No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዘያ 25 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በዔውቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን ተጠሪ፡- ሱፏር ማክስ ኦብቲካል ሚዱያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር መዛገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች ሐምል 24 ቀን 2010 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፍደራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዓ በመ/ቁ ከሱ-1019 ነሐሴ 17 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 04/07/2010 እንዱሁም የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 24/08/2010 ዓ.ም በማጽናታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመ በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው።
ጉዲዩ የንግድ ትርፍ ግብርን የሚመለከት ነው። ተጠሪ በ21/02/2007 ዓ.ም የደረሰውን የ2010 ዓ.ም የግብር ዖመን የንግድ ትርፍ ግብር በመቃወም ለአቤቱታ አጣሪ ኮሚቴ ቢያቀርብም ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዓ ያቀረበው ይግባኝ ይዖት ድርጅቱ በኤላክትሮኒክስ ነክ አታሚነት ዖርፍ ሐምል 16/2000 በተሰጠው ፈቃድ ሲዱ እና ዱቪዱ፤ ኦዱዩ ቪዱዬ እና ተያያዥ ምርቶችን የሚያመርት መሆኑን፤ ለዘሁ ተግባር በኢንቨስትመንት ማበረታቻው በመጠቀም የማምረቻ ማሽን ዔቃዎችን ያስገባ መሆኑን፤ በዘህም ለ2000 ዓ.ም በጀት ዓመት ቀሪው 14 ቀን ቢሆንም የ2000 ዓ.ም የሐብትና ዔዲ መግለጫ ለግብር አስገቢው መ/ቤት አሳውቋል፤ ሆኖም በዘህ ዖመን ንግድ ፈቃድ የወሰደበት እንጂ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ማምረትና መሸጥ ያልተጀመረበት ሆኖ ሳለ የሐብትና ዔዲ መግለጫ ሲዖጋጅ ለምስረታና ማሽነሪ ግዢ የወጡትን ወጪዎች በበጀት ዓመቱ የደረሰ ኪሳራ እንደሆነ የሚያሳይ ሰነድ ቀርቧል፤ ግብይት ባልተደረገበት በጀት ዓመት ላታይ እና ሉያዛ የሚችል ኪሳራ አለመኖሩ የሚታወቅ በመሆኑ በ2001 በበጀት ዓመት ላይ ሉያዛ የሚገባ በመሆኑ ማስተካከያ እንዱደረግ ለግብር አስገቢው ባለሥልጣን አሳውቀናል፣ በ2001 እና በ2002 በጀት ዓመት ኪሳራ የታየ እና በ2003 ትርፍ ማስመዛገብ የጀመርን መሆኑ የተረጋገጠ ሆኖ አመልካች በ21/07/07 በተጻፈ የንግድ ትርፍ ግብር ማስታወቂያ በ2002 ዓ.ም ግብር የሚከፍልበት ትርፍ አለ በማለት ግብር ፤ወለድና መቀጫ በማስላት በድምሩ .41 እንድንከፍል በግብር ውሳኔ አሳውቆናል ስለሆነም በ2000 በጀት ዓመት ኪሳራ ተብል የቀረበው በ2001 በቀረበው የሂሳብ ሰነድ የተስተካከለ በመሆኑና ኪሳራ ደርሶበታል የሚባለው ማምረት እና ግብይት መፈፀም ከጀመረ ጊዚ ጀምሮ በመሆኑ ኪሳራው የደረሰው በ2001 ዓ.ም ይባልልን፣ በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 28/1/ መሰረት ኪሳራው ለሶስት ተከታታይ ዓመት የሚሸጋገር በመሆኑ በ2002 የግብር ዖመን ኪሳራ አለመድረሱ በሑሳብ በባለሙያ ተረጋግጦ ቀርቦ ኪሳራ የለም በ2001፤ የደረሰውም ኪሳራ ወደ 2002 ማሸጋገር አትችለም ተብል አቤቱታው ውድቅ የተደረገው ይሻርልኝ የሚል ነው።
አመልካች በሰጠው መልስም ግብር ከፊዩ የሚያቀርበው መረጃ በግብር ህጉ በደንብ እና በመመሪያ መሰረት መሆን የሚጠበቅበት በ2000 ዓ.ም ግብይት መፈፀም አልጀመርኩም ይበል እንጂ እንደጀመረ አረጋግጠናል፣ ለዖመኑ ኪሳራ ተብል የተገለፀው በእርጅና ቅናሽ ላይ መቀነስ የነበረበት ገንዖብ መጠን ነው፣ ማስተካከያ ቀርቧል ይበል እንጂ አልቀረበም፣ በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 28/1/ እና /3/ ኪሳራ ሉሸጋገር የሚችልበትንና ሁኔታና ጊዚ የተደነገገ ሲሆን በደንብ ቁጥር 78/94 አንቀጽ 12 ደግሞ ኪሳራው ሉሸጋገር የሚችለው በግብር ባለሥልጣኑ ኦዱት ተደርጏ ተቀባይነት ሲያገኝ ወይም በውጭ ኦዱተር የተመረመረ ሂሳብ ሲቀርብ በመሆኑ ተጠሪ የ2000 ግብር ዖመን የሂሳብ መዛገቡ በባለሥልጣኑ ኦዱተር ስላልተረጋገጠ ያልተያዖላቸው ሲሆን የ2001 ኪሳራ ግን በውጭ ኦዱተር የተረጋገጠ በመሆኑ በባለሥልጣኑ ባይረጋገጥም በውጭ ኦዱተር የተረጋገጠ በመሆኑ ኪሳራው ተይዜለት በ2003 ካገኘው ትርፍ ተካክሶ ግብር የተወሰነ በመሆኑ ተጠሪ እንደሚለው አይደለም፤ ይህም የተጠሪ ጥያቄ እርስ በርሱ የሚጋጭ ነው፤ ኪሳራ የሚሸጋገረው ወደ ተገኘበት የግብር ዖመን ነው። ስለሆነም ውሳኔው ተገቢ በመሆኑ ይጽናልኝ፣ ተጠሪ በ2000፣ በ2001፣ በ2002 የግብር ዖመን ኪሳራ ያሳወቀ በመሆኑ በተጠቀሰው አንቀጽ መሰረት የ2002 ኪሳራ ሉሸጋገር አይችልም ብሎል።
የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዓው የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ በ2000 ዓ.ም የምስረታ ወጪን በስህተት የኪሳራ ማሳወቂያ ላይ በመሙላት የተፈጠረውን ስህተት ማረሚያ የሚሆን የ2001 ዓ.ም የሐብትና ዔዲ መግለጫ ላይ ማስተካከያ አቅርቤያለው በሚለው ላይ የሂሳብ መግለጫው በድጋሚ ታይተው እንዱቀርቡ ለተከራካሪዎች ታዜ የአሞላል ስህተቱ የማስተካከያ እርምጃ ተጠሪ የወሰደ መሆኑን፣ መቼ የሚለውም የቀረበው ማስተካከያ ላይ ሲታይ በ2001 ዓ.ም የሐብት እና ዔዲ ማሳወቂያ ላይ እንደሆነ ጉባዓው የተገነዖበ መሆኑን ገልጾ የ2000 ዓ.ም ኪሳራን በስህተት ማሳወቁን ከቀረበው ሰነድች እና ተፈፀመ የተባለው ስህተት ማስተካከያ ማቅረቡም በግራ ቀኙ የተረጋገጠ፤ በ2000 ዓ.ም ኪሳራ ደርሷል ተብል የተያዖው በስህተት እንደሆነ በጉባዓው የተረጋገጠ በመሆኑ ኪሳራው የደረሰው በ2001 እና በ2002 ዓ.ም በመሆኑ በዘሁ አግባብ የግብር ኃላፉነት ተስተካክል እንዱሰላ ጉባዓው በማለት ወስኗል።
አመልካች በዘህ ፍርድ ቅር በመሰኘት ያቀረበውን ይግባኝ የተመለከተው የፋደራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን አስቀርቦ ከሰማና ከመረመረ በኋላ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዓውን ውሳኔ ሲያፀናው የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም በይግባኝ ቀርቦ ተጠሪን መጥራት ሳያስፈልገው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ይግባኙን ዖግቷል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዖትም የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዓ በ2000 ዓ.ም ኪሳራ በስህተት ለአመልካች ያሳወቀ ስለመሆኑ ከቀረቡት ሰነድች ጉባዓው የተረዲ መሆኑን የገለፀ ቢሆንም በአንድ የግብር ዖመን የቀረበ ሂሳብ መዛገብ ስህተት ካለበት ማስተካከያ መቅረብ ያለበት በቀጣዩ የግብር ዖመን ሆኖ ተቀባይነት የሚያገኘውም ግብር የሚከፈልበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሲያጸድቀው እና ማስተካከያ ሲሰጥበት ነው ተጠሪ ይህንን አላስረዲም፣ ማስተካከያውም መቅረብ ያለበት በ2001 ማሳወቅ የነበረበት በመሆኑ አያገለግልም፤ የቀረቡትን ማስረጃዎች በሚገባ አልተመዖኑም፤ በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤትም በተከራካሪዎች ወገኖች ያልተነሳን የንግድ ፈቃድ መኖርና ማረጋገጥ ጉዲይ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፤
በ2000 ኪሳራ ተደርጏ የቀረበው የሂሳብ መግለጫ የእርጅና ቅናሽ ተብል ለአመልካች ያሳወቀ ስለመሆኑ የፍሬ ነገር ክርክሩን በሚያጣራው አካል የተረጋገጠ ነው በማለት ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም የምስራቅ ቅርንጫፍ የግብር አወሳሰን አሰባሰብ እና ክትትል የሥራ ሂደት የሂሳብ መዛገቡ ላይ ምንም ማስተካከያ እንዲልቀረበ አረጋግጧል፣ ስለሆነም ለጉባዓው ተጣርቷል የተባለበት ስህተት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ከግብር አዋጁ 286/94 አንቀጽ 28/1/ አንጻር ለመመርመር ተጠሪ ቀርቦ መልስ እንዱሰጥ በታዖዖው መሰረት በሰጠው መልሱ በ2000 ዓ.ም ድርጅቱ ገና የንግድ ሥራውን ለመጀመር ቅድመ ዛግጅት ሂደት ላይ የቆየበት ጊዚ በመሆኑ በሐብትና ዔዲ ማሳያ ላይ ኪሳራ በመገለጹ እና በተግባር ኪሳራ ሳይደርስ አመልካች የወሰደ ቢሆንም በ2001 የሀብትና ዔዲ መግለጫ ላይ ተስተካክል እንዱቀርብ ተደርጓል፣ ይህ በጉባዓውም ተረጋግጧል ተወስኗል፤ በሂሳብ አያያዛ ረገድ የተፈፀሙ ስህተቶች ደግሞ የፍሬ ነገር ክርክር እንጂ የህግ ጉዲይ ባለመሆኑ በአዋጅ 286/94 አንቀጽ 112/1/ እና በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 320/1/ መሰረት ይግባኙ የሚፈቀድ አይደለም። ተጠሪ ስህተቱን በቀጣዩ የግብር ዖመን በ2001 አሳውቀናል። ስለሆነም በአዋጁ አንቀጽ 28 መሰረት እንድንስተናገድ የሶስት የግብር ዖመን ኪሳራ አልተጠየቀም ፤የክርክሩም ጭብጥ አይደለም፤ ጉባዓው በስህተት የቀረበውም አጣርቶ በሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች እና ሰነድች ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑ የተሰጠ ውሳኔ ነው ፤ይግባኝ ሰሚው ፋ/ከ/ፍ/ቤት ይህንኑ ነው ያፀናው ስለሆነም ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱም በጽሁፍና በቃል በነበረው ክርክር ድርጅቱ ኪሳራ ሉደርስበት የሚችለውን የንግድ ሥራ ቁመና የነበረውን በማረጋገጥ የተሰጠ እንጂ አንደ አዱስ ጭብጥ ተይዜ የተወሰነ አይደለም፣ ተጠሪ በ2000 ዓ.ም የተፈጠረውን ስህተት እንደተረዲ በ2001 የሂሳብ መግለጫ ላይ ማስተካከያ አሳውቀናል ማስረጃውም ለሥር ፍ/ቤት የቀረበ እንጂ በ2002 የቀረበ አይደለም ማስተካከያው ዖገየ በሚል ምክንያት የግብር ኃላፉነት መጣል ተቀባይነት ያለው አይደለም፤ የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ የፍሬ ነገርን የማጣራት ሥልጣን የጉባዓው ነው በማለት የሰጠው እንጂ የከፍተኛው ፍ/ቤት ሥልጣን የለውም አላለም። ስለሆነም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ሉጸና ይገባል ብሎል። አመልካችም አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው ሲቀርብ ከተያዖው ጭብጥ አንጻር አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምረነዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዖብ የሚቻለው ተጠሪ በኤላክትሮኒክሰ ነክ አታሚነት ዖርፍ ሐምል 16 ቀን 2000 ዓ.ም ፈቃድ የወሰደ መሆኑንና በዘሁ ዖመን የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ያልጀመረበት ቢሆንም የ2000 በጀት ዓመት የሀብትና ዔዲ መግለጫ ሲዖጋጅ የካፕታል ዔቃዎች እና የእርጅና ቅናሽ ተቀናናሽ መሞላት ካለበት ፍርም ኪሳራ ማሳወቂያ ላይ የተላለፈና ስህተት በ2001 የድርጅቱ ሂሳብ መግለጫ ማሳወቁን ይህም በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዓውም መረጋገጡን በተጨማሪም በሰነድች እና በግራ ቀኙ መረጋገጡን ስለሆነም የ2001 የደረሰው ኪሳራ ታስቦ ወደ 2002 የግብር ዖመን ሉሸጋገር የሚገባ በመሆኑ ይኸው ተሰልቶ ግብሩ እንዱወሰን የሚጠይቅ መሆኑን ነው።
በመሰረታዊነት በንግድ የግብር ዖመን የደረሰ ኪሳራ ሉሸጋገር የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 28/1/ እና /3/ እንደተመለከተው ከሚቀጥለት ሶስት የግብረ ዖመናት ውስጥ የሚገኝ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ላይ መጀመሪያ ያጋጠመው ኪሳራ በኋላ ካጋጠመው አስቀድሞ በማካካስ ሉሸጋገር የሚችል እና ይህም በማናቸውም ሁኔታ ከሁለት ሶስት ዓመታት ከሚቆጠሩ ስድስት ዓመታት በላይ ሉሸጋገርና ሉቀናነስ እንደማይችል እና በደንብ ቁጥር 78/1994 እንደተሻሻለው አንቀጽ 12 መሰረት የግብር ከፊዩ ኪሳራ ሉሸጋገር የሚችለው በግብር ባለሥልጠኑ ኦዱት ተደርጏ ተቀባይነት ሲያገኝ ወይም በውጭ ኦዱተር የተመረመረ የሂሳብ መግለጫ ሲቀርብ ነው።
በያዛነው ጉዲይ ተጠሪ የሂሳብ ሪፕርት በ2000፣ በ2001 እና 2002 የግብር ዖመን የሐብትና ዔዲውን ሲያሳውቅ የ2000 ዓ.ም የሐብትና ዔዲ መግለጫው ሲዖጋጅ ድርጅቱ ሐምል 16/2000 ዓ.ም የንግድ ፈቃደን የወሰደ በመሆኑ የካፑታል ዔቃዎች እና የእርጅና ቅናሽ ተቀናናሽ መሙላት ሲገባው የኪሳራ ማሳወቂያ ፍርም መሙላትና ማስተላለፈን ይህንኑ ስህተት በ2001 ሂሳብ ላይ ያሳዩ መሆኑን፤
የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዓ ማስረጃዎችን በመመርመር መገንዖቡን፣ በተጨማሪም በተከራካሪ ወገኖች የተረጋገጠ በመሆኑ በ2000 ኪሳራ ደርሳል ተብል የወሰደው ስህተት መሆኑን ማረጋገጡን ጉባዓው ፍሬ ነገሩንና ማስረጃዎችን በሚመዛን ጊዚ አረጋግጧል። በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 112/1/ መሰረት ደግሞ በጉባዓው በተሰጠ ውሳኔ ላይ በህግ ረገድ ስህተት ነው በማለት የሚቀርበው ብቻ ይግባኙ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ቀርቦ የሚታይ በመሆኑና ይኸው ፍሬ ነገር እና ማስረጃ በመመዖን የተደረሰበት ድምዲሜ በፋደራል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የፀና በመሆኑ ይህ ችልትም እንዲለ በመቀበል በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት የተባለውን ብቻ መርምረናል።
በዘህ መሰረት ተጠሪ ኪሳራውን ያሳወቀው በ2001 ስለሚሆን ይኸው በ2001 በጀት ዓመት በተጠሪ የደረሰው ኪሳራ በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 28/1/ እና /3/ በሚቀጥለት ሶስት የግብር ዖመናት ውስጥ በሚገኝ ግብር በሚከፈልበት ገቢ ላይ ያጋጠመው ኪሳራ በኋላ ካጋጠመው አስቀድሞ በሚካካስ የሚሸጋገር በመሆኑ በአመልካች አዱት ተደርጏ ተቀባይነት ካገኘ ወይም ተጠሪ በውጭ ኦዱተር የሂሳብ መግለጫው ያቀረበ ከሆነ ኪሳራው ሉሸጋገርለት የሚገባ ነው።
በአጠቃላይ ተጠሪ በ2000 በጀት ዓመት ኪሳራ በስህተት ያሳወቀ ስለመሆኑና በ2000 ደርሷል የተባለው ኪሳራ በ2001 ዓ.ም ያሳወቀው መሆኑን በግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባዓ በፍሬ ነገር እና ማስረጃ ምዖና ወቅት የተረገገጠ በመሆኑ ኪሳራው በሚቀጥለው ሁለት ሶስት ዓመት በማሸጋገር የንግድ ትርፍ ግብሩ ተሰልቶ እንዱወሰን በማለት በስር ፍቤቶች የሰጡት ውሳኔ አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 28/1/ እና /3/ ፣ 112 እና ደንብ ቁጥር 78/1994 እንደተሻሻለው አንቀጽ 12 የተመለከተውን መሰረት ያደረገ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስሀተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም። በዘህ መሰረት የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍደራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዓ በመ/ቁ ከሱ-1019 ነሐሴ 17 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠውን እና በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 04/07/2010 እንዱሁም በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 24/08/2010 ዓ.ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
አመልካችና ተጠሪ በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.