በአንድ የአፈፃፀም መዛገብ የፍርድ ባለዔዲ የነበሩ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አክሲዮኖች በፍ/ቤት በተሰጠ ዔግድ ትዔዙዛ ለ3ኛ ወገን እንዲይተላለፈ ከመታገዲቸው በፉት አክሲዮኖቹ ለላላ ወገን በሽያጭ ስለመተላለፊቸዉ ፤በንግድ ሚኒስቴር የአክሲዮን መዛገብ ላይ ስለመመዛገባቸው እነ አብደሰላም ሰይደ አብዳ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አክሲዮኖች በሀራጅ ተሸጠዉ ለፍርድ ባለመብት እንዱከፈል የተሰጠ የአፈጻጸም ትዔዙዛ እንዱነሳ የሚቀርብ መቃወሚያ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ የንግድ ሕግ ቁጥር 522፣523(3)
No summary available.
መስከረም 25 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አባይ ባንክ አ.ማ ተጠሪ፡- አቶ ማርቆስ ጋትሮ መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዘህ መዛገብ የቀረበዉ ጉዲይ በሃዋላ የተላከ ገንዖብ ባንኩ ለማይገባ ሰዉ ከፍሎል በሚል ባንኩ ሃላፉ መደረጉን የሚመለከት ነዉ።ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ የወላይታ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ ፤የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።መዛገቡ እንደሚያሳየዉ የተጠሪ የክስ ምክንያት እ.ኤ.አ በ10/12/2018 ወይም እ.ኤ.አ በ01/04/2011 ዓ.ም ከሉባኖስ ሀገር እህቱ በአሰሪዋ በአቶ ኤልያስ ኢልሀበር አማካይነት በዌስተርን ዩኒየን ገንዖብ መላኪያ አማካኝነት 675 የአሜሪካን ድላር ወይም በወቅቱ ምንዙሪ ብር 18,839 የላከችለት ገንዖብ አመልካች ለማይገባው ሰው ስለከፈለ ገንዖቡ ለእኔ የተላከ ስለመሆኑ ከኢትዮ ቴላኮም ማረጋገጫ የተቀበልኩ በመሆኑ በቸልተኝነት ለላላ ሰው የከፈለውን ገንዖብ ከወለድና ወጪ ጋር እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ የሚል ሲሆን አመልካች በበኩለ የሰጠው መልስ ተጠሪ የሚጠበቅባቸውን ህጋዊነትን በማረጋገጥ የደረሳቸውን ግላዊ ሚስጥር ቁጥር ኮድ ይዖው በማቅረባቸው ባንኩ ባለው አሰራር ክፍያውን ለሚገባው ሰው በ02/04/2011ዓ.ም በአዱስ አበባ ከተማ ገላን ኮንድሚኒየም ቅርንጫፍ ለተጠሪ ከፍሎል፣ስለዘህ ከውጭ ሀገር ገንዖብ ሲላክ ለተቀባይ ግለሰብ የሚደርሰው ሚስጥር ቁጥርና የሚጠይቅ ልዩ ኮድ ያለ ሲሆን በዘሁ መሰረት ክፍያ የተፈፀመ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ክሱን በመጀመሪያ የተመለከተዉ የወላይታ ሶድ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን መርምሮ አመልካች ገንዖቡን አድራሻዉና ማንነቱ ላልታወቀ ሰው ያለአግባብ የከፈለ መሆኑን በማስረጃ ስለተረጋገጠ አመልካች ለተጠሪ የተላከለትን ገንዖብ የመክፈል ሃላፉነት አለበት በማለት ክስ የቀረበበትን ገንዖብ ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ተገቢ ነዉ በማለት አፅንቷል።
አመልካች በዘህ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሟል በማለት ያቀረበው ቅሬታ ይዖት ባጭሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ባንኮች በየትኛውም ግለሰብ ስም በዌስተርን ዩኒየን አማካኝነት ገንዖብ የተላከለት ሰው የመረጠው ባንክ በአካል ቀርቦ ክፍያ እስኪጠይቅበት ድረስ በግለሰቡ ስም ገንዖብ ስለመላኩ እና ስለተላከለት ገንዖብ መጠን ሉያውቅ የሚችልበት ምንም አይነት መንገድ የለም።በዘሁ መሰረት ባንኮች ክፍያ የሚፈፅሙት ገንዖቡ በስሙ የተላከለት ሰው የገንዖብ መቀበያ የሚስጥር ቁጥር እና ማንነቱን የሚያሳይ መታወቂያ ይዜ ለቀረበ ሰው ነው።ይህ የሚሆነው ገንዖብ የተላከለት ሰው ወይም ገንዖብ የላከው ሰው የሚስጥር ቁጥር ለላላ ሶስተኛ ሰው አሳልፍ ይሰጣለ ተብል ስለማይገመት እና አሳልፍ ከሰጡም መቆጣጠሪያ ዖዳ ስለማይኖር ነው።ገንዖቡ ከተላከለት ሰው ጋር ትክክለኛ የሚስጥር ቁጥር ለባንኩ በማቅረብ ለተፈፀመ ክፍያ ባንኩ ያለአግባብ ለማይመለከተው ሰው ክፍያ ፈፅሟል የሚያስብል አይደለም።ተጠሪ ማንነታቸውን የሚያሳይ የቀበላ መታወቂያ እና የሚስጥር ቁጥር ይዖው በመቅረባቸው አመልካች የተላከለት ገንዖብ ክፍያ ፈፅሟል፣ከተጠሪ ውጪ የሚስጥር ቁጥሩ ሉያውቅ የሚችል ላላ ሰው የላለ በመሆኑ አመልካች ክፍያውን የፈፀመው የባንክ አሰራር ተከትል ስለሆነ ክፍያ የተፈፀመው ላልተገባ ሰው ነው ተብል የተሰጠዉ ውሳኔ ስህተት በመሆኑ ተሽሮ አመልካች ገንዖቡን ለመክፈል ሃላፉነት የለበትም በማለት እንዱወሰን ጠይቋል።
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በዌስተርን ዩኒየን አማካኝነት ገንዖብ የተላከለት ሰው በአካል ቀርቦ ክፍያ እስኪጠይቅ ድረስ በግለሰቡ ስም ገንዖብ ስለመላኩና ስለተላከው ገንዖብ መጠን ሉታወቅ የሚችልበት መንገድ እንደላለ፣ገንዖብ በስሙ የተላከለት ሰው የገንዖብ መቀበያ የሚስጥር ቁጥር እና ማንነቱን የሚያሳይ መታወቂያ ይዜ ቀርቦ መክፈለ በተረጋገጠበት ሁኔታ ክፍያው የተፈፀመው ለላላ 3ኛ ወገን ነው ተብል አመልካች በድጋሚ ይክፈል የመባለን አግባብነት ከባንክ አሰራር ሂደት አንፃር ለማጣራት ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዝል።
በተጠሪ በኩል የቀረበው መልስ ባጭሩ በስር ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማጣራት የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማቅረብ አመልካች ገንዖቡን ከፍልለታል ለተባለው ግለሰብ በትክክል የወላይታ ዜን ዲሞት ፐላሣ ወረዲ የላራ ቀበላ ነዋሪ መሆኑ አለመሆኑን ለማጣራት በወቅቱ ያቀረበው መታወቂያ ወረቀት ላይ የፈረሙትና የታተመው ማህተም ህጋዊ መሆን አለመሆን ለማጣራት የቀበላው አስተዲደርና የቀበላዉ ስራ አስኪያጅ በሰጡት ምስክርነት ቃላቸው ግለሰቡ የላራ ቀበላ ነዋሪ አለመሆኑ ተገቢ ማጣራት በማድረግ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ስህተት አልተፈፀመም።ገንዖቡ ለእኔ እንደተላከ በተጠሪ ስልክ የተላከውን መልዕክት ከኢትዮ ቴለኮም ወደ ወረቀት ተቀይሮ በመጣ ማስረጃ ተረጋግጧል፣የሚስጥር ቁጥር በተመለከተ ቀደም ብል የሚስጥር ቁጥሩ ለባንኩ ስለሚደርስና ተቋሙ ከፍቶ የማየት እድል ከፍተኛ ስለሆነ ገንዖቡን እንደፈለገ እንዱያደርግ የሚከለክል የለም። የሚስጥር ቁጥር ይዜ የሚመጣ ሰው ማንነት በሚገባ የማረጋገጥ ሃላፉነት የአመልካች ሆኖ እያለ የክፍያ ሂደት ላይ በተገቢዉ ሳያጣራ መረጃዎችን በአግባቡ መፈተሽ ሲገባ ለእኔ የተላከውን ገንዖብ ባልታወቀ ሁኔታ ለላላ ሰው ስለከፈለ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ የህግ ስህተት የለውም ተብል እንዱፀና በማለት ተከራክረዋል።አመልካች አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዛገቡ ጋር ተያይዖዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምረናል።መዛገቡን መርምረን እንደተገነዖብነዉ ለክሱ ምክንያት የሆነዉ ገንዖብ በአመልካች በኩል ለተጠሪ እንዱከፈል በሃዋላ የተላከ ስለመሆኑ አላከራከረም።የሥር ፍርድ ቤት ገንዖቡ የተከፈለለት ሰዉ ይዜ የቀረበዉ መታወቂያ ከተባለዉ ቀበላ አስተዲደር የተሰጠ አለመሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ገንዖቡ ለተገቢዉ ሰዉ አልተከፈለም የሚል ድምዲሜ ላይ መድረሱን የዉሳኔዉ ይዖት ያሣያል።አመልካችም አጥብቆ የሚከራከረዉ ክፍያ የተፈጸመዉ በባንኩ አሰራር መሰረት በተገቢዉ መረጃ ማጣራት ተደርጎ ስለሆነ በሃላፉነት የሚያስጠይቅ ጥፊት የለም በማለት ነዉ።
በመሰረቱ የደንበኞችን ገንዖብ በሀገር ዉስጥም ሆነ ከሀገር ዉጪ ማስተላላፍ ስራ ከባንክ ስራዎች አንደ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 592/2000 አንቀጽ 2/2/መ/ ላይ ተመልክቷል።ባንክ በአደራ የተቀበለውን የደንበኛውን ገንዖብ የመጠበቅ ህጋዊ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ በንግድ ህጉ ከቁጥር 896 እስከ 902 ከተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዖትና መንፈስ የምንገነዖበው ጉዲይ ነው።የእነዘህ ድንጋጌዎች ይዖትና መንፈስ ሲታይ ባንኩና ደንበኛው የአደራ ስምምነት ውል መግባታቸውን በመግለጽ በውለ ተቃራኒ ስምምነት ከላለ በቀር ባንኩ በአደራ የተቀበለውን ገንዖብ ለታዖዖለት ሰዉ የማድረስ ወይም ለባለአደራዉ የመመለስ ግዳታ ያለበት መሆኑን ያመለክታል።ባንኩ በሕጉ የተጣለበትን ግዳታ ማለትም የደንበኛውን ገንዖብ የባንክ ስራ የሚጠይቀውን አሰራርና ስርዓት በመከተል መጠበቅና ሲጠይቅም ገንዖቡን መክፈል ነው።ባንክ ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርግ ቀርቶ በደንበኛው ገንዖብ ላይ ለሚደርስ ጉዲት ተጠያቂነት የሚኖርበት መሆኑንም ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዖትና ዓላማ የምንረዲው ጉዲይ ነው።ባንኩ የደንበኛውን መብትና ጥቅም ማስከበር የሚገባው ተገቢውን ጥንቃቄ ወይም የተለመደ አሰራር በመከተል እንዲለበት በልላ በኩል ባልተገባ መንገድ በደንበኛው ገንዖብ ላይ ጉዲት እንዲይደርስ መከላከል ጭምር በህግ ግዳታ የተጣለበት ስለመሆኑ እና እዉነታዎችን በማረጋገጥ ረገድ ተገቢዉን ትጋት ማድረግ ያለበት መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 592/2000 አንቀፅ 53 ድንጋጌ ይዖት የምንገነዖበዉ ጉዲይ ነው።
በዘህ መዛገብ በተያዖዉ ጉዲይ አመልካች ክፍያ የፈጸመዉ አስፈላጊዉን መረጃ ከገንዖብ ጠያቂዉ በማጣራት ስለመሆኑ በተለይም የላኪዉን ማንነት፣የተላከዉን ገንዖብ መጠን እና የሚስጥር ቁጥር ገንዖቡን ለመቀበል ከቀረበዉም ሰዉ በማረጋገጥ ክፍያ የፈጸመ ስለመሆኑ አላከራከረም።የስር ፍርድ ቤትም እነዘህ ፍሬ ነገሮች ከማጣራት አንጻር ባንኩ ስህተት ፈጽሟል አላለም።ነገር ግን ፍርድ ቤቱ አመልካችን ሃላፉ ያደረገዉ በዋናነት ተከፊዩ ወይም ገንዖቡን ተቀብሎል የተባለዉ ሰዉ ተጠሪ ሳይሆን በተጠሪ ስም ሀሰተኛ የቀበላ መታወቂያ ይዜ የቀረበ ላላ ሰዉ ነዉ በማለት ነዉ።ባንኩ ክፍያ የፈጸመዉ በባንኩ ያለዉ መረጃ ገንዖቡን ለመቀበል ከቀረበዉ ሰዉ መረጃ በማጣራት ስለመሆኑ እና የተላከለት ሰዉ ማንነት መታወቂያዉን በመመልከት በማገናዖብ አረጋግጦ ስለመሆኑ ይህም በባንኩ የተለመደዉ አሰራር መሰረት የተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ ሃላፉነት እንደላለበት አጥብቆ ተከራክሯል። በመሰረቱ ባንኩ የተከፊዩን ማንነት ለማረጋገጥ መታወቂያዉ የቀበላዉ ማህተም የተደረገበት እና የሚመለከተዉ ሃላፉ ስምና ፊርማ ያለበት መሆኑን በምልከታ ከማረጋገጥ በስተቀር ማህተሙ የቀበላዉ ነዉ ወይስ አይደለም፤ፊርማዉ የሚመለከተዉ ሃላፉ ነዉ ወይስ አይደለም በሚል ተጨማሪ ምርመራ እንዱያደረግ የሚያስገድድ የህግ ምክንያት የለም። የባንክ የስራ ባህርይም ይህንን የሚፈቅድ አለመሆኑ ይታወቃል።ባንኩ ክፍያ ሲፈጽም በዋናነት እንዱያረጋግጥ የሚጠበቀዉ ተከፊዩ ሰዉ ብቻ ያዉቀዋል ተብል የሚገመተዉን ፍሬነገር ማለትም ገንዖቡን የላከዉ ሰዉ ማንነት፤የተላከዉ ገንዖብ መጠን፤የሚስጥር ቁጥር እና የተላከለት ሰዉ ስም ነዉ።እነዘህ ፍሬ ነገሮች በባንኩ ካለዉ መረጃ ጋር በማዙመድ ተመሳሳይ መሆናቸዉ ከተረጋገጠ መረጃ ይዜ የቀረበዉ ሰዉ ትክክለኛ ተከፊይ ነዉ ተብል እንደሚታሰብ እና ገንዖብ ተቀባዩን ማንነት የሚያሳይ መታወቂያ አቅርቦ እንዱከፈለዉ ከታዖዖለት ሰዉ ስም ጋር አንድ መሆኑ ከታወቀ ባንኩ ተገቢዉን ጥንቃቄ ሳያደርግ ቀርቷል ተብል ተጠያቂ ላሆን የሚችልበት ምክንያት የለም።በዘህ ረገድ ይህ ሰበር ችልት በሰበር መ/ቁ/ 41535 ላይ የሰጠዉ ዉሳኔ እንደሚያሳዉ ባንኩ የተለመደዉን አሰራርና ተገቢዉን ጥንቃቄ አድርጎ ክፍያ ከፈጸመ የሰነድቹን ህጋዊነት አላረጋገጠም ተብል በድጋሚ እንዱከፍል ሃላፉነት የለበትም ሲል ዉሳኔ መስጠቱን ልብ ይለዋል።
ስለሆነም ተከፊዩ ይዜ የቀረበዉ መታወቂያ ላይ ያለዉ ፊርማ እና ማህተም የቀበላዉ አይደለም የሚል በሰዉ ምስክር ከመገለጹ ዉጪ ላልቹ መረጃዎች ማለትም የተላከዉ ገንዖብ መጠን፣የላኪዉ ስም እና የሚስጥር ቁጥሩ እንዱሁም ተከፊይ ሰዉ ስም ስህተት ነዉ አልተባለም።እነዘህ አስፈላጊና ወሳኝ መረጃዎች ከተከፊዩ ላላ ሰዉ ሉያዉቅ የሚችልበት ሁኔታ ስለመኖሩ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ባንኩ ለማይገባዉ ሰዉ ክፍያ ፈጽሟል ልባል አይችልም።በዘህም ሁኔታ ለማይገባ ሰዉ ተከፍል ቢሆን እንኳን የተታለለዉ መረጃዉን ያለአግባብ ያባከነዉ ተጠሪ ነዉ ከሚባል በስተቀር ባንኩ ነዉ ልባል አይችልም።
ሲጠቃለል አመልካች ክፍያ የፈጸመዉ በባንኩ የተያዘት መረጃዎች እና ተከፊዩ ሰዉ የሰጠዉ መረጃ ተዙማጅና ትክክል መሆናቸዉ በተለመደዉ አሰራር መሰረት በማረጋገጥ እስከሆነ ድረስ ክፍያዉን የተቀበለዉ በተጠሪ ስም ሀሰተኛ የቀበላ መታወቂያ ይዜ የቀረበ ላላ ሰዉ ነዉ በሚል ምክንያት ባንኩ ድጋሚ ገንዖቡን ለተጠሪ እንዱከፍል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉ ዉሳኔ ስለባንክ ክፍያ አፈጻጸም የተለመደዉን አሰራር እና የተረጋገጡ መሰረታዊ ፍሬ ነገር ጉዲዮችን እንዱሁም ህጉን ያገናዖበ ባለመሆኑ መሰረታዊ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል።በዘሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የወላይታ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 43492 ላይ በ21/02/1012ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና ይህንኑ በማጽናት የደ/ብ/ብ/ህ/ክልል ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/32198 ላይ 17/04/2012ዓ.ም የሰጠው ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ/ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ለክሱ ምክንያት የሆነውን ገንዖብ ለተጠሪ እንዱከፍል የሚገደድበት የህግ ምክንያት የለም ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.