ላይ በብረትድስት በመምታት የፈነከተቻትና ያቆሰለቻት ስለመሆኑ የዐቃቤ ህግ ክስ ያስረዲል። ይህን በተመለከተ የግል ተበዲይ የመሰከረች ቢሆንም በህክምና ማስረጃ መረጋገጥ ሲገባው ያለመረጋገጡ የሚያጠራጥር እንደሆነ አመልካች አጥብቀው ይከራከራለ። በክርክር ሂደትም በግል ተበዲይ ላይ የአካል ጉዲት መድረስ ያለመድረሱ የህክምና ምርመራ እንዱደረግ ጠይቀው በፍርድ ቤት በኩል የተከለከለ መሆኑ የፍትህ መጓደልን ያስከተለ መሆኑን አመልካች በቅሬታነት አንስተዋል።በግል ተበዲይ ላይ የደረሰው የአካል ጉዲት ካለ የህክምና ምርመራ እንዱ ደርግ አመልከች መጠየቁን ተጠሪ ሳይክድ ቁስለ ከዲነ በኃላ የህክምና ምርመራ ላደረግ ስለማይችል የሥር ፍርድ ቤት ጥያቄውን ውደቅ ማድረጉ ተገቢ ነው በማለት ተጠሪ ተከራክሯል።
በመሰረቱ ከሳሽ በክሱ የጠቀሳቸውን ፍሬ ነገሮችን አግባብነት ባለው ማስረጃ የማስረዲት ሸክም ያለበት መሆኑ የማስረጃ ህግ መሰረታዊ መርህ ነው። ዐቃቤ ህግ በክሱ ላይ ያቀረበውን ፍሬ ነገር በአግባቡ ካላስረዲና ጥርጣሬን የሚፈጥር ከሆነ ተጠቃሚው ተከሳሽ ይሆናል ማለት ነው። ስለሆነም በተያዖው ጉዲይ አመልካች ፈቃድ ሳይኖራው የግል ተበዲይን ወደ ውጭ ሀገር መላኩ በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር በመሆኑ አመልካች ጥፊተኛ ላደረግ የሚገባውም በወንጀል ህግ ቁጥር 598 (1) እንጂ በንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት አይደለም።በመሆኑም አመልካች በወንጀል ህግ ቁጥር 598 (2) መሰረት ጥፊተኛ መደረጉ መሰረታዊ የሆነ ህግ ስህተት ነው ብለናል። ስለዘህ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 113 (2) መሰረት አመልካች የተከሰሰበትን የህግ አንቀጽ ቀይረን በወንጀል ህግ ቁጥር 598 (1) ሥር ጥፊተኛነው ብለን በወንጀል ህግ ቁጥር 195 (2) (ለ) (2) መሰረት ወስነናል።
ቅጣትን በተመለከተ የወንጀል ህግ ቁጥር 598 በቅጣት መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት ደረጃ የወጣለት ነው።አመልካች ጥፊተኛ የተደረገበት የወንጀል ህግ ቁጥር 598 (1) ደረጃ 1፣እርከን 21 ሥር ያርፊል።ለአመልካች በሥር ፍርድ ቤት የተያዖው አራት የቅጣት ማቅለያ ተቀንሶ እርከን 17 ላይያርፊል።በዘህ እርከን ላይ ያለው ፍቅድሥልጣን 3 ዓመት ከ3 ወር - 3 ዓመት ከ11 ወር ነው።
በዘህ ፍቅድ ሥልጣን መሰረት በአመልካች ላይ 3 ዓመት ከ3 ወር /ሶስት ዓመት ከሶስት ወር/ ጽኑ እስራት ቅጣት ተወስኗል።
በልላ በኩል ክርክሩ አሁን ባለበት ደረጃ አመልካች ከማረሚያ ቤት ከላከው አቤቱታ እና የአመልካችም ባለቤት በችልት በአካል ቀርባ ችልቱ አይቶ ካረጋገጠው አመልካች በከፍተኛ የደም ግፉት ሕመም ታማሚ መሆኑን፤ ባለቤቱም የካንሰር ታማሚ መሆንዋ እና ጡትዋ በካንሰር ሕመም ምክንያት የተቆረጠ እና የኬሞትራፑ መደሃኒት በመውሰድ ላይ የምትገኝ መሆኑን እና ሕጻናት ልጆቻቸውም በችግር ውስጥ የሚገኙ መሆኑን ተገንዛበናል። በመሆኑም በአመልካች ላይ የተላለፈውን ቅጣት አፈጻጸም በተመለከተ በዘህ ሰበር ሰሚ ችልት ታይቶ እልባት ሉሰጠው የሚገባ ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሰረታዊነት ቅጣት ሉገደብ የሚችለውም ጥፊተኛ የተባለን ሰው ለጥፊቱ መነሻ የሆኑትን ምክንያቶችን በጠቅላላው በመመልከት በጥፊተኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት ለጊዚው በገደብ እንዱታገድ በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል እንዱሁም ወደ መደበኛ ማህበራዊ ኑሮው ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑ በታመነ ጊዚ ስለመሆኑ የቅጣት ገደብን አስመልክቶ ከተደነገጉት የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች መገንዖብ ይቻላል። ይህንንም ተፈጻሚ ለማድረግ ፍ/ቤቶች ቅጣትን ለመገደብ የሚያስችለ የተለያዩ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት እንዲለባቸው፤ እነዘህም ሁኔታዎች ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ሆኖ ጠባዩም አደገኛነት እንደላለው የሚታመንበት እንደሆነ፤ጥፊቱ በመቀጮ፤ በግዳታ ስራ ወይም ከሶስት አመት የማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፊተኝነቱን ካረጋገጠ በኋላ ለወደፉት ጠባዩን ለማረም እንደሚችል እምነት ሉጣልበት የሚችል ሆኖ ሲገኝ ነው።
የአመልካች የዖወትር ባሕርይ መልካም መሆኑ፤ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት ማሕበራዊ ተሳትፍ የሚያደርግ መሆኑ እና የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆኑ በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ከመሆኑ አኳያ እነኚህ የአመልካቹ ግላዊ ሁኔታዎች በወንጀል ሕጉ ቅጣትን ለመገደብ ከተቀመጡት ቅድመሁኔታዎች ውስጥ አመልካች ከፉለን የሚያሟላ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። በልላ በኩል አመልካች በከፍተኛ የደም ግፉት ሕመም በመሰቃየት ላይ የሚገኝ እና ባለቤቱም በካንሰር ህመም ምክንያት ጡትዋ ተቆርጦ የኬሞትራፑ ሕክምና በመውሰድ ላይ የምትገኝ በመሆኑ እና ሕጻናት ልጆቻቸውም በችግር ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው በወንጀል ሕጉ ቅጣት ስለሚገደብበት ሁኔታዎች አስመልክቶ በተደነገጉት ድንጋጌዎች ብቻ ሳንገደብ ጉዲዩን እንደሚከተለው አይተናል።
አመልካች በተጠቀሰው ህመም ምክንያት ህክምና የሚከታተል ስለመሆኑም ከአቤቱታው ጋር ተያይዖው የቀረቡት የህክምና ማስረጃዎች ያረጋግጣለ። አመልካች በፈጸመው የወንጀል ድርጊት ጥፊተኛ ተብል ቅጣት ተወስኖበት በማረሚያ ቤት የሚገኝ ሲሆን የባለቤቱ መታመም ተጨምሮ በልጆቻቸው አስተዲደግና እንክብካቤ ላይ የሚያደርሰው ተጽዔኖ ከኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ህገ መንግሥት እንዱሁም ከዓለም አቀፍ የህጻናት መብቶች ኮንቬንሽን አንጻር እንዳት ይታያል? የሚለውን እንመልከት።
የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲዊ ሪፐብላክ ህገ መንግሥት አንቀጽ 36 (1) (ሐ) ሕፃናት ወላጆቻቸውን ወይም አሳዲጊዎቻቸውን የማወቅና የእነሱንም እንክብካቤ የማግኘት መብት አላቸው በማለት ይደነግጋል። በዘህ ድንጋጌ ከተቀመጡት ፍሬ ነገሮች ውስጥ አንደ ህፃናት የወላጆቻቸውን እንክብካቤ የማግኘት መብት ነው። የዘህ ድንጋጌ ዓላማ ህፃናት በአእምሯቸውና በአካላቸው ያልበሰለ ለጋ በመሆናቸው የወላጆች ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ መገመት አያዲግትም። ላላኛው መሰረታዊ ነገር ህፃናት ለአንድ አገር እድገትና ልማት የወደፉት ተስፊ እንዱሁም አገር ተረካቢዎች በመሆናቸው በመልካም አስተዲደግ ማደግ የሚገባቸው በመሆኑ ወላጆች በቅርበት ሆነው መከታተል፣ መቆጣጠርና ማሳደግ የሚገባቸው በመሆኑ ነው።
ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ በተጨማሪ ኢትዮጲያ በአዋጅ ቁጥር 10/1984 ያጸደቀችው ዓለምአቀፍ የሕጻናት መብት የቃልኪዲን ሰነድ ስምምነት ወላጆች በህፃናት አስተዲደግ እና እንክብካቤ ላይ ያላቸውን ሚና በግልጽ ያስቀምጣል። የዓለም አቀፈ የህፃናት መብቶች ስምምነት የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ቁጥር 44/25 እንደ ኤሮፒውያን አቆጣጠር 1989 የወጣው አንቀጽ 7 (1) ማንኛውም ህፃን ወላጆቹን የማወቅና ከወላጆቹ እንክብካቤ የማግኘት መብት እንዲለው ይደነግጋል። ለህፃናት አስተዲደርና አያያዛ ሁለቱም ወላጆች የጋራ ሃላፉነት ያለባቸው መሆኑን የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 18 (1/) ይደነግጋል። ይህ ድንጋጌም ለህፃናት አስተዲደግና አያያዛ ወላጆች ያላቸውን ኃላፉነት ያስቀምጣል።
የኮንቬንሽኑ አንቀጽ 18 (2) በዘህ ስምምነት የተመለከቱትን የህፃናት መብቶች ተፈጻሚነትን ለማረጋገጥ ህጻናትን የማሳደግ ሃላፉነታቸውን እንዱወጡ ለማድረግና ለማበረታታት ተዋዋይ አገሮች ለወላጆችና ለህጋዊ አሳዲሪዎች ተገቢውን እርዲታ ያደርጋለ ሲል ያስቀምጣል። ከእነዘህ ድንጋጌዎች የምንገነዖበው ለህፃናት መልካም አስተዲደግ መሰረቱ ወላጆች መሆናቸውን ነው።
በልላ በኩል የሕጻናት መብት የቃልኪዲን ሰነድ ስምምነትቱ አንቀጽ 3 ድንጋጌ እና የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 36/2 ድንጋጌ ሕጻናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰደበት ጊዚ በመንግሥታዊ ወይም በግል የበጎ አድራጎት ተቋሞች፤ በፍርድ ቤቶች፤ በአስተዲደር ባለስልጣኖች ወይም በሕግ አውጪ አካላት የሕጻናት ደሕንነት በቀደምትነት መታሰብ ያለበት መሆኑን ይደነግጋል።
በያዛነው ጉዲይ ከላይ እንደተገለጸው አመልካች በፈጸመው ወንጀል ምክንያት የቅጣት ውሳኔ ተላልፍበት ቅጣቱን በማረሚያ ቤት በመሆን በመፈጸም ላይ የሚገኝ ሲሆን ባለቤቱ ደግሞ በካንሰር ሕመም ምክንያት ጡትዋ ተቆርጦ የኬሞቴራፑ መድሃኒት በመውሰድ ላይ የምትገኝ በመሆኑ በሕፃናት ልጆቻቸው ላይ የሚደርስባቸውን ቁሳዊም ሆነ ኅሉናዊ ጫና መገመት አያዲግትም።
የአመልካች ልጆች አንድም አባታቸው በማረሚያ ቤት የሚገኝ በመሆኑ እናታቸውም በሕመም ምክንያት በሕክምና ላይ የምትገኝ በመሆኑ ምክንያት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገመንግስት እና አገሪቱ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ እና አሕጉራዊ የሕፃናት መብቶች ስምምነቶች ሕጻናቱ የተጠበቀላቸውን የወላጆቻቸውን እንክብካቤ የማግኘት መብት የሚያሳጣቸው ነው። በመሆኑም በአመልካች እና በባለቤቱ ላይ በተከሰተው ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ከአብራካቸው በተወለደ ህፃናት ላይ የሚደርስባቸውን ችግር ወይም የሕይወትና የኑሮ ጫና፣ እንዱሁም የኅሉና ጉዲት ታሳቢ በማድረግ ሕጋዊ መፍትሓ መስጠት የሚያስፈልግ ሆኖ ተገኝቷል።
አመልካች በፈጸመው ወንጀል ምክንያት በማረሚያ ቤት በመሆኑ እና ባለቤቱም በካንሰር ሕመም ምክንያት ጡትዋ ተቆርጦ የኬሞቴራፑ መድሃኒት በመውሰድ ላይ የምትገኝ በመሆኑ በሕፃናት ልጆቻቸው ላይ የሚደርሰውን ቁሳዊም ሆነ ኅሉናዊ ጫና ለማስቀረት ሲባል እንዱሁም ሕጻናቱ የወላጆቻቸውን እንክብካቤ እና ድጋፍ አግኝተው እንዱያድጉ ለማድረግ ሲባል፤ ፍ/ቤቶችም የሕጻናት ደሕንነት በቅድሚያ የማረጋገጥ ሕገመንግስታዊ ግዳታ ያለባቸው በመሆኑ በአመልካች ላይ የተወሰነውን ቅጣት በመገደብ ህፃናቱ ተገቢውን የወላጅ እንክብካቤ እንዱያገኙ ለማድረግ ያስችል ዖንድ የተወሰነውን ቅጣት እንዲይፈጸም ለማገድ በወንጀል ህግ ቁጥር 194 መሰረት የሚከለክል ህጋዊ ምክንያት ያለመኖሩን ተመልክተናል። ፍርድ ቤት በአንድ ሰው ላይ የቅጣት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ የቅጣት ውሳኔውን ለመገደብ እንደሚችልና የቅጣት ውሳኔው ሉገደብ የሚገባው ምን መሰረታዊ ሁኔታዎች ሲሟለ እንደሆነ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 192 ላይ መሰረታዊ መርሁ ተቀምጧል። ስለሆነም በአመልካች ላይ የተወሰነውን ቅጣት ለመገደብ የሚከለክል ሕጋዊ ምክንያት ባለመኖሩ ቅጣትን መገደብን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ውሣኔ ከተሰጠበት ጊዚ ጀምሮ አመልካች ያልፈፀመው ቀሪው የእስራት ቅጣት በሶስት ዓመት የጊዚ ገደብ ሉገደብለት ይገባል በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ.ም እና ሕዲር 10 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በቀን 25/08/11 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሻሽሎል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት አመልካች ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በወንጀልሕግቁጥር 598 (1) ነው በማለት ወስነናል። በዘሁ መሰረት በአመልካች ላይ የተላለፈው የቅጣት ውሳኔ ተሻሽል በሶስት ዓመት ከሶስት ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጣ እና ቀሪው የእስራት ቅጣት አፈጻጸም በሶስት ዓመት የጊዚ ገደብ እንዱገደብ በማለት ወስነናል።
የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት የገንዖብ መቀጮ ቅጣት በዘህ ውሳኔ አልተነካም።
ትዔዙዛ
አመልካች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 197 መሰት የብር 3000 / ሶስት ሺህ ብር /መተማመኛ ዋስትና እንዱያስይዛ ታዝል።ይኸው ሲፈጸም የሚመለከተው ማረሚያ ቤት አመልካችን ከእሥር እንዱለቅ ታዝል።
የውሳኔው ግልባጭ አመልካች ለሚገኝበት ማረሚያ ቤት እና ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
አመልካች በማረሚያ ቤት የሚገኝ በመሆኑ የዘህ ውሳኔ ግልባጭ በፍ/ቤቱ መልእክት ክፍል በኩል ለአመልካች ይድረሰው።
No topics extracted.