አንድ ከባድ የአካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ፈፅመሃል ተብል የተከሰሰ ተከሳሽ ድርጊቱን ለመፈጸም የተጠቀመበት መሳሪያ የላለ መሆኑ በማስረጃዎች በተረጋገጠበት ሁኔታ በከባድ የአካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ጥፊተኛ ልባል የማይገባ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 555 ፣556(1)
No summary available.
የሰበር መዛገብ ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በዔውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካቾች፡- አቶ ይገዘ ቡርዚ ተጠሪ፡- የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ፍትህ ቢሮ ዓቃቤ ህግ መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ወንጀልን ይመለከታል። አከራካሪው ጉዲይ የተጀመረው በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች ላይ በቀረበው ክስ መነሻነት ነው። የክሱ ይዖትም፡- አመልካች የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 555(1) የተመለከተውን በመተላለፍ መስከረም 17 ቀን 2009 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዚ በውሃ ምንጭ ቀበላ እባያ ግሮሰሪ ውስጥ የግል ተበዲይ ፀጋ ወይሾ የተባለውን በቦክስና በቴስታ ግራ በኩል አገጩን በመምታት የግራ መንጋጋ አጥንት እንዱሰበር በማድረጉ ከባድ የአካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ክስ ቀርቦበታል።
አመልካች የእምነት ክህደት ቃለ ሲጠየቅ ድርጊቱ አለመፈፀሙ ክድ ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የዐቃቤ ሕግ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ አመልካች የተከሰሰበት የህግ ዓንቀፅ በመቀየር የወንጀል ሕግ አንቀፅ 556(1) እንዱከላከለ ብይን ሰጥቷል።
ተከሳሾች መከላከያ ማስረጃ አቅርበው ያሰሙ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጉዲዩ ከመረመረ በኋላ የቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃ በመመዖን ተከሳሽ የቀረበበት ክስ ተከላክሎል በማለት በነፃ እንዱሰናበት ወስኗል።
የአሁኑ ተጠሪ በተሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ቅሬታው ባለመቀበል ሰርዜታል። በመቀጠል ተጠሪ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻር አመልካች በዓ/ህግ የቀረበበት ወንጀል የፈፀመ መሆኑ ተረጋግጧል።ተከሳሽ ባቀረበው የመከላከያ ምስክሮችም አልተከላከለም በማለት ክስ በቀረበበት የህግ ዓንቀፅ ወንጀል ህግ ዓንቀፅ 555(ሐ) ስር የጥፊተኛነት ውሳኔ ሰጥቷል ። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኋላ ቅጣቱን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማስላት አመልካችን በሁለት አመት ከሶስት ወር ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በመቃወም ለማሳረም ነው።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት ተፈፀመ ያለውን ስህተት በመዖርዖር ያቀረበ ሲሆን የቅሬታው መሰረታዊ ነጥቦች ሲጠቃለለ፡- የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ወንጀል መፈፀሜ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እንዱሁም የግራ ቀኙ ማስረጃ የመዖነበት አግባብ እና የስር ሁለቱም ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ለመሻር የሰጠው ምክንያት መሰረታዊ የማስረጃ ምዖና መርህ ያልተከተለ በመሆኑ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑ ገልፀው ሉታረም እንደሚገባ መጠየቃቸው የሚያሳይ ነው። ጉዲዩ ተመርምሮ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመወሰኑ ተጠሪ ቀርቦ በፅሁፍ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ይዖት ያለው ሲሆን ይህ ችልትም አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ፣ ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ ያስቀርባል በማለት የተያዖው ጭብጥ ብቻ መርምሮታል። እንደመረመርነው መዛገቡ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል በተያዖው ጭብጥ በአሁኑ አመልካች ተፈፀመ የተባለው ድርጊት አፈፃፀም እና ከተጠቀሙት መሳሪያ አንፃር ጥፊተኛ መባል ያለበት በወንጀል ህግ አንቀጽ 555(ሐ) ነው ?ወይስ የወንጀል ህግ አንቀጽ 556 (1) መሰረት ነው ? በሚል አግባብ ሲታይ አመልካች በቦክስ አና በቴስታ በመምታት በግል ተበዲዩ አካል ላይ ጉዲት ስለማድረሱ በሥር ፍርድ ቤቶች በተደረገው ክርክር በማስረጃዎች የተረጋገጠ ሲሆን ዋናው ምላሽ የሚያስፈለገው ጉዲይ ግን በማስረጃዎች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር አንጻር አግባብነት ያለውን የወንጀል ህግ አንቀጽ የመለየቱ ጉዲይ ነው።
በተያዖው ጉዲይ ላይ በስር ፍርድ ቤት የተሰሙት የዓ/ህግ ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል ሲታይ አመልካች በክሱ በተገለጸው ቦታና ጊዚ በተከሳሽ ግሮሰሪ እየተዛናኑ እያለ ሽንት ቤት ደርሶ ሲመለስ ባጃጅ ውስጥ ታሞ የተኛውን ጓደኛቸውን ተከሳሽ ውጣ ሲል ባጃጁ የኛ ነው ብል የግል ተበዲይ ሲናገረው ተከሳሹ አንድ ጊዚ በግራ ጉንጩ ላይ በቦክስ እና በቴስታ የመታው መሆኑ መስክረዋል።
በአንፃሩ የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮች የላሜራ ብረት መትቶት ጉዲት የደረሰበት መሆኑ ገልፀው የምስክርነት ቃል ሰጥተዋል፣ ጉዲቱን የሚያመለክት የሃኪም ማስረጃም ቀርቦ ከመዛገቡ ጋር የተያያዖ መሆኑ ተገንዛበናል። ስለሆነም ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር አመልካች በክሱ በተገለጸው የቦታ፣የጊዚ እና የወንጀል አፈጻጸም ዛርዛር መሰረት የግል ተበዲይ የሆነውን ፀጋ ወይሶ በቦክስ እና በቴስታ የመታው መሆኑ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ መረጋገጡን፣በአመልካቹ በኩል ቀርበው የተሰሙት የመከላከያ ምስከሮችም በዐቃቤ ሕግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ የተመሰከረውን የወንጀል ፍሬ ነገር ለማስተባበል ያልቻለ ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
አሁን ከዘህ ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው ጉዲይ በአመልካች መፈጸሙ የተረጋገጠው የወንጀል ተግባር የሚሸፈነው በወንጀል ህግ አንቀፅ 555 ስር ነው? ወይስ በወንጀል ህግ አንቀፅ 556(1) ስር ነው? የሚለው ነጥብ ነው:: በተያዖው ጉዲይ ድርጊቱ የተፈፀመው እና አመልካች ጉዲት ለማድረስ የተጠቀመበት መሳሪያ በተመለከተ በእርግጥም የከባድ የአካል ጉዲት ወንጀል ነው? ወይስ የቀላል የአካል ጉዲት የሚያቋቋም ነው? የሚለውን መለየት እንዱቻል ለድርጊቱ አፈፃፀምና አመልካች የተጠቀሙበት መሳሪያ ድርጊቱ የተፈፀመበት የተበዲይ የሰውነት ክፍል እንዱሁም የወንጀለ አፈፃፀም ሁኔታ መታየት ያለበት ነው።
በመሰረቱ አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀለን የሚያቋቁሙት ህጋዊ ግዘፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 414/1996 የወንጀል ህጉ አንቀፅ 23(2) በግልፅ ተደንግጓል። እንግዱህ አንድን ድርጊት ወንጀል ነው ብል ለመወሰን ህጋዊ፣ ግዘፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች ተጣምረው መገኘት የግድ ይላል። ህጋዊ ፍሬ ነገሮች የሚባለት ደግሞ ለጉዲዩ አግባብነት አለው ተብል የተጠቀሰውን ድንጋጌ ለማቋቋም ሙለ በሙለ መሟላት ያለባቸውን ነጥቦች ሲሆን ግዘፊዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች የሚባለት ደግሞ እንደየቅደም ተከተላቸው ከድርጊት ማድረግ ወይም አለማድረግና ከሀሳብ ክፍል ጋር በህጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች የሚመለከቱ መሆናቸው የሚታወቅ ነው። ላላው ወንጀል ክርክር አንድ ሰው ክሱን እንዱከላከል ወይም ጥፊተኛ ልባል የሚችለው ዐቃቤ ህግ በህጉ የተጣለበትን የማስረዲት ግዳታውን የተወጣ መሆኑን ሲረጋገጥ መሆኑም የሚታወቅ ነው። የወ/መ/ህ/ስ/ስ/ህ/ቁ 141 ድንጋጌ አቀራረፅና ይዖት ከወ/መሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 111 እና 112 ድንጋጌዎች ተጣምሮ ሲታይም በወንጀል ጉዲይ ዐቃቤ ህግ እንደክሱ በበቂ ሁኔታ የማስረዲት ግዳታ ያለበት መሆኑን የሚያስገነዛብ ነው። ይህን በህጉ የተመለከተውን የማስረጃ መለኪያ መስፈርት መሰረት በማድረግ የወንጀል ድርጊቱ መፈፀሙን የፈፀመውን ሰው ማንነት እና በአፈፃፀሙ ላይ የነበረውን የተሳትፍ ደረጃ ማረጋገጥ የግድ ይላል። ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን የአእምሮ ክፍል ሉያስረዲ የሚችለው የድርጊቱን አፈፃፀም በማረጋጥ ሲሆን ከድርጊቱ አፈፃፀም ድርጊት ፈፃሚው ወንጀለን ሲፈፅም የነበረውን የአእምሮ ሁኔታ ፍርድ ሰጪው አካል ሉረዲ የሚችል መሆኑም የሚታመን ነው።
ይህንኑ የህጉን ይዖትና መንፈስ ይዖን ወደዘህ ጉዲይ ስንመለስም ከመዛገቡ ይዖት ለመረዲት እንደተቻለው ተፈፀመ የተባለው ድርጊት አመልካች ስለመፈፀሙ የተረጋገጠ ጉዲይ ሲሆን አመልካች ወንጀለን ለመፈፀም የተጠቀመበት መሳሪያ የላለና በቦክስና በቴስታ የመታ በመሆኑ ከቀረቡት የዓ/ህግ ማስረጃዎች የተረጋገጠ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
ታስቦ የሚፈፀም ከባድ የአካል ጉዲት በወንጀል ሕግ አንቀፅ 555(ሐ) መሰረት ድርጊት ፈጻሚውን ሉያስጠይቅ የሚችለው ድርጊቱ ሆነ ተብል በማንኛውም ላላ መንገድ ከባድ የሆነ ጉዲትን ወይም በሽታን በልላ ሰው ላይ ያደረሰ እንደሆነ የሚያመለከት ነው። አንድ ሰው ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን ሃሳብና የድርጊት አፈጻጸም መሰረት ወንጀል ፈጽሞ ቢገኝ እና ይህም ሁኔታ በማስረጃ ሲረጋገጥ ተከሣሽ በዘህ አንቀጽ ስር ጥፊተኛ ልባል የሚችል መሆኑን የሕጉ ይዖት ያሳያል ።
በያዛነው ጉዲይ አመልካች የግል ተበዲይ ለሆነውን ፀጋ ወይሾ ላይ አስቦ በተበዲይ አካል ላይ ጉዲት ያደረሰ ቢሆን ጉዲት ያደረሰው በቦክስ እና በቴስታ መሆኑ እና ከባድ የሆነ ጉዲትን ወይም በሽታን በተበዲይ ላይ ያደረሰ መሆኑ ያልተረጋገጠ በመሆኑ፣ይህ ተግባር ከወንጀል ሕግ አንቀፅ 555 ከተመለከተው ውጪ ስለሆነ አመልካች የፈፀመው ተግባር ወንጀል ሕግ አንቀፅ 556(1) የተመለከተውን የህግ ድንጋጌ በመጣስ መሆኑ የሚያሳይ ነው።
ስለሆነም የአመልካች የወንጀል ድርጊት በስር ፍርድ ቤት የጥፊተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት የወንጀል ህግ ድንጋጌ የማይሸፈን በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አመልካችን በወንጀል ህግ ዓንቀፅ 555(ሐ) ጥፊተኛ በማለት ቅጣት መወሰኑ አግባብ ስላልሆነ፣ በተረጋገጠው የአመልካች የወንጀል አድራጎት የወንጀል ህግ አንቀጽ 556(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ጥፊተኛ ነው ብለናል።
በአመልካች ላይ ተጥል የነበረው የጥፊተኛነት ውሳኔ የተለወጠ ስለሆነ የቅጣት ውሳኔውም ሉስተካከል ይገባል። ቅጣትን በተመለከተ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 የወንጀል ደረጃና እርከን የወጣለት በመሆኑ በመመሪያው ዓንቀፅ 26 መሰረት የቅጣት አሰላል ስነ ስርአት ቅደም ተከተል ሲታይ የጥፊተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የወንጀለ ደረጃ ሉወሰን ስለሚገባው አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የህግ ድንጋጌ የወንጀል ህግ አንቀጽ 556(1) አንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በመቀጮ የሚያስቀጣ በመሆኑ በቀላል እስራት እንዱቀጣ ወስነናል።
ስለሆነም አመልካች በሰው አካል ወይም ጤና ላይ አስቦ ቀላል ጉዲት ያደረሰ ስለሆነ የወንጀለን ደረጃ 1 እርከን 2 የሚያርፍ ነው። በስር ፍ/ቤት የቀረበና ተቀባይነት ያገኘ የቅጣት ማክበጃም ማቅለያም ስላልነበረ የቅጣት እርከኑ አልጨመረም አልቀነሰም ስለሆነም የወንጀለን አፈጻጸም እና የደረሰውን ጉዲት ግምት ውስጥ በማስገባት በዘህ ጉዲይ የታሰረበት ካለ የሚታሰብለት ሆኖ አመልካች ለፈፀመው ወንጀል በሶስት ወር ቀላል እስራት ሉቀጣ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። በዘሁ መሰረት የስር ፍ/ቤት የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመት በመሆኑ በማሻሻል ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
1 . በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 05 ቀን 2011 ዓ.ም.
የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 195/ለ/2/ መሰረት ተሻሽሎል።
2 .አመልካች የወንጀል ህግ አንቀጽ 556(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ጥፊተኛ ነው በማለት በዘህ ጉዲይ የታሰሩበት ካለ ታሳቢ ሆኖ በሶስት ወር ቀላል እስራት እንዱቀጡ ተወሰኗል።
3 .በተሻሻለው የቅጣት ውሳኔ መሰረት እንዱፈፀም አመልካች ለሚገኝበት ማረሚያ ቤት ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል። ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.