የቤት ኪራይ እንዱከፈል መጠየቅ ካለበት ጊዚ ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ካልተጠየቀ የቤት ኪራይ ክፍያ እንደተከፈለ ይቆጠራል የሚለዉ የሕግ ግምት፣ ሁለት ዓመቱ ሳይደርስ ባለገንዖቡ ገንዖቡ እንዱከፈለዉ ባለዔዲዉ ላይ ክስ አቅርቦ እንደሆነ እዲዉ እንደተከፈለ ይቆጠራል የሚለው የህግ ግምት ቀሪ ስለሚያደርገው ክሱ በሁለት ዓመት ይርጋ የማይታገድ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024(መ)፣2025 (ለ)
No summary available.
ሰኔ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡ …. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር አመልካች፡ …… . ..አፍሪካ ክንፋ መረዲጃ እድር፡- ሺፈታ በለጠ ቀርበዋል።
ተጠሪዎች፡ ………. . .1. አቶ ዮሴፍ ደበበ የቀረበ የለም።
ይህ ክርክር የተጀመረዉ በፍዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣የአሁን አመልካች ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር።ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፍዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.214403 ታህሳስ 9 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን አመልካች )ባቀረበዉ ክስ ተከሳሾች ከ1/6/2007 ዓ.ም እስከ 30/11/2009 ዓ.ም ድረስ ያለዉን ዉዝፍ ኪራይ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ወለድን ጨምሮ ብር 464,887.50 እንዱከፍሎቸዉ ጠይቋል።
በዚህ ክስ ላይ ተከሳሾች ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከሳሽ ያቀረበዉ የኪራይ ይከፈለኝ ጥያቄ በ2 ዓመት ይርጋ የሚታገድ ስለሆነ መዝገቡ እንዱዘጋልን በማለት ተከራክሯል።
ከሳሽ በዚህ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በሰጠዉ ምላሽ ይህ ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2025 (ለ) መሰረት በይርጋ የሚታገድ አይደለም በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ የፍዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተከሳሾች በተነሳዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በሰጠዉ ብይን ከዚህ ቀደም በግራ ቀኛቸዉ መካከል በተደረገዉ ክርክር ተከሳሽ ቤቱን እንዱለቁ እና ኪራይ እንዱከፍለ የተጠየቀ ሲሆን ፍ/ቤቱ እስከ 30/11/2007 ዓ.ም ያለዉን ኪራይ የወሰነ ቢሆንም ከ1/12/2007 ዓ.ም ጀምሮ ላለዉ ጊዜ ዉዝፍ ኪራይ ጠይቋል ለማለት ስለማይቻል፣ ከሳሽ ከ1/6/2007 ዓ.ም እስከ 30/11/2007 ዓ.ም የጠየቀዉን ዉዝፍ የቤት ኪራይ ይከፈለኝ ጥያቄ በ2 አመት ይርጋ የሚታገድ ነዉ በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።
የሥር ከሳሽ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የቀረበዉን ይግባኝ ማመልከቻ በትዕዛዝ ዉድቅ በማድረግ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ለማሻር ነዉ።
የአሁን አመልካች በ25/4/2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ከዚህ ቀደም በዚህ ጉዲይ ከፍዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እስከ የፍዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እስከ 26/10/2009 ዓ.ም ድረስ ስንከራከር ስለነበርን በክርክር ላይ የቆየን በመሆኑ፣ በዚህ ምክንያት በ1/6/2007 ዓ.ም እስከ 30/11/2009 ዓ.ም ያለዉ ጊዜ በተመለከተ የ2 ዓመት ይርጋ የማይመለከተዉ ነዉ። የሥር ፍ/ቤቶች ከዚህ ቀደም የተሰጠዉን ዉሳኔ እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2025(ለ) ያላገናዘበ ስለሆነ ተሽሮ ታርሞ እንዱወሰንልን በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣አመልካች ያቀረበዉ ዉዝፍ የቤት ኪራይ ክፍያ ጥያቄ በ2 ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል ተብል የተሰጠዉ ዉሳኔ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024 እና 2025 አንጻር ፣ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ባዘዘዉ መሰረት መጋቢት 4 ቀን 2011 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት በአጭሩ፡ የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች ያቀረበዉ ዉዝፍ የቤት ኪራይ ይከፈለኝ ጥያቄ በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024 በ2 ዓመት ጊዜ ዉስጥ ያልተከፈለ የቤት ኪራይ እንደተከፈለ የህግ ግምት ይወሰድበታል በሚለዉ ድንጋጌ ሥር የሚወድቅ ስለሆነ የተሰጠዉ ዉሳኔ ምንም ዓይነት የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ የሥር ዉሳኔ እንዱጸናልን ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልን በማለት በዝርዝር ተከራክሯል።
የአሁን አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ይህ ችልት የግራ ቀኛቸውን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ የአሁን አመልካች እና ተጠሪዎች የቤት ኪራይ ክፍያ በተመለከተ ከፍዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጀምሮ እስከ የፍዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ሲከራከሩ ቆይተዉ፣ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በ
ሰኔ 26 ቀን 2009 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማሻሻል ወስኗል።
በዚህ ዉሳኔ ተጠሪዎች ከየካቲት 1 ቀን 2007 ዓ.ም እስከ ሐምል 30/2007 ዓ.ም ድረስ ያልከፈለትን የቤት ኪራይ እና በቀጣይም የዉለ ጊዜ በዉለ መሰረት ለአመልካች እንዱከፍለ ወስኗል። ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ ግራ ቀኛቸዉ ከሥር ፍ/ቤቶች ጀምሮ እስከዚህ ችልት ድረስ እስከ ሰኔ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በቤት ኪራይ ክፍያ ሲከራከሩ እንደነበር የሚያመለክት ነዉ።
ከዚህ በኋላ አመልካች ሐምል 22 ቀን 2009 ዓ.ም በተጻፈ ክስ ተጠሪዎች ከየካቲት 1 ቀን 2007 ዓ.ም እስከ ሐምል 30 ቀን 2009 ዓ.ም ያለዉን ዉዝፍ የቤት ኪራይ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ለማስከፈል ክስ ማቅረቡን ተገነዝበናል። ይህ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ሲሆን በሕጉ አግባብ መርምረናል።
እንደሚታወቀዉ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024 (መ) መሰረት ዕዲዉ እንዱከፈል መጠበቅ ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈል የቀረ ገንዘብ እንደተከፈለ ከሚቆጠሩት ጉዲዮች አንደ የቤቶች ኪራይ ዕዲ እንደሆነ ያመለክታል። የዚህ ድንጋጌ ዓላማ ሲታይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሳይከፈል ሁለት ዓመት ያለፈ እንደሆነ እና ከዚህ አንጻር መቃወሚያ የቀረበ እንደሆነ፣ ይህ የቤት ኪራይ ክፍያ እንደተከፈለ ስለሚቆጠር፣ የዚህ የቤት ኪራይ ክፍያ ይከፈለኝ ጥያቄ ተቀባይነት የሚያጣ ይሆናል ማለት ነዉ። ይህ ደግሞ የይርጋ ጉዲይ ሳይሆን የቤት ኪራይ ክፍያዉ እንደተፈጸመ በሕግ ግምት የሚወሰድበት መሆኑን ነዉ። ነገር ግን በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2025 ሥር የተመለከቱትን ሁኔታዎች የሚያስረዲ ማስረጃ በማቅረብ ይህን የሕግ ግምት ቀሪ ማድረግ እንደሚቻል ተመልክቷል። ከእነዚህ ሁኔታዎች ዉስጥ አንደ በዚህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ (ለ) ሥር የተደነገገዉ ፣በሕግ የተደነገገዉ የጊዜ ዉሳኔ ሳይደርስ ባለገንዘቡ ገንዘቡን እንዱከፍለዉ ባለዕዲዉን ከፍርድ ቤት አስጠርቶ እንደሆነ እዲዉ እንደተከፈለ መቆጠሩ ቀሪ ይሆናል፣ በማለት ይደነግጋል።
ከዚህ አንጻር አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች ከዚህ ቀደም ተጠሪዎች ቤቱን እንዱለቁ እና ዉዝፍ የቤት ኪራይ እንዱከፍለት በፍዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ሲከራከሩ ቆይተዉ ሰኔ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዉሳኔ ያገኘ እና እስከ 30/11/2007 ዓ.ም ድረስ ያለዉ የኪራይ ክፍያ እንዱከፍለ የተወሰነ መሆኑ ሲታይ አመልካች የቤት ኪራይ እንዱከፈለዉ ተጠሪዎችን ከፍ/ቤት አስጠርቶ ሲከራከሩ ቆይቶ በኋላ ዉሳኔ የተሰጠበት መሆኑን የሚያስገነዝብ ነዉ። በመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024 (ለ) መሰረት የቤት ኪራይ እንዱከፈል መጠየቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ያልተጠየቅ የቤት ኪራይ ክፍያ እንደተከፈለ ይቆጠራል የሚለዉ የሕግ ግምት፣ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2025 (ለ) ሥር የተመለከተዉ ሁኔታ መኖሩን የሚያስረዲ ማስረጃ የቀረበ እንደሆነ የቤት ኪራይ ክፍያዉ እንደተከፈለ ይቆጠራል የሚለዉ ግምት ቀሪ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነዉ። ስለዚህ የአሁን አመልካች የቤት ኪራይ ክፍያ እንዱከፈለዉ ያቀረበዉ ክስ በሁለት ዓመት ይርጋ የሚታገድበት የህግ አግባብ የለም።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች ዉዝፍ የቤት ኪራይ እንዱከፈለዉ በተጠሪዎች ላይ የቀረበዉ ክስ በሁለት ዓመት ይርጋ የሚታገድበት የህግ አግባብ በላለበት ክሱ በሁለት ዓመት ይርጋ የሚታገድ ነዉ በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የፍዳራል የመጀመሪያ ደረጃ በመ.ቁ.46706 በ10/7/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ብይን እና የፍዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.214403 ታህሳስ 9 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የፍዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተዘጋዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሐተታዉ በተመለከተዉ አግባብ የአሁን አመልካች ያቀረበዉ ክስ በሁለት ዓመት ይርጋ የሚታገድ ባለመሆኑ፣ በዋናዉ ጉዲይ ላይ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በማጣራት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 (1) መሰረት ተመልሶለታል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.