No summary available.
ጥቅምት 26/2012 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፋ ኃይለ ነጋሽ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡ የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ - የቀረበ የለም።
ተጠሪዎች፡
አቶ ታደሰ ኪዲነ ማርያም
አቶ ዲንኤል ኃይለ ቀርበዋል።
አቶ ኪሮስ ፀጋይ
አቶ ብርሃነ ፀጋይ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የአራጣ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበው የትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁ/100969 ላይ ጥቅምት 02/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በሽረ እንዲስላሴ ወረዲ ፍርድ ቤት በአሁን ተጠሪዎች ላይ የ1996 ዓ.ም የወንጀለ ህግ 712(1(ሀ)) ጠቅሶ ባቀረበው የአራጣ ወንጀል ክስ ነው። የክሱም ጭብጥ የአሁን ተጠሪዎች “ወልደ ገብርኤል አልጋሁን እና ጓደኞቻቸው ዕጣን ለቀማ ሕብረት ሽርክና ማህበር” ለተባለው ተበዲይ በሽረ እንዲስላሴ ከተማ ውስጥ በተለያዩ ቀናት የተለያየ መጠን ያለውን ገንዘብ በአራጣ በማበደር የአራጣ ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ክሱን እንዱከላከለ አድርጎ የመከላከያ ማስረጃቸውን ከሰማ በኋላ ተጠሪዎች የተከሰሱበትን የአራጣ ወንጀል ያልፈፀሙ ለመሆኑ የዐቃቤ ህግ ማስረጃን በሚያስተባብል መልኩ አስረድተዋል በሚል ከተከሰሱበት ወንጀል በወንጀል ህግ ሥነ ሥረዓት ቁጥር 149(2) መሰረት በነፃ አሰናብቷል። በዚሁ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የሰሜን ምዕራብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታው በወንጀል ህግ ሥነ ሥረዓት ቁር 195(1) መሰረት ሰርዟል።
ጉዲዩን በሰበር የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከላይ በተጠቀሰው የመዝገብ ቁጥር እና ቀን በዋለው ችልት የአራጣ ወንጀል የሚፈፀመው የተበዲይን ችግር፣ የበታችነት፣ ወይም የገንዘብ ችግር፣ ወይም መንፈሰ ደካማነት ወይም ልማድ ወይም ችልታ ማጣትን መሰረት ተደርጎ መሆኑን፤
እነዚህ ተግባራት ሉኖሩ የሚችለት በተፈጥሮ ሰው ላይ መሆኑን፤ በቀረበለት ጉዲይ ላይ የአራጣ ወንጀል ተፈጽሟል የተባለው በህግ የሰውነት መብት በተሰጠው ማህበር ላይ በመሆኑ በወንጀል ህጉ ስለ አራጣ ወንጀል ከአንቀፅ 712-715 ድረስ የተደነገጉት ለተፈጥሮ ሰው እንጂ በህግ የሰውነት መብት ለተሰጠው አካል ተፈፃሚነት የለውም፤ በፍሬ ነገር ደረጃም በግራ ቀኙ መካከል የአራጣ ብድር ግኑኝነት ያልነበረ ለመሆኑ በመከላከያ ማስረጃ በመረጋገጡ ተጠሪዎች ከክሱ በነፃ መሰናበታቸው ተገቢ ነው በማለት በውጤት ደረጃ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በአብላጫ ድምፅ አፅንቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች ታህሳስ 15/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ ሰበር ችልት ትርጉም ላይ ያለውን ቅሬታ በመጥቀስ በዚህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። ፍሬ ቃለም በወንጀል ህግ አንቀፅ 712(1(ሀ)) ስር “ማንኛውም ሰው” ተብል የተጠቀሰው የተፈጥሮም ሆነ በህግ የሰውነት መብት የተሰጠውን አካል የሚያጠቃልል ሆኖ እያለ የክልለ ሰበር ችልት የድንጋጌው ተፈፃሚነት ለተፈጥሮ ሰው ብቻ ነው ብል መተርጎሙ አግባብ ባለመሆኑ በህግ የሰውነት መብት ለተሰጣቸው ድርጅቶችም ተፈፃሚነት አለው በሚል ተተርጉሞ ተጠሪዎች በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ሉቀጡ ይገባል የሚል ነው።
የክልለ ሰበር ችልት ውሳኔ ከወንጀል ህግ አንቀፅ 23(2) እና 712(1(ሀ)) ጋር ተገናዝቦ ተመርምሮ በዚህ ችልት ትርጉም እንዱሰጥበት በዚህ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በመታዘዙ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ 1ኛ ተጠሪ ለብቻው፤ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች ደግሞ በጋራ ሰኔ 03/2011 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል።
ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ ዘርዘር ያለ ሲሆን አጠቃላይ ጭብጥ በሁለት ነጥብ ላይ ያተኮረ ነው።
የመጀመሪያው የአራጣ ወንጀልን የሚያቋቁሙት ድንጋጌዎች ስር የተቀመጡት መመዘኛዎች የተፈጥሮ ሰውን ብቻ የሚመለከቱ በመሆናቸው እና የአራጣ ብድር ተሰጥቷል የተባለው ለማህበር በመሆኑ የክልለ ሰበር ችልት በአተረጓጎም ረገድ የፈፀመው ስህተት የለም የሚል ነው። ሁለተኛው በስር ፍርድ ቤቶች በነፃ የተለቀቁት ከተበዲይ ጋር ተራ የብድር ውል ግኑኝነት እንጂ የአራጣ ብድር ያልነበረ ለመሆኑ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦ በመሆኑ ውሳኔው የሚነቀፍ አይደለም የሚል ነው።
አመልካች ሰኔ 14/2011 ዓ.ም በሰጠው የመልስ መልስ ቀደም ሲል ያቀረበውን የቅሬታ ነጥብ የሚያጠናክርበትን ምክንያት በማከል በቀረበው ቅሬታ መሰረት እንዱወሰንለት ጠይቋል።
በግራ ቀኙ የቀረበው ክርክር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በመሰረቱ ተጠሪዎች በተከሰሱበት የወንጀል ህጉ አንቀፅ 712 ስር “ማንም ሰው” ተብል የተጠቀሰው የወንጀል ፈፃሚውን ማንነት የሚመለከት እንጂ የተባዲዩን ማንነት የሚገልፅ አይደለም። ሆኖም ይህ ድንጋጌ ያለበት የወንጀል ህጉ ስድስተኛ መፀሃፍ፣ ምዕራፍ ሶስት፣ ክፍል ሶስት “የኀሉናን ወይም የሰውን ችግር መሰረት በማድረግ የሚፈፀሙ ወንጀልች” በሚል አርዕስት ስር በመሆኑ ዞሮ ዞሮ የአራጣ ወንጀል የሚፈፀምበት ተበዲይ ሰው መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
በህግ አስተምህሮ ሰው ማለት የተፈጥሮ ሰው እና በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው የንግድ ማህበር/ድርጅት/ ስለመሆኑ በችልቱ ግንዛቤ የሚወሰድበት ነው። በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት በልዩ ዓላማ የመብት እና ግዳታ ባለቤት እንዱሆን የተደረገ ቢሆንም የሚንቀሳቀሰውም ሆነ ስራውን የሚከውነው በተፈጥሮ ሰው አማካኝነት ነው። ድርጅቱን ለማንቀሳቀስ በህግም ይሁን በውል ስልጣን የተሰጠው የተፈጥሮ ሰው በተሰጠው የስልጣን ክልል ውስጥ ለድርጅቱ ጥቅም እና መብት እስከሰራ ድረስ በተሰራው ስራ ተጠቃሚውም ሆነ ተጎጂው ድርጅቱ ይሆናል።
ይህ በመሆኑም ነው ከድርጅቱ ኃላፊዎች ወይም ሰራተኞች አንደ ከድርጅቱ ስራ ጋር በተያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በህገወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም የድርጅቱን ህጋዊ ግዳታ በመጣስ ወይም ድርጅቱን በመሳሪያነት ያለአግባብ በመጠቀም በተለያየ የወንጀል ተሳትፎ ደረጃ ወንጀል አድርገው በተገኙ ጊዜ በእንደራሴዎቹ የተሳትፎ ደረጃ ልክ ድርጅቱ እራሱ ወንጀል እንዲደረገ ተቆጥሮ በወንጀል ጥፋተኛ ተብል የሚቀጣ ስለመሆኑ በወንጀል ህግ አንቀፅ 23(3) እና 34 ስር የተደነገገው። እናም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት የመብት እና ግዳታ ባለቤት በመሆኑ በህግ በግልፅ በተደነገገ ጊዜ በወንጀል ተከስሶ ሉቀጣ እንዱሁም እንደማንኛውም የተፈጥሮ ሰው የወንጀል ድርጊት ተጎጂ ላሆን ይችላል ማለት ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የተሰጠው ትርጉም የአራጣ ወንጀልን የሚያቋቁሙት ፍሬ ነገሮች በባህሪያቸው የተፈጥሮ ሰውን ብቻ የሚመለከቱ በመሆኑ ድንጋጌው በህግ የሰውነት መብት ለተሰጠው ድርጅት ተፈፃሚነት የለውም የሚል ነው።
በእርግጥ የአራጣ ወንጀል የሚፈፀመው የተበዲዩን ችግርተኝነት፣ የበታችነት፣ ወይም የገንዘብ ችግሩን ወይም መንፈሰ ደካማነቱን ወይም ልምድ ወይም ችልታ የላለው መሆኑን መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 712(1(ሀ)) ድንጋጌ ያስገነዝባል። በዚህ አንቀፅ ስር የወንጀለ ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች ተብለው የተጠቀሱት በአማራጭ መስፈርትነት የተቀመጡ ሲሆን አንዲንድቹ በትክክልም የተፈጥሮ ሰውን ብቻ የሚመለከቱ ሲሆን ላልቹ ደግሞ እንደ አግባብነታቸው በህግ የሰውነት መብት ለተሰጠው አካልም የሚሰሩ ናቸው። ለአብነት ያክል “መንፈሰ ደካማነት” እና “የበታችነት” የሚለው የተፈጥሮ ሰውን ብቻ የሚመለከት ሲሆን “ችግርተኝነት ወይም የገንዘብ ችግር” የተባለው ደግሞ ለተፈጥሮም ሆነ በህግ የሰውነት መብት ለተሰጠው አካል ሉፈፀም የሚችል ነው።
እናም የወንጀል ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮቹ በአማራጭነት የተቀመጡ በመሆናቸው እንደ ነገሩ ሁኔታ እና አግባብነት መመዘኛው ለተፈጥሮም ሆነ በህግ የሰውነት መብት ለተሰጠው ድርጅት/ማህበር/ ተግባራዊ ከሚደረግ በቀር ድንጋጌው ተፈፃሚነቱ ለተፈጥሮ ሰው ብቻ ነው የሚባል አይደለም።
በተያዘው ጉዲይ በተጠሪዎች ላይ የቀረበው የወንጀል ክስ በቀረበበት አግባብ ተረጋግጧል አልተረጋገጠም የሚለው ቀጥል የሚታይ ሆኖ በድርጊቱ ተበዲይ ተብል የተጠቀሰው የንግድ ማህበር እንደራሴዎች በክሱ ውስጥ የተጠቀሰውን ገንዘብ ከተጠሪዎች ሲበደሩ የነበረው ድርጅቱ አጋጥሞት በነበረው ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ምክንያት መሆኑን ከክርክሩ አጠቃላይ አመጣጥ መገንዘብ ተችሎል። የአንድ ድርጅት እንደራሴዎች ድርጅቱ ባጋጠመው የገንዘብ ችግር ምክንያት በአራጣ ገንዘብ ከተበደሩ እና ይህ ለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ማረጋገጥ ከተቻለ የንግድ ድርጅቱ በአራጣ ወንጀል ድርጊት ተበዲይነት የማይጠቀስበት ምክንያት የለም።
በመሆኑም የትግራይ ሰበር ችልት የወንጀል ህጉን አንቀፅ 712 የተረጎመበት መንገድ የድንጋጌውን አጠቃላይ ይዘት እና መንፈስ ያላገናዘበ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል የወንጀለን ድርጊት በተመለከተ ማስረጃና ፍሬ ነገርን የመመርመር እና የመመዘን ስልጣን ያላቸው በየደረጃው ያለ ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸውን ማስረጃዎች መርምረውና መዝነው በተጠሪዎች እና በተበዲይ ድርጅት መካከል የነበረው ግንኙነት የተራ ብድር እንጂ የአራጣ ብድር አለመሆኑን ያረጋገጡ ለመሆኑ ከቀረበው የመዝገብ ግልባጭ ለመገንዘብ ተችሎል። አመልካች ተጠሪዎች በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ሉባለ ይገባል ከማለት ባለፈ የስር ፍርድ ቤቶች የአራጣ ወንጀል አልተፈፀመም ለማለት በተጓዙበት መንገድ እና በደረሱበት ድምዲሜ ውስጥ የፈፀሙት መሰረታዊ የህግ ስህተት ምን እንደሆነ ለይቶ ያላመለከተ በመሆኑ ተጠሪዎችን ነፃ በመልቀቅ በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት አልተቻለም።
ሲጠቃለል ይህንን ጉዲይ በተመለከተ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁ/100969 ላይ ጥቅምት 02/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት በወንጀል ህግ አንቀፅ 712(1(ሀ)) ስር የተመለከተው የአራጣ ወንጀል ተፈፃሚነት የተፈጥሮ ሰው በሆነ ተበዲይ ላይ ብቻ ነው በማለት የሰጠው የውሳኔ ክፍል ብቻ ተሸሮ የተቀረው በወንጀል ህግ ሥነ ሥረዓት ቁጥር 195(2) መሰረት ፀንቷል።
በወንጀል ህግ አንቀፅ 712 ስር የተመለከተው የአራጣ ወንጀል በህግ የሰውነት መብት በተሰጠው ድርጅት/ማህበር/ ላይ ሉፈፀም ይችላል።
ውሳኔው መሻሻለን እንዱያውቅ የዚህ ፍርድ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.