ቅጣት ሉገደብ የሚችለው ጥፊተኛ የተባለን ሰው ለጥፊቱ መነሻ የሆኑትን ምክንያቶችን በጠቅላላው በመመልከት፤ የወንጀለ ከባድነት/ the gravity of the crime/ በማየት፤ በጥፊተኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት ለጊዚው በገደብ እንዱታገድ በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል እንዱሁም ወደ መደበኛ ማህበራዊ ኑሮው ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑ ሲታመን እና በአጠቃላይ ቅጣት ስለሚገደብባቸው ሁኔታዎች በወንጀል ሕጉ የተቀመጡት መስፈርቶች መሟላታቸው ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 192፣194፣196/2/ እና 197
No summary available.
የሰበር መዛገብ ሕዲር 22 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች/ቾች፡- መላኩ ያዔቆብ፡- አልቀረቡም።
ተጠሪ/ዎች፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ፡- ዐ/ህግ ኤፍሬም ደመቀ ቀረቡ።
መዛገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች በጠበቃው አማካኝነት የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፍባቀረበው የሰበርአቤቱታየስር ፍ/ቤቶች የአመልካችን የቅጣት ገደብ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለቱ ነው።
የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በስር ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ይዖት በአጭሩ፡- አመልካች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543/2 ድንጋጌን በመተላለፍ በቀን 08/2010 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በንፊስስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዲ 01 ልዩ ቦታው ሲፈን ተብል በሚጠራው አካባቢ የሰ.ቁ ኮድ 2-7769 አ.አ የሆነ ሞተር ሳይክል እያሽከረከረ ከቀኝ ወደ ግራ በማቋረጥ ላይ የነበሩትን ሟች ሸዋ ቀና ጥላሁን ቅድሚያ ሰጥቶ ማለፍ ሲገባው ሟችን ቅድሚያ በመከልከል በሞተር ሳይክለ የፉት ለፉት አካል የግራ ጎናቸውን በመግጨት በሞተሩ አካል ሟችን ወደፉት ጎትተቶ በመውሰድ አስፒልት ላይ እንዱወድቁ በማድረግ ሟች ስለታማ በሆነ ግዐዛ ቁስ አካል በራሳቸው፤ በደረታቸው እና በሆዲቸው ላይ በደረሰባቸው ጉዲት ምክንያት በቀን 09/08/2010 ዓ.ም ሕይወታቸው አንዱያልፍ ያደረገ በመሆኑ በፈጸመው በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
አመልካች ክሱ ተነቦለት ክሱን ሳይቃወም ወንጀለን የፈጸመ እና ጥፊተኛ መሆኑን እና ቅድሚያ በመከልከል ሟችን የገጫቸው መሆኑን በመግለጽ የእምነት ክሕደት ቃለን ሰጥቷል። ዓቃቤሕግ ባመነው መሰረት ጥፊተኛ ይባልልን በማለት በገለጸው መሰረትም ፍ/ቤቱ አመልካች ድርጊቱን የፈጸመ ስለመሆኑ ሙለ በሙለ አምኗል በማለት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 543/2/ ጥፊተኛ ብልታል።
ቅጣቱንም በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማስላት በዓቃቤሕግ በኩል የቀረበ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት የለም በማለት፤ አመልካች የዖወትር ባሕርይው መልካም መሆኑ፤ ክሱን ያመነ መሆኑ ፤ ከሟች ቤተሰቦች ጋር በመታረቅ ካሳ የከፈለ መሆኑን የሚያሳይ የእርቅ ስምምነት የቀረበ በመሆኑ፤ የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆኑ፤ በማሕበረሰቡ በጎ ተግባራት እና ልማት ተሳታፉ መሆኑ፤ አደጋው ከደረሰ በኋላ ሟችን ወደ ሕክምና ቦታ መውሰደን እና ለመርማሪ ፕሉስ እጁን መስጠቱ በድምሩ ስድስት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን በመያዛ በአንድ ዓመት ከሁለት ወር ቀላል እስራት እና በብር 500 መቀጮ እንዱቀጣ የወሰነ ሲሆን የገደብ ጥያቄውን በሚመለከት ግን ከአደጋው አሳሳቢነት አንጻር ተቀባይነት የለውም በማለት ወድቅ አደርጎታል። አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኘ ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይሀን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- አመልካች ፕሉስ ጣቢያም ሆነ ፍርድ ቤት በመቅረብ ቃላን በማመን ሰጥቻለሁ፤
መጸጸቴንም አሳይቻለሁ፤ የሟችን ሕይወት ለማትረፍ ኮንትራት ታክሲ ይዤ ወደ ሕክምና ቦታ ወስጃለሁ፤ አደጋው ከደረሰ በኋላም ሞተር ሳይክለን በመሸጥ የሟችን ቤተሰብ ክሻለሁ፤ አመልካች ባለትዲር ስሆን ቅጣቱ በተላለፈበት ወቅትም ባለቤቴ የ 9 ወር እርጉዛ ነበረች፤ የሶስት ልጆች አባት እና የቤተሰብ አስተዲዲሪም ነኝ፤ የወንጀል ሪከርድ የለኝም፤ ከሟች ቤተሰቦች ጋርም የታረቅኩ ሲሆን በገደብ ብለቀቅ የገደቡን ሁኔታ በሚገባ እንደሟሟላ አረጋግጫለሁ። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች አመልካች ቅጣቱ እንዱገደብ ያቀረብኩትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች የተከሰሰበትን ወንጀል አምኖ የጥፊተኝነት ውሳኔ በተሰጠበት፤ ከሟች ቤተሰብ ጋር እርቅ ፈጽሞ በካሰበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤት የቅጣት ገደብ ጥያቄውን አሁን ካለው የአደጋው አሳሳቢነት አንጻር ተቀባይነት የለውም በሚል ያለፈበትን አግባብነት በወንጀል ሕግ ቁጥር 192 እና ተከታይ ድንጋጌዎች እና ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ..መ.፤85596 ከሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ጋር በማገናዖብለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ፡- የስር ፍ/ቤት ከወንጀለ አፈጻጸም እና እየደረሰ ካለው የትራፉክ አደጋ አንጻር የአመልካች ቅጣት መታገድ የጥፊተኛውን ጸባይ ለማረም በቂ አይደለም፤ ላልችንም አያስተምርም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል፤ አመልካቸ ከፈጸመው የወንጀል ድርጊት ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. የቅጣት መገደብ እና አለመገደብ ነባራዊ ሁኔዎች ታይተው የወንጀል ሕግ ግብን ከማስፈጸም አንጻር ላሆን እንዱሚገባ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ የስር ፍ/ቤት አሁን ካለው የአደጋው አሳሳቢነት አንጻር ቅጣቱ ሉገደብ አይደገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ስለሆነ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸዉ ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ያስቀርባል ተብል የተያዖውን ጭብጥ ከግራቀኙ ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
አመልካች የቀረበበትን ክስ ሙለ በሙለ ያመነ እና በድርጊቱም መጸጸቱን እና ጥፊተኛ ልባል የሚገባ መሆኑን በመግለጽ የእምነት ክሕደት ቃለን የሰጠ መሆኑን፤ ፍ/ቤቱም አመልካች ባመነው መሰረት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 543/2 ጥፊተኛ ያለው መሆኑን፤ አመልካች አደጋው ከደረሰ በኋላ ሟችን ወደ ሕክምና ቦታ የወሰደ እና ለመርማሪ ፕሉስ እጁን የሰጠ መሆኑ፤ የዖወትር ባሕርይው መልካም መሆኑ፤ የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆኑ፤ በማሕበረሰቡ በጎ ተግባራት እና ልማት ተሳታፉ መሆኑ፤ ከሟች ቤተሰቦች ጋር በመታረቅ ካሳ የከፈለ መሆኑን የሚያሳይ የእርቅ ስምምነት የቀረበ በመሆኑ፤ የሟች ባለቤትም በችልት ቀርበው ከአመልካች ጋር የታረቁ መሆኑን፤ አመልካች ሁለንም እርዲታ ያደረገላቸው እና አሁንም እያገዙቸው ያለ መሆኑን በመግለጽ ቃላቸውን የሰጡ መሆኑን በስር ፍ/ቤት ከተረጋገጠው ፍሬነገር መገንዖብ ይቻላል።
የስር ፍ/ቤት የአመልካችን የገደብ ጥያቄ ውድቅ ያደረገው አመልካች ቅጣቱ እንዱገደብ ያቀረበው ምክንያት ቅጣት ስለሚገደብባቸው ሁኔታዎች በሕጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟለ መሆን አለመሆኑን መዛኖ ሳይሆን የአመልካች የቅጣት ገደብ ጥያቄ ከአደጋው አሳሳቢነት አንጻር ተቀባይነት የለውም በማለት መሆኑን ከውሳኔ ይዖት መገንዖብ ችለናል።
በመሰረቱ የወንጀል ሕጉ ዓላማ ወንጀል እንዲይፈጸም ማድረግ ሲሆን ይህንንም የሚያደርገው ስለወንጀልች እና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፤ ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነ ጊዚ ደግሞ ወንጀል ፈጻሚዎች ተቀጥተው ላላ ወንጀል ከመፈጸም እንዱቆጠቡ እና ለላልች ማስተማሪያ እንዱሆኑ ወይም እንዱታረሙ በማድረግ እንደሆነ ከወንጀል ሕጉ ዓላማ እና ግብ መገንዖብ ይቻላል።
ቅጣት ሲገደብ የፍርደ ውሳኔ በወንጀለኞች መዛገብ ላይ ተመዛግቦ ከላላው ውጤት ጋር ነዋሪ የሚሆን በመሆኑ ቅጣትን መገደብ በወንጀለኛው ላይ ቅጣት እንዲይፈጸም የማድረግ ውጤት ብቻ ያለው ሳይሆን ወንጀለኛው ዲግም ጥፊት ከመፈጸም እንዱታቀብ የማድረግ ውጤት ስላለው ቅጣትን መገደብ የወንጀል ሕጉ ዓላማ እና ግብ ከሚሳካባቸው መንገድች አንደ ነው።
ቅጣት ሉገደብ የሚችለውም ጥፊተኛ የተባለን ሰው ለጥፊቱ መነሻ የሆኑትን ምክንያቶችን በጠቅላላው በመመልከት በጥፊተኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት ለጊዚው በገደብ እንዱታገድ በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል እንዱሁም ወደ መደበኛ ማህበራዊ ኑሮው ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑ በታመነ ጊዚ ስለመሆኑ የቅጣት ገደብን አስመልክቶ ከተደነገጉት የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች መገንዖብ ይቻላል። ይህንንም ተፈጻሚ ለማድረግ ፍ/ቤቶች ቅጣትን ለመገደብ የሚያስችለ የተለያዩ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት እንዲለባቸው፤ እነዘህም ሁኔታዎች ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ሆኖ ጠባዩም አደገኛነት እንደላለው የሚታመንበት እንደሆነ፤ጥፊቱ በመቀጮ፤ በግዳታ ስራ ወይም ከሶስት አመት የማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፊተኝነቱን ካረጋገጠ በኋላ ለወደፉት ጠባዩን ለማረም እንደሚችል እምነት ሉጣልበት የሚችል መሆኑና በዘህ ውሳኔ ብቻእስከ መጨረሻው ሉሻሻል የሚችል መሆኑን ‘ያመነበት’ እንደሆነ፤ እንዱሁምጥፊተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈፀሙ በፉት ለተወሰነ ጊዚ ቅጣቱ ታግድለት አመለ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፊት ከማድረግም የሚታገድ መሆኑናስለጠባዩም መሻሻል አንድ ፅኑ ማስጠንቀቂያ ብቻ የሚበቃ መሆኑ ፍርድ ቤቱ ያመነበት እንደሆነ ቅጣቱ ከአፈፃፀም ታግድ እንዱቆይ ሉያዛ የሚችል ስለመሆኑ ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 192 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ይዖት መገንዖብ ይቻላል።
በልላ በኩል በጥፊተኛው ላይ የተወሰነው ቅጣት እንዲይገደብ ሉያደርጉ የሚችለ በሕጉ የተቀመጡ ሁኔታዎች ያለ መሆኑን፤እነኚህም ሁኔታዎች ጥፊተኛው ከዘህ በፉት የጽኑ እሥራት ቅጣት ወይም ከሦስት ዓመት የሚበልጥ ቀላል እሥራት ቅጣት ተፈርድበት እንደሆነ እና እንደገናም በተከሰሰበት ወንጀል ከእነዘህ ቅጣቶች አንደ የሚወሰንበት እንደሆነ ወይም ጥፊተኛው ከዘህ ቀደም ያልተቀጣ ሆኖ በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት አመት የበለጠ የጽኑ እሥራት ቅጣት የሚፈረድበት እንደሆነ ነው በማለት የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194 ድንጋጌ ላይ በዛርዛር ተመልክቷል። በሕጉ ከተመለከቱት ከእነኚህ ሁኔታዎች ውጪ የወንጀለ ከባድነት ወይም ጥፊተኛው ያደረሰው አደጋ አሳሳቢነት ቅጣት እንዱገደብ ለማድረግ የሚያስችል ምክንያት ነው ተብል በሕጉ ላይ አልተገለጸም። በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 196/2 የወንጀለ ከባድነት / the gravity of the crime /፤ በወንጀል ድርጊት መደጋገም ሉያደርስ የሚችለውን ጉዲት እና በጥፊተኛው ላይ ሉጣልበት የሚችለው እምነት ከግምት ውስጥ መግባት አለበት የሚባለው ፍ/ቤቱ ቅጣቱ እንዱገደብ አቋም ከያዖ በኋላ ቅጣቱ ተገድቦ የሚቆይበትን የፈተና ጊዚ ለመወሰን / …..
to fix the probation period ….. / እንጂ ጥፊተኛው ፈጽሞታል ከተባለው ወንጀል ወይም አድርሶታል ከተባለው አደጋ ጋር እየተገናዖበ ቅጣትን ለመገደብ ሉመዖን ይገባል ተብል እንደመስፈርት የተቀመጠ አይደለም።
በመሰረቱ ከባድ ወንጀልች ከፍተኛ ቅጣት የሚያስከትለ ናቸው። የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194/1/ለ ድንጋጌም ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ጥፊተኛው አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት የበለጠ የጽኑ እሥራት ቅጣት የሚፈረድበት እንደሆነ ቅጣትን ማገድ አይቻልም በማለት በግልጽ መደንገጉ ከመነሻውም ቢሆን ከባድ ወንጀል የፈጸመ ወንጀለኛ በሚጣልበት ከፍተኛ የቅጣት መጠን ምክንያት ቅጣት ሉገደብለት የማይችል በመሆኑ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 196/2 ላይ የተገለጸው ‘የወንጀለ ክብደት’ የሚለው ቃል ለፈተናው ጊዚ አወሳሰን ታሳቢ የሚደረግ መሆኑን የሚያሳይ እንጂ ጥፊተኛው የፈጸመው ወንጀል አሳሳቢነትን የሚመለከት አለመሆኑን እና ቅጣቱን ለመገደብበመመዖኛነት የተቀመጠ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው።
በልላ በኩል በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 197 የተመለከቱት ቅድመ-ሁኔታዎች ፈተና የሚሰጥባቸውን ሁኔታዎች እንደሆኑ ከድንጋጌው ርዔስ መገንዖብ የሚቻል ሲሆን እነኚህ ሁኔታዎች መሟላት አለመሟላታቸው ሉረጋገጥ የሚችለው ፍ/ቤቱ ከተከሳሹ የቀድሞ ታሪክ፤ የጠባዩ እና የዓመለ አካሄድ በመነሳት ቅጣቱን መገደብ እንዲለበት ሲያምን እና ጥፊተኛው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 197 ላይ የተመለከቱትን ቅድመ-ሁኔታዎች እንደሚያሟላ ማረጋገጫ እንዱሰጥ በማድረግ እንደሆነ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 192፤196/1 እና 197 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዖብ ይቻላል። ጥፊተኛው በድንጋጌው የተመለከቱትን ቅድመ- ሁኔታዎች ማሟላት አለሟሟላቱን ማረጋገጥ የሚቻለውም ጥፊተኛው ራሱ በራሱ ተነሳሽነት በሕጉ የተመለከቱትን ቅድመሁኔታዎች ያሟላ ሆኖ በተገኘ ጊዚ ወይም ፍ/ቤቱ ጥፊተኛው በሕጉ የተቀመጡትን ቅድመሁኔታዎች እንዱያሟላ እድል በሰጠው ጊዚ ነው።
ፍ/ቤቱ በጥፊተኛው ላይ የሚጣለውን ቅጣት ለጊዚው ማገድ ለወደፉቱ ጥፊቱን ለማረም እንደሚችል ሉያምን ወይም ላያምን የሚችለው የጥፊተኛውን የቀድሞ ታሪኩ፤ የጠባዩ እና የዓመለ አካሄድ አስመልክቶ በችልቱ የተረጋገጡትን እውነታዎች መነሻ በማድረግ ሲሆን ፍ/ቤቶች በሕግ እና በተገቢ ምክንያት የተደገፈ ውሳኔ መስጠት ያለባቸው ከመሆኑ አመልካች ቅጣቱን ለማስገደብ ያቀረባቸው ምክንያቶች ፍ/ቤቱን የሚያሳምኑ ናቸው ወይም አይደለም ለማለት ሕግን መሰረት በማድረግ እና አግባብነት ያለውን ምክንያት በመስጠት ላሆን ይገባል።
በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች የቀረበበትን ክስ ሙለ በሙለ ያመነ እና በድርጊቱም መጸጸቱን እና ጥፊተኛ ልባል የሚገባ መሆኑን በመግለጽ የእምነት ክሕደት ቃለን የሰጠ መሆኑን፤ ፍ/ቤቱም አመልካች ባመነው መሰረት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 543/2 ጥፊተኛ ያለው መሆኑን፤ አመልካች አደጋው ከደረሰ በኋላ ሟችን ወደ ሕክምና ቦታ የወሰደ እና ለመርማሪ ፕሉስ እጁን የሰጠ መሆኑ፤
የዖወትር ባሕርይው መልካም መሆኑ፤ የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆኑ፤ በማሕበረሰቡ በጎ ተግባራት እና ልማት ተሳታፉ መሆኑ፤ ከሟች ቤተሰቦች ጋር በመታረቅ ካሳ የከፈለ መሆኑን የሚያሳይ የእርቅ ስምምነት የቀረበ በመሆኑ፤ የሟች ባለቤትም በችልት ቀርበው ከአመልካች ጋር የታረቁ መሆኑን፤
አመልካች ሁለንም እርዲታ ያደረገላቸው እና አሁንም እያገዙቸው ያለ መሆኑን በመግለጽ አረጋግጠዋል። እነኚህ ሁኔታዎች የተከሳሹን የቀድሞ ታሪክ፤ የጠባዩን እና የዓመለን አካሄድ ለመመዖን የሚያስችለ እና ቅጣቱ ቢገደብ የአመልካችን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል እንዱሁም ወደ መደበኛ ማህበራዊ ኑሮው ለመመለስ የሚያስችለ አሳማኝ ሁኔታዎች ናቸው።
አመልካች ቅጣቱ እንዱገደብለት ያቀረባቸው ምክንያቶች የአመልካቹን የቀድሞ ታሪክ፤ የጠባዩን እና የዓመለን አካሄድ ለመመዖን የሚያስችለ አሳማኝ እና በአመልካች ላይ የተጣለው ቅጣት ታግድ ቢቆይ ዲግም ጥፊት ከመፈጸም እንዱቆጠብ ለማድረግ የሚያስችለ ሁኔታዎች ሆነው ሳለ ቅጣቱን መገደብ ሲገባው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194 ቅጣት እንዲይገደብ ለማድረግ የሚያስችለ ሁኔታዎች ውስጥ ያልተቀመጠውን መስፈርት መሰረት በማድረግ የአመልካች የቅጣት ገደብ ጥያቄ ከአደጋው አሳሳቢነት አንጻር ተቀባይነት የለውም በማለት የአመልካችን የገደብ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ በወንጀል ሕጉ ቅጣት ስለሚገደብባቸው የተቀመጡትን ቅድመሁኔታዎች ያላገናዖበ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም የስር ፍቤቶች በአመልካች ላይ ያስተላለፈት የአንድ ዓመት ከሁለት ወር ቀላል እስራት ቅጣት በሁለት ዓመት ገደብ ይቆይ በማለት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 192 እና 197/1 መሰረት ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ታሕሳስ 04 ቀን 2011 ዓ.ም በአመልካች ላይ ያስተላለፈትን የቅጣት ውሳኔ በማጽናት አፈጻጸሙን በሚመለከት ግን ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት ቀሪ እስራት ሳይፈጸም ለሁለት ዓመት እንዱገደብ በማለት ወስነናል።
ትዔዙዛ አመልካች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 197 መሰት የብር 1500 / አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር /መተማመኛ ዋስትና እንዱያሲዛ ታዝል።ይኸው ሲፈጸም የሚመለከተው ማረሚያ ቤት አመልካችን ከእሥር እንዱለቅ ታዝል።
መዛገቡ ተዖግቷል። ይመለስ
No topics extracted.