No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- ወ/ሮ ከበደች ዖሚካኤል ተጠሪ፡- የአራዲ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፊዮች ቅ/ጽ/ቤት መዛገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች ጥር 21 ቀን 2010 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ታሕሳስ 19 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው።
ጉዲዩ ግብርን የሚመለከት ሲሆን የአሁን አመልካች ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በዘህ የሰበር አቤቱታ የተያዖውን ጉዲይ በተመለከተ ያቀረቡት አቤቱታ ይዖት በአጭሩ በአራዲ ክፍለ ከተማ በመኪና ጌጣጌጥ ንግድ ስራ የተሰማሩ መሆኑን፤ ከተጠሪው ሚያዛያ 26 ቀን 2008 ዓ.ም ተወስኖ በደረሳቸው የኦዱት ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያቀረቡ ቢሆንም ኮሚቴው ቅሬታቸውን ሳይመረምር ውሳኔውን ያጸናው መሆኑን፤ በድርጅታቸው ውስጥ በአደራ ተቀምጠው በተገኙ የቀድሞ ባለቤታቸው የግል ማስታወሻዎች ላይ በመንተራስ ቀደም ሲል ከ2003 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ያሳወቁትን ዓመታዊ ሽያጭ ገቢ በመቀየር ፈጽሞ ባልሰሩት እና ባላገኙት ገቢ ብር 1,698,297.96 ግብር እና ታክስ ወለድ እና መቀጫ እንዱከፍለ የተጠየቁ መሆኑን እና የራሳቸው ባልሆነ የግኝት ምንጭ በመንተራስ ተገቢውን የመረጃ ማጣራት ስራ ሳይሰራ የተወሰነባቸው መሆኑን፤ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳሽ ቡድን ከድርጅቱ የላላ ግለሰብ ማስታወሻዎች ሲወስድ የአመልካች አለመሆኑን ያስረደ ቢሆንም በድጋሚ ተጠርተው በድርጅቱ በተገኙት ሰነድች ላይ የድርጅቱን ማህተም እንዱያሳርፈ የተገደደ መሆኑን በመግለጽ ሰነደን መሰረት በማድረግ የተሰጠው የግብር ውሳኔ እንዱሰረዛላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪ በሰጠው መልስ አመልካች እና ላልች በአካባቢው በተመሳሳይ ስራ ላይ የተሰማሩ ግብር ከፊዮች አየር በአየር ግብይት እንደሚያከናውኑ እና ምንጩ ያልታወቀ ሀብት እንደሚያንቀሳቅሱ በተደረገው ጥናት መሰረት በግብር ከፊይዋ ድርጅት በአካል በመገኘት ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻያገኛቸውን ሰነድች ለጉዲዩ አግባብነት ኦዱት በማድረግ በደረሰበት ውጤት መሰረት እና በቀን ገቢ ግምት መሰረት ለዖጉት የሀገር ውስጥ ችርቻሮ ንግዲቸው ያላሳወቁት ገቢ መኖሩ ተደርሶበት ከ2003 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ላለት የግብር ዖመናት ያቀረቧቸው የሂሳብ መዛገቦችን አስተካክል ተጨማሪ ግብር የወሰነ መሆኑን፤ የግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት በአመልካች ድርጅት በአካል በመገኘት ንግድ ባካሄደባቸው ወቅት ያዖጋጇቸው ማስታወሻ ደብተሮች ያገኘ መሆኑን፤ አመልካች ሰነድቹ የባለቤታቸው ለመሆኑ ምንም ዓይነት ማስረጃ ያላቀረቡ መሆኑን፤ በተቃራኒው ደብተሮቹ የተገኙት በድርጅታቸው ውስጥ ከመሆኑም በላይ በውስጣቸው የያዘት መረጃ አመልካች ስለሚሸጡት የመኪና ጌጣጌጥ ዔቃዎች ዓይነት እና ዛርዛር ዋጋ ዔቃዎቹ ለማን እንደተሸጡ በቅድሚያስለተፈጸሙ ክፍያዎች እና ስለቀሪ ክፍያዎች የሚሳዩ መረጃዎች መሆናቸውን፤ በሚስጥር ከተደረገው የብርበራ ቀን በኋላ አመልካችን ጨምሮ በተመሳሳይ ንግድ ላይ የተሰማሩ 15 ግብር ከፊዮች አየር ባየር ንግድ እንደሚያከናውኑ እና ምንጩ ያልታወቀ ሐብት እንደሚያንቀሳቅሱ በጥናት የተደረሰበት መሆኑን እና ማስታወሻዎቹ ለአመልካች ተሰጥተው የራሳቸው የሆኑትን አራት ደብተሮች የለዩ እና ማሕተም ያሳረፈበት መሆኑን በመግለጽ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ አመልካችዋ ገቢ ደብቀዋል በማለት ግብር እና ታክስን ለመወሰን የተጠቀመው እና መነሻ ያደረገው የአመልካች ናቸው የተባለትን አራት ማስታወሻ ደብተሮች የአመልካች መሆኑን በመጥቀስ ነው፤
በግብር አወሳሰን ስርዓት ውስጥ የታክስ ስወራን ለመከላከል እንደመረጃ የሚወስድበት አግባብ ግብር ከፊዮች በየእለቱ የሚያከናውኑትን የዔለት ከዔለት ሽያጭ በግል ማስታወሻም ሆነ በላልች አማራጭ ሂሳባቸውን የሚከታተለበት እና የሚያውቁበት እንዱሁም ላልች የግል ጉዲዮችንም የሚያዛበት ሁኔታ ላሆን እንደሚችል ታሳቢ ላደረግ የሚገባ ከመሆን ባለፈ የተደበቀ ገቢ መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ የመሆን ብቃት ሉኖረው እና ፍትሐዊ የአወሳሰን ዖዳ መሆኑን በአግባቡ ማረጋገጥን የሚጠይቅ ነው፤
በግል ማስታወሻ ደብተር ከተጠቀሰው ገንዖብ መጠን ውስጥ በሀሰተኛ ደረሰኝ ግብይት የተፈጸመበት ግኝት ወይም ያለደረሰኝ የደቤ ሽያጭ ወይም የእጅ በእጅ ሽያጭ የተሸጠ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል የሚያሳይ ውጤት በላለበት የግል ማስታወሻ ላይ የተጻፈውን የተለያየ ይዖት ያላቸውን ሁኔታዎች ብቻ በመውሰድ ግብር እና ታክስ እንዱወሰን መደረጉ አመልካች በየዓመቱ ካሳዩት እና ካሳወቁት የገቢ ዔድገት አንጻር የሚጣጣም እና ፍትሐዊ ሆኖ አልተገኘም፤ አመልካች በደረሰኝ ግብይት አለማከናወናቸውን የሚያሳይ ተጨባጭ ግኝት ስለመኖሩም አብሮ ላታይ ይገባል፤ የግል ማስታወሻ መያዛ የተለመደ የግል ጉዲይ ከመሆኑ አንጻር በግብር ከፊዮቸ ዖንድ የእጅ ማስታወሻ ከተገኘ ግብር ይጣልብኛል የሚል ስጋት ወደ መፍጠር የሚያመዛን ከመሆን በዖለለ በትክክለኛ ግኝት ላይ የተመሰረተ ሕጋዊ ውሳኔ ለመስጠት የሚያረጋግጥ ማስታወሻ አይደለም በማለት ይህንኑ መሰረት ተደርጎ የተሰጠውን የግብር ውሳኔ ሽሮታል።
የአሁን ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለአዱአበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ የግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል።
ተጠሪ በመቀጠል ለአዱስአበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። አቤቱታው የቀረበለት ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት የኢንተሉጀንስ ዲይሬክቶሬት በአካባቢው ተመሣሣይ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዳዎችን የንግድ ድርጅት ላይ ባደረገው ድንገተኛ ብርበራ ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን የግል ሰነድች ከአመልካች የንግድ ድርጅት ስለመገኘታቸው እና እነዘህም ሰነድች የአመልካች ስለመሆናቸው የግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ ተቀብል እነዘህ ሰነድች የግል ሰነድች በመሆናቸው ተጠሪ በእነዘህ የግል ሰነድቸ ብቻ ገቢን ደብቀዋል ለማለት የማይቻል እና የተጠሪን ገቢ በየዓመቱ የ26% ዔድገት ያሳየ በመሆኑ በእጅ ጽሐፍ በግል ማስታወሻ ደብተር ላይ የተጸፈን የቁጥር ጽሐፍ ብቻ እንደገቢ በመውሰድ ተጨማሪ ግብር መወሰኑ አግባብ አይደለም በማለት ነው፤ ይሁን እንጂ የተጠሪ ጽ/ቤት በእነዘህ የተጠሪ የግል ማስታወሻዎች ላይ ተመስርቶ ተጨማሪ ግብሩን የወሰነው በጥናት ላይ ተመስርቶ እና እነዘህ ሰነድች ተጠሪ ከሚነግደበት ንግድ ጋር በቀጥታ የተገናኘ እና በሑሳብ አዋቂ ተረጋግጦ እና ማስረጃ ቀርቦ በመሆኑ የግብር ይግባኘ ሰሚው ጉባኤ የሰጠው ውሳኔ የገቢ ግብር አዋጅን አንቀጽ 38/2/ሀ እና 66/5 እንዱሁም የፍ/ብ/ህ/ቁ 1677/1፤2017 እና 2018 ያላገናዖብ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ነው በማለት የግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ እና የስር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የተጠሪ ጽ/ቤት በቁጥር 29-4-1/2685/08 በቀን 26/08/08 ዓ.ም ለአመልካች ወስኖ የሰጣቸው ተጨማሪ የንግድ ትርፍ ግብር ፍሬግብር ወለድ እና መቀጫን ጨምሮ እና የተጨማሪ እሴት ታክሱን ፍሬግብሩን ወለድ እና መቀጫውን ጨምሮ የተሰጣቸውን የግብር ውሳኔ ማስታወቂያ በማጽናት ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- የአዱስአበባ ከተማ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የተፈጸመን የሕግ ስሕተት ማረም እንጂ ማስረጃን የመመዖን ስልጣን የለውም፤ በብርበራ የተገኙት ሰነድች የአመልካች አለመሆናቸውን ለጉባኤው ማስረጃ አቅርቤአለሁ፤ ጉባኤውም ደብተሮቹ የአመልካች ናቸው አላለም፤ ደብተሮቹ የአመልካች ናቸው ባልተባለበት ሁኔታ የአመልካች እንደሆኑ ተደርጎ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም፤ አመልካች ያላሳወቅኩት ወይም የደበቅኩት ገቢ የለም፤
የሑሳብ መዛገቤ ተቀባይነት አግኝቶ ግብር እና ታክሱ ስለመወሰኑ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አልካደም፤
ከ2003 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ባለው የግብር ዖመን ዓመታዊ ገቢዬ እየጨመረ የሄደበት ሁኔታ እንጂ አመልካች የቀነስኩት ገቢ እንዲለ በተጨባጭ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ የአዱስአበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት ሰነደ የአመልካች መሆኑ ተረጋግጧል በማለት የግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ እና የስር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሰጡትን ውሳኔ በመሻር የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ገቢያቸውን አሳውቀው ሳለ ከድርጅታቸው ተገኘ የተባለውን የግል ማስታወሻ ከሚደረገው ግብይት ግንኙነት አለው ተብል ግብር እንዱከፍለ የመደረጉን አግባብነት ከግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 38 እና 66/5 ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ ደብተሮቹ የአመልካች መሆናቸውን ጉባኤው ባረጋገጠበት ሁኔታ የንግድ እንቅስቃሴአቸውን በሚያሳዩት በእነዘሁ ደብተሮች ላይ ተመርኩዖን በኦዱት የወሰነው ተጨማሪ ግብር በሕጉ አግባብ በመሆኑ እና ተጠሪ አጥብቆ የሚከራከርበት የግብር ታክስ አሰራር ስርዓት መከበር ጉዲይ በመሆኑ የአዱስአበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኘ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም የግራቀኙን ክርክር ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች እና በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባል ተብል ከተያዖው ነጥብ ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
ተጠሪው መስሪያ ቤት ከ2003 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ላለት የግብር ዖመናት አመልካች ያቀረቧቸው የሂሳብ መዛገቦችን መርምሮ እና አስተካክል ተጨማሪ ግብር ሉወስን የቻለው አመልካች እና ላልች በአካባቢው በተመሳሳይ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ግብር ከፊዮች አየር በአየር ግብይት እንደሚያከናውኑ በተደረገው ጥናት በግብር ከፊይዋ ድርጅት በአካል በመገኘት ባደረገው ፍተሻ ንግድ ባካሄደባቸው ወቅት ያዖጋጇቸው ማስታወሻ ደብተሮች አግኝቻለሁ፤ አመልካች ሰነድቹን ለይተው ማሕተም አሳርፈውበታል፤ ሰነድቹ አመልካች ስለሚሸጡት የመኪና ጌጣጌጥ ዔቃዎች ዓይነት እና ዛርዛር ዋጋ ዔቃዎቹ ለማን እንደተሸጡ በቅድሚያ ስለተፈጸመ ክፍያዎች እና ስለቀሪ ክፍያዎች የሚሳዩ መረጃዎች ናቸው በሚል መሆኑን፤ አመልካች በበኩላቸውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተጨማሪ ያሳወቃውን የግብር ውሳኔ ልከፍል አይገባም በማለት የሚከራከሩት በብርበራ የተገኙት ሰነድች የአመልካች አይደለም፤ አመልካች የደበቅኩትም ሆኖ ያላሳወቅቱም ገቢ የለም በሚል መሆኑን፤ የግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባኤው አመልካች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተጨማሪ እንዱከፍለ ያሳወቃቸውን የግብር ውሳኔ ሉከፍለ አይገባም ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረሰው ሰነደ የተደበቀ ገቢ መኖሩን የሚያሳይ ሰነድ የመሆን ብቃት የለውም፤ በግል ማስታወሻ ደብተር ከተጠቀሰው ገንዖብ መጠን ውስጥ በሀሰተኛ ደረሰኝ ግብይት የተፈጸመበት ግኝት ወይም ያለደረሰኝ የደቤ ሽያጭ ወይም የእጅ በእጅ ሽያጭ የተሸጠ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል የሚያሳይ ውጤት በላለበት የግል ማስታወሻ ላይ የተጻፈውን የተለያየ ይዖት ያላቸውን ሁኔታዎች ብቻ በመውሰድ ግብር እና ታክስ እንዱወሰን መደረጉ አመልካች በየዓመቱ ካሳዩት እና ካሳወቁት የገቢ ዔድገት አንጻር የሚጣጣም እና ፍትሐዊ ሆኖ አልተገኘም በሚል መሆኑን፤ ጉዲዩን በሰበር የተመለከተው የስር ፍ/ቤትም ሰነድቹ የአመልካች የግል ሰነድች መሆናቸው ጉባኤው ተቀብልታል፤ የተጠሪ ጽ/ቤት በእነዘህ የተጠሪ የግል ማስታወሻዎች ላይ ተመስርቶ ተጨማሪ ግብሩን የወሰነው በጥናት ላይ ተመስርቶ እና እነዘህ ሰነድች ተጠሪ ከሚነግደበት ንግድ ጋር በቀጥታ የተገናኘ እና በሑሳብ አዋቂ ተረጋግጦ እና ማስረጃ ቀርቦለት በመሆኑ አመልካች የተጠየቁትን ተጨማሪ ግብር ሉከፍለ ይገባል ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረሰ መሆኑን ከክርክሩ ሑደት መገንዖብ ችለናል።
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 38/2 ድንጋጌ እንደሚያመለክተው በማንኛውም ላላ ሕግ ውስጥ ተቃራኒ የሆኑ ድንጋጌዎች ቢኖሩም የግብር አስገቢው ባለስልጣን በማንኛውም ጊዚ በግብር ከፊይ የቀረቡ ማንኛውንም መግለጫዎች ሰነድች እና የሂሳብ መዛገቦች ለማረጋገጥ ሕጋዊ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቆጣጣሪዎችን ወደ ግብር ከፊዩ የንግድ ወይም የሙያ ስራ ቦታ በመላክ ገቢ እና ወጪን የሚያሳዩ ሰነድችን፤ ለንግድ የተከማቹ ዔቃዎችን፤ ላልች ዔቃዎችን፤ ወይም የሑሳብ መዙግብትን እና ሰነድችን ለማመሳከር እና ለመመርመር እንደሚችል ይደነግጋል። የዘሁ አዋጅ አንቀጽ 66/5 በገቢ ማስታወቂያው ላይ የተመለከተው እና በዖመኑ መከፈል ያለበት ግብር፤ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተወሰነው ግብር ሆኖ ይቆጠራል፤ ሆኖም የግብር አስገቢው ባለስልጣን ስህተት ወይም ያልተካተተ ገቢ ያለ መሆኑን ያረጋገጠ እንደሆነ ውሳኔውን በዘያው መጠን በማሻሻል የግብር ውሳኔ ማስታወቂያ ይሰጣል በማለት ይደነግጋል።
በያዛነውም ጉዲይ አመልካች ከ2003 እስከ 2007 ዓ.ም ያቀረቡትን የሂሳብ ሰነድች በመመርመር ከአመልካች ግብይት ጋር በማገናዖብ ያላሳወቁት ገቢ አለ በሚል ግምት በአመልካች ድርጅት በመገኘት ንግድ ባካሄደበት ወቅት ያዖጋጃቸውን ማስታወሻዎች በንግድ ድርጅቱ ውስጥ ማግኘታቸውን ይኸው አመልካች ስለሚሸጡት የመኪና ጌጣጌጥ ዔቃዎች፤ ለማን እንዳት እንደተሸጠና ክፍያን የተመለከተ መሆኑን እና የተገኙት ማስታወሻዎችም ከአመልካች ስለመሆኑ በድርጅቱ እንዱረጋገጥ ካደረጉ በኋላ ተጨማሪ ግብር የተወሰነ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ በአዋጅ 286/94 አንቀጽ 38 እና 66/1/ የተመለከተ ነው።በዘህም መሰረት ተጠሪ ይህንኑ በአዋጁ በተመለከተው መሰረት በማድረግ አመልካች ገቢውን በየጊዚው እያሳወቀ ግብሩን እየከፈለ መሆኑ ብቻ በቂ አይደለም ብል በማመመኑና እነዘህን ሰነድች እና የሂሳብ መዛገብ በማናቸውም ጊዚ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚችል በመሆኑ በአመልካች የተገኙትን የግብይት ማስታወቀሻዎች በተጠሪ ባለሙያዎች ተመርምረው ተጨማሪ ግብር መወሰኑ የገቢ ግብር አዋጁን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር መሰረታዊ የህግ ስሀተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም ። በዘህ መሰረት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኘ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ታሕሳስ 19 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
አመልካችና ተጠሪ በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር ያወጡትን ወጪ የየራሣቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.