No summary available.
ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካቾች:-
ለዘህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረዉ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነዉ። በዘሁ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ የፍርድ ባለመብት፤ አቶ ጌታነህ ምናለ እና ወ/ሮ አልጋነሽ አበጀ የፍርድ ባለዔዲዎች ሲሆኑ የአሁን አመልካቾች ደግሞ የመቃወም አመልካቾች ነበሩ።
አመልካቾች በስር ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት ያቀረቡት የመቃወሚያ አቤቱታ ይዖት፡የፍርድ ባለዔዲዎች በድድላ ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዉስጥ ያላቸዉ የአክሲዮን ድርሻ ተሸጦ ለተጠሪ እንዱከፈል በሚል የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የተሰጠዉ የአፈጻጸም ትዔዙዛ የፍርድ ባለዔዲዎች በማህበር ዉስጥ 1ኛ የፍርድ ባለዔዲ ከነበራቸዉ 800 አክሲዮኖች ዉስጥ ለ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች እንደቅደም ተከተላቸዉ 266፣ 100 እና 434 አክሲዮኖችን በሽያጭ አስተላልፈዉ በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት በቁጥር ዋ/መ/5533/4ለ/05 የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም ያስተላለፈ ሲሆን 2ኛ የፍርድ ባለዔዲ ደግሞ ከነበራቸዉ 100 አክሲዮኖች ዉስጥ ለ1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች እንደቅደም ተከተላቸዉ 67 እና 44 አክሲዮኖችን በሽያጭ በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት በቁጥር ዋ/መ/5992/4ለ/05 ጥር 01 ቀን 2005 ዓ.ም ቀርበዉ አስተላልፈዉ ከማህበሩ ተሰናብተዋል። የአክሲዮን ድርሻቸዉ ስለመተላለፈም በንግድ መዛገብ ላይ ተመዛግቧል። ስለሆነም የፍርድ ባለዔዲዎች የአክሲዮን ድርሻ የላላቸዉና ትዔዙዘ የተሰጠዉ በአመልካቾች ሀብትና የአክሲዮን ድርሻ ላይ በመሆኑ የአፈጻጸሙ ትዔዙዛ ይነሳልን የሚል ነዉ።
ተጠሪ ለመቃወሚያዉ በሰጠዉ መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆኑት አክሲዮኖች የታገደት የፍ/ባለመብት ባቀረበዉ ክስ መነሻነት በመ/ መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም ነዉ። በወቅቱ የፍ/ቤቱን ትዔዙዛ ባደረስንበት ወቅት 1ኛ የፍርድ ባለዔዲ የድድላ ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ማህበር ሥራ አስኪያጅ ነበሩ። በወቅቱ በእግደ ምክንያት በማህበሩ ስም የሚገኝ ቤት መታገደን ገልጾ ማህበሩ እግደ እንዱነሳለት የጠየቀ ሲሆን በስር ፍ/ቤት ዔግደ እንዱነሳ ተደርጎ የሰበር አቤቱታ አቅርበንበት በንግድ ሕጉ አንቀጽ 522 መሰረት የአክሲዮን መተላለፈ በጽሁፍ ተረጋግጦ በባለአክሲዮኖች መዛገብ እስካልተመዖገበ ድረስ በ3ኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ አይሆንም ተብል እግደ እንዱነሳ የተባለበት ትዔዙዛ በዉሳኔ ተሽሯል። በወቅቱ አመልካቾች የማህበሩ አባላት መሆናቸዉን ማህበሩ የገለጸ በመሆኑ ጉዲዩ ፍጻሜ ማግኘቱን እያወቁ ያቀረቡት አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418(1) መሰረት ዉድቅ ላደረግ ይገባል። የአክሲዮኖቹ ሽያጭ በንግድ መዛገብ ላይ ተመዛግቧል የሚል ክርክር ቢያቀርቡም የምዛገባ ቀናት ተብለዉ የተጠቀሱት ቃለ-ጉባኤዎቹ በሰነድች ማረጋገጫ እና ምዛገባ ጽ/ቤት የተመዖገቡበት ቀን እንጂ በንግድ ሕጉ መሰረት በንግድ መዛገብ መመዛገባቸዉን አያሳይም፤ የቀረበዉ ማስረጃ በቃለ ጉባኤዎቹ ላይ የንግድ ሚኒስቴር ማህተም መደረጉን ከሚያሳይ በቀር የአክሲዮን ማስተላለፈ በንግድ ሕግ ቁጥር 523 መሰረት መመዛገቡን አያሳይም፤ የቀረበ የሰነድ ማስረጃም የለም። አሁን በማስረጃነት የተያያዖዉ ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠዉ ሰነድም አመልካቾች ይህንን አቤቱታ ከማቅረባቸዉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብል መሆኑ ሲታይ አስቀድሞ ያስመዛገቡ ለማስመሰል እየጣሩ መሆኑን ነዉ። ስለሆነም አቤቱታዉ ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክሯል።
የስር ፍ/ቤት የአመልካቾችን የመቃወም አቤቱታ እና የተጠሪን መልስ መርምሮ በአክሲዮኖች ላይ ዔግድ በተሰጠበት ወቅት የፍርድ ባለዔዲዎች በማህበሩ የነበራቸዉን የአክሲዮን ድርሻ በሽያጭ ለላላ ሰዉ ስለማስተላለፊቸዉ በሰነድች ምዛገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት ከመመዛገቡ በቀር በወቅቱ የአክሲዮን ማስተላለፍ የንግድ ሕግ ቁጥር 523 መሰረት የተመዖገበ አለመሆኑን የሚያስገነዛበን በመሆኑና ካልተመዖገበ ደግሞ የተጠሪን ጨምሮ ባለ ላልች 3ኛ ወገኖች ላይ በመቃወሚያነት ላቀርብ የማይገባ በመሆኑ ቀደም ሲል የፍርድ ባለዔዲዎች በድድላ ኢንተርናሽል ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዉስጥ ያላቸዉ የአክሲዮን ድርሻ በሀራጅ ጨረታ ተሸጦ ገንዖቡ ለተጠሪ እንዱከፈል በሚል የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ እንዱነሳላቸዉ አመልካቾች ያቀረቡት መቃወሚያ ዉድቅ ተደርጓል በማለት አፈጻጸሙን እንዱቀጥልበት ትዔዙዛ ሰጥቷል። በዘህ የአፈጻጸም ትዔዙዛ ቅር በመሰኘት አመልካቾች ቅሬታ ቢያቀርቡም ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በትዔዙዛ የስር ፍ/ቤትን ዉሳኔ አጽንቶታል። አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነዉ።
No topics extracted.
አመልካቾች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዖት፡- የፍርድ ባለዔዲዎች በአክሲዮን ማህበሩ ዉስጥ የአክሲዮን ድርሻ መኖሩ ተረጋግጦ ሳይታገድ በሰበር መ/ በስር ፍ/ቤት የተሰጠዉ የዔግድ ትዔዙዛ አይነሳም መባለ የፍርድ ባለዔዲዎች በአክሲዮን ማህበሩ ዉስጥ የአክሲዮን ድርሻ አላቸዉ ለማለት የሚያስችል በቂ ምክንያት አይደለም። አመልካቾች የማህበሩን አክሲዮኖች ከላልች ባለአክሲዮኖች በመግዙት በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት ቀርበዉ በ29/08/2005 ዓ.ም በተመዖገበ ቃለ ጉባኤ እንዱሁም ሚያዘያ 29 ቀን 2005 በተደረገ ምዖገባ በንግድ መዛገብ አስመዛግበን የያዛን ሲሆን የማህበሩን አክሲዮን አሳድገን የማህበሩን የአክሲዮን ድርሻ ሙለ በሙለ ይዖን እንገኛለን።
የፍርድ ባለዔዲዎች በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት በቀን 18/06/2005 ዓ.ም እና በ01/05/2005 ዓ.ም ከማህበሩ ያላቸዉን ድርሻ ከእኛ በፉት የአክሲዮን አባላት ለነበሩ ግለሰቦች በሽያጭ አስተላልፈዉ የተሰናበቱ እና የአክሲዮን ድርሻዉም ስለመተላለፈ በንግድ መዛገብ ላይ በ15/01/2005 ዓ.ም፣ በ01/05/2005 ዓ.ም በ19/06/2005 ዓ.ም በሽያጭ ስለመተላለፈ ተመዛግቧል። በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን የዔግድ አይነሳም ትዔዙዛ መኖሩን አመልካቾች ያወቅነዉ የስር ፍ/ቤት የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም በሰጠዉ ትዔዙዛ የፍርድ ባለዔዲዎች ድርሻ በሀራጅ ተሸጦ ለፍርድ ባለመብት እንዱከፈል የሚለዉ ትዔዙዛ ከደረሰን በኋላ ስለሆነ አመልካቾች ተከራካሪ ባልሆኑበት ማህበሩ መብትና ጥቅም የለዉም የተባለበት ዉሳኔ መሰረት የባለዔዲዎች አክሲዮን ድርሻ መኖሩ ተረጋግጦ ባልታገደበት ባለዔዲዎች የአክሲዮን ድርሻ አላቸዉ መባለ ስህተት ነዉ።
የስር ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት ያቀረብነዉን የክስ አቤቱታ መደበኛዉን የክስ መስማት ሂደት ሳይከተልና ያቀረብነዉን ክስና ማስረጃ በተገቢዉ ሳይመዛን የሰጠዉ ዉሳኔ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ የሰጠዉን አስገዲጅ ትርጉም የጣሰ በመሆኑ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። የአክሲዮን መተላለፈ በሚገባ ሁኔታ በሰነድች ማረጋገጥና ምዛገባ ጽ/ቤት ፀድቆ መተላለፈን 3ኛ ወገኖች በሚያዉቁት ሁኔታ የተመዖገበ ሆኖ እያለ አልተመዖገበም መባለ ስህተት ነዉ።
እንዱሁም ንግድ ሚኒስቴር መጋቢት 14 ቀን 2009 ዓ.ም በጻፈዉ ማስረጃ የአክሲዮን መተላለፈን 3ኛ ወገኖች እንዱያዉቁ በንግድ ሚኒስቴር የንግድ መዛገብ ላይ ስለመመዛገቡ የስር ፍ/ቤት በፍርድ ሀተታዉ አረጋግጧል። የአክሲዮን መተላለፍ ለዉጡና ማሻሻያዉ በሕግ እንዱመዖገብ በተቀመጠዉ አስገዲጅ የምዛገባ ጊዚያት የሚመዖገብ ሆኖ እያለ የምዛገባዉ ጊዚዉ አልተጠቀሰም በሚል ሽያጩ በንግድ መዛገብ ላይ አልተመዖገበም መባለ ስህተት በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ዉሳኔ ይሻርልን የሚል ነዉ።
የአመልካቾች አቤቱታ ተመርምሮ ከዘህ ቀደም በአሁኑ ተጠሪ፣ በፍርድ ባለዔዲዎችና በማህበሩ መካከል የነበረዉ ዔግድ ይነሳልን ክርክር አሁን ክርክር ባስነሳዉ የአክሲዮን ድርሻ ላይ ነዉ ወይስ የማህበሩ ንብረት በሆነዉ ቤት ላይ? ይህ ክርክር እስከ ሰበር ሰሚ ችልት ደርሶ በዉሳኔ በተቋጨ ጊዚ የአሁን አመልካቾች የክርክር ተካፊይ ነበሩ ወይስ አልነበሩም? የአሁን አመልካቾች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መነሻ የክርክር ተካፊይ የሆነዉ ክርክሩ በሚታይበት ጊዚ የአሁን አመልካቾች የአክሲዮን ድርሻ ሽያጭ በዉልና ማስረጃ ምዛገባ ጽ/ቤት የተደረገ ከመሆኑም በላይ በንግድ ሕጉ ቁጥር 522 መሰረት የአክሲዮኖቹ መዛገብም ላይ የተመዖገበ ነዉ በሚል አቅርበዉ የሚከራከሩ እንደመሆኑ መጠን አሁን በግራ ቀኙ የተነሳዉ ክርክር አስቀድሞ በሰበር ሰሚዉ ችልት ቀርቦ ዉሳኔ ያገኘ ጉዲይ ነዉ ማለት ይቻላል? አይቻልም? የአክሲዮን ድርሻ በሽያጭ ለመተላለፈስ ይኸዉ በሽያጭ የማስተላለፍ ተግባር በ3ኛ ወገን ላይ ዉጤት ያስከትል ዖንድ በንግድ ሚኒስቴር አማካኝነት በባለ አክሲዮኖች መዛገብ ላይ ተመዛግቧል ሲል ያቀረበዉ ክርክር በንግድ ሕግ ቁጥር 523 የተመለከተዉን መስፈርት ያሟላ ነዉ ወይስ አይደለም? ከሚለት ነጥቦች አንጻር ጉዲዩ ይታይ ዖንድ ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን የግራ ቀኙን መልስ እና የመልስ መልስ በጽሁፍ በማቀባበል እንዱከራከሩ ተደርጓል።
ተጠሪ በሰበር መልሱ ያቀረበዉ ክርክር ይዖት፡- ተጠሪ በስር ፍ/ቤት በመ/ መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በሰጠዉ የእግድ ትዔዙዛ መሰረት በፍርድ ባለዔዲዎች በእነ አቶ ጌታነህ ምናለ ስም በድድላ ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዉስጥ ተመዛግበዉ የሚገኙ አክሲዮኖቹን በአግባቡ እንዱታገደ አድርጓል። የዔግድ ትዔዙዘ ለማህበሩ እንዱደርስ የተደረገ ሲሆን በወቅቱ የዔግድ ትዔዙዘን የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ነኝ በማለት ፈርመዉ የተቀበለት አቶ ጌታነህ ምናለ ናቸዉ። ማህበሩ አክሲዮኖቹ በሽያጭ ለላላ 3ኛ ወገን በመተላለፊቸዉ ምክንያት ለማገድ አልችልም በማለት ለስር ፍ/ቤት የሰጠዉ ምላሽ የዔግድ ትዔዙዘን መቀበለን ያመለክታል። በወቅቱ ማህበሩ በንብረቴ ላይ የተላለፈዉ የዔግድ ይነሳልኝ ሲል ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም የዔግድ ትዔዙዘ የተላለፈዉ በማህበሩ ቤት ላይ ሳይሆን በባለዔዲዎቹ የአክሲዮን ድርሻ ላይ ነዉ። የስር ፍ/ቤትም ሚያዘያ 12 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዔዙዛ የአክሲዮን ድርሻዎቹ እንዱታገደ በ24/07/2005 ዓ.ም የተሰጠዉ የዔግድ ትዔዙዛ እንዱነሳ ነዉ።
በሰ/መ/ ሰበር ሰሚ ችልት እግደ ሉነሳ አይገባም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ የአክሲዮኖቹ ሽያጭ በንግድ ሕግ ቁጥር 522 እና 523(3) መሰረት ባለመመዛገቡ በ3ኛ ወገን ላይ በመቃወሚያነት ላቀርብ እንደማይችል ገልጾ ነዉ። በመሆኑም የተሰጠዉ ዉሳኔ የፍርድ ባለዔዲዎቹ የማህበሩ ባለአክሲዮኖች መሆናቸዉን በተዖዋዋሪ መንገድ ያመለከተ ነዉ። በተጠቀሰዉ የመዛገብ ቁጥር ሰበር ሰሚ በሰጠዉ ዉሳኔ ማህበሩ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት የለዉም አላለም። አመልካቾችም በዘህ መዛገብ ተከራካሪ አልነበርንም በማለት ያቀረቡት ክርክር ተገቢነት የለዉም። ማህበሩ የአክሲዮን መተላለፈ በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት መመዛገቡን ብቻ በመግለጽ ሲከራከር ቆይቷል።
ችልቱም በጽ/ቤቱ ብቻ መመዛገቡ በቂ አለመሆኑን ገልጾ ዉሳኔ ሲሰጥ ደግሞ የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ከማህበሩ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደላላቸዉ በማስመሰል በቃለ-ጉባኤዉ የሚኒስትሩ መስሪያ ቤት ማህተም እንዱያርፍባቸዉ ጥያቄ ባቀረቡት መሰረት ማህተም ያረፈባቸዉን ቃለ ጉባኤዎች ለስር ፍ/ቤት በማቅረብ ምዛገባ እንደተከናወነ አድርገዉ የሚያቀርቡት ክርክር አግባብነት የለዉም።
አመልካቾች በስር ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት ያቀረቡት አቤቱታ በአግባቡ ታይቶና ተመርምሮ ዉሳኔ የተሰጠበት ነዉ። የአክሲዮን መተለለፍ የተደረገባቸዉን ቃለ ጉባኤዎች በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት የተመዖገበቡትን ቀን በንግድ መዛገብ የተመዖገቡበት ቀን እንደሆነ በማስመሰል እንዱሁም አቤቱታዉን ለፍ/ቤቱ ከማቅረባቸዉ ከአንድ ቀን በፉት ቃለ ጉባኤዎቹ በማህተም ተረጋግጦ እንዱሰጣቸዉ ጠይቀዉ የንግድ ሚኒስቴር ማህተም ያረፈባቸዉን ቃለ ጉባኤዎች በማስረጃነት አቅርበዋል። ይሁን እንጂ ማህተም ማረፈ በንግድ ሕጉ ቁጥር 523 መሰረት በንግድ መዛገብ መመዛገብን አያረጋግጥም። ስለሆነም በስር ፍ/ቤት አክሲኖቹ በአግባቡ መታገዲቸዉ እና ማህበሩ ያካሄደዉ የአክሲዮን ማስተላለፍ በሕጉ መሰረት በአግባቡ አለመመዛገቡ ተረጋግጦ በስር ፍ/ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔ በአግባቡ ስለሆነ ይጽናልን የሚል ነዉ።
አመልካቾች በበኩላቸዉ የሰበር አቤቱታቸዉን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የግራቀኙ ክርክር ባጭሩ ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን እኛም አቤቱታ ከቀረበበት ዉሳኔ እና አግባብነት ካለዉ የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዖብ መዛገቡን መርምረናል። የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘ ጭብጦች አንጻር መርምረን እንደተረዲነዉ መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በስር ፍ/ቤት የተሰጠዉ የእግድ ትዔዙዛ የፍርድ ባለዔዲዎች በድድላ ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ዉስጥ የነበሯቸዉ የአክሲዮን ድርሻዎች የታገደ መሆኑን፤ የፍርድ ባለዔዲዎች በማህበሩ ዉስጥ የነበሯቸዉን አክሲዮኖች በሽያጭ ለአመልካቾች የ1ኛ የፍርድ ባለዔዲ 750 አክሲዮኖች መስከረም 15 ቀን 2005 ዓ.ም፣ 26 አክሲዮኖች ጥር 01 ቀን 2005 ዓ.ም እና 24 አክሲዮኖች የካቲት 19 ቀን 2005 ዓ.ም እንዱሁም የ2ኛ የፍርድ ባለዔዲ አክሲዮኖች ጥር 01 ቀን 2005 ዓ.ም የተላለፈበት ቃለ-ጉባኤ በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት ተመዛግቦ የተላለፈ መሆኑ፤ ማህበሩ በስር ፍ/ቤት በተሰጠ የእግድ ትዔዙዛ ቤቱ መታገደን ገልጾ የፍርድ ባለዔዲዎች የአክሲዮን ድርሻቸዉን ለላልች ሰዎች አስተላልፈዉ ከማህበሩ በመልቀቃቸዉ የዔግድ ትዔዙዛ እንዱነሳለት ጠይቆ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ መስከረም 27 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የአክሲዮን መተላለፈ በንግድ ሚኒስተር በንግድ መዛገብ አልተመዖገበም በማለት በንግድ ሕግ ቁጥር 522 እና 523 መሰረት የአክሲዮን ሽያጩ እስኪመዖገብ ድረስ በ3ኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ስለማይችል የእግድ ትዔዙዘ ሉነሳ አይገባም በማለት የወሰነ መሆኑ በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ነዉ።
አመልካቾች የፍርድ ባለዔዲዎች የአክሲዮን ድርሻ በሀራጅ ተሸጦ ለተጠሪ ይከፈል ተብል የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የተሰጠዉን የአፈጻጸም ትዔዙዛ በመቃወም አቤቱታ ያቀረቡት የፍርድ ባለዔዲዎች የነበሩ አክሲዮኖች በሽያጭ አስቀድሞ የተላለፈላቸዉና መተላለፊቸዉም በሰነድች ማረጋገጥና ምዛገባ ጽ/ቤት እና በንግድ ሚኒስቴር የንግድ መዛገብ የተመዖገበ በመሆኑ የአፈጻጸም ትዔዙዘ እንዱነሳ ሲሆን የስር ፍ/ቤት የአፈጻጸም ትዔዙዘ ሉነሳ አይገባም በማለት ለሰጠዉ ዉሳኔ በዋናነት የሰጠዉ ምክንያት የፍርድ ባለዔዲዎች የአክሲዮን ድርሻቸዉን ለአመልካቾች በሽያጭ ያስተላለፈበት ቃለ-ጉባኤ በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት የተመዖገበ ቢሆንም በንግድ ሕግ ቁጥር 522 እና 523 አግባብ የፍርድ ባለዔዲዎች አክሲዮን በሽያጭ እንዲይተላለፍ በስር ፍ/ቤት መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም ከተሰጠዉ የዔግድ ትዔዙዛ በፉት በንግድ ሚኒስቴር የንግድ መዛገብ መመዛገቡን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካለመቅረቡም በላይ በሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ የአክሲዮኖች ማስተላለፍ ሂደት በአክሲዮኖች መዛገብ አለመመዛገቡን ያረጋገጠበት ነዉ በማለት የአመልካቾችን አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉን ነዉ። አመልካቾች አጥብቀዉ የሚከራከሩበትም ሆነ የዘህን ችልት ምላሽ የሚሻዉ አብይ ጭብጥ የስር ፍ/ቤት ክርክር ያስነሱ የማህበሩ አክሲዮኖች ወደ አመልካቾች በሽያጭ መተላለፊቸዉ የፍርድ ባለዔዲዎች አክሲዮኖች ወደ 3ኛ ወገን እንዲይታለፈ በስር ፍ/ቤት የእግድ ትዔዙዛ ከመሰጠቱ በፉት በንግድ ሚኒስቴር አክሲዮኖች መዛገብ ላይ አልተመዖገበም በማለት የደረሰበት ድምዲሜም ሆነ የአመልካቾችን መቃወሚያ ዉድቅ ማድረጉ በአግባቡ ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉ ሲሆን በተጨማሪም እንደአስፈላጊነቱ ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘ ላልች ጭብጦችን ጭምር ቀጥለን እንመለከታለን።
በመሰረቱ የንግድ ሕግ ቁጥር 522 የአክሲዮኖች መተላለፍ በጽሁፍ የተረጋገጠ መሆን አለበት፤
መተላለፈም በአክሲዮኖቹ መዛገብ ላይ ካልተጻፈ በቀር ማህበሩና ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ ላሆን አይችልም በማለት ሲደነግግ ቁጥር 523(3) ደግሞ አክሲዮን የተላለፈለት ለማህበሩ ባዔድ ለሆነ ሰዉ ሲሆን ማህበርተኞቹ የተስማሙበት ዉሳኔ በንግድ መዛገብ ላይ እንዱመዖገብ ያስፈልጋል በማለት በግልጽ ደንግጎ ይገኛል። ከእነዘህ ድንጋጌዎች ይዖት መገንዖብ የሚቻለዉ የአክሲዮን መተላለፍ ገዥና ሻጭን ለማስገደድ በጽሁፍ መደረግ ያለበት ሲሆን ማህበሩን ለማስገደድና የተላለፈለት ሰዉ በባለአክሲዮንነት ሙለ መብት ለመጠቀም ስለአክሲዮን መተላለፈ ማህበርተኞች የተስማሙበት ዉሳኔ በአክሲዮኖች መዛገብ ሉመዖገብ ይገባል። እንዱሁም በ3ኛ ወገኖች ላይ እንደመቃወሚያ ላቀርብ የሚችለዉ የአክሲዮኖቹ መተላለፍ በንግድ ሚኒስቴር የአክሲዮኖች መዛገብ ላይ ሲመዖገብ ነዉ። ይህን አስመልክቶ ከዘህ ቀደም አሁን ክርክር ባስነሱ አክሲዮኖች መተላለፍ ላይ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ግልጽ ትርጉም ሰጥቶበታል። ስለዘህ የአክሲዮኖች መተላለፍ በ3ኛ ወገን ላይ መቃወሚያ ላሆን የሚችለዉ ስለአክሲዮኖች መተላለፍ ዉል ሲኖር ወይም ማህበርተኞቹ የአክሲዮኖችን መተላለፍ ተቀብለዉ የተስማሙበት ሰነድ በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት ተረጋግጦ መመዛገቡ ሳይሆን በአክሲዮኖች መዛገብ መመዛገቡ ነዉ።
በተያዖዉ ጉዲይ አመልካቾች አክሲዮኖቹ የተላለፈላቸዉ መሆኑ በሰነድች ማረጋገጥና ምዛገባ ጽ/ቤት የተመዖገበዉም ሆነ በንግድ ሚኒስቴር በአክሲዮኖች መዛገብ የተመዖገበዉ የስር ፍ/ቤት መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም የዔግድ ትዔዙዛ ከመስጠቱ በፉት ነዉ የሚለዉን ክርክር ለማረጋገጥ ያቀረቡት ክርክርና ማስረጃዎች ማህበሩ የፍርድ ቤቱ የዔግድ ትዔዙዛ እንደደረሰዉ በቁጥር ARD/316/05 በ05/09/2005 ዓ.ም በጻፈዉ ደብዲቤ የፍርድ ባለዔዲዎቹ የማህበሩ አባል እንዲልሆኑና የአክሲዮን ድርሻ የላላቸዉ መሆኑን የገለጸበት፤ በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት የፍርድ ባለዔዲዎች አክሲዮኖች ወደ አመልካቾች በሽያጭ መተላለፊቸዉን የሚገልጸዉ ቃለ-ጉባኤ በቁጥር ዋ/መ/5992/4ለ/05 ጥር 01 ቀን 2005 ዓ.ም የተመዖገበበት እና የንግድ ሚኒስቴር መጋቢት 14 ቀን 2009 ዓ.ም ለድድላ ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በጻፈዉ ደብዲቤ ማህበሩ በ1998 ዓ.ም ሲቋቋም ጀምሮ የንግድ ምዛገባና ፈቃድ አዉጥቶ በመስራት ላይ መሆኑንና በተለያዩ ጊዚያት ማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ ለዉጡንና የአክሲዮን ማስተላለፍ የሚያደርግባቸዉን ቃለ-ጉባኤ በማጸደቅ የተመዖገበ መሆኑን ጠቅሶ፤ የቀረቡት ቃለ-ጉባኤ ሰነድችም ማህተም አርፍና ተረጋግጠዉ የተመዖገቡ መሆኑን የገለጸበት ናቸዉ። ከእነዘህ ሰነድች መካከል በንግድ ሕጉ ቁጥር 522 መሰረት የአክሲዮን መተላለፈ በ3ኛ ወገኖች መቃወሚያ በሚሆን መልኩ በአክሲዮኖች መዛገብ ላይ በስር ፍ/ቤት የዔግድ ትዔዙዛ ከተሰጠበት መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በፉት መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የለም። ይህን ማስረጃ የማቅረብና የማስረዲት ኃላፉነት የአመልካቾች ሲሆን የአክሲዮን መተላለፈ በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት ጥር 01 ቀን 2005 ዓ.ም መመዛገቡ እንደተረጋገጠ ሁለ በአክሲዮኖች መዛገብ የተመዖገበበትን ግልጽ ቀን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ በቻለ ነበር። የስር ፍ/ቤት የቀረቡለትን ክርክርና ማስረጃዎች መርምሮና መዛኖ የአክሲዮኖች መተላለፍ ፍ/ቤቱ ዔግድ ከሰጠበት መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በፉት በአክሲዮኖች መዛገብ መመዛገቡ አልተረጋገጠም ሲል የደረሰበት ድምዲሜ የሚነቀፍበት በቂ ምክንያት ካለመኖሩም በላይ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ማስረጃን ለመመዖንና ፍሬ ነገርን ለማረጋገጥ ስልጣን የተሰጣቸዉ የስር ፍ/ቤቶች ከደረሰቡበት የፍሬ ነገር ድምዲሜ ዉጪ ማስረጃ ለመመዛንና ፍሬ ነገርን ወደ ማረጋገጥ የሚገባበት የሕግ አግባብ የለም።
ክርክር ያስነሱ አክሲዮኖች ወደ አመልካቾች በሽያጭ የተላለፈት በስር ፍ/ቤት የዔግድ ትዔዙዛ ከተሰጠበት መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በፉት ቢሆንም በአክሲዮኖች መዛገብ አለመመዛገቡ በስር ፍ/ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ ከተረጋገጠዉ አንጻር ሲታይ በንግድ ሕግ ቁጥር 522 እና 523(3) መሰረት የአክሲዮን ሽያጩ በተጠሪ ላይ መቃወሚያ ሆኖ ላቀርብ አይችልም። ስለሆነም የስር ፍ/ቤት ምንም እንኳ የአክሲዮን ሽያጩ የተከናወነዉም ሆነ የማህበሩ አባላት ተስማምተዉ በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ ጽ/ቤት የተመዖገበዉ ተጠሪ በአክሲዮኖቹ ላይ የዔግድ ትዔዙዛ ካሰጠበት መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በፉት ቢሆንም ከዘህ ቀን በፉት በአክሲዮኖች መዛገብ ላይ መመዛገቡ አለመረጋገጡን በመግለጽ አመልካቾች አክሲዮኖች በሀራጅ ተሸጠዉ ለተጠሪ እንዱከፈለ የስር ፍ/ቤት የሰጠዉ የአፈጻጸም ትዔዙዛ እንዱነሳ ያቀረቡትን መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ መወሰኑ የሚነቀፍ አይደለም።
የአመልካቾች አቤቱታ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል በተያዘ ላልች ጭብጦች ላይ ምላሽ መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ ታልፎል።
ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤት የፍርድ ባለዔዲዎች የነበሩ የድድላ ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አክሲዮኖች በስር ፍ/ቤት በተሰጠ ዔግድ ትዔዙዛ ለ3ኛ ወገን እንዲይተላለፈ ከመታገደ በፉት አክሲዮኖቹ ለአመልካቾች በሽያጭ ስለመተላለፊቸዉ በንግድ ሚኒስቴር የአክሲዮን መዛገብ ላይ ስለመመዛገቡ አልተረጋገጠም በማለት የአመልካቾችን መቃወሚያ ዉድቅ ማድረጉ የንግድ ሕግ ቁጥር 522 እና 523(3) ድንጋጌዎችንና እነዘህን ድንጋጌዎችን አስመልክቶ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በተመሳሳይ አክሲዮኖች በሽያጭ መተላለፍ ላይ የሰጠዉን አስገዲጅ ትርጉም ያገናዖበ በመሆኑ ዉሳኔዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አልተቻለም። በመሆኑም የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 01 ቀን 2010 ዓ.ም ተሰጥቶ፤ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት መ/ ታሕሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም በተሰጠ ትዔዙዛ የጸናዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዛገቡ ዉሳኔ ያገኘ ስለሆነ ተዖግቷል። ይመለስ።