አንድ ተከሳሽ ማንኛውም የንግድ ዔቃን ከመደበኛው የግብይት አሰራር ውጭ በማናቸውም ማጓጓዣ ከተፈቀደ የስርጭት መስመር ውጭ ሲያጓጉዛ የተያዖ ስለመሆኑ ሳይረጋገጥበት፤ዔቃውም የተፈቀደ የስርጭት መስመር ያለው መሆን አለመሆኑና ከመስመር ውጪ ሲጓጓዛ የነበረ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በወንጀል ጥፊተኛ ልባል የማይገባው ስለመሆኑ የነጋዳዎች እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 24/3/ እና 43/4/ 168067 ሰይድ አሉ አበጋዛ እና የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የንግድ እና ሸማቾች ዓቃቤ ሕግ 29/09 / 2011 ዓ.ም. 59. አንድን ዔቃ ከውጪ የሚያስመጣ ሰው ለጉምሩክ ሥርዓት አፈጻጸም ሲባል ስለሚያስመጣው ዔቃ አስፈላጊ የሆኑ መግለጫዎችን በመስጠት በዱክላራሲዮን ላይ በማስመዛገብ ወደ ሐገር ውስጥ የሚገቡ ዔቃዎች በላኪው እና በአስመጪው መካከል በሚደረግ ስምምነት ወደ ሐገር ውስጥ የሚገቡ ከመሆናቸው አኳያ ወደ ሐገር ውስጥ እንዱገባ የተደረገው ዔቃ አስመጪው በዱክላራሲዮን ካስመዖገበው ዔቃ የበለጠ ዋጋ ያለው ሆኖ በተገኘ ጊዚ አስመጪው የተላከውን ዔቃ ሉያውቅ የሚችልበት ሁኔታ የለም ተብል ከወንጀል ተጠያቂነት ነፃ ላደረግ የማይገባ ስለመሆኑ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 13/4/፣169/2/
No summary available.
ሕዲር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ አልቀረበም ተጠሪዎች፡- 1.ክኤሳድ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃላ/የተ/የግ/ማሕበር ጠበቃቸው ወርቅነህ በረደድ 2. አቶ ሀይለ አስገድም ቀረቡ :: 3. አቶ ክብሮም ሀይለ አስገድም - ቀረቡ:: መዛገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 22 ቀን 2010 ዓ.ም ተጠሪዎችን ከቀረበባቸው ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ በማሰናበት የሰጠው ብይን እና ይህንኑ ብይን በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ብይን መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
የአሁን አመልካች በአሁን ተጠሪዎች ላይ ያቀረባቸወ ክሶች ሁለት ሲሆኑ ክሳቸውም፡በ1ኛ ክስ፡- የአሁን 1ኛ ተጠሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 34/1 እና የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 169/2 እና 173 ድንጋጌን በመተላለፍ ከቻይና ሐገር በዱክላራሲዮን ቁጥር ሲ-2195/2016 በቀን 12/12/2008 ዓ.ም እና በደረሰኝ ቁጥር ኤ.ኤች 16ኤ081 በቀን 20/10/08 ዓ.ም ብዙቱ 6372 ደርዖን ኦ.ኤል ፔላስቲክ ጆግ ወደ ሐገር ውስጥ ለማስገባት አሳውቆ የነበረ ሲሆን በኢትዮጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዱስአበባ ቃሉቲ ጉምሩክ ቅርንጫች ጽ/ቤት በቀን 18/12/08 ዓ.ም በአካል ሲፈተሸ በሰነድ ላይ ያልተገለጸ ብዙቱ 3186 ደርዖን ኩባያ በመገኘቱ ተደብቀው የተገኙት የዔቃዎች ዋጋ 11,182.86 ድላር ወይም 247,646.67 ብር መሆኑን እና ይህም በሰነደ ከተገለጸው አጠቃላይ የዔቃው ዋጋ 11,278.44 ድላር .43 ብር ጋር ሲነጻጸር የዋጋ ልዩነቱ ከ50% በላይ ወይም 99% ሆኖ በመገኘቱ በፈጸመው የማጭበርበር ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
2ኛ ክስ፡- የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 34/1 እና የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 169/2 ድንጋጌን በመተላለፍ 2ኛ ተጠሪ የ1ኛ ተጠሪ ማሕበር ስራ አስኪያጅ በመሆን፤ 3ኛ ተጠሪ ደግሞ በውክልና ማሕበሩን ሲመሩ ተገቢውን የአሰራር ስርዓት ባለመዖርጋት የድርጅቱን ጥቅም በሕገወጥ መንገድ ለመምራት በማሰብ 1ኛ ተጠሪ በ1ኛ ክስ የተገለጸውን ወንጀል እንዱፈጽም በማድረጋቸው በፈጸሙት የማጭበርበር ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪዎች ድርጊቱን አልፈጸምንም ብለው ክደው በመከራከራቸው የአመልካችን ማስረጃዎች ከሰማ በኋላ በላኪው በኩል የተጠየቀው ጆግ ብቻ እንጂ ኩባያ የማይጨምር በመሆኑ ላኪው ያልተጠየቀውን ኩባያ በመላኩ በስህተት መሆኑን በመግለጽ የእርማት ደብዲቤ ወደ ሐገር ውስጥ ተልኮ በባለስልጣኑ የወንጀል ምርመራ ክፍል የደረሰ ስለመሆኑ በዓቃቤሕግ ምስክርም ተገልጿል፤ በአካላዊ ፍተሻ የተገኙት ጆጎች መጠን ደረጃ ልዩነት ሳይኖራቸው ግማሽ በሚሆን መጠን ላይ ባለት ጆጎች ውስጥ አራር አራት ኩባያዎች መገኘታቸው በተከሳሽም ሆን ብለው ኩባያዎቹን ደብቆ ለማስገባት የወንጀል ሐሳብ የነበራቸው መሆኑን አያሳይም፤ ከድርጅት ሀላፉዎች አንጻር በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ላይ የቀረበው ክስ የሚነቀፍ ባይሆንም ልዩነቱ 99% መሆኑ ክስ የቀረበበት ዔቃ በስህተት ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን የሚጠቁም እንጂ አስቀድሞ በሰነድች ያልተጠቀሱትን ኩባያዎች በድብቅ ወደ ሐገር ውስጥ ለማስገባት ሃሳብ የነበረቻው መሆኑ በቂ ማስረጃ ባለመቅረቡ እና ተገውን ቀረጥ እና ታክስ በማስከፈል እና አስፈላጊውን አስተዲደራዊ እርምጃ መውሰድ ተገቢ በመሆኑ እና በተከሳሾች ላይ በወንጀል ተጠያቂነት ረገድ ጠንካራ በቂ እና አሳማኝ ማስረጃ በላለበት ሁኔታ የወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም በማለት ተጠሪዎችን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141 መሰረት ከቀረበባቸው ክስ በነጻ አሰናብቷቸዋል። አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- ወደ ሐገር ሲገባ ተደብቆ የተገኘው የዔቃ ዋጋ በሕጋዊ መንገድ ወደ ሐገር ከገቡት ዔቃዎች ዋጋ ጋር ሲነጻጸር 99% ባላይ መሆኑ ተረጋግጧል፤ ልዩነቱ ሉፈጠር የቻለውም በአካላዊ ፍተሻ በሕጋዊ ዔቃ ውስጥ ተደብቀው ብዙታቸው 3186 ኩባያዎች በጆጎቹ ውስጥ ተደብቆ የተገኘ መሆኑን አስረድተናል፤ ይህም የተጠሪዎችን ወንጀል የመፈጸም ሀሳብ ክፍል የሚያረጋግጥ ነው፤ የስር ፍ/ቤት 1ኛ የዓቃቤሕግ ምስክር በወቅቱ 3ኛ ተጠሪ ዔቃው በስህተት እንደተላከላቸው በመግለጽ የእርምት ደብዲቤ ወደ ምርመራ ክፍል አስገብተው የነበረ መሆኑን ገልጿል ከማለት ውጪ ማስረጃው ቀርቦ የነበረ መሆን አለመሆኑን አላረጋገጠም፤ ላኪው ድርጅት ለትርፍ የሚሰራ ከመሆኑ አንጻር ይህን ያህል ልዩነት ያለውን ዔቃ ክፍያ ሳይፈጸምለት በስሕተት ይልካል ብል ድምዲሜ መውሰድ ተገቢነት የለውም ፤ ስሕተቱ መፈጸሙን በተመለከተም ከላኪው ድርጅት የተገለጸ ነገር የለም፤ ስሕተቱ ተፈጸመ ቢባል እንኳን ተጠሪዎች ወንጀል የመፈጸም ሀሳብ ባይኖራቸው ዔቃው ወደሐገር ውስጥ ገብቶ ከመፈተሹ በፉት ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያሳውቁ ነበር እንጂ ድርጊቱ መፈጸሙ ከታወቀባቸው በኋላ መከራከሪያ ሆኖ ላቀርብ አይገባም የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ ከውጪ ሐገር ወደ ሐገር ውስጥ ፔላስቲክ ጆግ ለማስገባት አሳውቆ ውስጡ ኩባያ መገኘቱ ባልተካደበት ሁኔታ ተጠሪዎች ክሱን እንዱከላከለ ብይን ሳይሰጥ በነጻ የመሰናበታቸውን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል።
ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪዎች መልስ ይዖት በአጭሩ፡- እሽጉ በምስክሩ ፉት ሲከፈት ጉምሩክ አስተላላፉው በቦታው የነበረ ሲሆን ተጢዎች በቦታው አልነበሩም፤ ተጠሪዎች በቦታው የተገኙት ዔቃው ልዩነት ተገኝቶበታል ከተባለ በኋላ ነው፤ 3ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ ስም ያዖዘት ጆግ ብቻ እንደሆነ እና ኩባያውን እንደማያውቁት እና በስሕተት አንደተላከ ገልጸው የማስተካከያ ደብዲቤ ለባለስልጣኑ የወንጀል ምርመራ ገልጸዋል፤ 2ኛ ምስክርም በዱክላራሲዮን የተመዖገበው ዔቃ ጆግ ብቻ መሆኑን፤ በአካላዊ ፍተሻ ኩባያ የያዘ መሆናቸውን፤ የተገኘው ዔቃ አስቀድሞ ከተገለጸው ጋር ሲነጻጸር 99% መሆኑን ገልጸዋል፤ ተጠሪዎች በጆጎቹ ከለላነት ኩባያውን ወደ ሐገር ለማስገባት ሀሳብ እንደነበራቸው አልተረጋገጠም፤ ዔቃው ወደ ሐገር የገባው በስሕተት መሆኑን የአመልካች ምስክር አረጋግጧል፤ የተገኘው ጆግ መጠን ከታዖዖው ጋር ምንም የዓይነትም ሆነ የደረጃ ልዩነት ሳይኖራቸው ግማሽ መጠን ባለው ጆግ ውስጥ አራት አራት ኩባያ መገኘቱ በተጠሪዎች በኩል ኩባያ አለመታዖዘ እና በላኪው ስሕተት ምክንያት ችግሩ የተፈጠረ ስለመሆኑ የሚያሳይ ነው፤ አስመጪው የሚያስመጣቸው ዔቃዎች እንዱመጡለት የሚያደርገው ሐገር ውስጥ በመሆን ከባንክ ጋር በሚደረግ ግንኙነት ሲሆን ተጠሪዎች እንዱላክልን የጠየቅነው በግዢ ሰነድ የተመለከቱትን እቃዎች ብቻ ነው፤ ላኪው አገር የሚልከውን ምስክር ወረቀት እና የቅድመ ጭነት ምርመራ ሲቀርብ እና ዔቃው በአካል ሲፈተሸ ምን እንደመጣ ከምናውቅ በቀር አስቀድመን ልናውቅ የምንችልበት ላላ መንገድ የለም፤ ዔቃው ተጠሪዎች ባለንበት አልታሸገም ፤ ተጠሪዎች የወንጀል ሀሳብ የነበረን ስለመሆኑ በክሱ እና በማስረጃው ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ዔቃው በ1ኛ ተጠሪ ስም መምጣቱን መነሻ በማድረግ ተጠያቂ ልንሆን አይገባም የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዖውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ ያቀረበው ብዙታቸው 6372 ደርዖን የሆኑ ፔላስቲክ ጆግ ወደ ሐገር ውስጥ ለማስገባት አሳውቀው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተደረገው አካላዊ ፍተሻ በሰነድ ላይ ያልተገለጹ ብዙታቸው 3186 ደርዖን ኩባያዎች ተገኝተዋል፤ ተደብቀው የተገኙት የዔቃዎች ዋጋ 11,182.86 ድላር ወይም 247,646.67 ብር መሆኑን እና ይህም በሰነደ ከተገለጸው አጠቃላይ የዔቃው ዋጋ 11,278.44 ድላር .43 ብር ጋር ሲነጻጸር የዋጋ ልዩነቱ 99% ሆኖ በመገኘቱ በጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀል ተጠያቂ ሉሆኑ ይገባል በሚል ሲሆን ዔቃው ከጂቡቲ ወደ ቃሉቲ ጉምሩክ ገብቶ እሽጉ ሲፈታ በተደረገው አካላዊ ፍተሻ በሰነድ ከተገለጸው ውጪ ብዙታቸው 3186 ኩባያዎች በጆጎቹ ውስጥ የተገኙ መሆኑ እና ተደብቀው የተገኙት የዔቃዎች ዋጋ 11,182.86 ድላር ወይም 247,646.67 ብር መሆኑን እና ይህም በሰነደ ከተገለጸው አጠቃላይ የዔቃው ዋጋ 11,278.44 ድላር .43 ብር ጋር ሲነጻጸር የዋጋ ልዩነቱ 99% በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬነገር ነው።
የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 13/4 ዱክላራሲዮኑ ከተመዖገበ በኋላ ለማጭበርበር በማሰብ ወይም በከባድ ቸልተኝነት የተፈጸመ ግድፈት በአዋጁ መሰረት ያስቀጣል በማለት ይደነግጋል። የአዋጁ አንቀጽ 169/2 ተደብቆ የተገኘው ዔቃ በዱክላራሲዮን ላይ ከተገለጸው ጠቅላላ ዋጋ 50% በላይ ሆኖ ከተገኘ ዔቃዎችን በመደበቅ ሕገወጥ በሆነ መንገድ ወደ ሐገር በማስገባት ወይም ከሐገር ለማስወጣት የሞከረ ማናቸውም ሰው ከአምስት ዓመት በማያንስ እና ከአስር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት እና ከብር 50,000 በማያንስ እና ከብር 100,000 በማይበልጥ የገንዖብ መቀጮ ይቀጣል በማለት ይደነግጋል።
የስር ፍ/ቤት ተጠሪዎችን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ያሰናበታቸው በላኪው በኩል የተጠየቀው ጆግ ብቻ እንጂ ኩባያ የማይጨምር በመሆኑ ላኪው ያልተጠየቀውን ኩባያ መላኩ በስህተት መሆኑን በመግለጽ የእርማት ደብዲቤ ወደ ሐገር ውስጥ ተልኮ በባለስልጣኑ የወንጀል ምርመራ ክፍል የደረሰ ስለመሆኑ በዓቃቤሕግ ምስክርም ተገልጿል፤ በአካላዊ ፍተሻ የተገኙት ጆጎች መጠን ደረጃ ልዩነት ሳይኖራቸው ግማሽ በሚሆን መጠን ላይ ባለት ጆጎች ውስጥ አራር አራት ኩባያዎች መገኘታቸው በተከሳሻም ሆን ብለው ኩባያዎቹን ደብቆ ለማስገባት የወንጀል ሐሳብ የነበራቸው መሆኑን አያሳይም በማለት ነው። በመሰረቱ አንድን ዔቃ ከውጪ የሚያስመጣ ሰው ለጉምሩክ ሥርዓት አፈጻጸም ሲባል ስለሚያስመጣው ዔቃ አስፈላጊ የሆኑ መግለጫዎችን በመስጠት በዱክላራሲዮን ላይ ማስመዛገብ ያለበት ስለመሆኑ እና ወደ ሐገር ውስጥ የሚገባው ዔቃ በዱክላራሲዮን ላይ ከተመዖገበ በኋላ ለማጭበርበር በማሰብ ወይም በከባድ ቸልተኝነት የተፈጸመ ግድፈት የሚያስቀጣ መሆኑን ከጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 13/4 መገንዖብ ይቻላል። በዘህ አግባብ ተመዛግበው ወደ ሐገር ውስጥ የሚገቡ ዔቃዎች በላኪው እና በአስመጪው መካከል በሚደረግ ስምምነት ወደ ሐገር ውስጥ የሚገቡ ከመሆናቸው አኳያ ወደ ሐገር ውስጥ እንዱገባ የተደረገው ዔቃ አስመጪው በዱክላራሲዮን ካስመዖገበው ዔቃ የበለጠ ዋጋ ያለው ሆኖ በተገኘ ጊዚ አስመጪው የተላከውን ዔቃ ሉያውቅ የሚችልበት ሁኔታ የለም ተብል ክሱ የቀረበበት ተከሳሽ መከላከል ሳያስፈልገው ከወዱሁ በነጻ ሉሰናበት ይገባል ተብል ድምዲሜ የሚወሰድበት አይደለም።
በያዛነው ጉዲይ የስር ፍ/ቤት ተጠሪዎችን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ያሰናበተው በላኪው በኩል የተጠየቀው ጆግ ብቻ እንጂ ኩባያን አይጨምርም፤ ላኪው ያልተጠየቀውን ኩባያ መላኩ በስህተት መሆኑን በመግለጽ የእርማት ደብዲቤ ወደ ሐገር ውስጥ ተልኮ በባለስልጣኑ የወንጀል ምርመራ ክፍል የደረሰ በመሆኑ በአካላዊ ፍተሻ የተገኙት ጆጎች መጠን ደረጃ ልዩነት ሳይኖራቸው ግማሽ በሚሆን መጠን ላይ ባለት ጆጎች ውስጥ አራት አራት ኩባያዎች መገኘታቸው ተጠሪዎች ሆን ብለው ኩባያዎቹን ደብቀው ለማስገባት የወንጀል ሐሳብ የነበራቸው ስለመሆኑ አያሳይም በማለት ነው። የስር ፍ/ቤት ተጠሪዎችን በዘህ አግባብ በነጻ ያሰናበታቸው ቢሆንም ተጠሪዎች በአዋጁ መሰረት በዱክላራሲዮን አስመዛግበው ላስገቡት ዔቃ ትክክለኛነት ሀላፉነት ያለባቸው በመሆኑ፤ ተጠሪዎች በዱክላራሲዮኑ ላይ ወደ ሐገር ውስጥ ለማስገባት በዱክላራሲዮን ካስመዖገቡት ፔላሲቲክ ጆጎች ውጪ ብዙታቸው 3186 ኩባያዎች በጆጎቹ ውስጥ የተገኙ መሆኑ እና ተደብቀው የተገኙት የዔቃዎች ዋጋ 11,182.86 ድላር ወይም 247,646.67 ብር መሆኑን እና ይህም በሰነደ ከተገለጸው አጠቃላይ የዔቃው ዋጋ 11,278.44 ድላር .43 ብር ጋር ሲነጻጸር የዋጋ ልዩነቱ 99% በመሆኑ፤ ዔቃው ወደ ሐገር ውስጥ የሚገባው በላኪው ድርጅት እና በተጠሪ መካከል በሚደረግ ስምምነት በመሆኑ፤
ላኪው ደርጅት በንግድ ላይ የተሰማራ አትራፉ ድርጅት ከመሆኑ አኳያ ከተጠሪዎች ዔውቅና ውጪ ክፍያ ያልተፈጸመባቸውን እና እንዱላኩ ያልተጠየቁ ዔቃዎችን ይልካል ተብል አስቀድሞ ድምዲሜ ላይ መድረስ የማይቻል በመሆኑ፤ ግብይቱ በባንክ መፈጸሙ ተጠሪዎች የተላከው ዔቃ በዱክላራሲዮን ከተመዖገበው ዔቃ የተለየ ዔቃ መሆኑን ሉያውቁ አያስችላቸውም ተብል ድምዲሜ ላይ ለመድረስ የማያስችል በመሆኑ፤ ተጠሪዎች በእርግጥም ዔቃው በስሕተት የገባ ነው የሚለ ከሆነ በአካላዊ ፍተሻ በሰነድ ከተገለጸው ዔቃ ውጪ ላላ ዔቃ እንደገባ ከመረጋገጡ በፉት አስቀድመው ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አለማሳወቃቸው በክሱ የተገለጸውን የወንጀል ድርጊት የመፈጸም ሀሳብ እንደነበራቸው አመላካች ነው ከሚባል በቀር ዔቃው በስሕተት የገባ ነው ብል ከወዱሁ ለመደምደም እና ተጠሪዎች የቀረበባቸውን ክስ ሳይከላከል ከወዱሁ በነጻ ለማሰናበት የሚያስችል ባለመሆኑ ተጠሪዎች የቀረበባቸውን ክስ ሉከላከለ ይገባል። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ዓቃቤሕግ ባቀረበው ማስረጃ ተጠሪዎችን በክሱ የተገለጸውን ወንጀል የፈጸሙ ስለመሆናቸው ያረጋገጠ ሆኖ ሳለ ተጠሪዎችን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ማሰናበቱ፤
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍ/ቤትም ይህንኑ ሳያርም ማለፈ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ብይን በወ/መ/ሥ/ስ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሽሯል።
ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ማስረጃ ተጠሪዎች በክሱ የተገለጸውን የወንጀል ድርጊት ስለመፈጸማቸው በበቂ ሁኔታ ያረጋገጠባቸው በመሆኑ ተጠሪዎች የቀረበባቸውን ክስ ሉከላከለ ይገባል በማለት ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪዎችን በነጻ በማሰናበት የሰጠው ብይን የተሻረ እና ተጠሪዎች የቀረበባቸውን ክስ እንዱከላከለ የተወሰን መሆኑን አውቆ ተጠሪዎች መከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርቡ ካደረገ በኋላ የግራቀኙን ማስረጃ መርምሮ ተገቢውን እንዱወስን በማለት ጉዲዩን መልሰንለታል።
ት ዔ ዙ ዛ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በብይን የዖጋውን መዛገብ እንደገና በማንቀሳቀስ ተጠሪዎች መከላከያ ማስረጃ ካላቸው አስቀረቦ ሰምቶ ተገቢውን እንዱወስን ታዝል።
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዖግቷል። ይመለስ::