No summary available.
ሀምላ 30 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መዓዙ አሸናፉ ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ኑረዱን ከድር አመልካች፡- ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ - ጠ/ቴዎድሮስ ተስፊዬ ተጠሪ፡- ጀነራል ኢንሹራንስ ብሮከርስ - ጠ/ተካልኝ ዓለሙ መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዘህ መዛገብ የተያዖው ክርክር የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪና ስራ አስኪያጇ ወ/ሮ ጌጤነሽ ኃ/ማሪያም በአሁን በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው።
የተጠሪ ክስ ይዖት፡- ኢስት አፍሪካ አትዮጵያ ሉሚትድ የተባለው ኩባንያ በስሩ የሚገኙ ድርጅቶችን የመድህን ሽፊን በተመለከተ የተለያዩ አገልግልቶች ለማግኘት ሰኔ 23 ቀን 1996 ዓ.ም (ጁን 30/2004) በተፃፈ ከሳሽን መርጦ የወከለ መሆኑን ለተከሳሽ አሳውቋል፤ ይህም ላልች በአዋጅ ቁጥር 86/1988 አንቀጽ 11 የተመለከቱትን በመድን ድለላ መስክ የሚከናወኑ ተግባራትን የሚያጠቃልል ሲሆን ከሳሽ ይህን የመድን ገቢውን አደራ በመቀበል ከመስከረም 21 ቀን 1997 ዓ.ም (ኦክቶበር 2004) እስከ ሰኔ 23 ቀን 1997 ዓ.ም (ጁን 30/2005)፣ ከሰኔ 24ቀን 1997 ዓ.ም (ጁላይ 1/2005) እስከ ሰኔ 23/1998 ዓ.ም (ጁን 30/2005) እንዱሁም ከሰኔ 24/1998 ዓ.ም (ጁላይ 1/2006) እስከ ሰኔ 23 ቀን 1999 ዓ.ም (ጁን 30 ቀን 1997) ላለት ሶስት ዓመታት በደንበኛው ስር የሚገኙ 22 ድርጅቶች የመድን ሽፊናቸውን ከተከሳሽ እንዱያገኙ አድርጌያለሁ፤ ከሳሽ እነዘህን በርካታ የመድን ፕሉሲዎች በተመለከተ የካሳ ክፍያና ላልች የውል አስተዲድርን (contract administration) የሚመለከቱ ተግባራትን አከናውኗል፤ ተከሳሽ በከሳሽ አማካኝነት በመጣለት የመድህን ሥራ ብር 7,262,987.79 አረቦን ከደንበኛው ላይ ተቀብሎል፤ ከዘህ የአረቦን ገንዖብ ላይ የመድህን ድለላ ኮሚሽን ለከሳሽ መክፈል ይገባዋል፤ በመድህን ገበያው እንደሚሰራበት አንድ መድህን ሰጪ ደንበኛው ከሚከፍለው የአርቦን መጠን ላይ ለግል ተሸከርካሪዎች መድን 12.5%፣ ለንግድ ተሸከርካሪዎች መድን 10%፣ ለእሳትና መብረቅ 17.5% እንዱሁም ለላልች የመድን ፕሉሲዎች 15% የድለላ ኮሚሽን መክፈል አለበት፤ በዘህ መሰረት ተከሳሽ ለቀረበለት የኮሚሽን ክፍያ ጥያቄ በሰጠው ምላሽ በከሳሽ ያገኘውን የድለላ አገልግልት የሚያምን ቢሆንም መድን ገቢው የተከሳሽ ኩባንያ ባለአክሲዮን በመሆኑ ኮሚሽን ያለመክፈል የውስጥ መመሪያ አለን በሚል ከሳሽን የማይመለከት ምክንያት አቅርቧል፤ ነገር ግን ተከሳሽ ለከሳሽ የሚከፍለውን ኮሚሽን አስመልክቶ የብሮከር ኮድ ቁጥር 01G00135 ሉከፈለው የሚገባውን የኮሚሽን ገንዖብ የሚያሳይ መረጃ አውጥቷል፤ እንዱሁም ከኮሚሽኑ ገንዖብ ላይ ብር 5,085.00 ለከሳሽ ከፍሎል፤
ቀሪውን ገንዖብ ለመክፈል ፈቃደኛ አይደለም፤ ስለሆነም ተከሳሽ ላገኘው አገልግልት መክፈል ያለበትን ብር 1,057,908.31 (አንድ ሚሉዮን ሃምሳ ሰባት ሺህ ዖጠኝ መቶ ስምንት ከ31/100) የኮሚሽን ክፍያ ከነወለደ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
አመልካች ለክሱ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር መልስ አቅርቧል። አመልካች በሰጠው መልስ ኢስት አፍሪካ (ኢትዮ) ሉሚትድ ለመድን ሥራ ከሳሽን ወክሎል በሚል የተገለፀውን በተመለከተ እ.ኤ.አ በ30/06/2004 በመድን ገቢው በተፃፈው ደብዲቤ የመጨረሻ አንቀጽ ስር ጀነራል ኢንሹራንስ ብሮከርና አማካሪዎች የመ/ቤቱን የመድህን ፍላጎት እንዱያጠናና እንዱመረምር በድርጅቱ የተመደበና ኃላፉነት የተሰጠው መሆኑን ከመግለጽ በቀር የተለያዩ የመድን ሽፊኖችን ለማግኘት ከሳሽን የመረጠ ስለመሆኑ አያስረዲም፤ ከዘህ በተቃራኒ ደብዲቤው መድን ገቢው ከተከሳሽ ጋር የኢንሹራንስ ሽፊን ያለው ሲሆን ወደፉትም የሚኖረውን ግንኙነት እራሱ እንደሚያሳውቅ አረጋግጧል፤ በንግድ ህግ ቁጥር 56(1) መሰረት የድለላ ስራ ማለት ውል የሚዋዋለ ሰዎችን ፈልጎ የሚያገናኝና የሚያዋውል ሲሆን የመድን ስራን ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ መሰረት ደግሞ በመድህን ገቢዎች ወይም የጠለፊ ዋስትና ለማግኘት ጥያቄ በሚያቀርቡ ሰዎች ስም የመድህን ንግድ ስራን ከመድህን ሰጪው ጋር የሚያገናኝ እና የመድን ውል ለመዋዋል ለሚፈልጉ ቅድመ ዛግጅትን የሚያመቻች ነው፤ በተያዖው ጉዲይ ግን ከሳሽ ከፍሲል ከተመለከቱት ድርጊቶች የትኛውንም አልፈፀመም፤ መድን ገቢው የተከሳሽ ኩባንያ መስራች ባለአክሲዮን ሲሆን በስሩ ያለት ድርጅቶች ንብረት በተከሳሽ በኩል የኢንሹራንስ ሽፊን ሲሰጣቸው የነበረው ያለ መድን ድለላ ነው፤ ተከሳሽ የድለላ ክፍያ የሚፈጽመው በህግ ላይ በተመለከተው መሰረት አዱስ ደንበኛ አምጥተው ለሚያገናኙ ደላልች ብቻ ነው፤ ተከሳሽ ለከሳሽ የኮሚሽን ጥያቄ የሰጠው ደብዲቤ በየትኛውም መመዖኛ ከሳሽ መድን ገቢውን ከተከሳሽ ጋር የሚያገናኝ ስራ መስራቱን አያረጋግጥም፤ ስለሚከፈለው ገንዖብ መረጃ አውጥቷል የተባለውን በተመለከተም በብሮከር ኮድ ቁጥር 01/J00135 የወጣውን መረጃ ተከሳሽ አያውቀውም፤ ተከፈለ የተባለው ገንዖብም ለከሳሽ ያልተከፈለና ከመድን ገቢው ጋር የተገናኘ አይደለም፤ መድን ገቢው የሚያስተዲድራቸው ንብረቶች የተከሳሽ መድን የነበራቸው ሲሆን ሽፊኑ የተሰጠውም ሆነ የሚታደሰው ካለምንም አገናኝ በመሆኑ ከሳሽ ክስ ባቀረበበት ጉዲይ የድለላ ስራ አልሰራም በመሆኑም ተከሳሽ ለክሱ ኃላፉነት የለበትም፤ ተከሳሽ ለክሱ ኃላፉ ነው ቢባል እንኳ በመድን ስራው አማካኝነት ተከሳሽ ገቢ አግኝቷል የተባለ ቢሆንም ይህንን የሚያስረዲ ማስረጃ አልቀረበም፤ ከሳሽ ያለምንም የሂሳብ ሰነድ እና የሰራውን ስራ የሚገልጽ ማስረጃ ያቀረበው የገንዖብ መጠን ተቀባይነት የለውም፤ ስለሆነም ከሳሽ የጠየቀው የገንዖብ መጠን በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል፤ ይህ የሚታለፍ ከሆነም ለከሳሽ ሉከፈል የሚገባው ክፍያ መድን ገቢው የከፈለው የአርቦን ክፍያ እና ከሳሽ በመድን ገቢው በተፃፈው ደብዲቤ ላይ በተመለከቱት ድርጅቶች ስም ያስገባው የኢንሹራንስ ሽፊንና የተከፈለ የአርቦን ክፍያ በገለልተኛ የሂሳብ ባለሙያ ተለይቶ እንዱቀርብ ትዔዙዛ ተሰጥቶ በሚቀርበው ምላሽ መሰረት እንዱወሰን በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በዘህ መልኩ የቀረበለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተከሳሽ ያቀረበውን መቃወሚያ መርምሮ ሚያዘያ11/2005 ዓ.ም ብይን ተሰጥቶበታል። ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተም ተከሳሽ ለከሳሽ የተጠየቀውን የድለላ ኮሚሽን የመክፈል ኃላፉነት አለበት ወይስ የለበትም? ኃላፉት አለበት ከተባለስ ሉከፍል የሚገባው የገንዖብ መጠን ምን ያህል ላሆን ይገባል? የሚለ ጭብጦች በመያዛ ክርክርና ማስረጃውን መርምሮ ውሳኔ ሰጥቷል። በሰጠው ውሳኔ የመድን ውል ደንበኛው ከመግባቱ በፉት ጨረታ አውጥተው የመድን ውል እንዱፈጸም እና የመድን ውልች ስለሚታደሱበት አግባብ ከተከሳሽ ጋር በመነጋገር ውለ እንዱታደስ የማድረግ፤ ደንበኛውን በመድህን ውል ዘሪያ የማማከር እንዱሁም የካሳ ጥያቄዎች ሲኖሩ ተከታትል የማስፈፀም ስራዎችን ከደንበኛው ውክልና በመውሰድ ሲሰራ የነበረ መሆኑ በከሳሽ በኩል ከቀረቡት ለተከሳሽ የተፃፈ ደብዲቤዎች፤ ተከሳሽ ለከሳሽ ከፃፈው ደብዲቤ፤ ከመድን ገቢው ለፍርድ ቤቱ ከተሰጠው ምላሽ፤ እንዱሁም ምስክሮች በሰጡት ቃል የተረጋገጠ ሲሆን ተከሳሽ ይህን የሚያስተባብል ማስረጃ አላቀረበም። በመሆኑም የመድን ስራን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 746/2004 አንቀጽ 2(19) አንፃር ከሳሽ ደንበኛው የሆነውን ኢስት አፍሪካ ሉሚትድ ግሩፔ በመወከል ከ1996 ዓ.ም እስከ 1999 ዓ.ም ድረስ የመድን የደላላነት ሥራዎች የሰራ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል። በልላ በኩል ስራው የተሰራው የተከሳሽ ኩባንያ ዋና ባለአክሲዮን ለሆነ ወገን በመሆኑ የድለላ ኮሚሽን ልከፍል አይገባም በማለት ተከሳሽ ቢከራከርም ይህን ይደግፊል የሚለውን የዲይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ አያይዜ ካለማቅረቡም በላይ ውሳኔው አለ ቢባል እንኳ ተከሳሽ በራሱ አስተዲደር አካል የተላለፈንና ላልች አካላትን የማይገዙ ውሳኔን መሰረት በማድረግ ከኃላፉነት የሚድንበት አግባብ የለም፤ ስራዎቹ መሰራታቸው እስከተረጋገጠ እና በስራውም አማካኝነት ተከሳሽ ገቢ ማግኘቱ ከተረጋገጠ የኮሚሽን ክፍያ የማይከፍልበት አግባብ አይኖርም። በመሆኑም በተጠሪ ለተሰሩት የመድህን ደላላነት ስራዎች ወይም አገልግልቶች አመልካች ኮሚሽን የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት ወስኗል። ሉከፈል የሚገባውን የገንዖብ መጠን በተመለከተም ከሳሽ በማስረጃነት የተከሳሽን የዲታ ቤዛ ግልባጭ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሽ ማስረጃውን እንደማያውቀውና ከዲታቤዘ የወጣ አለመሆኑን ክድ ቢከራከርም ብሄራዊ ባንክ ጉዲዩን አጣርቶ እንዱገልጽ ታዜ ማስረጃው ከተከሳሽ ኩባንያ ዲታ ቤዛ የወጣ መሆኑን አረጋግጧል፤ ተከሳሹም ከዲታ ቤዛ የተገኘው ማስረጃ ይዖት ላይ ምንም አይነት ክርክር አላቀረበም፤ በመሆኑም በማስረጃው የተመለከተውን ብር 1,057,908.31 (አንድ ሚሉዮን ሀምሳ ሰባት ሺህ ዖጠኝ መቶ ስምንት ብር ከ31/100) የመጨረሻው የድለላ ስራ ከተሰራበት ህዲር 25/1999 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል በማለት ወስኗል።
በዘህ ውሳኔ ባለመስማማት አመልካች ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ውሳኔው ጉድለት የለበትም ተብል ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዝል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን በመቃወም ነው። አመልካች ሚያዘያ 18/2010 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የበታች ፍርድ ቤቶች ባሳለፈት ውሳኔና ትዔዙዛ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚልበትን ምክንያት በመዖርዖር አቅርቧል። አቤቱታው በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው ህግ አዋጅ ቁጥር 86/1986 ነው ወይስ ይህን አዋጅ የተካው አዋጅ ቁጥር 746/2004፤ ተጠሪ ለሰጠው አገልግልት አመልካችን የመጠየቅ መብት አለው ቢባል የአሁን አመልካች ባቀረበው ክርክር እንደገለፀው ለተሰራው ሥራ ሉከፈል የሚገባው ክፍያ በገለልተኛ ባለሙያ ይጣራልኝ በማለት ያቀረበው ክርክር ታልፍ የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለማየት ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል። ተጠሪ ጥቅምት 9/2011 ዓ.ም በተጻፈ መልስ በኃላፉነትም ሆነ በመጠን ረገድ የተሰጠው ውሳኔ ስህተት የላለበት በመሆኑ የሰበር ቅሬታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል። አመልካችም ክርክሩን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከፍሲል የተገለፀው ሲሆን በበኩላችን የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ ጉዲዩ ለዘህ ሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዖው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዖብ እንደተቻለው ተጠሪ አመልካቹ ካገኘው የአርቦን ክፍያ ገቢ መክፈል ያለበትን የመድን ድለላ አገልግልት የኮሚሽን ክፍያ ብር 1,057,908.31 (አንድ ሚሉዮን ሃምሳ ሰባት ሺህ ዖጠኝ መቶ ስምንት ከ31/100) ከነወለደ እንዱከፍል እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቁን ሲሆን አመልካች በበኩለ ተጠሪ ክስ ባቀረበበት ጉዲይ የድለላ ስራ አልሰራም ስለሆነም ለክሱ ኃላፉነት የለብኝም፤ አመልካች ለክሱ ኃላፉ ነው ቢባል እንኳ በመድን ስራው አማካኝነት አመልካች ያገኘውን ገቢ የሚያስረዲ ማስረጃ አልቀረበም፤ ተጠሪ ያለምንም የሂሳብ ሰነድ ያቀረበው የገንዖብ መጠን ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም፤
ይህ የሚታለፍ ከሆነም ለተጠሪ ሉከፈል የሚገባው ክፍያ በገለልተኛ የሂሳብ ባለሙያ ተለይቶ እንዱቀርብ ትዔዙዛ ተሰጥቶ በሚቀርበው ምላሽ መሰረት እንዱወሰን በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤት ክርክርና ማስረጃውን መርምሮ ከፍሲል የተገለፀውን ውሳኔ ሰጥቷል።
በመድን ሥራ አዋጅ ቁጥር 746/2004 አንቀጽ 2(19) ስር እንደተደነገገው ‛የመድን ደላላ“ ማለት ኮሚሽን በማስከፈል በመድን ገቢው ሰው ስም የመድን ውል ለመዋዋል የሚያስችለ ቅድመ ዛግጅቶችን የሚያመቻች፤ የመድን ውል ቀጣይ አስተዲደርና እድሳትን በሚመለከት እገዙ የሚያደርግ፤ እንዱሁም በመድን ውለታና በካሳ ክፍያ ጥያቄ ላይ ለመድን ገቢው የማማከር አገልግልት የሚሰጥ ነው። የተሻረው የመድን ስራ ስለመፍቀድና ስለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 86/1986 አንቀጽ 2(11) ለ‛መድን ደላላ“ የሰጠው ትርጓሜ ይዖትም ከዘህ የተለየ አይደለም። ከዘህም ላላ በንግድ ህጉ ስለደላልች ትርጓሜ በሚሰጠው አንቀጽ 56(1) ስር ‛ደላላ“ ማለት ውል የሚዋዋለ ሰዎችን ይልቁንም እንደ ሽያጭ፣ ኪራይ፣ ኢንሹራንስ፣ የማመላለሻ ውልንና እንደዘህ ያለትን ውልች የሚዋዋለ ሰዎችን ፈልገው የሚያገናኙና የሚያዋዉለ ራሱን የቻለ የሞያ ተግባራቸው አድርገው ጥቅም ለማግኘት የሚሰሩ ሰዎች ወይም ይህንኑ የደላልነት ሥራ የሚሰራ የንግድ ማህበር ነው በማለት ትርጉም ተሰጥቶታል።
በተያዖው ጉዲይ የሥር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ የመድን ውል እንዱፈጸም እና እንዱታደስ የማድረግ፤ የመድን ውልች ስለሚታደሱበት አግባብ ከአመልካች ጋር በመነጋገር ውለ እንዱታደስ የማድረግ፤ ደንበኛውን በመድህን ውል ዘሪያ የማማከር እንዱሁም የካሳ ጥያቄዎች ሲኖሩ ተከታትል የማስፈፀም ስራዎችን ከደንበኛው ውክልና በመውሰድ ሲሰራ የነበረ መሆኑ ከተፃፃፎቸው ደብዲቤዎች፤ ፍርድ ቤቱ ካስቀረበው ማስረጃ እንዱሁም ምስክሮች በሰጡት ቃል በማረጋገጥ ተጠሪ ደንበኛው የሆነውን ኢስት አፍሪካ ሉሚትድ ግሩፔ በመወከል ከ1996 ዓ.ም እስከ 1999 ዓ.ም ድረስ የመድን የደላላነት ሥራዎች የሰራ መሆኑንና በስራውም አማካኝነት አመልካች ገቢ ማግኘቱን በማረጋገጥ በተጠሪ ለተሰራው የመድህን ደላላነት ስራ አመልካች ኮሚሽን የመክፈል ኃላፉነት እንዲለበት ወስኗል። የሥር ፍርድ ቤት እዘህ መደምደሚያ ላይ የደረሰው ፍሬ ነገሩን ለማጣራት እና ማስረጃ ለመመዖን ባለው ስልጣን መሰረት በማጣራትና በማስረጃ በማረጋገጥ ነው። እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በተሰጠው ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት ካለ ከሚመለከት በቀር መሰል የፍሬ ነገር ክርክርን መርምሮ እና ማስረጃ መዛኖ ውሳኔ የሚሰጥ ስላለመሆኑ ከህገ መንግስቱ አንቀፅ 80(3(ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ግልፅ ድንጋጌ መገንዖብ ይቻላል። ተጠሪ የመድን ውል እንዱፈጸም እና እንዱታደስ የማድረግ፤ ደንበኛውን በመድህን ውል ዘሪያ የማማከር እና የካሳ ጥያቄዎች ተከታትል የማስፈፀም ስራዎችን ሲሰራ የነበረ መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ ከፍሲል ከተጠቀሰው የህጉ ትርጉም አንፃር ኮሚሽን የሚያስከፍል የድለላ ሥራ መስራቱን መገንዖብ ይቻላል። በመሆኑም በተጠሪ ለተሰራው የመድህን ደላላነት ስራ አመልካች ኃላፉነት አለበት ተብል በተሰጠው ውሳኔ በዘህ ችልት የሚታረም የህግ ስህተት የለም ብለናል።
በልላ በኩል የክፍያውን መጠን በተመለከተ ከፍሲል እንደተጠቀሰው ተጠሪ 8.31 (አንድ ሚሉዮን ሃምሳ ሰባት ሺህ ዖጠኝ መቶ ስምንት ከ31/100) ከነወለደ እንዱከፈለው የጠየቀ ሲሆን አመልካች በበኩለ በስር ፍርድ ቤት ለክሱ በሰጠው መልስ በመድን ስራው አማካኝነት አመልካች ያገኘውን ገቢ የሚያስረዲ ማስረጃ ስላልቀረበ ተጠሪ ያለምንም የሂሳብ ሰነድ በክሱ ያቀረበው የገንዖብ መጠን ተቀባይነት የለውም እንዱባል፤ ይህ የሚታለፍ ከሆነም ክፍያው በገለልተኛ የሂሳብ ባለሙያ ተለይቶ እንዱቀርብ ትዔዙዛ እንዱሰጥ ጠይቋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ባሳለፈው ውሳኔ እንደተመለከተው በአመልካች ዲታ ቤዛ ተገኘ የተባለን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ተጠሪ የጠየቀውን ክፍያ ከነወለደ እንዱከፈል ከመወሰኑ በቀር ኮሚሽን ለተጠየቀበት የድለላ ስራ ክፍያ አወሳሰን በሚረዲ መልኩ ተጠሪ ያሰጠው የኢንሹራንስ ሽፊንና በመድን ገቢዎች የተከፈለ የአርቦን ክፍያ እንዱሁም ለጉዲዩ ተግባራዊ የሚሆነው የኮሚሽን መጠን በዛርዛር በገለልተኛ የሂሳብ ባለሙያ ተለይቶ እንዱቀርብ ተደርጎ ከስምምነታቸው እና ከህጉ እንዱሁም ከቀረበው ክርክር አንጻር ተለይቶ ውሳኔ አለመሰጠቱን ተገንዛበናል።
ስለሆነም ጉዲዩ ከዘህ አንጻር ሳይታይና ሳይጣራ እንዱሁም ዛርዛር ምክንያት ሳይሰጥ በዲታ ቤዛ ተገኘ የተባለን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ብቻ ተጠሪ የጠየቀውን ብር 1,057,908.31 (አንድ ሚሉዮን ሃምሳ ሰባት ሺህ ዖጠኝ መቶ ስምንት ከ31/100) ከነወለደ አመልካች እንዱከፍል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.