የአንድ ሕንጻ ባለሀብት ወይም ባለይዜታ ሕንጻው ሉያደርስ ይችላል ተብል ያልታሰበ ድንገተኛ ነገር ቢያደርስ ሕንጻው ለሚያደርሰው ጉዲት ከውል ወጪ ኃላፉነት ያለበት ሲሆን ጉዲት የደረሰበት ባለንብረትም የኢንሹራንስ ውል ያለው ከሆነ ኢንሹራንስ ድርጅቱ ለደረሰው ጉዲት ተገቢውን ከፍያ ከከፈለ በኋላ ጉዲት በደረሰበት ሰው ተተክቶ የህንፃውን ባለሀብት ለመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2088 ፣2077፣ የንግድ ህግ 683
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 12/9/2011 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡-
ተጠሪ፡-
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ ሰበር መዛገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የቀረበው አመልካች ሐምል 10 ቀን 2010 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሚያዛያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዙዛ እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 8 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው። ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዖረዛርና በሰበር ሰሚው ችልት በኩል ላታይልኝ ይገባል የሚለውን ዲኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ አመልካች ክስ ያቀረበው ከተጠሪ ህንጻ ላይ የወደቀ ፍራሽ የደንበኛዬ መኪና ላይ ወድቆ በመኪናው ላይ ጉዲት አድርሷል በሚል ሲሆን የውል ወይም ከውል ወጪ የሚል ነገር ሉነሳ አይችልም። በውል ምክንያት ነው ክስ የሚቀርበው ከተባለ እንኳ ወደ ውል ችልት ወይም መብት ይጠበቅልኛል እንጂ የስር ፍ/ቤቶች በደፈናው ክሴን ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም። የአመልካች ደንበኛ የተከራየው ቤት ለቢሮ የሚሆን ክፍል እንጂ መኪና ማቆሚያ ቦታ አይደለም። መኪና ማቆሚያ ቦታ ማንኛውም የተጠሪ ተጠቃሚ የሆነው ሰው ሁለ የሚጠቀምበት በመሆኑ እንደውል የሚቆጠር ባለመሆኑ ክሴ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ የአሁን አመልካች ባቀረበው ክስ ንብረትነቱ የተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ከሆነው ህንጻ ላይ የህንጻው ፍርስራሽ ወድቆ የከሳሽ ደንበኛ በሆነው መኪና ላይ ወድቆ ጉዲት አድርሶበታል። ከሳሽ ከደንበኛው ጋር ባለው ውል መሰረት .19 ለማስጠገኛ ከፍሎል። ተከሳሽ ሉከፍለኝ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ከ16/6/2007 ዓ/ም ጀምሮ ከወለድ ጋር እንዱከፍለኝ ሲል ጠይቋል። ተከሳሽም የከሳሽ ደንበኛ ጉዲት አድርሷል በተባለው ህንጻ ላይ ተከራይ ያለ በመሆኑ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2088(1) መሰረት ሉጠይቀኝ አይችልም። በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2089 ጥቅም በላለው ግንኙነት ህንጻው ለሚያደርሰው ጉዲት የህንጻው ባለቤት ጥፊት ከላለበት ሃላፉነት የለበትም። ተከሳሽና የከሳሽ ደንበኛ ውል ያለን በመሆኑ እና በተከሳሽ ጥፊት ምክንያት ጉዲት የደረሰ ባለመሆኑ ተከሳሽ ኃላፉነት የለበትም። ካለጨረታ የተደረገ ጥገና ተከሳሽን የሚጎዲ በመሆኑ ውድቅ ይደረግልኝ። ከሳሽ ተተክቶ መጠየቅ የሚችለው ደንበኛው ባለው መብት በመሆኑና ደንበኛው ሉጠይቅ የማይችለውን መዲረግ ስለማይችል ክሱ ውድቅ ይሁንልኝ በሚል መልስ ሰጥተዋል። የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 8 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2088(1) እና (2) እንዱሁም በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2077 መሰረት የከሳሽ ደንበኛ ከተከሳሽ ጋር የቤት ኪራይ ውል የነበራቸው በመሆኑ ከተከራየው ህንጻ ላይ በወደቀው ፍራሽ ምክንያት በደረሰው ጉዲት የሚጠይቀው ባላቸው ውል መሰረት በማድረግ እንጂ ከውል ውጪ ሃላፉነት ህጎች በመጠቀም አይደለም። ከሳሽም ደንበኛው በላለው መብት ሉተካ አይችልም። በመሆኑም ተከሳሽ ከውል ውጪ የሚመነጭ ሃላፉነት የለበትም ሲል ክሱን ውድቅ አድርጎታል። ከሳሽ የአሁን አመልካች ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ በመ/ ሚያዛያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል ይግባኙም ሰርዜታል።
የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል። መዛገቡም ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት ጉዲት የደረሰበት መኪና ባለቤት ለጉዲቱ መንስኤ ከሆነው የህንጻው ባለቤት ጋር የኪራይ ውል ግንኙነት ያለው መሆኑ ከተረጋገጠ በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2088(2) ከውል የመነጨ ክስ የማቅረብ መብት ያለው በመሆኑ የአሁን አመልካች በዘህ መብት በመዲረግ ከግራ ቀኙ የኪራይ ውል ስምምነት አድማስ እና ተፈጻሚነት ካላቸው ህጎች አንጻር ክርክሩ ሉመራ ይገባ ነበር ወይስ አልነበረም? ከዘህ አንጻር አመልካች ደንበኛው ባለው ከውል የመነጨ ግዳታ ክስ የማቅረብ መብት ሉዲረግ ይገባል ወይስ አይገባም ከሚለው ነጥብ አንጻር ለመመርመር ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዲልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ሲል ተከራክሯል። አመልካችም ህዲር 13 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲሆን፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልሱን እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል። እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ደንበኛ የሆነው በአሁን ተጠሪ ህንጻ ላይ ተከራይቶ የነበረ መሆኑ፣ የአሁን አመልካች ደንበኛ መኪና ቆማ ባለችበት ከተጠሪ ህንጻ ላይ የወደቀው የህንጻው ፍርስራሽ ወድቆባት ጉዲት ያደረሰበት መሆኑ አላከራከረም። የስር ፍ/ቤቶች በአሁን አመልካች ደንበኛ እና በተጠሪ መሀከል የቤት ኪራይ ውል ያለ በመሆኑ በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2088(2) ድንጋጌ መሰረት የአመልካች ደንበኛ ተጠሪን ሉጠይቀው የሚችለው በመሀላቸው ባለው የገቡት የውል ግዳታ መሰረት በመሆኑና የአሁን አመልካችም በደንበኛው ተዲርጎ ክስ ማቅረብ የሚችለው ደንበኛው ባለው መብት ልክ በመሆኑ አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበው ከውል ውጪ ኃላፉነት ተቀባይነት የለም በሚል ክሱን ውድቅ አድርገውታል። የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2088(1) ጉዲቱን ካደረሰው አደገኛ ኢንደስትሪ፣ ወይም እንስሳ፣ ወይም ሕንጻ ወይም ላላ ነገር ግንኙነት ያለውና በሕግ በኩልም ለነዘሁም ሃላፉ ከተባለው ሰው ጋራ ተዋውያለሁ የሚለው ሰው አሥጊ የሆኑ ነገሮቸን በመፍጠር ወይም በእንስሳዎች ወይም በሕንጻዎች ወይም በልላ ነገሮች ለሚደርሱ ጉዲቶች የኃላፉነትን ደንቦች በመጥቀስ ከኃላፉነት ለመዲን እንደማይቻል ይደነግጋል። በዘህ ጉዲይ ህንጻን በተመለከተ ከሚደርስ ጉዲት ጋር በተገናኘ ጉዲቱን ያደረሰው ህንጻ ኃላፉ ከሆነው ሰው ጋር የውል ግንኙነት ባለው ሰው ምክንያት ለሚደርሱ ጉዲቶች ይሄው ሰው ከኃላፉነት መዲን እንደማይችል የሚደነግግ ሲሆን በዘህ ጊዚ ጉዲቱን ያደረሰው ሰው ኃላፉነት የሚመራው በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2088(2) በሚደነግገው መሰረት በመሀላቸው ባለው ውል መሰረት እንደሆነ የሚደነግግ ነው። የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2077(2) ድንጋጌም ይህንኑ የሚያስገነዛብ ነው። በመሆኑም የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2088 ድንጋጌ የሚያመለክተው ከህንጻ ባለቤት ወይም ኃላፉ ከሆነው ሰው ጋር ውል ባደረገው ሰው ምክንያት የሚመጣ የጉዲት ሃላፉነት የሚመራው ባደረገው ውል መሰረት መሆኑን እንጂ ስለ ህንጻው ባለቤት ወይም ኃላፉ የሆነው ሰው የሚያወራ አይደለም። በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2077(1) ያንድ ሕንጻ ባለሀብት ወይም ባለይዜታ ሕንጻው ሉያደርስ ይችላል ተብል ያልታሰበ ድንገተኛ ነገር ቢያደርስም፣ ይህ ሕንጻ በሚያደርሰው ጉዲት ኃላፉ እንደሆነ ደንግጎ ይገኛል። በዘህ ጉዲይ የአሁን ተጠሪ ጉዲት ያደረሰው ሕንጻ ባለቤት መሆኑን እና ከህንጻው ላይ የወደቀው ፍርስራሽ በአመልካች ደንበኛ መኪና ላይ ጉዲት ያደረሰ መሆኑን አያስተባብልም። እንዱሁም የጉዲቱን መጠን በተመለከተ አመልካች የጠየቀው የመኪናዋ ማስጠገኛ ዋጋ በጨረታ የተደረገ ጥገና ባለመሆኑ ይጎዲኛል ከማለት ውጪ፣ ጉዲት የደረሰባት መኪና የተጠገነችው ከጨረታ ወጪ ስለመሆኑና ከተጠየቀው የማስጠገኛ ዋጋ አነስተኛ ዋጋ የቀረበ ስለመሆኑም ያቀረበው ክርክርና ማስረጃ የለም። በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2077(1) ድንጋጌ መሰረት የአሁን ተጠሪ ሕንጻው ለሚያደርሰው ጉዲት ከውል ወጪ ኃላፉነት ያለበት ሲሆን የአሁን አመልካችም ከደንበኛው ጋር ካለው የኢንሹራንስ ውልና ከንግድ ህጉ አንቀጽ 683 ድንጋጌ የመነጨ ተተክቶ የአሁን ተጠሪን ለመጠየቅ መብት አለው። ይህ ሆኖ እያለ የስር ፍ/ቤቶች የፍሬ ነገር ክርክሩን ካለመገንዖብ ከህጉ ድንጋጌ ትርጉም ውጪ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሚያዛያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዙዛ እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 8 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአሁን ተጠሪ ከህንጻው ላይ የወደቀው ፍርስራሽ በአሁን አመልካች ደንበኛ መኪና ላይ ላደረሰው ጉዲት ከውል ውጪ ኃላፉነት አለበት። የተጠሪ ህንጻ ላደረሰው ጉዲት የአሁን አመልካች በደንበኛው ተተክቶ የጉዲት ካሳ መጠየቅ ይችላል። የተጠሪ ህንጻ በአመልካች ድንገተኛ መኪና ላይ ላደረሰው ጉዲት ለመኪና ማስጠገኛ የወጣውን ወጪ .19 ተጠሪ ለአሁን አመልካች ይክፈለው። ተጠሪ አመልካች እንዱከፍለው ከጠየቀበትና ሉከፍለው ፍቃደኛ ካልሆነበት ከ16/6/2007 ዓ/ም ጀምሮ ከ9 % ወለድ ጋር ክፍያውን እስኪፈጽም ድረስ ታስቦ እንዱከፍለው ብለናል።
በዘህ መዛገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
የዘህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.