በወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ መሰረት በሰው መግደል ወንጀል በተመሰረተ ክስ ላይ የግል ተበዲይ ህይወት በጠፊበት እና ወንጀለ የአካል ጉዲት ማድረስ ስለመሆኑ በማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የተከሳሾች የሀሳብ ክፍል ከባድ የአካል ጉዲት ለማድረስ ነው በሚል የክሱን የህግ ድንጋጌ ወደ አንቀጽ 556/2/ሀ ዛቅ በማድረግ የሚሰጥ የቅጣት ውሳኔ ተቀባይነት የላለው የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕግ እና እነ ሀብታሙ በለጠ (3 ሰዎች)
No summary available.
የሰ/መ/ ሕዲር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕግ ተጠሪዎች፡-
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.1 መጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ሀሳብ በሟች ላይ መጠነኛ የሆነ የአካል ጉዲት እንዱደርስበት ማድረግ በመሆኑ ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው በተከሰሱበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ ሳይሆን በአንቀጽ 556/2/ሀ ነው፤1ኛ ተጠሪም ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 ነው በማለት 1ኛ ተጠሪን በዖጠኝ ዓመት ጽኑ እሥራት፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችን እንደቅደም ተከተላቸው ደግሞ በስድስት ወር እና በስምንት ወር እሥራት እንዱቀጡ ሲል የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለቱ ነው።
ጉዲዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ነው። የአሁን አመልካች ተጠሪዎች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 32/1/ሀ እና 539/1/ሀ ድንጋጌን በመተላለፍ ሰውን ለመግደል አስቀድመው ሀሳብ በመያዛ እና ሟች 2ኛ ተጠሪን በቦክስ በመምታት በተማሪዎች መሀል አዋርድታል ልንበቀለው ይገባል በሚል ሀሳብ ተነሳስተው የ3ኛ ተጠሪ የእህት ልጅ የሆነውን 1ኛ ተጠሪን በስልክ ደውለው ከጠሩ በኋላ ሟችን እንዱበቀልላቸው በማግባባት የሟችን ፍቶ በማሳየት ሚያዛያ 21 ቀን 2009 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 1፡50 ሰዓት በባሕርዲር ከተማ ቀበላ 10 ልዩ ቦታው ጌታቸው ግሮሰሪ አካባቢ የ5ኛ ዓመት የኢንጅነሪንግ ተመራቂ ተማሪ የሆነውን ሟች ተመስገን ተሾመን ከጓደኞቹ ጋር እራት በልቶ ሲመለስ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ሟችን ለ1ኛ ተጠሪ ጠቁመው ካሳዩት በኋላ 1ኛ ተጠሪም ተደብቆ ቆይቶ ሟችን በድንጋይ ግንባሩ ላይ በመምታት የገደለው ሲሆን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በመላ ሀሳባቸው እና ድርጊታቸው የወንጀለን ውጤት በመቀበል ሟች እንዱገደል ያደረጉ በመሆኑ በፈጸሙት በዋና ወንጀል አደራጊነት ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ተከሰዋል በማለት ያቀረበውን ክስ የተመለከተው የባሕርዲር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪዎችን በተከሰሱበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 539/1/ሀ ድንጋጌ መሰረት ጥፊተኛ በማለት 1ኛ ተጠሪ በአሥራ ስምንት ዓመት ጽኑ እሥራት፤ 2ኛ ተጠሪ በአሥራ ስድስት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እሥራት፤ 3ኛ ተጠሪ ደግሞ በአሥራ ስምንት ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ሲል ወስኗል።
ተጠሪዎች ይህን ውሳኔ በመቃወም 1ኛ ተጠሪ ለብቻ፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ አንድ ላይ በመሆን በተለያየ መዛገብ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል።
ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ተጠሪዎች በተለያየ መዛገብ ያቀረቡትን የይግባኝ አቤቱታ አጣምሮ ግራቀኙን ካካራከረ በኋላ በዓቃቤ ሕግ በኩል በማስረጃነት የቀረበው የተጠሪዎች የእምነት ቃል የሚያሳየው ሟች ከ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጋር በሚኖርበት ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የተጣለ እና 3ኛ ተጠሪን በመሳደቡ እና ለመደብደብ በመሞከሩ፤ 2ኛ ተጠሪንም በቦክስ ፉቱ ላይ መቶ ምልክት ስላደረገበት ሟች ከዘህ ድርጊቱ እንዱቆጠብ 1ኛ ተጠሪ ቀለል ያለ ጉዲት አድርሶ እንዱያስፈራራው ፈልገው ነው፤ ምንም እንኳን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ከሟች ጋር ቀደም ሲል ተጣልተው የነበረ ቢሆንም 1ኛ ተጠሪ ሟችን በድንጋይ ፈራ ተባ እያለ እና ለመምታት እያወላወለ አንድ ጊዚ መቶት መሮጡ የሚያሳየው 1ኛ ተጠሪ ሟችን ቀላል ጉዲት አድርሶ እንዱያስፈራራላቸው አስበው ለ1ኛ ተጠሪ አሳይተውት ሟች በድንጋይ ተመቶ የሞተ መሆኑን ነው፤ በመሆኑም የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎቸ ሀሳብ ሟች ቀለል ያለ ጉዲት እንዱደርስበት ማድረግ እንጂ እንዱሞት ስላልሆነ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/2 እና 58/3 በተቀመጠው አግባብ ሉቀጡ የሚገባው በሀሳባቸው ልክ በመሆኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎቸ ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 556/2/ሀ መሰረት ነው፤ 1ኛ ተጠሪም ሟችን ለመግደል አስቀድሞ ሀሳብ እንደነበረው ዓቃቤሕግ አላስረዲም፤ የድርጊት አፈጻጸሙም የተለየ ጨካኝነቱን እና ነውረኝነቱን የሚያሳይ ስላልሆነ ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 መሰረት ነው በማለት 1ኛ ተጠሪ በዖጠኝ ዓመት ጽኑ እሥራት፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እንደቅደም ተከተላቸው ደግሞ በስድስት ወር እና በስምንት ወር እሥራት እንዱቀጡ ሲል ወስኗል። አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- ተጠሪዎች ወንጀለን የፈጸሙት ሟች 2ኛ ተጠሪን በተማሪ መሐል በቦክስ መቷል በሚል ቂም መሆኑን፤ ለ1ኛ ተጠሪ የሟችን ፍቶ ያሳዩት እና 1ኛ ተጠሪ ለመምታት በዛግጅት ላይ እንዲለ 3ኛ ተጠሪ የሴት ልጅ በለው በማለት ይዜት በነበረው ድንጋይ ግንባሩን የመታው መሆኑን፤
ሟች በደረሰበት ምት ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ መሆኑን አስረድተናል፤ ሟች በቀን 26/07/09 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ 3ኛ ተጠሪ እወጋሃለሁ እያለ ሲዛትበት የነበረ እና ተረጋግቶ መማር እንዲልቻለ ለሚማርበት ዩኒቨርሲቲ በአቤቱታ መግለጹ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎቸ ሟችን ለመግደል ቀድመው ሃሳብ የነበራቸው መሆኑን ያሳያል፤ የሀሳብ ክፍል ሉረጋገጥ የሚችለው ከድርጊት አፈጻጸም ሆኖ ሳለ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት እነኚህን ሁኔታዎች ሳያገናዛቡ ተጠሪዎች ሟችን አስቀድሞ የመግደል ሀሳብ አልነበራቸውም በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች አስቀድሞ የነበረውን ቂም ምክንያት በማድረግ 1ኛ ተጠሪ እንዱበቀልላቸው በመንገራቸው የፈጸሙት መሆኑ በተመሰከረበት ሁኔታ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪዎችን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ መሰረት ጥፊተኛ ያለማለቱን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎም 1ኛ ተጠሪ መጥሪያ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ በአዱስ ዖመን ጋዚጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባል ተብል የተያዖውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 556/2/ሀ መሰረት ነው፤ 1ኛ ተጠሪም ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 መሰረት ነው ከሚል መደምደሚያ ላይ ሉደርስ የቻለው የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ሀሳብ ሟች ቀለል ያለ ጉዲት እንዱደርስበት ማድረግ እንጂ እንዱሞት አልነበረም፤
1ኛ ተጠሪም ሟችን ለመግደል አስቀድሞ የነበረው ሀሳበ እንደነበረው ዓቃቤሕግ አላስረዲም፤ የድርጊት አፈጻጸሙም የተለየ ጨካኝነቱን እና ነውረኝነቱን አያሳይም በሚል ነው። በመሆኑም የስር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪዎች የተከሰሱበትን የሕግ አንቀጽ ለመቀየር የሰጠው ምክንያት ተገቢ ነው ወይስ አይደለም ለሚለው የክርክሩ መሰረታዊ ነጥብ ምላሽ ለመስጠት በዓቃቤሕግ በኩል በስር ፍ/ቤት የቀረቡትን የሰው ምስክሮች ቃል እና የሰነድ ማስረጃዎች ይዖት መመልከት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
በዘሁ መሰረት፡- 1ኛ የዓቃቤሕግ ምስክር ለፍ/ቤቱ የሰጠው የምስክርነት ቃል ይዖት፡- በዔለቱ ሟችን እና ላልች ጓደኞቹን እራት ለመብላት ሲጠብቃቸው የነበረ መሆኑን፤ 2ኛ ተጠሪ ስልክ ደውል አንጠጣም ወይ ያለው መሆኑን፤ ምስክሩም እራት በልቼያለው መሆኑን፤ ጓደኞቹን እየጠበቀ ሳለ ስልክ የደወለለት መሆኑን፤
ተነስቶ ሲሄድ 2ኛ ተጠሪ ደውል እራት አልበላህም ወይ ያለው መሆኑን፤ ምስክሩም አዎ ሲለው ብላና እንጠጣለን ያለው መሆኑን፤ ምስክሩም ስጨርስ እደውላለሁ ብልት የሄደ መሆኑን፤ እራት ከሚበለበት ቦታ ሲደርስ ጓደኞቹ ሲጠብቁት የነበረ መሆኑን፤ ምግቡ እስኪደርስ ድረስ ስልክ የተደወለለት እና የአባቱ ስልክ መሆኑን፤ ምግቡን እየተሻሙ ስለሚበለ ስልኩን ድምጽ አልባ አድርጎ ኪሱ ውስጥ ያስገባ መሆኑን፤ በልተው ሲወጡ ሟችን ስልክ ሲያወራ የነበረ መሆኑን፤ ሟች እና 2ኛ ተጠሪ የድርማቸው ልጆች በመሆናቸው እናስታርቃቸው ያለ መሆኑን እና ሾላ ዙፍ ያለበት ቦታ ሲደርሱ አንድ ሜትር ሟች ወደ ኋላ ቀረት ያለ መሆኑን፤ ከዘያም ኳ የሚል ድምጽ የሰሙ መሆኑን፤ ደንግጠው ዜር ሲለ ሟች ወደፉት ተንደርድሮ ሲወድቅ ከዘያን ቀን በፉት አይተውት የማያውቁ ልጅ ስላዩ ተከትለውት የሄደ መሆኑን፤ ሟችን ክሉኒክ የወሰደት መሆኑን እና ሪፈር ተጽፍላቸው ሆስፑታል ሲደርሱ ሟች ሕይወቱ ያለፈ መሆኑን፤ 1ኛ ተጠሪ ተጠሪዎች ደውለው ሚሽን እንዲለት እና መጠጥ ቤት ሲጠጡ አምሽተው የሟችን ፍቶ ያሳዩት መሆኑን፤ ሟች አዋርድኛል ሰድቦኛል ብመታው ሪከርድ አለብኝ ተመራቂ ስለሆንኩ አካዲሚክ ዱስሚሳል ሉያጋጥመኝ ይችላል፤ ሟችን አስፈራራልኝ ምታልኝ ያለት መሆኑን፤ ከሾላ ስር ተደብቆ ፈርቶ ሉተወው ሲል ፉት ለፉት ሆኖ ስኴር ሸሚዛ የለበሰው ነው አንተ የሴት ልጅ በለው ሲለው አይኔን ጨፍኖ በድንጋይ እንደመታው ሲናገር የሰማ መሆኑን በመግለጽ መመስከሩን የሚያሳይ ነው። ላልች ምስክሮችም በተመሳሳይ የመሰከሩ መሆኑን የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ያሳያል።
የዲግማዊ ምኒሉክ ሆስፑታል የጻፈው የአስከሬን ምርመራ ማስረጃ ሟች በድብደባ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ መሆኑን፤ አስከሬኑ በጋዛ ክምችት ያለ እና መበስበስ ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑን፤ በቀኝ ግንባሩ በኩል ሁለት ቦታ በትንሹ የአጥንት ጉዲት የሚታይ መሆኑን በጭንቅላቱ ቆዲ ውስጥ ደም የፈሰሰ መሆኑን፤ የራስ ቅለ ያልተሰበረ መሆኑን፤ ጭንቅላቱ ተከፍቶ ሲታይ አንጎለ ከደም ጋር የተቀላቀለ ወደ ፈሳሽነት የተቀየረ መሆኑን ለሞት ያበቃው የጭንቅላት ጉዲት እና የአንጎል ጉዲት መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ሟች ከሚማርበት ዩኒቨርሲቲ ቴክኖልጂ ኢንስቲትዩት የተላከ ማስረጃ ሟች የ5ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ መሆኑን፤ በአንድ ድርም ውስጥ የሚኖረው 2ኛ ተጠሪ የዙቻ ወንጀል ፈጽሞብኛል በማለት መረጃ የሰጣቸው መሆኑን የሚገልጽ ነው።
1ኛ ተጠሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 35 መሰረት የሰጠው ቃል ይዖት፡- ተጠሪዎች ስልክ ደውለው ዙሬ ተልዔኮ አለ መምጣት አለብህ ያለት መሆኑን፤ የምን ተልዔኮ ብል ሲጠይቃቸው ስትመጣ ይነገርሃል ያለት መሆኑን እና ኮንሰርት ለማየት ስመጣ እደውልልሃለሁ ያላቸው መሆኑን፤ በመቀጠልም 3ኛ ተጠሪ ደውልለት 10፡00 ሰዓት ላይ የተገናኙ መሆኑን እና መጠጥ የገዙለት መሆኑን፤ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር እየተደዋወለ ልጁን እየተከታተልከው ነው ወይ ያለው መሆኑን እና ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ተገናኝተው የሄደ መሆኑን፤ 1ኛ ተጠሪም ወደ ኮንሰርት ሄድ ረብሻ ስለነበር ሳይገባ የቀረ መሆኑን፤ በመቀጠልም መጠጥ ቤት ገብቶ ሲጠጣ የነበረ መሆኑን፤ 3ኛ ተጠሪም ስልክ ደውል ሙን ላይት ከሚባለው ቦታ እንድትመጣ ያለው መሆኑን፤ ካለት ቦታ ላይ ሄድ መጠጥ የጠጣ መሆኑን፤ ወዱዘህ ለምን መጣን ሲላቸው 3ኛ ተጠሪ እኔ የተጣላሁት ልጅ አለ፤ ከሰው መሃል ክብሬን ገፍኛል በቦክስ መቶ ጥልኛል ያለው መሆኑን፤ በምን ምክንያት ተጣላችሁ ሲለው በብሓር ምክንያት ነው እናንት ጉረኞች ናችሁ የተለየ ምን አላችሁ ብልኛል ያለው መሆኑን፤ አንተም ሰው ነህ እሱም ሰው ነው ሲለው ፈርቼ እንዲይመስልህ ግቢ ፈርመናል በሀምሳ ቀን ላላ ጥፊት ከተገኘብን ያባርሩናል ያለው መሆኑን፤ 2ኛ ተጠሪ ለሟች ጓደኛ ስልክ ደውል ለእራት ትመጣላችሁ ወይ ያለው መሆኑን እና እንመጣለን ሲለው ደስ ያለው መሆኑን፤ ሟች እና ጓደኞቹ እራት ወደሚበላበት ቦታ ሲያልፈ ያሳዩት መሆኑን፤ ብዘ ጠብቆ አልወጣ ሲለው ታክሲ አላገኝም ልሂድ ያላቸው መሆኑን፤ ከዘያም ሟች እና ጓደኞቹ ሲወጡ 2ኛ ተጠሪ ደውል ስልክ ደውል ስልክ የሚያናግረው ነው መጣልህ ያለው መሆኑን እና ዜር ብል በድንጋይ ከኋላው በኪል አንድ ጊዚ የመታው መሆኑን በመግለጽ ቃለን የሰጠ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
2ኛ ተጠሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 35 መሰረት የሰጠው ቃል ይዖት፡- በዔለት ግጭት ከሟች ጋር ከአንድ ወር በላይ የተጣለ መሆኑን፤ የጠቡ ምክንያት ሙዘቃ ከፍቶ ድርም ውስጥ ስፕርት ሲሰራ ሟች ጠላ ቤት አስመሰላችሁት ያላቸው መሆኑን፤ የልከር በር ተዖግቶ ስለነበር ዖጋ አድርጎት ሲልፍ አንተ ዔብድ ነህ ወይ ሲለው እብድ አይደለሁም ያለው መሆኑን፤ ሟችም ትረብሻለህ ሲለው ተያይዖው በጥፉ ሲመታው ሟችም በቦክስ የመታው መሆኑን እና ፉቱ ላይ የተሰፊ መሆኑን፤ ላልች ጓደኞቹ በድርጊቱ ይናደደ የነበረ መሆኑን፤ እሱም ዋጋ ከፍለን እንመረቅ ሳንመረቅ እንዲንቀር ያላቸው መሆኑን፤ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ስለጠቡ ያወሩ መሆኑን እና ከፉቱ ላይ የሆነ ምልክት መኖር አለበት በማለት ሟችን እንዱመታው የነገረው መሆኑን የሚያሳይ ነው።
3ኛ ተጠሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2 መሰረት የሰጠው ቃል ይዖት፡- ካምፒስ ግቢ ውስጥ 2ኛ ተጠሪ ሙዘቃ ከፍቶ ስፕርት ሲሰራ ሟች ሙዘቃውን ቀንስ በማለት ተጣልተው 2ኛ ተጠሪ ዓይኑ አካባቢ የተመታ እና ጉዲት የደረሰበት መሆኑን ሲነግረው ተናድ 1ኛ ተጠሪን ዖንዖልማ ከተባለ ቦታ ወደ ባሕርዲር ከተማ እንዱመጣ ስልክ የደወለለት መሆኑን፤ ሟች ግቢ ውስጥ መቶ እንደዖረረው እና በተማሪዎች ፉት እንዲዋረደው የነገረው መሆኑን፤ ቀለል ያለ ጉዲት እንዱደርስበት የነገው መሆኑን፤
2ኛ ተጠሪም ከሟች ጋር የተነሳውን ፍቶ ያሳየው መሆኑን እና በጣም እንዱጎዲ ሳይሆን እንዱደነግጥ አድርገህ ቀለል ያለ ጉዲት አድርስበት ያለው መሆኑን፤ ቀይ እስኴር ሸሚዛ የለበሰው ነው በማለት ያሳዩት መሆኑን የሚያሳይ ነው።
በመሰረቱ አንድ ሰው ወንጀል አደረገ የሚባለው ሕገ ወጥነቱና አስቀጪነቱ በሕግ የተደነገገን ድርጊት ፈጽሞ በተገኘ ጊዚ መሆኑ እና አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለውም ወንጀለን የሚቋቁሙት ሕጋዊ፤ ግዘፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ መሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23 (1) እና (2) ስር ተደንግጎ የሚገኝ ሲሆን በወንጀል ጉዲይ የሚቀርብ የክስ ማመልከቻ ደግሞ ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል እንዱሁም የወንጀለ መሰረታዊ ነገርና ሁኔታዎች የተገለጹበት ላሆን እንደሚገባ እና ስለ ወንጀለና ስለሁኔታው የሚሰጠው ዛርዛር መግለጫ ተከሳሹ ፈጸመ የተባለውን ተግባር ወንጀል ከሚያደርገው ሕግ አነጋገር ጋር በጣም የተቀራረበ መሆን እንደሚገባው በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 111 እና 112 ድንጋጌዎች ላይ የተደነገገውም ከሳሹን ወገን በወ/ሕ/አንቀጽ 23(2) ስር የተመለከቱት የወንጀል መማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች ተሟልተው መገኘታቸውን ለማስረዲት እንዱያስችለው መሆኑን ከድንጋጌዎቹ ይዖት መገንዖብ ይቻላል። ይህም ከሳሽ ወገን በክሱ መሰረት የማስረዲት ግዳታ ተወጥቷል ልባል የሚችለው ቀደም ሲል በተጠቀሱት የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 111 እና 112 ድንጋጌዎች መሰረት አዖጋጅቶ ባቀረበው የክስ ማመልከቻ መሰረት ተከሳሹ ወንጀል መፈጸሙን ማስረዲት በቻለ ጊዚ ነው። ተከሳሽ ባቀረበው መከላከያ ማስረጃ በዓቃቤሕግ ማስረጃ የተረጋገጠበትን ፍሬነገር በቂ እና አሳማኝ ልባል በሚችል ማስረጃ ካላስተባበለም ጥፊተኛ እንደሚባል ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 149/1 ድንጋጌ ይዖት መዖገንዖብ ይቻላል።
በያዛነው ጉዲይ ዓቃቤሕግ ያቀረባቸው የሰው ምስክሮች እና የሰነድ ማስረጃዎች ይዖት የሚያስገነዛቡት በሟች እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል አስቀድሞ ጸብ የነበረ መሆኑን፤ በሟች እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል ጸብ ከተፈጠረ በኋላ ሟች ለሚማርበት ዩኒቨርሲቲ ቴክኖልጂ ኢንስቲትዩት በአንድ ድርም ውስጥ የሚኖረው 2ኛ ተጠሪ የዙቻ ወንጀል ፈጽሞብኛል በማለት ያሳወቀ መሆኑን፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ስልክ ደውለው ዙሬ ተልዔኮ አለ መምጣት አለብህ በማለት 1ኛ ተጠሪን የጠሩት መሆኑን፤ የምን ተልዔኮ ብል ሲጠይቃቸው ስትመጣ ይነገርሃል ያለት መሆኑን፤ 2ኛ ተጠሪ ለሟች ጓደኛ ስልክ ደውል ለእራት ትመጣላችሁ ወይ ያለው መሆኑን እና እንመጣለን ሲለው ደስ ያለው መሆኑን፤ በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጥሪ መሰረት 1ኛ ተጠሪ ወደ ተባለው ቦታ ሲሄድ መጠጥ የገዙለት መሆኑን፤ 3ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር እየተደዋወለ ልጁን እየተከታተልከው ነው ወይ ያለው መሆኑን እና ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ተገናኝተው የሄደ መሆኑን፤ 3ኛ ተጠሪም ስልክ ደውል ሙን ላይት ከሚባለው ቦታ እንድትመጣ ያለው መሆኑን፤ ካለት ቦታ ላይ ሄድ መጠጥ እየጠጡ ወዱዘህ ለምን መጣን ሲላቸው 3ኛ ተጠሪ እኔ የተጣላሁት ልጅ አለ፤ ከሰው መሃል ክብሬን ገፍኛል በቦክስ መቶ ጥልኛል ያለው መሆኑን፤ በምን ምክንያት ተጣላችሁ ሲለው በብሓር ምክንያት ነው እናንት ጉረኞች ናችሁ የተለየ ምን አላችሁ ብልኛል ያለው መሆኑን፤ በመቀጠልም ፈርቼ እንዲይመስልህ ግቢ ፈርመናል በሀምሳ ቀን ላላ ጥፊት ከተገኘብን ያባርሩናል ያለው መሆኑን፤ ሟች እና ጓደኞቹ እራት ወደሚበላበት ቦታ ሲያልፈ ያሳዩት መሆኑን፤ ከዘያም ሟች እና ጓደኞቹ ሲወጡ 2ኛ ተጠሪ ደውል ስልክ የሚያናግረው ነው መጣልህ ያለው መሆኑን እና ዜር ብል በድንጋይ ከኋላው የመታው መሆኑን እና ሟች ወደፉት ተንደርድሮ የወደቀ መሆኑን እና በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዲት ሕይወቱ ያለፈ መሆኑን ነው።
በስር ፍ/ቤት ቀርበው የተሰሙት የዓቃቤሕግ ማስረጃዎች የሚያስገነዛቡት ከላይ የተመለከተውን ነው የምንል ከሆነ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 35 መሰረት ለፍ/ቤት በሰጡት ቃል፤ 3ኛ ተጠሪ ደግሞ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2 መሰረት ለፕሉስ በሰጠው ቃል ሀሳባችን የነበረው በሟች ላይ ቀላል ጉዲት እንዱደርስ ነበር በማለት ያስመዖገቡት ቃል ብቻውን ተነጥል ተጠሪዎች ሉቀጡ የሚገባው በሀሳባቸው ልክ ነው ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ ነው ወይ? የሚለው የዘህ ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ ነው።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪ ሀሳብ በሟች ላይ ቀለል ያለ ጉዲት እንዱደርስ ነበር ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረሰ ቢሆንም ተጠሪዎች ክሱን እንዱከላከለ ብይን ከተሰጠ በኋላ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 142/3 መሰረት ለፍ/ቤቱ በሰጡት ቃል ድርጊቱን አልፈጸምንም በማለት ከመካዲቸው በቀር ሀሳባችን የነበረው በሟች ላይ ቀላል ጉዲት እንዱደርስበት ነበር በማለት የሰጡት ቃል ካለመኖሩም በላይ ሀሳባቸው በሟች ላይ ቀላል ጉዲት እንዱደርስ ስለመሆኑ በልላ ደጋፉ ማስረጃ የተረጋገጠ ስለመሆኑ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ይዖት አያሳይም። በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጥሪ መሰረት ድርጊቱን የፈጸመው 1ኛ ተጠሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 35 መሰረት በሰጠው ቃልም ተጠሪዎች በሟች ላይ ቀለል ያለ ጉዲት እንዱያደርስበት የነገሩት ስለመሆኑ በመግለጽ የሰጠው ቃል የለም። ይልቁንም ሟች እና 2ኛ ተጠሪ በዩኒቨርሲቲው ድርም ውስጥ ሙዘቃ ከፍታችኋል በሚል ተጣልተው ሟች እና 2ኛ ተጠሪ የተደባደቡ እና በዘህ ምክንያት በመካከላቸው አለመግባባት የተፈጠረ መሆኑ፤ ሟች 2ኛ ተጠሪ ዙቻ ይፈጽምበት እንደነበረ ለዩኒቨርሲቲው ቀደም ብል ያሳወቀ መሆኑ፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ስልክ ደውለው ዙሬ ተልዔኮ አለ መምጣት አለብህ በማለት 1ኛ ተጠሪን የጠሩት መሆኑ፤ 3ኛ ተጠሪ ሟች ከሰው መሃል ክብሬን ገፍኛል በቦክስ መቶ ጥልኛል የተጣላነው በብሓር ምክንያት ነው እናንት ጉረኞች ናችሁ የተለየ ምን አላችሁ ብልኛል ያለው መሆኑ፤ በመቀጠልም ፈርቼ እንዲይመስልህ ግቢ ፈርመናል በሀምሳ ቀን ላላ ጥፊት ከተገኘብን ያባርሩናል ያለው መሆኑ፤ 3ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር እየተደዋወለ ሟች እራት ወደሚበላበት ቦታ መምጣት አለምምጣቱን ለማረጋገጥ መከታተላቸው፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች 1ኛ ተጠሪን መጠጥ በመጋበዛ ሟች ራት በልቶ እስኪወጣ ድረስ እንዱጠብቅ ማድረጋቸው እና ሟች ከጓደኞቹ ጋር እራት በልቶ ሲመለስ ስኴር ሸሚዛ የለበሰው እና ስልክ የሚያወራው ነው በማለት ሟችን ለይተው ማሳየታቸው ዓቃቤሕግ ባቀረባቸው ላልች ደጋፉ ማስረጃዎች መረጋገጡ ሲታይ ከሳሽ የሆነው ዓቃቤሕግ ባቀረበው የወንጀል ክስ ውስጥ የገለጻቸውን ፍሬ ጉዲዮች ትክክለኛነት ተጠሪዎች ስለመፈጸማቸው ለማሳየት ያቀረባቸው ማስረጃዎች እርስ በርሳቸው የሚደጋገፈና ተያያዥነት ያላቸው እና የተጠሪዎች ሀሳብ በሟች ላይ ቀላል ጉዲት እንዱደርስ ሳይሆን ሟችን የመግደል ሀሳብ እንደነበር የሚያሳይ ነው። የተጠሪዎች ሀሳብ የመግደል ሀሳብ ከነበረ ቀጥል መታየት ያለበት ተጠሪዎች ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው በየትኛው የወንጀል ሕጉ ድንጋጌ ነው? የሚለው ነው።
አንድ ሰው በወንጀል ሕግ አንቀፅ 539(1(ሀ)) መሰረት ጥፊተኛ ልባል የሚችለው ሰውን ለመግደል አስቀድሞ የነበረው ሐሳብ ወይም ምክንያት፤ ለመግደል የተጠቀመበት መሣሪያ ወይም ዖዳ፤ ያገዲደለ ሁኔታ ወይም ግድያው የተፈጸመበት ቅጣትን የሚያከብድ ጠቅላላ ምክንያት አንቀጽ 84 ወይም 86 ስር ሲታይ ወንጀል አድራጊው በተለይ ጨካኝ፣ ነውረኛ ወይም አደገኛ መሆኑን የሚያመለክት ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ ነው በማለት ይደነግጋል። ከድንጋጌው ይዖት መገንዖብ የሚቻለው በድንጋጌው ላይ የተጠቀሱት ነጥቦች እያንዲንዲቸው ራሣቸውን ችለው የሚቆሙ መሆኑን ነው።
በያዛነው ጉዲይ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በሟች እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት መነሻነት የያዘትን ቂም መሰረት በማድረግ 1ኛ ተጠሪን ተልዔኮ አለ በማለት በመጥራት እና ሟችን ለይተው በማሳየት ሟች በድንጋይ ተመቶ እንዱሞት ለማድረግ ዋናውን ዔቅድ ያቀነባባሩ እና የወንጀለ ዋና ጠንሳሽ መሆናቸው የተረጋገጠ በመሆኑ የ1ኛ ተጠሪ የወንጀል ድርጊት በሟች ላይ የሚያመጣውን ውጤት ሙለ ለሙለ መቀበላቸውን የሚያሳይ ነው። ወንጀለ ቂምን መሰረት በማድረግ ሶስቱም ግብረአበሮች ተሳታፉ ሆነው የፈጸሙት በመሆኑ እና ሟች ጭንቅላቱን በድንጋይ ተመቶ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰው ጉዲት ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ መሆኑ በሕክምና ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪዎቸ ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 539/1/ሀ ድንጋጌ መሰረት ነው።
በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ሀሳብ በሟች ላይ መጠነኛ የሆነ የአካል ጉዲት እንዱደርስበት ማድረግ በመሆኑ ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው በተከሰሱበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ ሳይሆን በአንቀጽ 556/2/ሀ ነው፤ 1ኛ ተጠሪም ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 ነው በማለት 1ኛ ተጠሪን በዖጠኝ ዓመት ጽኑ እሥራት፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችን እንደቅደም ተከተላቸው ደግሞ በስድስት ወር እና በስምንት ወር እሥራት እንዱቀጡ ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ሰጥተናል።
በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.1 መጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሽሯል።
በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የባሕርዲር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ 04- 04796 ሕዲር 29 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና ታሕሳስ 04 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ጸንቷል።
ትዔዙዛ
የፋዳራል፤ የክልለ እና የአዱስ አበባ ፕሉስ 2ኛ እና 3ኛ ተጠዎችን በተገኙበት ቦታ ይዖው ለሚመለከተው ማረሚያ ቤት እንዱያስረክቡ ታዝል።
የሚመለከተው ማረሚያ ቤት አስተዲደርም 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በፕሉስ ተይዖው ሲቀርቡለት 1ኛ ተጠሪም በማረሚያ ቤት የሚገኝ በመሆኑ ሶስቱም ተጠሪዎች በዘህ ጉዲይ ከዘህ በፉት የታሰሩት ካለ ታሳቢ በማድረግ በዘህ ችልት በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ተከታትል ቅጣቱን እንዱያስፈጽም ታዝል። ይጻፍ
መዛገቡ ውሳኔ ስለገኘ ተዖግቷል። ይመለስ።
በተራ ቁጥር 4 እና 5 ላይ የተመዖገበው ዳኞች በዘህ መዛገብ በቀረበው ጉዲይ አከራካሪ በሆነው ጭብጥ አብላጫ ድምፅ የያዘት የስራ ባልደረቦቻችን በሰጡት ውሣኔ ስላልተስማማን ለልዩነት ያበቁንን ምክንያቶች ከዘህ ቀጥል አስፍረናል።
በመዛገቡ ላይ ከቀረቡት ክርክሮች መካከል ዋናውና በመካከላችን አከራካሪ የነበረው ነጥብ ተጠሪዎች ጥፊተኛ ተብለው ቅጣት ሉወሰንባቸው የሚገባው የባህር ዲር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሰጠው ፍርድ በከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ነው ወይስ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አሻሽል እንደወሰነው 1ኛ ተጠሪ በተራ የሰው ግድያ ወንጀል፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ታስቦ በሚፈፀም ቀላል የአካል ጉዲት ወንጀል የሚለው ነው። የስር ፍርድ ቤት የሆነው የባህር ዲርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ከሟች ጋር የነበራቸውን ቂም መነሻ በማድረግ ሶስቱም የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ /ሀ/ ና አንቀጽ 539/1/ /ሀ/ የተመለከተውን ክልከላ ተላልፈው ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ፈፅመው የሚል ውሣኔ ሰጥቷል።የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ መነሻነት የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በቀረበው የዐ/ህግ ማስረጃ አመልካቾች ድርጊቱ መፈፀማቸው ተረጋግጦባቸው የዐ/ሕግ ማስረጃ ያላስተባበለ በመሆናቸው የጥፊተኝነት ፍርድ መሰጠቱ ተገቢ ሆኖ ሣለ ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው ግን 1ኛ ተጠሪ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 እና 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪ ታስቦ በሚፈፀም ቀላል የአካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ነው ሲል የከፍተኛው ፍርድ ቤቱን ውሣኔ አሻሽሎል። ይህ ውሣኔ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር በሚ ችልት ተመርምሮ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ስለመሆኑ ትእዙዛ ተሰጥቶበታል።
ከላይ እንደተገለፀው በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪዎች የወንጀል ድርጊት መፈፀማቸው ስለተረጋገጠባቸው የጥፊተኝነት ፍርድ መወሰኑ ተገቢ ሆኖ ሣለ አከራካሪ የነበረውና ለልዩነታችን ምክንያት የሆነው ተጠሪዎች ወንጀል መፈፀማቸውን ለማስረዲት ዐ/ሕግ ለስር ፍርድ ቤት ያቀረባቸው ማስረጃዎች ካረጋገጡት ፍሬ ነገር አንፃር ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው በየትኛው ድንጋጌ ነው።
ዐ/ሕግ ባቀረበው ማስረጃ 1ኛ ተጠሪ ይህን ድርጊት የፈፀመውም 2ኛ ና 3ኛ ተጠሪዎች ሟች ሁለተኛ ተጠሪን ደብድቦት ስለነበር በዘህ ድርጊት በሁለተኛ ተጠሪ የደረሰውን የሞራል ጉዲት ለማካካስ በማሰብ 1ኛ ተጠሪ ሟችን እንዱያስፈራራቸውና እንዱያስደነግጥላቸው ስለጠየቁት ለማስፈራራትና ለማስደንገጥ አስቦ ፈራ ተባ እያለ አንድ ጊዚ ድንጋይ ወርውሮ የሟችን ጭንቅላት መምታቱን በዘህ ምት ምክንያት ሟች ለሞት መብቃቱ የስር ፍርድ ቤቶች የመዛገብ ግልባጭ ያስገነዛባል።
በወንጀል ሕግ አንቀጽ 539 ድንጋጌ መሰረት አንድ ሰው የሰው ግድያ ወንጀል ፈፅሟል ተብል ጥፊተኛ የሚባለውና የሚቀጣው የሰው መግደል ወንጀል ከመፈፀሙ በፉት አስቀድሞ ሰውን ለመግደል በማሰብ የነበረውን ሃሳብና ሃሳቡን ከፍፃሜ ለማድረስ ያደረገውን ዛግጅት እንዱሁም የተጠቀሰበትን መሣሪያ ለወንጀለ መፈፀም ያበቃውን ምክንያትና አገዲደለን ሁኔታ ወይም አድራጊውን ጨካኝነት ወይም ነውረኝነት ግምት ውስጥ በማስገባት ላሆን እንደሚገባ ተደንግጓል። በዘህ ድንጋጌ መሰረት አድራጊው ወንጀል ለመፈፀም ማሰብ ብቻ ሣይሆን አስቀድሞ መግደል አለብኝ ብል ማቀድን መዖጋጀትን እና ባቀደው መሰረት መፈፀሙ መረጋገጥ ይኖርበታል። ተከሳሽ በእነዘህ መመዖኛዎች መሰረት ድርጊቱን የፈፀመ ስለመሆኑ በቅድሚያ የማስረዲት ሀላፉነቱ የዐ/ሕግ ስለመሆኑ የታመነ ነው።
በልላ በኩል ወንጀል ተፈፅሟል ለማለት የድርጊት ፈፃሚውን ወንጀል ለመፈፀም የነበረውን ሐሳብና በተፈፀመው ድርጊት የተገኘውን ውጤት ለማግኘት አስቦ አድራጊው ድርጊቱን ስለመፈፀሙ በታመነ ጊዚ ስለመሆኑ፤ ነገር ግን አድራጊው መፈፀም ካሰበው ድርጊት ለተፈፀመው ድርጊት ባስከተለው ውጤት ተጠያቂ ላሆን እንደማይገባ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23፤32/2/፤58 ይደነግጋል።
በተያዖው መዛገብ ቅድሚያ የማስረዲት ሃላፉነቱን ለመወጣት ማስረጃ ያቀረበው ዐ/ሕግ ባቀረበው ማስረጃ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች 1ኛ ተጠሪ ሟችን እንዱገልላቸው ፍፁም ሐሳብ ያልነበራቸው መሆኑን፤
1ኛ ተጠሪም ድረጊቱን የፈፀመው ሟችን ለመግደል አስቦ ሣይሆን 2ኛና 3ኛ ተጠሪዎች በነበሩት መሰረት ለማስፈራራትና ለማስደንገጥ ብል እንደሆነ ተረጋግጧል።
ይህ ከሆነ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ሟች በ1ኛ ተጠሪ እንዱገደል አስቀድሞ ሐሳብ የነበራቸው ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበትና ይልቁንም ዐ/ሕግ ራሱ ባቀረበው ማስረጃ 1ኛ ተጠሪ ሟችን እንዱያስፈራራላቸው አስበው የጠየቁትና በዘሁ መሰረት ማስፈራራት ድረጊቱን ለመፈፀም አስቦ 1ኛ ተጠሪ በፈፀመው ድርጊት ሟች ስለሞተ ብቻ ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ፈፅመዋል በሚል 1ኛ ተጠሪም 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በለመኑት መሰረት ሟችን ለማስፈራራት አስቦና አቅድ ይህን ለመፈፀም ሟችን አንድ ጊዚ በድንጋይ ሲመታው ስለሞተ ከላይ የተዖረዖሩት የከባድ የሰው መግደል ወንጀል ማቋቋሚያ ከሆኑት መመዖኛዎች መካከል አንደም ሣያሟላ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ጥፊተኛ ተብለው ቅጣት የወሰነባቸው የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሣኔ እንዱፀና መደረጉ መሰረታዊ የማስረጃ ምዖና መርህን የጣሰ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ውሣኔ ነው በሚል ምክንያት ከባልደረቦቻችን የተለየ ሐሳብ ስለያዛን፤ ይልቁንም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት 1ኛ ተጠሪን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 ተላልፍ ተራ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ፈፅሟል በሚል 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች 1ኛ ተጠሪ በሟች ላይ እንዱፈፀም የፈለጉትን ድርጊት መጠየቅ አለባቸው በሚል የወንጀል ሕግ አንቀጽ 556/2/ ተላልፈው ቀላል የአካል ጉዲት ወንጀል እንዱፈፀም መስማማታቸውን ድርጊቱ እንዱፈፀም ማድረጋቸው ተረጋግጧል በሚል የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ በማሻሻል መወሰኑ ተገቢ ነበር በሚል በሀሳብ ተለይተናል።
No topics extracted.