ከአንድ የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዖ ንብረት የሚወረሰዉ ወይም ለመንግስት ገቢ የሚደረገዉ በወንጀል ህጉ እና በወንጀል ስ/ስ/ህጉ መሰረት በቅጣት መልክ በመሆኑ ንብረቱ የሚወረስ መሆን አለመሆኑ ዉሳኔ ማግኘት ያለበት በወንጀል መዛገብ እንጂ በወንጀል መዛገብ ላይ የተሰጠን ውሳኔ ብቻ መነሻ በማድረግ በአዱስ መልክ በሚቀርብ የፍትሐብሕር ክርክር ስላለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀጽ 98፤100(1) እና 140
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ - 137908 ቀን - 21/05/2010 ዳኞች፡- ዲኜ መላኩ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ አልቀረበም።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፀሐይ አሰፊ ከጠበቃ ደመነ ቱንኤ ጋር ቀረቡ።
መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ተጠሪ በሕፃናት ማሳደጊያ ሰበብ ከተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅት በተገኘዉ ገንዖብ ያፈሩት ሀብት እና ንብረት እንዱመልሱ እንዱሁም በሕፃናት ላይ ለደረሰዉ የሞራል ካሳ ገንዖብ እንዱከፍለ የቀረበዉን ክስ መሰረት በማድረግ የተሰጠዉን ፍርድ በመቃወም የቀረበ የሰበር አቤቱታን የሚመለከት ነዉ።
ክርክሩ የተጀመረዉ በጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የአመልካች ክስ ይዖትም በአጭሩ፤ ተጠሪ የሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ፉቃድ ሳይኖራቸዉ ያላቸዉ በማስመሰል ፀሐይ አሰፊ የሕፃናት ማሳደጊያ ማዔከል በሚል ስያሜ ከ1983 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ ቁጥራቸዉ 282 የሚሆኑ ወላጅ አልባ ሕፃናትን ለላላ ድርጅት አሳልፈዉ የሰጡ መሆናቸዉን፣ በዘህ ምክንያት ከአርባ ምንጭ ከተማ 1000 ካ/ሜትር ቦታ ወስደዉ 800,000.00 ብር የሚገመት ቤት መገንባታቸዉን፣ ከተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ገንዖብ በማግኘት የተለያዩ ንብረቶችን በህገ ወጥ መንገድ ማፍራታቸዉን፣ በዘህም ምክንያት በወንጀል ተከስሰዉ ጥፊተኛ ተብለዉ የተቀጡ በመሆኑ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 100(1) መሰረት በህገ ወጥ መንገድ ያፈሩትን ንብረት ለመንግስት ገቢ ማድረግ ያለባቸዉ በመሆኑ የተለያዩ ንብረቶች ዋጋ ብር 1,916,300.00፣ በ282 ሕፃናት ላይ ለደረሰ የሞራል ጉዲት ካሳ ብር 282,000.00 እንዱከፍለ እና በአርባ ምንጭ ከተማ በ1000 ካ/ሜትር ላይ ያረፈዉን ቤት እና ቦታዉን ለመንግስት እንዱያስረክቡ ይወሰንለት ዖንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነዉ።
ተጠሪ ለቀረበባቸዉ ክስ በሰጡት መልስ፤ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ናቸዉ የሚሎቸዉን ነጥቦች ካነሱ በኋላ፣ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዖብ/ንብረት ለመንግስት ገቢ ማድረግ የሚቻለዉ በወንጀለ ማቋቋሚያ ድንጋጌ ላይ በግልጽ የተመለከተ ሲሆን በመሆኑ እና ተጠሪ ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ህጉ አንቀጽ 433 ድንጋጌ ንብረት የሚወረስ ስለመሆኑ የማይደነግግ መሆኑን፣ ተጠሪ ካላቸዉ የሰብአዊነት እና የእናትነት ፍቅር በመነሳሳት ወላጆቻቸዉን በሞት ያጡ እና በችግር ላይ ያለትን ሕፃናት በሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ተጣርቶ በሚቀርብላቸዉ መሰረት ተቀብለዉ ወደ ሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ከማስተላለፍ በስተቀር በስማቸዉ የሚታወቅ የሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት የላላቸዉ መሆኑን፣ ተጠሪ እ.ኤ.አ ጥር 10/2007 እስከ እ.ኤ.አ ነሐሴ 05/2011 ዓ.ም ድረስ ከኤስ ኦ ኤስ አንፊንትስ ኢትዮጵያ ጋር የስራ ዉል በመፈጸም የድርጅቱ የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ኃላፉና ተጠሪ በመሆን ሲሰሩ መቆየታቸዉን፣ ድርጅቱ የተጠሪን የመኖሪያ ቤት ተከራይቶ ሲሰራ መቆየቱን እና አመልካች በክሱ የጠቀሳቸዉ 282 ሕፃናትም ድርጅቱ በስሙ የተረከባቸዉ እንጂ በግል ያልተረከቡ መሆኑን፣ ችግረኛ ሕፃናትን ተቀብለዉ በግል ገንዖባቸዉ በራሳቸዉ መኖሪያ ቤት የሚያሳድጉ መሆኑን ተገንዛቦ የአርባ ምንጭ ከተማ ማዖጋጃ ቤት 1000 ካ/ሜ ቦታ የሰጣቸዉ ሲሆን በቦታዉ ላይ የተሰራ ቤት በግላቸዉ የሰሩት መኖሪያ ቤት እንጂ የሕፃናት ማሳደጊያ ቤት አለመሆኑን፣ በ25 ሕፃናት ስም በየወሩ ሲላክ የነበረዉ 120.00 ብር በኢ/ንግድ ባንክ አ/ምንጭ ቅርንጫፍ ሂሳብ ቁጥር 1033 ገቢ ሲደረግ የነበረዉም በድርጅቱ ባለሙያ ህጋዊነቱ ተጣርቶ ሂሳቡ የተዖጋ መሆኑን፣ ተጠሪ ለስራ ሲጠቀሙበት የነበረዉ እና አመልካች በክሱ የጠቀሰዉ መኪናም የልጃቸዉ መሆኑን፣ አመልካች በክሱ የዖረዖራቸዉ ላልች የተለያዩ ቁሳቁሶችም የተጠሪ የግል ንብረቶች መሆናቸዉን፣ ለ282 ሕፃናት የተጠየቀ የሞራል ካሳም የህግ መሰረት የላለዉ መሆኑን በመጥቀስ የቀረበባቸዉ ክስ ዉድቅ ሆኖ ይወሰንላቸዉ ዖንድ ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዘህ መልኩ ግራ ቀኝ ያቀረቡትን ክርክር እና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን እንዱሁም የሰዉ ምስክሮችን አቅርቦ ከሰማ እና ከመረመረ በኋላ፤ በአርባ ምንጭ ከተማ 1000 ካ/ሜትር ቦታ ለተጠሪ ላሰጥ የቻለዉ ለወላጅ አልባ ሕፃናት ማሳደጊያነት መሆኑ ስለተረጋገጠ ተጠሪ ይህን ቦታ ሉመልሱ እንደሚገባ፣ በቦታዉ ላይ የተገነባ ቤት በህገ ወጥ መንገድ በተገኘ ገንዖብ ስለመሆኑ አመልካች በማስረጃዎቹ ያላስረዲ መሆኑን እና ተጠሪ ቤቱን የሰራዉ ያለማንም ተቃዉሞ መሆኑ ስለተረጋገጠ የግንባታዉ ወጪ ተገምቶ ሲቀርብ አመልካች እንዱከፍል በማለት የወሰነ ሲሆን፤ ላልች የተለያዩ ንብረቶችን ተጠሪ በህገ ወጥ መንገድ ያፈሩ መሆኑን አመልካች ያላስረዲ መሆኑን በመግለጽ በዘህ ረገድ የቀረበዉን ዲኝነት ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበዉ አቤቱታም ተቀባይነት አላገኘም።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም ይህኑን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን አመልካች በቀን 10/06/09 ዓ.ም አዖጋጅቶ ባቀረበዉ የሰበር አቤቱታ፤ ተጠሪ በሕፃናት ማሳደጊያ ስም በአርባ ምንጭ ከተማ በተሰጣቸዉ ቦታ ላይ የሰሩት በሕፃናት ስም ከተለያዩ ድርጅቶች በተገኘ ገንዖብ መሆኑ እየታወቀ ቤቱን በተመለከተ መንግስት ካሳ ከፍል መሬቱን እንዱወስድ መወሰኑ፣ መኪናዉን እና ለሕፃናት ማሳደጊያ የሚሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶች ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተቋቋመ ኮሚቴ ታሽጎ እያለ ተጠሪ ገንጥለዉ መዉሰዲቸዉ ተረጋግጦ እያለ አመልካች እንደ ክሱ አላስረዲም በሚል ምክንያት ዉድቅ መደረጉ እንዱሁም ተጠሪ በወንጀል ተከሶ ጥፊተኛ መሆናቸዉ እና በወንጀል ፍሬ የተገኘ ሀብት ደግሞ ሉወረስ እንደሚገባ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አስገዲጅ ዉሳኔ ሰጥቶ እያለ ተጠሪ ኃላፉነት የለባቸዉም ሲል በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወስኖ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ፀንቶ የተወሰነ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑን ጠቅሶ ታርሞ ይወሰንለት ዖንድ ዲኝነት ጠይቋል።
አቤቱታዉ ተመርምሮም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ከወንጀል ዉሳኔዉ ጋር ተገናዛበዉ የታዩ መሆን አለመሆናቸዉን ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ ቀርበዉ እንዱከራከሩ ጥሪ የተደረገላቸዉ ሲሆን፣ በዘህም መሰረት በቀን 24/09/2010 ዓ.ም ተዖጋጅቶ በጠበቃቸዉ አማካይነት በጽሐፍ በቀረበ መልስ፤ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም የሚለባቸዉን ምክንያቶች በመዖርዖር ፀንቶ እንዱወሰንላቸዉ ጠይቀዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዖት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን ይህ ችልትም ለአቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መዛገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ተጠሪ በወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ በመገኘታቸዉ ብቻ ከ1000 ካ/ሜትሩ የከተማ መሬት ዉጪ ያለትን እና አመልካች በክሱ ያመለከታቸዉ ንብረቶችን ወይም የንብረቶቹን ዋጋ ለመንግስት ገቢ እንዱያደርጉ ለመጠየቅ የሚያስችለዉ መብት አለዉ ወይስ የለዉም? መብት አለዉ የሚባል ከሆነ በክሱ የተዖረዖሩትን ንብረቶች ተጠሪ በሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ስም በህገ ወጥ መንገድ ያፈሩ መሆን አለመሆኑ ከግራ ቀኝ ክርክር አንፃር በስር ፍርድ ቤት በአግባቡ ተጣርቷል ወይ? የሚለ ጭብጦች የዘህን ችልት ምላሽ የሚሹ ሆነዉ ተገኝተዋል።
በመግቢያዉ እንደተመለከተዉ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ላቀረበዉ ክስ መሰረት ያደረገዉ 1ኛ ተጠሪ ፉቃድ ሳይኖራቸዉ ፉቃድ ያላቸዉ በማስመሰል የሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት በስማቸዉ በማድረግ ሕፃናትን በመዉሰድ ለላላ ድርጅት ሲሰጡ የነበረ በመሆኑ በወንጀል ተከሰዉ ጥፊተኛ መባላቸዉን፣ ይህን ህገ ወጥ ድርጊት በመፈጸም ከተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ባገኙት ገንዖብ የተለያዩ ንብረቶችን በማፍራታቸዉ እና የከተማ ቦታ በመዉሰዲቸዉ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 100(1) መሰረት ንብረቱ ለመንግስት ገቢ መደረግ የሚገባዉ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ። ይህንን መሰረት በማድረግም ተጠሪ ለመንግስት ገቢ ሉያደርጉ ይገባል የሚላቸዉን ንብረቶች ዛርዛር በማቅረብ ግምቱን እንዱከፍል፤
በሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ስም የተሰጣቸዉን 1000 ካ/ሜትር ይዜታም እንዱመልሱ የጠየቀ መሆኑን መዛገቡ ያሳያል።
በመሰረቱ በወንጀል ጉዲይ ንብረት ወይም ሀብት ሉወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ማድረግ በወንጀል ህጉ ከተመለከቱት የቅጣት እና የጥንቃቄ እርምጃዎች አንደ ስለመሆኑ ንብረት ስለሚወረስበት ሁኔታን የሚመለከቱ የወንጀል ህጉ ድንጋጌዎች ከሚገኙበት የህጉ ሁለተኛ መጽሐፍ ምዔራፍ ሁለት ድንጋጌዎች አጠቃላይ አወቃቀር እና ይዖት መረዲት ይቻላል። በወንጀል ጉዲይ ንብረት ወይም ሀብት ሉወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ማድረግ የሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች፤ ቅጣቱ ንብረት መዉረስን እንደሚያካትት በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል በግልጽ የተደነገገ ሲሆን፣ የጥፊተኛነት ዉሳኔ በተሰጠበት የወንጀል ስራ ወንጀለኛዉ በቀጥታም ሆነ በተዖዋዋሪ መንገድ ያገኘዉ ንብረት ሲኖር፣ አንድ ሰዉ ለወንጀል ስራ እንዱነሳሳ ወይም ወንጀለን ለመስራት እንዱረዲዉ ወይም ወንጀለን ለፈጸመበት ዋጋ እንዱሆነዉ የተሰጠዉ ወይም ሉሰጠዉ የታቀደዉ ንብረት ሲኖር፣ ወንጀልን ለመፈጸም ሉያገለግለ የሚችለ ወይም ለወንጀል ተግባር ያገለገለ ወይም የወንጀል ተግባር ፍሬ የሆኑ አደገኛ የሆኑ ነገሮች ሲሆኑ ስለመሆኑ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 98፣ 100(1) እና 140 ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል። ንብረት እንዱወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ማድረግ በወንጀለኛዉ ላይ ሉጣለ ከሚችለ ቅጣቶች አንደ በመሆኑም፣ ፍርድ ቤቶች የጥፊተኝነት እና የቅጣት ዉሳኔን ተከትል ንብረት ወይም ሀብት እንዱወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዱሆን መወሰን የሚችለት እነዘህን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ አቃቤ ህግ ሉወረሱ የሚገባቸዉን ንብረቶች ዛርዛር በወንጀል ክሱ ካመለከተ፣ ንብረቶቹም ከፍ ሲል በተመለከቱት ድንጋጌዎች አግባብ የተገኙ ስለመሆኑ በወንጀል ፍርድ ሂደት ከተረጋገጠ እና በወንጀል መዛገቡ ላይ አቃቤ ህግ ንብረቶቹ እንዱወረሱ ካመለከተ ስለመሆኑ ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች እንዱሁም በወንጀል ሥ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 211 ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዖት እና መንፈስ መረዲት ይቻላል።
ከዘህ አንፃር የተያዖዉን ጉዲይ ስንመለከት፣ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ፣ አመልካች በተጠሪ ላይ ላቀረበዉ ክስ መሰረት ያደረገዉ 1ኛ ተጠሪ ፉቃድ ሳይኖራቸዉ ፉቃድ ያላቸዉ በማስመሰል የሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት በስማቸዉ በማድረግ ሕፃናትን በመዉሰድ ለላላ ድርጅት ሲሰጡ የነበረ በመሆኑ በወንጀል ተከሰዉ ጥፊተኛ መሆናቸዉን ነዉ። በርግጥ ተጠሪ ከዘሁ ጉዲይ ጋር በተያያዖ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 433 ስር ጥፊተኛ ተብለዉ የተወሰነባቸዉ ስለመሆኑ ግራ ቀኝ አልተካካደም። ይሁንና በወንጀል ህጉ አንቀጽ 433 መሰረት ጥፊተኛ በሆነ ሰዉ ላይ የሚጣል ቅጣት ንብረት መዉረስን ወይም ለመንግስት ገቢ ማድረግን እንደሚያካትት በድንጋጌዉ አልተመለከተም። ተጠሪ ፍቃድ ሳይኖራቸዉ ሕጻናትን በማሳደግ ስራ ላይ በመሰማራት በፈጸሙት የወንጀል ተግባር በቀጥታ ወይም በተዖዋዋሪ መንገድ ያገኙት ንብረት ካለ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 98(2) መሰረት ሉወረስ የሚችልበት ሁኔታ ቢኖርም፣ ይህ የሚሆነዉ፣ ከላይ በተገለጸዉ ምክንያት፣ አቃቤ ህግ የወንጀል ክሱን ሲያቀርብ ተጠሪ ጥፊተኛ በተባለበት ድርጊት ምክንያት በቀጥታ ወይም በተዖዋዋሪ ያፈሩት ንብረት ስለመኖሩ ገልፆ በዘህ መልኩ ተጠሪ ያፈሩት ንብረትም በወንጀል መዛገቡ ላይ ተረጋግጦ ንብረቱ እንዱወረስም በወንጀል መዛገቡ ላይ አቃቤ ህጉ በሚያቀርበዉ የቅጣት አስተያየት መሰረት ፍርድ ቤቱ ትዔዙዛ ሲሰጥ ነዉ።
ከዘህ ዉጪ፣ በወንጀል መዛገብ ላይ ቀርቦ ክርክር ተደርጎበት ተረጋግጦ በቅጣት መልክ ንብረት እንዱወረስ የወንጀል መዛገቡን በያዖዉ ፍርድ ቤት ባልታዖዖበት ሁኔታ፣ ቀደም ሲል በወንጀል መዛገብ ላይ የተሰጠዉን የጥፊተኝነት እና የቅጣት ዉሳኔ መሰረት በማድረግ በክሱ የተመለከቱትን ንብረቶችን ተጠሪ ለመንግስት ገቢ እንዱያደርጉ በፍትሐብሕር መዛገብ ዲኝነት የጠየቀበት አግባብ የወንጀል ድርጊትን መነሻ በማድረግ ንብረት ሉወረስ የሚችልበትን ዓላማ መሰረት ያደረገ ሆኖ አልተገኘም።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠሪ በፈጸሙት የወንጀል ድርጊት ምክንያት በመንግስት ላይ ያደረሱት ፍትሐብሓራዊ ጉዲት ካለ በፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ 2035 እና 2162 መሰረት ኃላፉነት የሚኖርባቸዉ በመሆኑ አመልካች የደረሰዉን ጉዲት ጠቅሶ በተጠሪ ላይ ክስ እንዲያቀርብ የሚከለክለዉ የለም። ይሁንና ይህ ሂደት የሚመራዉ በመደበኛዉ የፍትሐብሕር የሙግት ስርዓት በመሆኑ፣ ክርክሩ በፍትሐብሕር ሥ/ሥርዓት ህጉ የተመለከቱትን ደንቦች እና መርሆዎች የተከተለ ላሆን ይገባል። በህጉ ከተመለከቱት ደንቦች ዉስጥም ከሳሽ ለክሱ መነሻ በሆነዉ ነገር ወይም ክሱ በተመሰረተበት ሀብት ላይ መብት ወይም ጥቅም ያለዉ መሆኑን የማሳየት ግዳታ አንደ እና ዋነኛዉ ነዉ። የዘህ መርህ ጠቀሜታ ጉዲት ከደረሰበት ሰዉ በቀር አንድ ላላ ሰዉ ስለ እርሱ ሆኖ ወይም እርሱን ተክቶ ክስ እንዲይመሰርት ለማድረግ በመሆኑ ክሱ የሚቀርብለት ፍርድ ቤትም ከሳሽ ክሱን ለማቅረብ መብት ወይም ጥቅም ያለዉ መሆን አለመሆኑን የማረጋገጥ ግዳታ አለበት (የፍ/ሥ/ሥ/ህጉ አንቀጽ 33/2/ እና 231/1-ሀ/ ድንጋጌዎች ይመለከቷል)። በዘህ ረገድ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክስ ለመንግስት ገቢ እንዱደረግ በክሱ ከጠቀሳቸዉ ንብረቶች ዉስጥ አንደ በአርባ ምንጭ ከተማ በሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ስም ለተጠሪ ያላግባብ የተሰጠ 1000 ካ/ሜትር ቦታ ሲሆን፣ ተጠሪ በፈጸሙት ህገ ወጥ ድርጊት መሬቱ በእጃቸዉ የገባ መሆኑን አረጋግጦ አመልካች መንግስትን ወክል መሬቱ እንዱመለስ ለማስወሰን ክስ ለማቅረብ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣን ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 106/99 መሰረት ስልጣን ያለዉ ከመሆኑም በላይ ከዘህ ጋር በተያያዖ የተሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም ተጠሪ ያቀረቡት አቤቱታ ባለመኖሩ ይህን በተመለከተ የተሰጠዉን ዉሳኔ ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም።
ይሁንና ከመሬቱ ዉጪ ያለትን ላልች ንብረቶችን በተመለከተ አመልካች ለክሱ መሰረት ያደረገዉ ተጠሪ በሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ስም ከተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ባገኙት ገንዖብ ተጠሪ በክሱ የተመለከቱትን ንብረቶች ማፍራታቸዉን ነዉ። አመልካች ይህን ክስ ሲያቀርብ ተጠሪ ከላልች በጎ አድራጎት ድርጅቶች ባገኙት ገንዖብ ንብረቶቹን ማፍራታቸዉ የአመልካችን መብት እንዳት ሉጎዲ እንደሚችል ያልገለጸ ከመሆኑም በላይ፣ ተጠሪ ሕፃናትን የማሳደግ ህጋዊ ፉቃድ ሳይኖራቸዉ ፉቃድ ያላቸዉ በማስመሰል የፈጸሙት ድርጊት እዉነት መስልአቸዉ እርዲታዉን ሲያደርጉ የነበሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ስም በክሱ አላመለከተም። አመልካች እነዘህን በጎ አድራጎት ድርጅቶችን ጭምር ወክል መከራከር የሚችል ስለመሆኑም አልገለጸም። ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ወደ ዋናዉ ክርክር ከመግባቱ በፉት አመልካች በክሱ ካመለከታቸዉ ንብረቶች ጋር በተያያዖ መብት ወይም ጥቅም ያለዉ መሆን አለመሆኑን በቅድሚያ ማረጋገጥ ነበረበት።
የፍሬ ነገር ክርክሩን በተመለከተ አመልካች በክሱ ባመለከተዉ እና ለመንግስት እንዱመለስ በተወሰነዉ 1000 ካ/ሜ ቦታ ላይ ለሕፃናት ማሳደጊያ የሚሆኑ የተለያዩ ክፍልች ያለት ቤት መሰራቱን፣ ለዘሁ ዓላማ የሚዉለ የተለያዩ ቁሳቁሶች መኖራቸዉ፣ የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 3-20744 የሆነ መኪና በተጠሪ ስም ተገዛቶ በእጃቸዉ የሚገኝ እና ለስራዉ የሚጠቀሙበት ስለመሆኑ ተረጋግጧል። ይህ ከተረጋገጠ ተጠሪ እነዘህን ንብረቶች ሉያፈሩ የሚችለበት ላላ የተለየ ገቢ ያላቸዉ መሆን አለመሆኑ በተጨማሪ ማስረጃ ተጣርቶ ሉወሰን የሚገባዉ ነዉ።
ሲጠቃለል ከወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዖ ንብረት የሚወረሰዉ ወይም ለመንግስት ገቢ የሚደረገዉ በወንጀል ህጉ እና በወንጀል ስ/ስ/ህጉ መሰረት በቅጣት መልክ ከመሆኑ አንፃር ሲታይ ንብረቱ የሚወረስ መሆን አለመሆኑ ዉሳኔ ማግኘት ያለበት በወንጀል መዛገብ እንጂ በወንጀል መዛገብ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ብቻ መነሻ በማድረግ በአዱስ መልክ በሚቀርብ የፍትሐብሕር ክርክር ላሆን አይችልም። ይህ ከሆነ ተጠሪ በፈጸሙት የወንጀል ድርጊት ምክንያት ያፈሯቸዉ ንብረቶች የአመልካችን ጥቅም ወይም መብት የሚነካ ከሆነ ክሱ የሚቀርበዉ እና ሙግቱም የሚመራዉ መደበኛዉን የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት በተከተለ መንገድ በመሆኑ፣ አመልካች መብት ወይም ጥቅም ያለዉ መሆኑን በክሱ በግልጽ ሳያሳይ እና ፍርድ ቤቱም ይህን በቅድሚያ ማረጋገጥ ሲገባዉ ይህን ሳያደርግ ከከተማ ቦታ ዉጪ ያለትን ንብረቶች በተመለከተ ወደ ፍሬ ነገር ክርክር ገብቶ አከራክሮ ያዉም በክሱ የተመለከቱትን ንብረቶች ለማፍራት የሚያስችላቸዉ ተጠሪ የተለየ ገቢ ያላቸዉ መሆን አለመሆኑ በአግባቡ ሳይረጋገጥ በጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ፀንቶ የተወሰነዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
የደቡብ ብ/ብ/ሕዛቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 21/04/08 ዓ.ም በዋለዉ ችልት፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይ/ሰሚ ችልት በመ/ቁ/11000 ላይ እንዱሁም የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/26888 የሰጧቸዉን ዉሳኔዎች በማጽናት፣ የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
በአርባ ምንጭ ከተማ የተሰጣቸዉን 1000 ካ/ሜትር ቦታ ተጠሪ እንዱመል በሚል የተሰጠዉን የዉሳኔ ክፍል በማጽናት፤ ቀሪዉን የዉሳኔ ክፍል በመሻር ወስነናል።
የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በጎ አድራጎት ድርጅቶች በሚል የገለፃቸዉ ድርጅቶች እነ ማን ናቸዉ? አመልካች ከ1000 ካ/ሜትር ቦታ ዉጪ ቀሪዎቹን ንብረቶችን በተመለከተ ክስ ለማቅረብ የሚያስችለዉ ከህግ የመነጨ መብት አለዉ ወይስ የለዉም?
አመልካች ክሱን ለማቅረብ መብት ያለዉ መሆኑ ተረጋግጦ ወደ ፍሬ ነገር ክርክር የሚገባ ከሆነ በ1000 ካ/ሜትር ቦታ ላይ የተገነቡትን ቤቶች ጨምሮ ላልች በክሱ የተመለከቱትን ንብረቶች ለማፍራት የሚያስችላቸዉ ተጠሪ የተለየ የገቢ ምንጭ አላቸዉ ወይስ የላቸዉም? በሚለት ጭብጦች ላይ የግራ ቀኝ ክርክር እና ተጨማሪ ማስረጃዎችን በመስማት እንዱሁም የፍ/ሥ/ሥርዓት ሕጉ በሚፈቅደዉ መሰረት ጭብጦቹን በአግባቡ አጣርቶ በጉዲዩ ላይ ፍትሐዊ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉን ተገቢዉን ሁለ በማድረግ ጉዲዩን አጣርቶ ዉሳኔ እንዱሰጥበት መዛገቡ በፍ/ሥ/ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 343(1) መሰረት ተመልሶለታል።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ይመለስ።