ከተገኘ ገቢ የሚከፈል ግብርንና የተሰበሰበን ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ደረሰኞች ሐሰተኛ መሆናቸው ብቻ አንድን ተከሳሽ ጥፊተኛ አቶ ገበያው ሽቴ እና የማይችልና ሐሰተኛ ደረሰኝ ናቸው የተባለት ደረሰኞች አፈጣጠርና ለገቢ ሰብሣቢው መስሪያቤት አቀራረብ ሂደት ላይ የተከሳሹን ድርሻና በሕግ የተጣለበት ግዳታ ከወንጀል ህግ መሰረታዊ መርህና የወንጀል ማስረጃ ምዖና መርህን በተከተለ መንገድ ሉመረመር የሚገባው ስለመሆኑ ከወንጀል ሕግ አንቀፅ 23(1) ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 22፣49፣50 (1) የሰሜን ሸዋ ዜን ገቢዎች ዐ/ህግ
No summary available.
ታሕሳስ 20 ቀን 2012 ዓም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ ገበያው ሽቴ ጠበቃቸው፡- አቶ ብናልፈው ነጋ ቀርበዋል:: ተጠሪ፡- የሰሜን ሸዋ ዜን ገቢዎች ዐ/ህግ፡- አልቀረቡም:: መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ከተገኘ ገቢ የሚከፈል ግብርንና የተሰበሰበን ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን ለገቢ ሰብሣቢው ተቋም ገቢ አለማድረግ እንዱሁም ሐሰተኛ ወይም አሣሣች የክፍያ ደረሰኝ ማቅረብን በሚመለከት የቀረበ የወንጀል ክስን የሚመለከት ሲሆን አመልካች ልዩ ልዩ ግብይት መፈፀሜን ያረጋግጡልኛል በሚል ለገቢ ሰብሣቢ መስሪያ ቤቱ ያቀረባቸው ደረሰኞች እንዱታተሙ ፍቃድ ያልተሰጠባቸው፣በቀሪውና ለከፊይ በሚሰጠው ደረሰኝ የተፃፈው የገንዖብ መጠን የተለያዬ መሆኑን እንዱሁም የቀንና የቁጥር ቅደም ተከተል መዙባት ምክንያት በማድረግ መከፈል የነበረበትን ግብር አለመክፈል፣ ሃሰተኛ ወይም አሣሳች ደረሰኝ ለገቢ ሰብሣቢ መስሪያ ቤቱ ማቅረብ እና ከልዩ ልዩ ግብይቶች የሰበሰበውን ተጨማሪ እሴት ክፍያ በወቅቱ አሣውቆ ገቢ አለማድረግ ሶስት የወንልጀ ድርጊቶችን የፈፀመ ጥፊተኛ ነው ተብል በስምንት ዓመት ከአምስት ወር ፅኑ እስራትና በአንድ መቶ ሺህ ብር መቀጮ እንዱቀጣ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ውሣኔ ተብል እንዱታረም የቀረበ ክርክርን ይመለከታል።
ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ ግንቦት 29 ቀን 2009 ዓ.ም በተፃፈ ክሱ የአሁን አመልካች ደብረ ብርሃን ከተማ በኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ኪራይ የንግድ ስራ የተሰማራ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዛጋቢ መሆኑን በመዖርዖር፡- በ1ኛ ክስ በ2005ዓ.ም የግብር ዖመን 1,409,349.95 ብር ግብር የሚሰበሰብበት ገቢ አግኝቶ 485,322.49 ብር ግብር በወቅቱ መክፈል ሲገባው ባለመክፈለ የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 76/94 አንቀፅ 97 የሚደነግገውን ተላልፍ ግብር አለመክፈል፡- በ2ኛ ክስ አመልካች በ2005ዓ.ም 1,409,349.95 ብር ዋጋ ያለው ግብይት በመፈፀሙ ከዘህ ውስጥመክፈልየነበረበትን ተጨማሪ እሴት ታክስ አንሶ እንዱከፈል በማቀድ ከአቶ ያለው አበበ፣ከአቶ ታፈረ ሰንደቁ እንዱሁም ከአቶ ተፈሪ ባንቴ ጋር በገባቸው የገልባጭ መኪና ኪራይ ውልች ገንዖብ የከፈለ እንዱሁም ከአቶ ሁሴን ኢብራሂም የተሸከርካሪ ጎማ ገዛቶ ክፍያ የፈፀመ በማስመሰል በታክስ ማስታወቂያ ወቅት 19 ሀሰተኛና የተጭበረበሩ ደረሰኞች ለገቢ ሰብሣቢ መስሪያ ቤቱ በማቅረቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 50(3)(ለ) የተመለከተውን በመተላለፍ ለገቢ ሰብሣቢ መስሪያ ቤቱ ሃሰተኛና የተጭበረበሩ ደረሰኞችን ማቅረብ፡- በ3ኛ ክስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዛጋቢ የሆነው አመልካች ከልዩ ልዩ ገቢዎች የሰበሰበውን 4517.49 ብር በሐምል ወር 2005ዓ.ም ለገቢ ተቋሙ አሣውቆ መክፈል ሲገባው ባለመፈፀሙ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ አለማድረግ በጥቅለ ሶስት ወንጀልችን ፈፅሟል የሚለ ክሶችን አቅርቦበታል።
አመልካች ክድ በመከራከሩ የስር ፍርድ ቤት የሆነው የሰሜን ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ካዲመጠ በኋላ አመልካች በሁለተኛው ክስ ከተዖረዖሩት 19 ደረሰኞች መካከል ከአቶ ሁሴን ኢብራሂም ተሰጥቶኛል ሲል ያቀረበው አንድ ደረሰኝ እንዱሁም ከአቶ ታፈረ ሰንደቁ ተሰጥቶኛል በሚል ያቀረባቸው ሰባት ደረሰኞች እውነተኛ መሆናቸው ተረጋግጧል፤ ቀሪዎቹ ከአቶ ያለው አበበ የቀረቡት ደረሰኞች በበራሪው ላይ የተፃፈው የገንዖብ መጠን በቀሪው ላይ አለመፃፈን፣ አቶ ያለው አበበ ደረሰኞችን እንዱያሳትም ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑን የቁጥርና የቀን ቅደም ተከተል የተዙባ መሆኑ፤ እንዱሁም ከአቶ ታፈረ ሰንደቁ ተሰጥቶኛል በሚል የቀረቡት አምስት ደረሰኞች በበራሪው ላይ የተፃፈው የገንዖብ መጠን በቀሪው ላይ አለመፃፈን ተፈሪ ሰንደቁ ደረሰኙን እንዱያሣትም ፈቃድ አለማግኘቱን የደረሰኝ ቁጥርና የተሰጡበት የቀን ቅደም ተከተል መዙባቱ ደረሰኞች ላይ የተከናወነው የፍረንሲክ ምርምራ አረጋግጧል፤ አመልካችም ደረሰኞቹን ግለሰቦች ሰጡኝ ከሚል በስተቀር ግለሰቦች እንዱያሣትሙ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑንና በተሰጡት ደረሰኞች ላይ የተፃፈባቸው ገንዖብ በቀሪዎቹ ላይ ስለመፃፈ ሕጋዊ ስለመሆናቸው አላስረዲም ስለሆነም ሀሰተኛ በሆኑት አስራ አንድ ደረሰኞች መክፈል የነበረበትን 192,534.43 ብር ግብር አለመክፈለ ሀሰተኛ ደረሰኝ ማቅረቡ እንዱሁም 4517.49 ብር ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰብስቦ ገቢ ማድረግ ሲገባው ገቢ አለማድረጉ ተረጋግጧል በሚል በሶስቱም ክሶች ጥፊተኛ ብል በስምንት ዓመት ከአምስት ወር ፅኑ እስራትና በአንድ መቶ ሽህ ብር ቅጣት እንዱቀጣ ወስኗል።
በዘህ ውሣኔ ቅር የተሰኘው አመልካች የይግባኝ አቤቱታውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት በማጣቱ ይህን የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። የአመልካች ጠበቃ ሐምል 30ቀን 2011ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታቸው አመልካች ከአቶ ያለው አበበ፣ ከአቶ ተፈሪ በንቲ፤
ከአቶ ታፈረ ሰንደቁ ጋር የመኪና ኪራይ ውል ስለመግባቱ የውል ሰነድችን በማቅረብ፣ ለተጠቀሱት ሰዎች ክፍያ በመፈፀም ወጪ ያወጣ ስለመሆኑ ደረሰኞችን በማቅረብ፤ ያለው አበበና ተፈሪ በንቲ ከአመልካች ጋር በገቡት የመኪና ኪራይ ውል መሰረት ገንዖብ ተቀብለው ደረሰኝ ስለመስጠታቸው ለገቢ ሰብሣቢው መስሪያቤት አረጋግጠው ሣለ፤ አቶ ተፈሪ ሰንደቁ የኪራይ ዋጋ መቀበለንና ደረሰኝ መስጠቱን ሣይክድ ገንዖቡን አመልካች እንደፃፈው ቢገልፅም በፍረንሲክ በተደረገው ምርምራ ደረሰኙን ራሱ ፅፍ ያወጣው ስለመሆኑ በተረጋገጠበት፤ አቶ ሁሴን ኢብራሂም የተገዙውን ጎማ በሚመለከት በቀረበው አንድ ደረሰኝ ግብይት አልፈፀምኩም ቢለም እንዱሁም ከአቶ ተፈረ ሰንደቁ የተሰጡት ሰባት ደረሰኞች በፍረንሲክ ተመርምረው እውነተኛ ደረሰኞች መሆናቸው በተረጋገጠበት ጥፊተኛ መባላቸው፤ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ ሐሰተኛ ማስረጃ ማቅረብ ጥፊት የሚባለው ግብር ላለመክፈል የላለን ፍሬ ነገር እንዲለ አስመስል ማቅረብን በሚመለከት ሲሆን አመልካች ደረሰኞችን ያቀረባቸው በወጪ እንዱያዛላቸው ሆኖ ሣለና ደረሰኞች ያለፈቃድ መታተማቸው በቀሪና በበራሪው ላይ የተለያዬ መጠን ያለው ገንዖብ መፃፈ የቀን ቅድም ተከተል መዙነፈ ደረሰኞችን ሃሰተኛ ሉያስብላቸው የማይችል ሆኖ ሣለ፣ በበራሪውና በቀሪው ላይ አስተካክል መፃፍ የአመልካች ግዳታ ሣይሆን፤ ይልቁንም አመልካች ባቀረበው ማስረጃ ግብይት በመፈፀም ወጪ ማውጣቱን ባረጋገጠበት፤ አመልካች ከአቶ ሁሴን ኢብራሑም ያቀረበው ደረሰኝ ትክክለኛ በመሆኑ ተጠያቂነት የለበትም ከተባለ በኋላ በ3ኛው ክስ ጥፊኛ መባለ በቀረቡበት ክሶች ጥፊተኛ ተብል ቅጣት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት መሆኑን በመዖርዖር እንዱታረምለት ጠይቋል።
የአመልካችን የሰበር አቤቱታ የመረመረው አጣሪ ችልት አመልካች ከተጠቀሱት ሰዎች ጋር ግብይት መፈፀሙ በተረጋገጠበት፤ በአስራ አንደ ደረሰኞች ላይ ተረጋገጠ የተባለው የቀንና የቁጥር ቅድም ተከተል መዙባት፣ በቀሪዎች ላይ የገንዖብ መጠን አለመፃፍ፣ ከሚመለከተው ተቋም ደረሰኞች እንዱታተሙ ፈቃድ ያልተሰጣቸው መሆን በተለይም ደረሰኞችን ከሰጡት ሰዎች ጋር የወንጀል ተሣትፍ የነበረው ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት አመልካችን በሃላፉነት ሉያስጠይቅ የሚችል ስለመሆን አለመሆኑና የሶስተኛው ክስ መሰረት የሆነው ደረሰኝ በፍፈረንሲክ ምርምራ ትክክለኛ መሆኑ በተረጋጠበት በሶስቱም ክሶች ጥፈተኛ ተብል ቅጣት የመወሰኑን ተገቢነት ተመርምሮ እንዱወሰን ተጠሪም የመልስ ክርክር እንዱያቀርብ ትዔዙዛ በመስጠቱ መዛገቡ ለዘህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪ መስከረም 30ቀን 2011 (ፍርድ ቤቱ የአፃፃፍ ስህተት እንደሆነ ግንዙቤ ወስድበታል)በተፃፈ መልሱ ለቀረቡበት ክሶች ምክንያት የሆኑት ደረሰኞች መካከል ስምንቱ አጠራጣሪ በሆነ የፍረንሲክ ምርምራ ውጤት ሕጋዊ ናቸው መባለ ተገቢ አለመሆኑን፤ አመልካች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዛጋቢ በመሆኑ ግብይትም ሉፈፅም የሚገባው ከላልች ቫት ተመዛጋቢዎች ሆኖ ሣለ ከሕግ ውጪ ከተርን ኦቨር ታክስ ተመዛጋቢዎች ጋር ግብይት ፈፅሞ በወጪ እንዱያዛለት ደረሰኝ ማቅረቡ ከመነሻው ሕገ ወጥ መሆኑን፣ ደረሰኞች አንዱታተሙ ከገቢ ሰብሣቢ መስሪያ ቤቱ ፈቃድ ያልተሰጠባቸው መሆኑ መረጋጡን፤ የአመልካችና ደረሰኙን የሰጡት ሰዎች የወንጀል ተሣትፍ ከጅምሩ የዐ/ሕግ ክስ መሰረት አለመሆኑን፤ የሶሰትኛውን ክስ በሚመለከት አመልካች በወቅቱ ገቢ አሣውቆ ስለመክፍለ ማረጋገጫ አለማቅረቡን ያቀረበው ደረሰኝም በ2005ዓ.ም ግብይት ስለመፈፀሙ አለመረጋገጡን በጥቅለ የስር ፍርድ ቤት አመልካችን በሶስቱም ክሶች ጥፊተኛ ብል ቅጣት በመወሰኑ የፈፀመው መሰረታዊ የሕግ ስህትት የለም ተብል የአመልካች አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግለት የመልስ ክርክሩን አቅርቧል።
አመልካች የሰበር አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ ክርክሩን አቅርቧል።
ከፍ ሲል የተመለከትነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ውሣኔ እንዱሰጥበት ለለዬው ማስቀረቢያ ነጥብ መልስ ለመስጠት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው ምርመረናል።
እንደሚታወቀው የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3)(ሀ)ና አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 10 እንደሚደነግጉት የክልልና የፋዳራል ፍርድ ቤቶች እንዱሁም የዲኝነት ስልጣን በሕግ የተሰጣቸው ላልች አካላት የቀረበላቸውን ጉዲይ አከራክረው የመጨረሻ ውሣኔ ሲሰጡ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፃማቸው በክርክር ሂደት ሲረጋገጥ የማረም ስልጣን ለዘህ ችልት ተሰጥቶታል። በዘህ መሰረት በያዛነው ክርክር የዘህ ችልት ስልጣን አከራካሪ የሆነ ፍሬ ነገርን በማስረጃ ማጣራት ሣይሆን የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የቀረበውን ክርክር መርምረው ውሳኔ ሲሰጡ የፈፀሙት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ካለ ማረም መሆኑን ከወዱሁ ልብ ልባል ይገባል።
የወንጀል ሕግ አንድ ሰው በሕግ አድርግ ወይም እንዲታደርግ ብል የሚደነግግ መደረግ ያለባቸውንና መደረግ የላለባቸውን ድርጊቶች በዛርዖር የሚያመለክትና በመደረጋቸውና ባለመደረጋቸው የተነሣ የድርጊቱን ፈፃሚዎች የሚቀጣ የቅጣቱን መጠንና ዓይነት የሚወሰን ሕግ ነው። ይህም ማለት ወንጀል ድርጊት ተፈፅሟል የሚባለው በወንጀል ሕግ የተከለከለ ድርጊቶችን መፈፀም ወይም እንዱፈፀሙ የተታዖዘ ድርቶችን አለመፈፀም ነው።
ከዘህ መርህ በመነሣት ወደያዛነው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረባቸው የሶስቱም ክሶች መነሻቸው ሀሰተኛ ወይም አሣሣች ደረሰኝ ማቅረቡ እንደሆነ የስር ፍርድ ቤቱ የውሣኔ ግልባጭ ያሰገነዛባል። አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 50(1) ለታክሱ ባለስልጣን ሰራተኛ አንድን ነጥብ በሚመለከት የሐሰት ወይም አሳሳች ማስረጃ ያቀረበ ወይም ማስረጃው አሣሣች እንዲይሆኑ መካተት የሚገባቸውን ነገሮች ቀንሶ ያስቀረ ወንጀል እንፈጸመ የሚቆጠርበት መሆኑና በዘሁ አዋጅ በአንቀፅ50(3) (ሀ)ና(ለ) ድንጋጌ መሰረት የሐሰት መግለጫው የተሰጠው እንዱካተት የሚገባው ነገር ያልተካተተው ሆነ ተብል ወይም በከባድ ቸልተኝነት የሆነ እንደሆነ ወንጀል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የቅጣቱ መጠን ከፍ እንደሚል ይደነግጋል። እነዘህን ድንጋጌዎች ተላልፎል በሚል በአመልካች ላይ የቀረቡትን ክሶች የአመልካች ድርጊት ወንጀል መሆን ያለመመሆናቸው ሉወሰን የሚገባው በኢ.ፋ.ዳ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 23(2) የተደነገጉትን የወንጀል ማቋቋሚያ መመዖኛዎችና በአንቀፅ 58(1)(ሀ) ላይ የተደነገገውን ድርጊቱ ወንጀል ነው ለማለት ታስቦ የተፈፀመ መሆን እንደሚገባው የተደነገገውን መርህ ግምት ውስጥ በማስገባት ላሆን ይገባል።
ይህ ከሆነ ተጠሪ ዐ/ሕግ ያቀረበውን ክስ ማስረዲት የሚጠበቅበት አመልካች ሃሰተኛ ደረሰኙን ማቅረቡን ብቻ ሣይሆን ሃሰተኛ ደረሰኙን በማዖጋጀት ተሳትፍ ማድረጉን ወይም ራሱ በክሱ ላይ እንደጠቀሰው አመልካች ግብር ቀንሶ እንዱከፍል እና የሰበሰበውን ተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ላለማድረግ በማሰብ ሃሰተኛ መሆኑን እያወቀ ገቢ ማድረጉን ማስረዲት ይኖርበታል።
ይህ ሆኖ ሣለ የግራቀኙን ክርክር ከስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ግልባጭ ጋር በማገናዖብ ስንመረምረው ዐ/ህግ በክሱ ላይ ሃሰተኛ ናቸው የሚላቸውን ደረሰኞች ለአመልካች ቆርጠው የሰጡት ሰዎች በክልለ ውስጥ ሕጋዊ ነጋዳዎች ከመሆናቸውም በላይ እነዘህ ደረሰኞች ከእነሱ የወጡ ስለመሆኑ ደረሰኙን በሰጡት ሰዎች አልተካደም። ይህም ሆኖ የስር ፍርድ ቤት ደረሰኞቹ ሀሰተኛ ናቸው አመልካችም ጥፊተኛ ነው ለሚለው መደምደሚያ ያበቁት ሶስት ምክንያቶች ናቸው። እነዘህም በተለምድ ቀሪ እና በራሪ በሚባለው ወይም ለከፊዩ በሚሰጠውና ከጥራዘ ጋር በሚቀረው ደረሰኝ ላይ የተፃፈው ገንዖብ መበላለጥ በአንዲንድች ላይ ለከፊዩ በተሰጠው ላይ ተፅፍ በቀሪው ላይ ያለመፃፍ፤ የቁጥርና የቀን ቅደም ተከተል መዙነፍ እና ደረሰኙን የሰጡት ሰዎች ከገቢ ሰብሣቢው መስሪያ ቤት ደረሰኞችን እንዱያሣትሙ ፈቃድ ያልተሰጣቸው መሆኑ ናቸው።
በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 23(1) ድንጋጌ መሰረት አንድ ሰው በሕግ እንዱያደርግ (እንዱፈፅም) ወይም እንዲያደርግ(እንዲይፈፅም) በሕግ ግዳታ የተጣለበትን ተላልፍ የሚያስቀጣ ድርጊት ፈፅሞ ሲገኝ ወንጀል እንፈጸመ ታምኖበት ቅጣትም እንደሚወሰንበት ይደነግጋል። ስለሆነም ከላይ ለቀረቡት ደረሰኞች ሐሰተኛ መሆናቸው ብቻ አመልካችን ጥፊተኛ ሉያስብለው ስለማይችል የስር ፍርድ ቤት ሐሰተኛ ደረሰኝ ናቸው በተባለት ደረሰኞች አፈጣጠርና ለገቢ ሰብሣቢው መስሪያቤት አቀራረብ ሂደት ላይ የአመልካችን ድርሻና በሕግ የተጣለበት ግዳታ ከወንጀል ሕግ አንቀፅ 23(1) መርህ አንፃር ሉመረመር ይገባል።
እነዘህ ደረሰኞች ከተጠቀሱት ነጋዳዎች ለአመልካች የተሰጡበት በመካከላቸው በነበረው የአከራይና ተከራይ ግብይት ምክንያትና አመልካች ተከራይ(ገዥ) ደረሰኙን ያወጡት ሰዎች ደግሞ አከራይ(ሻጭ) እንደነበሩ የግራቀኙ ማስረጃና የስር ፍርድ ቤት መዛገብ ግልባጭ ያስገነዛባል። ይህ ከሆነ ለከፊዩ በሚሰጠውና ከጥራዘ ጋር በሚቀረው ደረሰኝ ላይ የተፃፈው ገንዖብ መበላለጥ አንዲይኖር ማድረግ፣ ለከፊዩ በተሰጠው ደረሰኝ የተፃፈውን ገንዖብ መጠን በቀሪው ላይ መፃፍ፣ የቁጥርና የቀን ቅደም ተከተል መዙነፍ እንዲይኖር መጠንቀቅ፣ ደረሰኞች እንዱታተሙ ፈቃድ የወጣባቸው ስለመሆኑ ማረጋገጥ የአመልካች ግዳታ ላሆን ይገባዋልን የሚለው የግራቀኙ የክርክር ነጥብ በመሆኑ ሉመረመር ይገባዋል።
ከዘህ አንፃር ማንም ምክንያታዊ ሰው በኑሮ ልማድ እንደሚገነዖበውና አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 22 እንደሚደነግገው ትክክለኛ ደረሰኝ የመስጠት ግዳታ የተጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዛጋቢ የሆነው ሻጭ ስለመሆኑ ተደንግጓል። የምክንያታዊ ገዥ ሃላፉነት ለከፈለው ገንዖብ ደረሰኝ እንዱሰጠው ከመጠየቅ በዖለለ ደረሰኞች ፈቃድ ወቶባቸው መታተማቸውን ወይም ለከፊዩ በተሰጠው ደረሰኝ ላይ የተፃፈው ገንዖብ በቀሪው ላይ መፃፍ አለመፃፈን፣ የደረሰኞች ቅድም ተከተል ስለመጠበቁ ወይም አለመጠበቁ የማረጋገጥ ግዳታ የገዥ ስለመሆኑ ዐ/ሕግ በክሱ ላይ የጠቀሣቸው አዋጆች አልደነገጉም።
በልላ በኩል ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ደረሰኞች በማዖጋጀት ረገድ አመልካችና ደረሰኞችን ያወጡት ሰዎች ወንጀል ለመፈፀም ስምምነት ለማድረጋቸውና አመልካችም ተሳትፍ የነበረው ስለመሆኑ ወይም ደረሰኙን በማዖጋጀት ወይም ሐሰተኛ መሆናቸው እያወቀ ግብሩን አሣንሶ ለመክፈል በማሰብ ድርጊቱን ስለመፈፀሙ ዐ/ህግ አላስረዲም።
ተጠሪ ካቀረባቸው ማስረጃዎች መካከል የተጠሪ ምስክር በጥቅለ ሁለም ደረሰኞች ሃሰተኞች መሆናቸውን የመሰከረ ሲሆን ሃሰተኛ ናቸው ያለበት ምክንያት ለክሱ ምክንያት ከሆኑት 19 ደረሰኞች ውስጥ አስራ አንደ የቀን እና የቁጥር ቅደም ተከተል የተዙነፈባቸው እንዱሁም እንዱታተሙ ፈቃድ ያልተሰጠባቸውና ለአመልካች በተሰጠው ድርሻ ገንዖብ ተፅፍ በቀሪው ላይ ባለመፃፈ ቢፃፍም ተበላልጦ መፃፈን ምክንያት በማድረግ ስለመሆኑ መዛገቡ ያስረዲል። ሆኖም አመልካች ደረሰኞች በእጁ የገቡት ደረሰኞችን ከሰጡት ሕጋዊ ነጋዳዎች ጋር በፈፀመው ግብይት ስለመሆኑ በግራ ቀኙ ማስረጃ በተረጋገጠበት፤ በአንፃሩ ተጠሪ አመልካች ያቀረባቸውን ደረሰኞች ሐሰተኛ ስለመሆናቸው እያወቀ ወይም ሉያውቅ የሚችልበት ሁኔታ መኖሩ ባልተረጋገጠበት የአመልካች ግዳታ ባልሆኑ ከላይ በተጠቀሱት መመዖኛዎች ደረሰኞች ሕጋዊ አይደለም በሚል ብቻ አመልካችን ጥፊተኛ ሉያደርገው የሚችል ማስረጃና ክርክር ባልቀረበበት በ1ኛ እና በ2ኛ ክሶች ስለመፈፀሙ በበቂ ሁኔታ ተመስክሮበታል በሚል እንዱከላከል ብይን መሰጠቱና በኋላም አልተከላከለም በሚል ጥፊተኛ መባለ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
ሶስተኛውን ክስ በሚመለከት የተጠሪ ክስ መሰረት የሚያደርገው ከልዩ ልዩ ግብይት የተሰበሰበ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ በሐምል ወር 2005ዓ.ም ለገቢ ተቋሙ አሣውቆ ገቢ ማድረግ ሲገባው ባለማድረጉ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 ድንጋጌን ተላለፎል የሚል ነው።
አመልካች የሰበሰብኩትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ባለመድረጌ የተፈጠረ ችግር ሣይሆን ልዩነቱ የተከሰተው ከአቶ ሁሴን ኢብራሂም ጎማ ስገዙ የከፈልኩትን ተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ አቅርቤ ተጠሪ ሐሰተኛ ነው በሚል ለመያዛ ፈቃደኛ አለመሆኑ ተከትል የመጣ ችግር እንደሆነ ይከራከራል።
በተጠሪ ገቢ ያልሆነው ገንዖብ ምንጭ አመልካች ከአቶ ሁሤን ኢብራሑም ጋር በነበረው የጎማ ግዥ ግብይት ነው በሚለው ክርክር ላይ ግልፅ ተቃውሞ ሣያቀርብ አመልካች ከሁሴን ኢብራሑም ጋር የጎማ ግዥ የፈፀመው በ2005ዓ.ም ሣይሆን በ2006ዓ.ም መሆኑን ራሱ አቶ ሁሴን ኢብራሂም አረጋግጧል ይህ ደግሞ የ2006 ደረሰኝን ለ2005ማቅረቡ ጥፊት እንደሆነ ይከራከራል። ሆኖም በአመልካች ጠያቂነት ደረሰኙ በፍረንሲክ ሲመረመር እውነተኛ ደረሰኝ ስለመሆኑ ተረጋግጧል። ምርምራው የተደረገው አንድ ነጠላ ፍሬ ነገርን ለማረጋገጥ ታስቦ ስለመሆኑ በተለየ ሁኔታ ካልተገለፀ በስተቀር የአንድ ደረሰኝ በፍረንሲክ ላቦራቶር ተምርምሮ እውነተኛ ነው ከተባለ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በደረሰኙ ላይ የተፃፈትን ፍሬ ነገሮች በሞላ የሚያጠቃልል ነው። ስለሆነም የሶስተኛው ክስ መሰረት አመልካች ከአቶ ሁሴን ኢብራሂም የተቀበለው ደረሰኝ መሆኑ ባልተካደበት፣ ይህ ደረሰኝ በተጠሪ በኩል ሃሰተኛ ነው በሚል ተቀባይነት በማጣቱ ክርክር ተደርጎበት እውነተኛ መሆኑ በተረጋጠበት የስር ፍርድ ቤትም የምርመራውን ውጤት ውድቅ ባላደረገበት የደረሰኙ እውነተኛ መሆን የአመልካች ክርክር ተገቢ መሆኑን ባረጋገጠበት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 149(2) መሰረት አመልካችን በነፃ ማሰናበት ሲገባ ጥፊተኛ ማለቱ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረባቸውን 1ኛና 2ኛ ክሶች በሚመለከት አመልካች ከሕጋዊ ነጋዳዎች ጋር ግብይት በመፈፀሙ ለከፈለው ክፍያ ከነጋዳዎች ደረሰኝ መቀበለን ባስረዲበት የእሱ ግዳታ ባልሆኑ መመዖኛዎች ማለትም ለከፊዩ በሚሰጠውና ከጥራዘ ጋር በሚቀረው ደረሰኝ ላይ የተፃፈው ገንዖብ መበላለጥ፣ ለከፊዩ በተሰጠው ደረሰኝ የተፃፈውን ገንዖብ መጠን በቀሪው አለመፃፍ፣ የቁጥርና የቀን ቅደም ተከተል መዙነፍ መኖር፣ ደረሰኞቹ እንዱታተሙ ፈቃድ የወጣባቸው አለመሆናቸው በሚለት መመዖኛዎች ተመዛነው ሀሰተኛ ናቸው የተባለትን ደረሰኞች ለገቢ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት አመልካች ስለቀረበ ብቻና ደረሰኞቹ ሃሰተኛ ስለመሆናቸው እውቅና ኖሮት ስለማቅረቡ ግምት የሚያስወስደ ሁኔታዎች ስለመኖራቸው በተጠሪ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ገንዖብ ልዩነቱ የተፈጠረው ገቢ ሰብሣቢ መስሪያ ቤቱ ትክክለኛውን ደረሰኝ ሀሰተኛ ነው በሚል አልይዛም በማለቱ እንደሆነ በተረጋገጠበት የስር ፍርድ ቤት አመልካችን ጥፊተኛ ብል ቅጣት መወሰኑ የይግባኝ ክርክሩን የመረመረው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይህን አለማረሙ ፍርድ ቤቶች ሉተገብሩት የሚገባውን መሰረታዊ የወንጀል ማስረጃ ምዖና መርህን ያልተከተ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ውሣኔ በመሆኑ ተከታዩ ተወስኗል።
ውሣኔ
የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ 4 በሆነው ሰኔ 28ቀን 2011ዓ.ም በዋለው ችልት አመልካችን በቀረቡበት ሶስት ክሶች ጥፊተኛ ብል በስምንት ዓመት ከአምስት ወር ፅኑ እስራትና በአንድ መቶ ሺህ ብር እንዱቀጣ የወሰነው ውሳኔና ይህን ተከትል አመልካች ያቀረበውን ይግባኝ ክርክር የመረመረው የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሰት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዛገብ በሆነው ሐምል 18ቀን 2011ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዔዙዙ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2)(ለ)(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በተጠሪ ከቀረቡበት ክሶች ከላይ በተገለፁት ምክንያቶች በነፃ እንዱሰናበት ተወስኗል።
ትዔዙዛ
የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሀን ማረሚያ ቤት አመልካች በልላ ወንጀል የማይፈለግ ከሆነ ዙሬውኑ ከእስር እንዱፈታው ታዝል፤ ይፃፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይለመስ።የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.