አንድ ሰው ለብዛበዙ ዓላማ ሲባል በሕገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን የማዖዋወር ወንጀል ፈፅመኻል ልባል ስለሚችልበት አግባብ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዛውውር እና ስደተኞችን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 909/07 አንቀጽ 3/2/ሀ/
No summary available.
ሕዲር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች/ቾች፡- አሕመድ ኢብራሂም ንጉሴ - አልተጠሩም።
ተጠሪ/ዎች፡- የኦሮሚያ ክልል ዓቃቤ ሕግ - ዐ.ህግ ምዔራፍ ወርቁ - ቀረቡ።
መዛገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች ሕዲር 09 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ አመልካች በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ማዖዋወር ወንጀል በቀረቡበት ስድስት ክሶች ተሳትፍ ውጤቱንም የወሰደ በመሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 60/ሐ እና 184/2 ጥፊተኛ መባለ ተገቢ ነው ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለቱ ነው።
ጉዲዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ምዔራብ ወለጋ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው።የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች እና በስር 1ኛ ተከሳሽ ላይ በስር ፍ/ቤት ያቀረባቸው ክሶች ስድስት ሲሆኑ ይዖታቸውም፡- 1ኛ ክስ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና አዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 3/2/ሀ ድንጋጌን በመተላለፍ ጉቴ በተባለ ልዩ ቦታ በቀን 30/04/10 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 5፡00 ሰዓት ማንነቱ ካልታወቀ እና ለጊዚው በቁጥጥር ስር ያልዋለ ግለሰብ የግል ተበዲይ አሲያ አባጋሮ ሱቅ ሄዲ ስትመለስ አብደልቃድር አባጋሮ ጥሩ ስራ አግኝቶልሻል አትፈልጊም ወይ? የሚደርስሽ ጥሩ ስራ እና ጥሩ ቦታ ነው በማለት በማባበል፤ አልፊው ስትገባ በማግስቱም መጥቶ በማባበል ነገ ስለምትሄደ በማለዲ 1ኛ ተከሳሽ ጋር አደርሳችኋለሁ በማለት፤ በማግስቱም ከቤት በማስወጣት ስሙ ካልታወቀ ግለሰብ ጋር በመሄድ 1ኛ ተከሳሽ ከላላ ሰው ጋር በመሆን ተቀብል አመልካች ቤት በማምጣት በመሸሸግ፤ ለጊዚው በቁጥጥር ስር ያልዋለች የአመልካች ባለቤት ጋር ተበዲይዋን ፍቶ በማንሳት አትፍሪ ችግር የለም ሲቸግርሽ ለእኔ ትነግሪኛለሽ ፍቶሽን ደግሞ ብትጠፉ ትፈለጊበታለሽ ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ ውጪ ሐገር ሄደሽ እንድትሰሪ አደርግሻለሁ በማለት ወደ ሰው ቤት አሳልፈው በመስጠት ከሰዎች ጋር በስልክ እየተግባቡ ፕሉስ ባደረገው ክትትል የተያዖ በመሆኑ በፈጸመው በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ማዖዋወር ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
2ኛ ክስ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና አዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 3/2/ሀ ድንጋጌን በመተላለፍ በ1ኛ ክስ በተገለጸው ሁኔታ ስሙ እና ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ የግል ተበዲይ ሩሴ አባሲመንን በቀን 03//05/10 ከቤት በማውጣት ስሙ ካልታወቀ ግለሰብ ጋር ሄዲ 1ኛ ተከሳሽ ስሙ ካልታወቀው ግለሰብ ተቀብል ነቀምቴ ከተማ በማሳድር በቀን 04/05/10 አመልካች ቤት በማሳደር ሸሽጎ በቁጥጥር ስር ካልዋለች የአመልካች ባለቤት ጋር በ1ኛ ክስ የተገለጸውን ድርጊት በመፈጸም ላይ ሳለ ፕሉስ ባደረገው ክትትል ስለተያዘ በፈጸመው በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ማዖዋወር ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
3ኛ ክስ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና አዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 3/2/ሀ ድንጋጌን በመተላለፍ ለጊዚው በቁጥጥር ስር ካልዋለች አለውያ ሰዑድ ጋር በመሆን የግል ተበዲይ ነብያት መሐመድን በቀን 03/05/10 ከቀኑ በግምት 8፡00 ሰዓት 1ኛ ተከሳሽ ከበደላ ከተማ ወደ ነቀምቴ ከተማ እየተጓዖች ሳለ ከጎንዋ በመቀመጥ ጊምቢ ከተማ ጥሩ ስራ አለ ወደዘያው አደርስሻለሁ በማለት በላልች ክሶች ላይ የተገለጹትን ተበዲዮች ሲሳያት በደላላ እጅ ወደ ላላ ሰው ቤት አልገባም እንጂ ስራ እፈልጋለሁ ስትለው የደላላ እጅ አላውቅም በማለት በድጋሚ አባብሎት በነቀምቴ ከተማ አሳድሯት በቀን 04/05/2010 በግምት 3፡00 ሰዓት በአመልካች ቤት በማምጣት ሸሽገው ከአመልካች ባለቤት ጋር በቤታቸው ሸሽገው 1ኛ ተከሳሽ ገንዖብ ተቀብልባት አመልካች እና ባለቤቱ ደግሞ ፍቶ በማንሳት አትፍሪ ስትጠፉ ትፈለጊበታለሽ ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ ውጪ ሐገር እንድትሰሪ እናደርግሻለን በማለት ወደ ላላ ሰው ቤት አሳልፈው ለመስጠት በስልክ እየተግባቡ ሳለ በፕሉስ ክትትል ስለተያዘ በፈጸመው በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ማዖዋወር ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
4ኛ ክስ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና አዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 3/2/ሀ ድንጋጌን በመተላለፍ ለጊዚው በቁጥጥር ስር ካልዋለች አለውያ ሰዑድ ጋር በመሆን ወ/ት ሳቢቃ ካማል የተባለችውን የግል ተበዲይ በቀን 30/04/10 ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ተበዲይ ሱቅ ሄዲ ስትመለስ 1ኛ ተከሳሽ በመንገድ አስቁሟት አዱስአበባ አደርስሻለሁ እዘያ ሄደሽ ጥሩ ስራ ሰርተሸ ገንዖብ ታገኛለሽ እራስሽንም ቤተሰብሽንም ትረጃለሽ በማለት፤ እማራለሁ አልሄድም ስትለው ሐሙስ ቀን ድረስ ተማሪ ከዘያ በኋላ ትሄጃለሸ በማለት በቀን 03/05/10 ጠዋት እንዱሄደ በመንገር፤ ተበዲይዋ ቤተሰቦችዋን ደብቃ ከቤት ወጥታ እንድትሄድ በማድረግ በ6ኛ ክስ ላይ ከተገለጸችው የግል ተበዲይ ጋር 1ኛ ተከሳሹ በመኪና አሳፍሮአቸው ነቀምት ከተማ አሳድሯት በማግስቱም በአመልካች ቤት በማምጣት ሸሽገው ለጊዚው በቁጥጥር ስራ ካልዋለች የአመልካች ባለቤት ጋር በመሆን በራሳቸው ቤት ውስጥ በመሸሸግ፤
1ኛ ተከሳሽ ገንዖብ ተቀብል አመልካች እና ባለቤቱ ደግሞ ፍቶ በማንሳት ወደ ውጪ ትሄጃለሽ በማለት በማባበል ወደ ላላ ሰው ቤት አሳልፍ ለመስጠት ከላልች ሰዎች ጋር በስልክ እየተግባቡ ሳለ በፕሉስ ክትትል የተያዘ በመሆኑ በፈጸመው በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ማዖዋወር ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
5ኛ ክስ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና አዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 3/2/ሀ ድንጋጌን በመተላለፍ ለጊዚው በቁጥጥር ስር ካልዋለች አለውያ ሰዑድ ጋር በመሆን የግል ተበዲይ ወ/ት ለይላ አህመድ የተባለችውን 1ኛ ተከሳሽ ጓደኛዋን ሳቢቃ ከማል በሕገወጥ መንገድ ለማዖዋወር በተደጋጋሚ ሲጠይቃት ቆይቶ በቀን 02/05/10 ከቀኑ በግምት 5፡00 ሰዓት መንገድ ላይ አግኝቷት ጊምቢ ወደ ተባለ ጥሩ ሐገር አደርስሻለሁ እዘያ ገንዖብ አግኝተሸ እራስሽን ችለሽ ቤተሰብሽንም ትረጃለሽ በማለት በማባበል በማግስቱ ጉዜ ስለሆነ ተዖጋጂ በማለዲ ተነስተን እንሄዲለን እኔ ቶባ ከተማ እጠብቅሻለሁ በማለት በቀን 03/05/10 ዓ.ም ጠዋት ከቤት በማውጣት 1ኛ ተከሳሽ መኪና አሳፍሯት ነቀምት ከተማ አሳድሯት በማግስቱ ወደ አመልካች ቤት በማምጣት ሸሽገው ለጊዚው ካልተያዖችው የአመልካች ባለቤት ጋር በመሆን ከላይ ባለት ክሶች በተገለጸው ሁኔታ የተያዘ በመሆኑ በፈጸመው በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ማዖዋወር ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
6ኛ ክስ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና አዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 3/2/ሀ ድንጋጌን በመተላለፍ ለጊዚው በቁጥጥር ስር ካልዋለች አለውያ ሰዑድ ጋር በመሆን የግል ተበዲይ ወ/ት አይሻ አህመድ የተባለችውን በጓደኛዋ ሳቢቃ ከማል በቀን 02/05/10 ዓ.ም የሐሰት ቃል በመንገር በማታለል በማግስቱ ከቤት በማውጣት በ4ኛ ክስ ተበዲይ ከሆነችው ከሳቢቃ ከማል ጋር በመሆን 1ኛ ተከሳሽ መኪና አሳፍሮ ነቀምት ከተማ አሳድሯት በማግስቱ በአመልካች መኖሪያ ቤት በማምጣት ሸሽገው 1ኛ ተከሳሽ ገንዖብ ተቀብልባት ካልተያዖቸው የአመልካች ባለቤት ጋር በመሆን ከላይ ባለት ክሶች በተገለጸው ሁኔታ የተያዘ በመሆኑ በፈጸመው በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ማዖዋወር ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
ተከሳሾች ክሱ ተነቦላቸው እንዱረደት ከተደረገ በኋላ ተቀብለውታል የተባለው የገንዖብ መጠን በክሱ ውስጥ አልተገለጸም በማለት ክሱን ተቃውመው ክሱ በዘህ አግባብ እንዱሻሻል የተደረገ መሆኑን የውሳኔው ይዖት ያሳያል። አመልካች የእምነት ክሕደት ቃለን ሲጠየቅም በዓቃቤሕግ ክስ መሰረት ድርጊቱ ያልተፈጸመ መሆኑን፤ በቀን 4/5/10 ዓ.ም ፕሉስ ተበዲዮችን በ2ኛ ተከሳሽ ቤት ሄድ ሲቆጣጠር 1ኛ ተከሳሽ በ2ኛ ተከሳሽ ቤት የሚቀመጥ ልጅ ስላለው ወደ 2ኛ ተከሳሽ ቤት ሄድ በር ሲያንኳኳ ወደ ራሱ ቤት ያስገባቸው ቀድሞውኑ 1ኛ ተከሳሽን ስለሚያውቅ እንጂ ስለተበዲዮቹ የሚያውቀው ነገር የላለ መሆኑ እና 1ኛ ተከሳሽም ማዖዋወሩን የሚያውቀው ነገር የላለ መሆኑን፤ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር የተባለውን ወንጀል ያልፈጸመ መሆኑን፤ በአመልካች ቤት ቆይተው የሄደት አንድ ሰዓት ለማይበልጥ ጊዚ መሆኑን በመግለጽ የእምነት ክሕደት ቃለን የሰጠ በመሆኑ ፍ/ቤቱ የዓቃቤሕግን ማስረጃዎች ሰምቷል።
ፍ/ቤቱ የዓቃቤ ሕግን ማስረጃ ከሰማ በኋላ ዓቃቤሕግ ባቀረበው ማስረጃ 1ኛ ተከሳሾች ተበዲዮችን ጥሩ ገንዖብ ታገኛላችሁ በማለት ተስፊ ስጥቶአቸው መልምል በማጓጓዛ ወደ ግምቢ ከተማ ማምጣቱን፤ 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ ከሰዎች ጋር በስልክ መነጋገሩን እና ተበዲዮችን ከ1ኛ ተከሳሽ ተቀብል በድርጊቱ መሳተፈን ስላስረዲ ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ እንዱከላከለ በማለት ብይን ሰጥቷል። በዘሁ መሰረት የስር 1ኛ ተከሳሽ መከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለት ያስመዖገበ መሆኑን እና አመልካች ደግሞ ሁለት መከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ ያሰማ መሆኑን መዛገቡ ያመለክታል።
ፍ/ቤቱም በመቀጠል የግራቀኙን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የዓቃቤሕግ ምስክሮች ከጥርጣሬ በላይ በሆነ መልኩ ተከሳሾች የተከሰሱበትን ወንጀል መፈጸማቸውን አስረድተዋል፤ የአመልካች መከላከያ ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል አጠራጣሪ ነው፤ አመልካች ተመልምለው የተስፊ ቃል ተሰጥቶአቸው ተጭነው ወደ ቤቱ የመጡትን ተበዲዮችን ከ1ኛ ተከሳሽ ተቀብል በር ከፍቶ መቀበለ ዋሳችሁ እኔ ነኝ የምትቸገሩት ነገር የለም ከ2-3 ዓመት ከሰራችሁ ወደ ውጪ ሐገር እልካችኋለሁ በማለት የተስፊ ቃል መስጠቱ የተረጋገጠ በመሆኑ አዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 3/2/ሀ መሰረት በስድስቱም ክሶች ጥፊተኞች ናቸው በማለት የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል። ቅጣቱንም በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 መሰረት በማስላት በ 25 ዓመት ጽኑ እስራት እና መቀጮ እንዱቀጣ ሲል ወስኗል። አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም። አመልካች በመቀጠል ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቧል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው ሲል አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- በተጠሪ ምስክሮች እንደተገለጸው የግል ተበዲይ ናቸው የተባለት ወጣት ሴት ሰራተኞች ወደ ጊምቢ ከተማ የመጡት በቤት ሰራተኝነት አገልገልው የሚገባቸውን ተመጣጣኝ ደመወዛ ለማግኘት ከመሆኑ በቀር ለብዛበዙ ዓላማ አይደለም፤ ደመወዙችን ተመጣጣኝ አይደለም ባለም ጊዚ ሥራውን አቋርጠው የመሄድ ሙለ መብት አላቸው፤ ይህም በማናቸውም የቤት ሰራተኛ የቅጥር ግንኙነት የተለመደ ተግባር ነው፤ በመሆኑም የወንጀለ ማቋቋሚያ ግዘፊዊ ፍሬነገር ባልተሟላበት ሁኔታ የጥፊተኝነት ውሳኔ መሰጠቱ አግባብ አይደለም፤ አመልካች የግል ተበዲዮችን ያየሁት ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ሆነው ወደ ቤቴ በመጡ ጊዚ ነው፤ የሰር 1ኛ ተከሳሽ ልጅ በእኔ ቤት ተቀጥራ ትሰራ የነበረ በመሆኑ ልጁን ለመጠየቅ ነው የሚል ግንዙቤ ነበረኝ፤ የልጁ ቀጣሪ ከመሆኔ ውጪ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ላላ ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም፤ አመልካች በቤቴ እንዲለሁ በቁጥጥር ስር በዋልኩበት ጊዚ የሞባይል ስልኬ ወዱያው የተያዖ በመሆኑ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር አስቀድሞ የነበረ ግንኙነት ቢኖረኝ ኖሮ ተጠሪ በቴላኮም ማስረጃ ከማስረዲት የሚያግደው ነገር አልነበረም፤ ፍቶ አንስተሀል የሚለው እውነት ቢሆን ኖሮ ተጠሪውም የፍቶግራፍ ማስረጃውን እንደማስረጃ ያቀርበው ነበር፤ ፍቶግራፍ ማንሳቴ ተረጋግጦ ቢሆን ኖሮ እንኳን ይህን ማድረጌ ብቻ በሕገወጥ የሰዎች ዛውውር የእድሜየን ግማሽ ማረሚያ ቤት እንዲሳልፍ የሚያደርገኝ አይደለም፤ አመልካች ስለግለሰቦቹ ከተማ መምጣት ምንም እውቀት ያልነበረኝ በመሆኑ ወደ ውጪ አገር ትሄዲለችሁ ልል የምችልበት መነሻ ሁኔታ ስለላለ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ሕገወጥ የሰዎች ዛውውር ለመፈጸም ሀሳብ የነበረው ለመሆኑ እና በድርጊቱም ስለመሳተፈ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 909/07 አንቀጽ 3/2/ሀ መሰረት በቀረቡበት ስድስት ክሶች ጥፊተኛ የመባለን አግባባነት ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ፡- አመልካች ከስር 1ኛ ተከሳሽ፤ ለጊዚው ካልተያዖች ባለቤቱ እና ማንነቱ ካልታወቀ ግለሰብ ጋር በመሆን ስራ ሰርታችሁ ትለወጣላችሁ በማለት ስድስት ሴት ልጆችን መልምል በመኪና ወደ ነቀምት ከተማ ወስዶቸው ካሳደሯቸው በኋላ በማግስቱ ወደ ጊምቢ ከተማ አስገብቶ በማቆየት ለልጆቹ ምግብ ከሰጡ በኋላ ሥራ ሰርታችሁ ትለወጣላችሁ፤ ከ 2 ወይም 3 ዓመት በኋላ ወደ ውጪ አገር ትሄዲላችሁ በማለት ለማስታወሻ የሚሆን ፍቶ አንስቶአቸው እንደነበር እና ከብር 1000 እስከ 1500 ብር ይዙችሁ ትመጣላችሁ በማለት ስልክ ከላላ ሰው ጋር እየተደዋወለ ሳለ ድንገት ፕሉሰ ደርሶባቸው እጅ ከፍንጅ እንደተያዘ ያስረዲን በመሆኑ ለብዛበዙ ዓላማ ሉያውል እንደነበር አመላካች ነው፤ አመልካች በዓቃቤሕግ ማስረጃ የተረጋገጠበትን ፍሬነገር ባቀረበው ማስረጃ ያላስተባበለ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶቸ አመልካችን ጥፊተኛ በማለት የሰጡት ውሳኔ ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባል ተብል የተያዖውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባል በማለት የተያዖው ነጥብ አመልካች ሕገወጥ የሰዎች ዛውውር ለመፈጸም ሀሳብ የነበረው ለመሆኑ እና በድርጊቱም ስለመሳተፈ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 909/07 አንቀጽ 3/2/ሀ መሰረት በቀረቡበት ስድስት ክሶች ጥፊተኛ የመባለን አግባብነት ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 ጋር በማገናዖብ ለመመርመር በሚል በመሆኑ የዐቃቤሕግ ምስክሮች አመልካችን በሚመለከት በስር ፍ/ቤት የሰጡትን የምስክርነት ቃል ይዖት መመልከት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
የተጠሪ ምስክሮች ለስር ፍ/ቤት የሰጡት የምስክርነት ቃል ይዖት ጠቅለል ብል ሲታይ ማንነቱን የማያውቁት ሰው ትሄዲላችሁ ብል ያባበላቸው መሆኑን እና ወደ ላላ ከተማ ጉዜ ሲያደርጉ የጉዜ ወጪ ሲሸፍን የነበረው 1ኛ ተከሰሳሽ መሆኑን፤ ካለበት ከተማ ወደ ጊንቢ ከተማ የአመልካች ባለቤት ወደ ሆነችው አለውያ ቤት የገቡ መሆኑን እና ስትጠፈ ትፈለጉበታላችሁ ተስተካከለ ብለው ፍቶ ያነሳቸው መሆኑን፤ሐገሪቱ ጥሩ ናት ሰርታችሁ ትለወጣላችሁ ከ2 እስከ 3 ዓመት ስትሰሩ ደግሞ ወደ ውጪ አገር ትሄዲላችሁ ያላቸው መሆኑን፤ 1ኛ ተከሳሽ ስልክ ሲደወልለት አንተ የምትለውን ልጆች አምጥቼልሀለሁ ያላቸው መሆኑን፤ የአመልካች ባለቤት አሲያ እና ሳቢቃ አስቀራቸዋለሁ ላልቹን እንደፈለግክ አድርግ ያለች መሆኑን፤ ስልክ ደውላም ገንዖብ ይዖሽ ነይ ያለች መሆኑን እና አሲያን እና ሳቢቃን አስቀርተው ከቤት እየወጡ ሳለ ፕሉሰ የመጣባቸው መሆኑን በመግለጽ የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን 6ኛ ምስክር ደግሞ በጊምቢ ከተማ የአመልካች ባለቤት ቤት ሲባል መረጃ ሰምተው ሄደው በቤት ውስጥ ያለ ልጆች አምጧቸው ሲባል ሰዎቹን ያመጧቸው መሆኑን፤ 1ኛ ተከሳሽን ሲያናግሩ ከጅማ ዜን የአመልካችን ባለቤት ላነጋግራት መጥቻለሁ ያላቸው መሆኑን፤ ፕሉስ ጽ/ቤት ልጆቹን የወሰዶቸው መሆኑን እና ፕሉስ ሲመረምራቸው 1ኛ ተከሳሽ በፈለጋችሁበት ቦታ ገንዖብ ታገኛላችሁ ብል አባብል አምጥቶናል በማለት ገልጸዋል በማለት የመሰከረ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
በመሰረቱ አንድ ሰው ወንጀል አደረገ የሚባለው ሕገወጥነቱና አስቀጪነቱ በሕግ የተደነገገን ድርጊት ፈጽሞ በተገኘ ጊዚ መሆኑ እና አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለውም ወንጀለን የሚቋቁሙት ሕጋዊ፤ ግዘፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ መሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23 (1) እና (2) ስር ተደንግጎ የሚገኝ ሲሆን በወንጀል ጉዲይ የሚቀርብ የክስ ማመልከቻ ደግሞ ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል እንዱሁም የወንጀለ መሰረታዊ ነገርና ሁኔታዎች የተገለጹበት ላሆን እንደሚገባ እና ስለ ወንጀለና ስለሁኔታው የሚሰጠው ዛርዛር መግለጫ ተከሳሹ ፈጸመ የተባለውን ተግባር ወንጀል ከሚያደርገው ሕግ አነጋገር ጋር በጣም የተቀራረበ መሆን እንደሚገባው በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 111 እና 112 ድንጋጌዎች ላይ የተደነገገውም ከሳሹን ወገን በወ/ሕ/አንቀጽ 23(2) ስር የተመለከቱት የወንጀል መማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች ተሟልተው መገኘታቸውን ለማስረዲት እንዱያስችለው መሆኑን ከድንጋጌዎቹ ይዖት መገንዖብ ይቻላል። ይህም ከሳሽ ወገን በክሱ መሰረት የማስረዲት ግዳታ ተወጥቶአል ልባል የሚችለው ቀደም ሲል በተጠቀሱት የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 111 እና 112 ድንጋጌዎች መሰረት አዖጋጅቶ ባቀረበው የክስ ማመልከቻ መሰረት ተከሳሹ ወንጀል መፈጸሙን ማስረዲት በቻለ ጊዚ ነው። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ተከሳሹ መከላከያ ማስረጃ አቅርቦ ክሱን እንዱከላከል በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.142 መሰረት ትዔዙዛ ላሰጥ የሚችለው ከሳሽ ወገን ያቀረበው ማስረጃ ተከሳሹን ጥፊተኛ የሚያደርገው መሆኑን ሲያረጋግጥ ስለመሆኑ በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁ. 141 ስር በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል።
አመልካች የተከሰሰበት ሕገወጥ የሰዎች ዛውውርን እና ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 3/2/ሀ ማንኛውም ሰው በኢትዮጲያ የግዙት ክልል ውስጥም ሆነ ከኢትዮጲያ የግዙት ክልል ውጪ ለብዛበዙ ዓላማ ሲባል በአገር ውስጥ ስራ እና ሰራተኛን ለማገናኘት ወይም ለስራ ወይም ለስራ ልምምድ ወደ ውጪ አገር ለስራ መላክ በሚል ሽፊን ዙቻን ሀይልን ወይም ላላ ማናቸውም ዖዳ በመጠቀም፤ በማገት፤ በመጥለፍ ወይም በተንኮል በማለታለል ወይም የተስፊ ቃል በመስጠት ሰዎችን የመለመለ ያጓጓዖ፤ ያዖዋወረ፤ ያስጠለለ፤
ወይም የተቀበለ እንደሆነ እና ይህም ድርጊት በሕጻናት በሴቶች ወይም በአእምሮ ወይም በአካል ጉዲተኞች ላይ የተፈጸመ እንደሆነ ከ 25 ዓመት በማያንስ ጽኑ እሥራት ወይም እድሜልክ ጽኑ እስራት እና -500000 በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል በማለት ይደነግጋል። በዘህ ድንጋጌ መሰረት የተከሰሰን ሰው ጥፊተኛ ለማለት ተከሳሹ በድንጋጌው በተገለጸው አግባብ ድርጊቱን የፈጸመ ስለመሆኑ በቅድሚያ ሉረጋገጥበት ይገባል።
የብዛበዙ ዓላማ ማለት ደግሞ በላልች ሰዎች ዛሙት አዲሪነት መጠቀም ወይም ማናቸውም ዓይነት ወሲባዊ ብዛበዙን፤ የጉልበት ብዛበዙን የግዲጅ ስራን ወይም አገልጋይነት፤ ባርነት ወይም ባርነት መሰል ተግባር፤ የወሲብ አገልጋይነትን ጨምሮ ሰውን የማይገባ አገልጋይ ማድረግ፤ በመያዣነት መያዛ ወይም አሳልፍ ለላላ መስጠት፤ የሰው ልጅን አካል ማውጣት ወይም መወሰድ፤ አስገድድ በልመና ተግባር ማሰማራት ወይም ሕጻናትን ለወታደራዊ አገልግልት ማሰማራት እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 2/4 ላይ ከተሰጠው ትርጉም መገንዖብ ይቻላል።
በያዛነው ጉዲይ ክሱን ለማስረዲት የቀረቡት የዓቃቤሕግ ምስክሮች ካለበት ከተማ ወደ ጊንቢ ከተማ የአመልካች ባለቤት ወደ ሆነችው አለውያ ቤት የገቡ መሆኑን እና ስትጠፈ ትፈለጉበታላችሁ ተስተካከለ ብለው ፍቶ ያነሳቸው መሆኑን፤ ሐገሪቱ ጥሩ ናት ሰርታችሁ ትለወጣላችሁ ከ2 እስከ 3 ዓመት ስትሰሩ ደግሞ ወደ ውጪ አገር ትሄዲላችሁ ያላቸው መሆኑን በመግለጽ ከመመስከራቸው በቀር አመልካች በተከሰሰበት የአዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 3/2/ሀ ድንጋጌ አግባብ አመልካች ለብዛበዙ ዓላማ ሲል ዙቻን ሀይልን ወይም ላላ ማናቸውም ዖዳ በመጠቀም፤ በማገት፤ በመጥለፍ ወይም በተንኮል በማታለል ወይም የተስፊ ቃል በመስጠት በሕገወጥ መንገድ ያዖዋወራቸው መሆኑን በመግለጽ የሰጡት የምስክርነት ቃል የለም። አመልካች በሕጉ በተገለጸው አግባብ የግል ተበዲዮችን በሕገወጥ መንገድ ስለማዖዋወሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ የተከሰሰበትን የሕግ ድንጋጌ ጥሷል በማለት ጥፊተኛ ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት ስለላለ አመልካች ከቀረበበት ክስ በነጻ ሉሰናበት ይገባል።
በአጠቃላይ የስር ፍ/ቤቶች አመልካች በሕጉ አግባብ ድርጊቱን ስለመፈጸሙ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በአመልካች ላይ ያስተላለፈት የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም አመልካችን በሚመለከት የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና የቅጣት ውሳኔ፤ ይህን ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በቀን 11/08/2010 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሽሯል።
ትዔዙዛ የሚመለከተው ማረሚያ ቤት በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የምዔራብ ወለጋ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም አመልካችን በሚመለከት የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና የቅጣት ውሳኔ፤ ይህን ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በቀን 11/08/2010 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሸሮ አመልካች በነጻ እንዱሰናበት የተወሰነ መሆኑን አውቆ አመልካችን ከእስር እንዱለቅ ታዝል። ይጻፍ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።