አንድ ውል ለተፈለገው ዓላማ ሳይውል ከቀረ ለውል መሰረዛ ምክንያት የሚሆን ሲሆን ውለ ከተሰረዖ በኋላ ተዋዋይ ወገኖች ከውል በፉት ወደ ነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ የማድረግ ውጤት የሚያስከትልና ወጋገን ባንክ አ.ማ. እና የኢትዩጵያ የንግድ እና ሚያዛያ 28 ቀን 2011 ዓ.ም በመሰረዘ ምክንያት የደረሰ ጉዲት ካለ ለደረሰ ጉዲት በካሣ መልክ አንደ ለላላው የመክፈል ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ ፍ/ብ/ሕጉ አንቀጽ 1771/2/፣1788፣179ዐ፣1791፣1799፣1815 የዖርፍ ማህበራት ም/ቤት 50. አንድ ውል እንደ ውለ ባለመፈፀሙ ለደረሰ ጉዲት ኪሳራ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት ተዋዋይ ወገን ሉከፍል የሚገባውን የኪሳራ መጠን ለመወሰን በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የውል ዓይነት፣የነበራቸውን ግንኙነት እንዱሁም ቀድሞ የሚታወቁ ሁኔታዎች ሁለ ግምት ውስጥ ሉገቡ የሚገባቸው ስለመሆኑ አንድ የኪራይ ውል እንደ ውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት የደረሰ ኪሳራ የሚቆረጠው በኪራይ ውል ስላት ተመን መሰረት ሲሆን የኪራዩን ገንዖብ ልክ ለመወሰን አግባብነት የሚኖረው ማስረጃ የማዖጋጃ ቤት ባለስልጣናት የሚወሰኑት ታሪፍ በመሆኑ ለተመሳሳይ ቤት የሚታወቅ ታሪፍ ቢኖር በመጠየቅ እንዱሁም ታሪፍ ከላለ የቦታዎቹን ልማድ በመከተል ሉወሰን የሚገባ መይ ሪል ስቴት ዳቨልፔመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አቶ ያየህ ይራድ ፍቅሬ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1771፣1799፣1801፣2950(2)
No summary available.
ሰኔ 28ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር አመልካች፡- መይ ሪል ስቴት ዳቨልፔመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተጠሪ፡- አቶ ያየህ ይራድ ፍቅሬ መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በግራ ቀኙ መካከል በተደረገው የህንፃ ክፍል ሰርቶ የማስረከብ ውል መነሻነት ክስ ቀርቦ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ የአሁን አመልካች አከራካሪውን ቤት ለተጠሪ እንዱያስረክብ እና በውለ መሰረት ቤቱን በጊዚው ባለማስረከቡ በተጠሪ ላይ በኪራይ ማጣት የደረሰውን ኪሳራ እንዱከፍል፤ እንዱሁም የኪራዩ መጠን ተጣርቶ እንዱወሰን በማለት ውሳኔ አሳልፎል።
ኪራይን በተመለከተ ተጠሪ የሚገነባው ቤት በወር ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ይከራይ እንደነበር ጠቅሰው ቤቱን ማስረከብ ከነበረበት የካቲት 2000 ዓ.ም ጀምሮ በዘህ አግባብ ተሰልቶ እንዱከፈላቸው የጠየቁ ሲሆን አመልካች በበኩለ ኪራይ ሉከፍል የማይገባበትን ምክንያት እና የኪራዩ መጠን በማስረጃ የተደገፈ አለመሆኑን በማንሳት ተከራክሯል።
የስር ፍርድ ቤት ክርክር የተነሳበት ቤት ስፊት እና ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው በአካባቢው የሚገኙ ቤቶች በምን ያህል እንደሚከራዩ ተጣርቶ እንዱቀርብ በቅድሚያ ለቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዲ 8 አስተዲደር ፍትህ ጽቤት ትዔዙዛ ሰጥቶ ጽ/ቤቱ በቁጥር ቀ/ክ/ከ/ወ/08/ፍ/ጽ/ቤት 1353/09 በቀን 29/05/2009 ዓ.ም በላከው ምላሽ ከአካባቢው በተገኘው መረጃ ከ2000 ዓ.ም እስከ 2005 ዓ.ም ባለው ጊዚ ባለሁለት መኝታ 83 ካ.ሜ የህንጻ ቤት በአማካይ ከብር 8,000.00 እስከ 10,000.00 እንደሚከራይ እንዱሁም 115 ካ.ሜ ከብር 12,000.00 እስከ 15,000.00 እንደሚከራይ ገልጿል። ፍርድ ቤቱ የቀረበው ማስረጃ አከራካሪውን ጭብጥ በተፈለገው ሁኔታ እና ደረጃ አጣርቶ ለመወሰን የሚያስችል አይደለም በማለት በድጋሚ ተጣርቶ እንዱቀርብ ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ትዔዙዛ ሰጥቶ ባለስልጣኑ በቁጥር ሞዔ/3-20/10/17833 በቀን 14/09/2009 ዓ.ም በፃፈው ምላሽ ስፊቱ 152.2 እና 152.6 የሆኑ ቤቶች በ2007 ዓ.ም ርክክብ ተደርጎ የተከራዩበትን ዋጋ የገለፀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ክርክር የተነሳበት ቤት ስፊት 225 ካ.ሜ በመሆኑ የቀረበው ምላሽ ጉዲዩን ለመወሰን የሚያስችል አይደለም በማለት አልፍታል።
ከዘህ በኋላ ፍርድ ቤቱ የኪራዩን መጠን በተመለከተ ግራ ቀኙ ምስክሮቻቸውን አቅርበው እንዱያስረደ ትዔዙዛ ሰጥቷል። በዘህ መሰረት ተጠሪ በአካባቢው በደላላነት እንደሚሰሩ የገለፁ አንድ ምስክር አቅርበው አሰምተዋል። ምስክሩ በሰጡት ቃል ቤቶቹ ከ2000 እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ከ2,000.00 የአሜሪካ ድላር ጀምሮ እንደሚከራዩ መስክረዋል። አመልካች በበኩለ ያቀረባቸው ሁለት ምስክሮች ከ2000 – 2005 ዓ.ም ድረስ በአካባቢው ቤቶች ተሰርተው ባለመጠናቀቃቸው እንደማይከራዩ መስክረዋል። በመጨረሻ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ፍርድ የአመልካች ምስክሮች የሰጡትን ቃል ውድቅ በማድረግ የተጠሪ ምስክር ከጠቀሱት ዋጋ ላይ መነሻውን 2,000.00 የአሜሪካ ድላር በመያዛ ኪራዩ ሉሰላ ይገባል ብሎል። በዘህ መሰረት በወቅቱ በነበረው የምንዙሬ መጠን አስልቶ ከየካቲት 2000 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2005 ዓ.ም ላለው ጊዚ ብር 1,768,407.60 (አንድ ሚሉዮን ሰባት መቶ ስድሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሰባት ብር ከስድሳ ሳንቲም) ኪሳራ በኪራይ መልክ ከነወለደ አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል በማለት ወስኗል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዝል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዘህ ነው።
ጥር 13/2011 ዓ.ም የቀረበው የሰበር አቤቱታ በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ አመልካች እንደውላቸው ቤቱን በጊዚው ሰርቶ ባለማስረከቡ በተጠሪ ላይ በደረሰው የገንዖብ ጉዲት ሉከፍል የሚገባውን የካሳ መጠን በኪራይ መልክ አስልቶ ለማስከፈል የፋ/ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከመንግስታዊ ተቋማት ስለኪራዩ መጠን የሚገልጽ ማስረጃ ካስቀረበ በኃላ ወደጎን በመተው በአንድ ሰው ምስክርነት ቃል ላይ ብቻ ተንተርሶ የሰጠውን ዲኝነት ከማስረጃው አግባብነት አንፃር ተገቢ መሆን አለመሆኑንና ተያያዥ ጉዲዮችን አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ ሚያዘያ 25/2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ በሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ተብል ቅሬታው ውድቅ እንዱደረግ ተከራክረዋል። አመልካችም ክርክሩን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተጠቀሰው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ከክርክሩ መረዲት እንደሚቻለው የግራ ቀኙ ግንኙነት ውልን መሰረት ያደረገ ነው። እንደውለ ያልተፈፀመለት ወገን እንደውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት ለደረሰበት ጉዲት በጥቅም መቋረጥ መልኩም ሆነ በልላ ሁኔታ ኪሳራ የመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1771 ሥር በመርህ ደረጃ ተደንግጓል። በተያዖው ጉዲይ አመልካች በውለ መሰረት ቤቱን በጊዚው ለተጠሪ ባለማስረከቡ በተጠሪ ላይ በኪራይ ማጣት መልክ የደረሰውን ኪሳራ እንዱክስ ተጠሪ መጠየቃቸውና የሥር ፍርድ ቤትም በዘሁ መሰረት ውሳኔ ላይ መደረሱ የህጉን ይዖትና መንፈስ የተከተለ አይደለም የሚሰኝ ሆኖ አላገኘነውም።
በአንፃሩ የውል ጥሰት ሲኖር ሉከፈል የሚገባውን ኪሳራ አቆራረጥ በተመለከተ በህጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች፤ እንዱሁም ኪሳራው የሚቆረጠው በኪራይ ስላት ተመን ነው ቢባልና ግራቀኙ አስቀድመው የተመኑት ኪራይ ልክ ባይኖር ኪራዩን ለመወሰን አግባብነት የሚኖረው ማስረጃ ምን አይነት ነው የሚለትን በተመለከተ ከህጉ ጋር አያይዜ በመመልከት የሥር ፍርድ ቤቶች ባሳለፈት ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን በመመርመር ውሳኔ ላይ ሉደረስ እንደሚገባ ተገንዛበናል።
በፍ/ብ/ህ/ቁ 1771 ሥር በመርህ ደረጃ የተደነገገው የውል አለመፈፀም ስለሚያስከትለው የጉዲት ኪሳራ የተመለከተው ቢኖርም የሚከፈለው ኪሳራ የሚታሰበው በፍ/ብ/ህ/ቁ 1799 ሥር እንደተደነገገው አእምሮ ያለው ሰው ውለ ባለመፈፀሙ ይደርሳል ብል በሚገመተው አስተያየት ልክ ነው። በዘህ አኳኀን የውለ መሰረቶች ናቸው ተብለው የሚያዘት የውለን አይነት መመልከት ብቻ ሳይሆን የተዋዋዮችን የሙያ፣ ሥራ፣ ከዘህ በፉት የነበራቸውን ግንኙነት፣ ባለዔዲው የሚያውቃቸውን ሁኔታዎች እና ማናቸውንም አጋጣሚ ሁኔታዎች ሁለ በመመልከት ስለመሆኑ ይደነግጋል። ይህም ብቻ ሳይሆን ኪሳራው ባለገንዖቡ በደረሰበት እርግጠኛ ጉዲት ልክ እንዱሆን አድርጎ መወሰን የሚቻል ቢሆንም እንዱህ አይነት ውሳኔ ላሰጥ የሚችለው ግን ባለገንዖቡ ውል ሲያደርግ ጉዲቱን ይበልጥ የሚያከብደበትን ልዩ ልዩ ምክንያቶች ለባለዔዲው አስቀድሞ ያስታወቀ ሲሆን መሆኑን ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1801 ግልጽ ድንጋጌ መገንዖብ ይቻላል።
በተያዖው ጉዲይ የሥር ፍርድ ቤት በውለ የተመለከተውን የማስረከቢያ ጊዚ እና በተጠሪ የተጠየቀውን የኪራይ ኪሳራ ብቻ በመመልከት በተጠሪ ላይ ይደርሳል ያለውን እርግጠኛ ጉዲት ልክ ላይ ውሳኔ ከመስጠቱ በቀር እንደ ህጉ ድንጋጌዎች የውለን አይነት፣ የተዋዋዮችን ሥራና የነበራቸውን ግንኙነት እንዱሁም ከቀረበው የዲኝነት ጥያቄ አንፃር ባለዔዲ የሆነው የአሁን አመልካች የሚያውቃቸውን ሁኔታዎች ሁለ እንዱሁም ጉዲቱን የሚያከብደ ሁኔታዎች አስቀድሞ እንዱያውቅ የተደረገበት ሁኔታ መኖር አለመኖሩን ሁለ በማጣራት ውሳኔ ላይ መደረሱን መዛገቡ አያሳይም። ክርክሩ ከፍሲል በተጠቀሰው የህግ አግባብ ታይቶ እና ጉዲዩ በአግባቡ ተጣርቶ ኪሳራው ካልተወነ ውሳኔው ህጉን መሰረት ያደረገ ነው ልባል አይችልም።
በልላም በኩል ኪሳራው የሚቆረጠው በኪራይ ውል ስላት ተመን መሰረት ነው ቢባልና ግራቀኙ አስቀድመው የተመኑት የገንዖብ ልክ ባይኖር የኪራዩን ገንዖብ ልክ ለመወሰን አግባብነት የሚኖረው ማስረጃ ምን አይነት እንደሆነ በህጉ ተመልክቷል። በፍ/ብ/ህ/ቁ 2950(2) የቤት ኪራይ ልክ በሚያጠራጥር ጊዚ የማዖጋጃ ቤት ባለስልጣናት በወሰኑት ታሪፍ መሰረት ወይም የተወሰነ ታሪፍ ከላለ የቦታዎቹን ልማድ በመከተል ሉወሰን እንደሚገባ ይደነግጋል። ከዘህ አንፃር ሲታይ አመልካች እንደውለ ቤቱን በጊዚው ሰርቶ ባለማስረከቡ በተጠሪ ላይ በደረሰው የገንዖብ ጉዲት ሉከፍል የሚገባውን የካሳ መጠን በኪራይ መልክ አስልቶ ማስከፈል ተገቢ መሆኑ ከታመነበትና የኪራዩ መጠን አከራካሪ በሆነበት የፋ/ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከመንግስታዊ ተቋማት ስለኪራዩ መጠን የሚገልጽ ማስረጃ ካስቀረበ በኃላ ይህን ወደጎን በመተው በደላላነት የተሰማሩ ሰው የሰጡት ምስክርነት ቃል ላይ ተንተርሶ የሰጠው ዲኝነት ከማስረጃው አግባብነት አንፃር ሲታይም ህጉን የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ የአሁን አመልካች እንደውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት በተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት የመካስ ኃላፉነት አለበት በሚል የተሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ቢሆንም ሉከፈል የሚገባውን የኪሣራ መጠን በመወሰን ረገድ ግን በግራቀኙ መካከል የተደረገውን የውል አይነት፣ የነበራቸውን ግንኙነት እንዱሁም የአሁን አመልካች አስቀድሞ የሚያውቃቸውን ሁኔታዎች ሁለ በማጣራት ውሳኔ ላይ አለመደረሱ እንዱሁም ኪሳራው የሚቆረጠው በኪራይ ውል ስላት ተመን መሰረት ነው ቢባልም የኪራዩን ገንዖብ ልክ ለመወሰን አግባብነት የሚኖረው ማስረጃ የማዖጋጃ ቤት ባለስልጣናት የወሰኑት ታሪፍ ስለመሆኑ ወይም የተወሰነ ታሪፍ ከላለ የቦታዎቹን ልማድ በመከተል ሉወሰን እንደሚገባ በህጉ ተመልክቶ እያለ በዘህ አግባብ ጉዲዩ ሳይታይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ ጥቅምት 15/2011 ዓ.ም ያሳለፈው ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአሁን አመልካች እንደውለ ባለመፈፀሙ በተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት ኪሳራ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ተብል አስቀድሞ የተሰጠው ውሳኔ እንደተጠበቀ ነው ብለናል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የተዖጋውን መዛገብ በማንቀሳቀስ ሉከፈል የሚገባውን የኪሣራ መጠን በመወሰን ረገድ በግራቀኙ መካከል የተደረገውን የውል አይነት፣ የነበራቸውን ግንኙነት እንዱሁም የአሁን አመልካች አስቀድሞ የሚያውቃቸው ሁኔታዎች ሁለ ኪሳራውን ለመወሰን ግምት ውስጥ ሉገቡ የሚገባቸው ጉዲዮች መሆናቸውን ተገንዛቦ ይህን መነሻ በማድረግ የህጉን ይዖትና መንፈስ ተከትል ውሳኔ እንዱሰጥ፤ ኪሳራው የሚቆረጠው በኪራይ ውል ስላት ተመን መሰረት ነው ስለተባለም የኪራዩን ገንዖብ ልክ ለመወሰን አግባብነት የሚኖረው ማስረጃ የማዖጋጃ ቤት ባለስልጣናት የወሰኑት ታሪፍ በመሆኑ ለተመሳሳይ ቤት የሚታወቅ ታሪፍ ቢኖር በመጠየቅ እንዱሁም ታሪፍ ከላለ የቦታዎቹን ልማድ በመከተል በአግባቡ አጣርቶ እንዱወስን ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 343(1) መሰረት መልሰናል። ይፃፍ።
በዘህ ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኙ ያደረጉት ክርክር ያስከተለውን ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.