የኢንሹራንስ ፕለሲ የኢንሹራንስ ዉል አካል በመሆኑ በኢንሹራንስ ፕሉሲዉ ላይ የተመለከተዉ ቃል የኢንሹራንስ ዉል ቃል ተደርጎ ሉወሰድ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1733፣የንግድ ሕግ ቁጥር 657(1 እና 2) (19) እና ጀነራል ኢንሹራንስ ብሮከርስ
No summary available.
ኅዲር 30 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ነጋ ባንቲሁን ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት መዛገቡ ተመርምሮ ከዘህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የኢንሹራንስ ካሳ የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩን በመጀመሪያ ዲኝነት ስልጣን የዲኛው የግልግል ጉባኤ ሲሆን በጉባኤው የአሁን አመልካች ከሳሽ ሲሆኑ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክሯል። ከክርክሩ እንደተረዲነው አመልካች በስር የግልግል ዲኝነት ጉባኤ በቀን 01/10/2008 ዓ/ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ ከተጠሪ ድርጅት በ15/11/2006 ዓም በተደረገ የኢንሹራንስ ውል ከ16/11/2006 ዓ/ም እስከ 7/5/2007 ዓ/ም የሚቆይ በዉለ በተመለከቱት የአደጋ ምክንያቶች ጉዲት በደረሰ ጊዚ ብር 10‚528‚000.00 ካሳ ለማግኘት ከተጠሪ የመድን ሽፊን መግኘታቸውን፤ በዘህ የኢንሹራንስ ውል የተሰጠው የሽፊን አይነት እሳት እና መብረቅ፣ ጎርፍ፣ ውርጭ፣ ንፊስ፣ አውል ንፊስ፤ እና ከ35 ሚ.ሜ በላይ በሆነ ከባድ ዛናብ ምክንያት በጥጥ አዛዔርት ላይ ጉዲት ወይም ጥፊት ቢደርስ ካሳ የሚከፈላቸው መሆኑን ገልፀው የአመልካች የጥጥ አዛዔርት ከቀን 01/03/2006 ዓ/ም እስከ 03/13/2006 ዓ/ም ድረስ በአካባቢው በዖነበው ከባድ ዛናብና ጎርፍ እንዱሁም በቀን 25/1/2007 ዓም በዖነበው ከባድ ዛናብ ምክንያት የአመልካች የጥጥ ማሳ በጎርፍ በመጥለቅለቁና ሙለ ለሙለ በጎርፍ በመውደሙ አመልካች ለተጠሪ ጉዲቱን ወዱያውኑ በማሳወቅ በመድን ውለ መሰረት የጉዲት መነሻ 25% ተቀንሶ ኢንሹራንስ የተገባለት መጠን 75% ብር 7‚896‚000.00 በጥጥ አዛርዔት ላይ ጉዲት ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ 9% ወለድ ጋር እንዱከፈላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል ።
የአሁን ተጠሪ ድርጅት የአመልካች ክስ ደርሶት በቀን 14/10/2008 ዓ/ም በሰጠው መልስ አመልካች በቀን 15/11/2006 ዓ.ም ተፈርሟል ሲለ የጠቀሱት የመድን ውል ፕሉሲ ጊዚያዊ ውል መሆኑን፤ ይህ ጊዚያዊ ውል የመጨረሻው ውል እስከሚዖጋጅ ድረስ የሚያገለግል መሆኑን፤ይህ ጊዚያዊ ውል የተሰጠው እርሻው በባለሙያ እስኪታይና እስከሚመረመር ድረስ እንዱያገለግል መሆኑን፤ በዘሁ መሰረት ጊዚያዊ ውለ በቀን 08/12/2006 ዓ/ም የባለሙያ ሪፕርት ከተዖጋጀ በኋላ ለጥጥ እርሻው የሚከፈለው የዐረቦን መጠን አመልካች መጀመሪያ ከከፈለት የዐረቦን መጠን ላይ ተጨማሪ የሚያስከፍል መሆኑን ቢገለፅላቸውም ከሳሽ የሰሉጡን ተጨማሪ ክፍያ ብቻ በመክፈል የጥጡን ተጨማሪ ክፍያ ባለመክፈላቸው በቀን 12/12/2006 ዓ.ም ጊዘያዊ የመድን ውለ ተሰርዜ በዋናዉ ውል የተተካ መሆኑን፤ጊዚያዊ ውለ በልላ ውል ከተተካ በኋላ በጥጥ አዛርዔት ላይ የደረሰውን ጉዲት በሚመለከት ተፈፃሚነት ያለው ጊዚያዊ ውለ ሳይሆን ዋናው ውል መሆኑን፤ በዘህ ውል መሰረት በውለ ሰንጠረዥ ሽፊን የተሰጣቸው የአደጋ ምክንያቶች እሳት እና የመብረቅ አደጋ፤ጎርፍ፤በረድ የቀላቀለ አውል ንፊስ እና ቁር/ውርጭ/ ብቻ መሆኑን ጠቅሶ ከ35 ሚ.ሜ. በላይ የሆነ ከባድ ዛናብ መዛነብና መጥለቅለቅ ዛናባማ አውል ንፊስ የተሰኙት የአደጋ ምክንያቶች በአመልካች እና በተጠሪ በቀን 12/12/2006ዓ.ም በተፈጸመ ውል በሽፊኑ አለመካተታቸውን፤ በመድን ውለ በተመለከተው ትርጉም መሰረት ጎርፍ አለመከሰቱን እና የመድን ውል ሽፊን የሚሰጣቸውና የማይሸፍናቸው አደጋዎች፤ቅድመ ሁኔታዎች፣ ማግለያዎችና ትርጓሜዎችን የሚይዖው ዛርዛር የመድን ፕሉሲው የመድን ውለ ሰንጠረዥ አካል ሆኖ ሳይነጣጠል ላቀርብ የሚገባው በመሆኑ በቀን 12/12/2006 ዓ.ም ከተፈረመው ዋናው ውል ውጭ የቀረበ ክስ ነዉ ተብል ዉድቅ እንዱደረግለት በመጠየቅ ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት ሥልጣን ያየው የግልግል ጉባኤ ግራ ቀኙን አከራክሮና ምስክሮች ሰምቶ በሰጠውውሳኔ አመልካች ለክሳቸው መሰረት ያደረጉት የመድን ውል በንግድ ሕጉ አንቀጽ 657/3 በተመለከተዉ መሰረት ዋናው የመድን ውል እስከሚፈጸም ድረስ የተደረገ አስገዲጅነት ያለውውል እንደሆነ እና ይህ ጊዚያዊ ውል አደጋው ከመድረሱ በፉት በዋናውውል መተካቱን እንዲረጋገጠ በመግለጽ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የመድን ውል በቀን 12/12/2006ዓ.ም የተፈጸመውውል ነዉ በሚል በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።እንዱሁም በዘህ ውል መሰረት ተጠሪ ካሳ ለመክፈል የሚገደደው በእሳት፣ በመብረቅ፣ በጎርፍ፣ በበረድ በቀላቀለ አውል ንፊስ እና ቁር(ዉርጭ) ምክንያቶች የደረሰ ጉዲት ቢኖር ብቻ ነው በሚል ከባድ ዛናብና የውሃ መጥለቅለቅ የሚለ የአደጋ ምክንያቶች በጊዚያዊ ውለ ሽፊን የተሰጣቸው ቢሆኑም ከዋናውውል የተቀነሱ የሽፊን አይነቶች ስለሆኑ በከባድ ዛናብና በውሃ ማጥለቅለቅ በአመልካች የጥጥ አዛዔርት ላይ ለደረሰ ጉዲት ተጠሪ የመድን ካሳ የመክፈል ኃላፉነት የለበትም በማለት በአብላጫ ድምጽ ወስኗል። እንዱሁም በመድን ውለ ለጎርፍ በተሰጠ ትርጉም መሰረት ጎርፍ የሚባለዉ ከመደበኛ የውሃ ማፍሰሻ ቦታ ወጥቶ እርሻውን ሲጎዲ በመሆኑ በዘህ አግባብ የጥጥ ማሳው በጎርፍ መጎዲቱን አመልካች በማስረጃ እንዲላስረደና በውለ ለ"ጎርፍ" የተሰጠው ትርጉም ግልጽ በመሆኑ መተርጎም አስፈላጊ አይደለም በማለት በውለ መሰረት በጎርፍ የደረሰ ጉዲት የለም በሚል ከዘህ አኳያ የተጠየቀውን የካሳ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በከፉል በረድ በቀላቀለ አውል ንፊስ ምክንያት በ15 ሄክታር የጥጥ ማሳ ላይ ለደረሰው ጉዲት ብር 180,000.00 ተጠሪ ለአመልካች ካሳ እንዱከፍል በቀን 14/04/2010ዓ.ም በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።
ከላይ በተገለጸው መሰረት በግልግል ጉባኤ በተሰጠ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን በመ/ ላይ አከራክሮ በቀን 29/08/2010ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው የፍርድ ውሳኔ የግልግል ጉባኤውን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል።አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም በዘህ አግባብ በተሰጡ ውሳኔዎች መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን በቀን 25/10/2010ዓ.ም ጽፈዉ ያቀረቡት አቤቱታ ይዖት በአጭሩ የሚከተለውነው።
የጎርፍ ውሃ እና የዛናብ መጥለቅለቅ በሚመለከት በመድን ውለ በተራ ቁጥር 2.1.2 ላይ ለጎርፍ የተሰጠ ትርጉም እንዱሁም በተራ ቁጥር 2.1.7 ላይ ደግሞ የዛናብ መጠን በየራሳቸው ተለይቶ የመድን ዋስትና ሽፊን ተሰጥቶ ሳለ በእነዘህ ምክንያቶች ለደረሰ ጉዲት የመድን ሽፊን አልተሰጠም ተብል በጉባኤውና በጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠው ትርጉም ግልጽ የሆነ የሕግ ስህተት እንደሆነ፤ በአመልካች የጥጥ አዛዔርት ላይ ጉዲት ያደረሰው ጎርፍ ከደምቢ ድል እና ከላሬ ወረዲ ከዖነበው ከባድ ዛናብ የመጣ መሆኑን ከጋምቤላ ክልል የአደጋ መከላከል መስሪያ ቤት በቀን 08/07/2007ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ የተረጋገጠውን ተጠሪ ሳያስተባብል አመልካች በሰነድ ማስረጃ አላስረዲም በሚል እና ውሃው ከቆመበት ፈንቅል ካልወጣ ጎርፍ እንደማይባል የተሰጠው ትርጉም የጎርፍ መነሻው ከባድ ዛናብ ብቻ መሆኑን የዖነጋ እና ውሃ በውስጣዊ ንቅናቄ ከቆመበት ፈንቅል ሲወጣ ማእበል እንጂ ጎርፍ ልባል እንደማይችል እየታወቀ ከእውነታው የራቀ ትርጉም መሰጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንደሆነ፤ በጊዚያዊና በዋናውውል መካከል ልዩነት አለመኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ውል የተባለውን አመልካች እንደማያውቁና እንዲልፈረሙና ስምምነታቸዉን ያልሰጡበት ውል እንደሆነ በመግለጽ እንደማያስገድዲቸው ላቀረቡት ክርክር ዋጋ ሳይሰጥ መታለፈ እንዱሁም በጎርፍ ተጥለቅልቆ የጥጥ እርሻው መጎዲቱ ከመንግስት ተቋም በመጣ ማስረጃና በተጠሪ ምስክር ጭምር ተመስክሮ የተረጋገጠዉ ታልፍ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንደሆነ፤
እንዱሁም የተጠሪ ምስክሮች የክረምት ጊዚ ካለፈ በኋላ ሄደው ያዩትን በመግለጽ የሰጡትን ምስክርነት ቃል ጎርፍና የውሃ መጥለቅለቅን ለመተርጎም መጠቀማቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት መሆኑን፤
አመልካች ሁለተኛውን ውል አለመፈረማቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ሁለቱም ውልች ላይ ጎርፍም ሆነ የውሃ መጥለቅለቅ የመድን ሽፊን የተሰጣቸው የአደጋ ምክንያቶች ሆነው እያለና በባለሙያ ምስክርነት ቃል እና ከጋምቤላ ክልል መንግስት ተቋማት ከተሰጡ ማስረጃዎች መካከል የተፈጠረ ልዩነት ካለም በልላ ገለልተኛ ማስረጃ ማረጋገጥ እየተቻለ በዘህ አግባብ በማስረጃ እንዱረጋገጥ ሳይደረግ የተደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው ተብል የግልግል ጉባኤው በአብላጫ ድምጽ የተሰጠውውሳኔ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በይግባኝ በማየት የሰጠውውሳኔ ተሽረው በጠየቁት መሰረት ተጠሪ ካሳ እንዱከፍላቸዉ እንዱወሰንላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት የሰበር አቤቱታውን፣ በግልግል ዲኝነት የተሰጠ ውሳኔ እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩ በይግባኝ ታይቶ የተሰጠ ውሳኔ መርምሮ በአመልካች የጥጥ አዛርዔት ላይ የደረሰ ጉዲት በጎርፍ ምክንያት መሆኑ በተከራካሪ ወገኖች የተካደ ባለመሆኑ ግራ ቀኙ በመድን ውል ላይ ለጎርፍ ከሰጡት ትርጓሜ አንፃር የተሰጡትን ውሳኔዎች አግባብነት ለመመርመር መዛገቡ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ትዔዙዛ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 01/04/2011ዓ.ም የተጻፈ መልስ ያቀረበ ሲሆን የመልሱ ይዖት በአጭሩ የሚከተለውነው።
የሰበር አጣሪ ችልቱ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል የያዖው ጭብጥ በአመልካች የጥጥ አዛርዔት ላይ በጎርፍ ምክንያት ጉዲት የደረሰ ስለመሆኑ በተከራካሪ ወገኖች የተካደ አይደለም በሚል መነሻ ቢሆንም ተጠሪ ከስር ክርክር ጀምሮ አንድም ጊዚ ጎርፍ ስለመድረሱ ያላመነና በማስረጃ አስደግፍ የተከራከረበት በመሆኑ የሰበር አጣሪው ጎርፍ መከሰቱ የታመነ ነው በማለት መዛገቡ ያስቀርባል ማለቱ ስህተት እንደሆነ፤ሰበር ሰሚ ችልቱ ተቀብል ማስተናገድ የሚገባው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመባቸውን ጉዲዮች ብቻ ሆኖ እያለ አመልካች በጥጥ እርሻዬ ላይ ጎርፍ ስለመከሰቱ በጋምቤላ ክልል በሚገኙ መስሪያ ቤቶች በተሰጡ ማስረጃዎች ተረጋግጦልኝ እያለ ጎርፍ አልተከሰተም በሚል አለአግባብ ታልፍብኛል በሚል ያቀረቡት ቅሬታ ግን በማስረጃ እና በፍሬ ነገር ክርክር ላይ የተመሰረተ ነው ተብል ውድቅ እንዱደረግለት፤ አመልካች ለጎርፍ በፕሉሲዉ ላይ በተራ ቁጥር 2.1.2 ለውሃ መጥለቅለቅ ደግሞ በተራ ቁጥር 2.1.7 ስር የመድን ሽፊን ተሰጥቶታል በሚል የጠቀሱት በቀጥታ ሽፊን ሉሰጣቸው የሚችለ የአደጋ ስጋቶች (risks coverable) ናቸው እንጂ ሽፊን የተሰጠው ተለይቶ የተቀመጠበት ሰንጠረዥ እንዲልሆነና በቀን 12/12/2006 ዓ.ም በተደረገ ውል ላይ ባለ ሰንጠረዥ ላይ የውሃ መጥለቅለቅ ሽፊን ያልተሰጠው አደጋ እንደሆነ፤ የመጀመሪያውውል በራሱ ጊዚያዊ ውል መሆኑ በግልጽ የተመለከተበት እንደሆነ፤ ላሰጥ የሚገባው የመድን ሽፊን ዓይነት እና የአመልካች የሚከፈል አቅም ከግምት ገብቶ አመልካች መክፈል ያለባቸዉ አርቦን ተሻሽል ዋና ዉል እንደሚፈጸም በጊዚያዊ ዉለ ላይ በተገለጸዉ መሰረት ዋናውውል የተፈጸመ መሆኑን፤ በዋናውውል ላይ የውሃ መጥለቅለቅ የመድን ሽፊን ያልተሰጠው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የውሃ መጥለቅለቅ የመድን ሽፊን ተሰጥቶታል ቢባል እንኳን በውለ አንቀጽ 2.1.7 ስር እንደተገለጸው መጥለቅለቁ መከሰት ያለበት ከ35ሚ.ሜ በላይ በሆነ ከባድ ዛናብ የተከሰተ መጥለቅለቅ መሆን ይገባዋል፤ ሆኖም ጉዲቱ ደረሰ በተባለባቸው ቀናት በዘህ ልክ ዛናብ አለመዛነቡን ለጉባኤውበቀረበው ማስረጃ ስለተረጋገጠና ከመነሻውም በዋናውውል የውሃ መጥለቅለቅ የመድን ሽፊን ያልተሰጠው በመሆኑ ከዘህ አንጻር የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት እንደላለው፤
ህዲር 1 ቀን 2007 ዓ.ም የእርሻ ባለሙያ የምርመራ ሪፕርት እንዱሁም በተጠሪ ሶስተኛ የሞያ ምስክር በተሰጠ ምስክርነት በ5 ሄክታር የአመልካች እርሻ ላይ አነስተኛ የውሃ መጥለቅለቅ እና መታቆር እንዱሁም በከፍተኛ ሁኔታ በአረም መወረርን ጠቀሰ እንጂ እርሻው በሙለ ተጥለቀለቀ አለማለቱን፤
የውሃ ማቆር ደግሞ ከውሃ መጥለቅለቅ የሚለይና ሽፊን ያልተሰጠው መሆኑ፤ጎርፍም ያልተከሰተ መሆኑን፤አመልካች በደፈናው በውሃ መጥለቅለቅ የጥጥ ሰብላን አወደመብኝ ከማለት ባሻገር በስር ያቀረቧቸውም ምስክሮች በእርሻው ላይ አደጋ እንደተከሰተ በቀን 03/13/2006 ዓ.ም በስልክ ሪፕርት መደረጉን ከመመስከር ባለፈ ስለ አደጋው አደራረስ፣የአደጋ ምክንያትም ሆነ የጉዲት መጠን ምንም እንዲላስረደና በአመልካች የሙያ ምስክሮች ተመስክሮ የተረጋገጠዉን የማስተባበል አቅም ያለው ምስክርነት እንዲልሆነ በመግለጽ ቅሬታው የፍሬ ነገር እና የማስረጃ ጉዲይ እንጂ የህግ ስህተትን የተመለከተ አይደለም ተብል ውድቅ እንዱደረግለት በመጠየቅ ተከራክሯል።
አመልካችም በቀን 23/04/2011 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በዘህ ሰበር ችልት ደረጃ ግራ ቀኝ ያደረጉት ክርክር ከዘህ በላይ የተመዖገበዉ ሲሆን እኛም ጉዲዩን ሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ሲል የያዖዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ እና ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለዉ የኢንሹራንስ ዉል በቀን 15/11/2006 ዓ.ም የተደረገዉ ነዉ ወይስ በቀን 12/12/2006 ዓ.ም የተደረገዉ ነዉ? እንዱሁም በአመልካች የጥጥ ማሳ ላይ ጉዲት የደረሰው በኢንሹራንስ ውለ ሽፊን በተሰጠው የአደጋ ምክንያት መሆን አለመሆኑንና ከዘህ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል። እንደመረመርነውም የግራ ቀኝ ክርክር መሰረት ያደረገው በግራ ቀኝ መካከል የተደረጉትን የኢንሹራንስ ውልች ሲሆን አመልካች የኢንሹራንስ ካሳ ለማስከፈል በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ መሰረት ያደረጉት በቀን 15/11/2006 ዓ.ም የተደረገ የኢንሹራንስ ውል ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ይህ በቀን 15/11/2006 ዓ.ም የተደረገ የኢንሹራንስ ውል ጊዚያዊ የኢንሹራንስ ውል እንደሆነና አገልግልቱም የአመልካች አረቦን የመክፈል አቅማቸው ከግምት ገብቶ አመልካች መክፈል ያለባቸው አረቦን ተሻሽል ዋና ውል እንደሚፈጸም በጊዚያዊ ውለ ላይ በተገለጸው መሰረት ዋናውውል እስከሚደረግ ድረስ የኢንሹራንስ ሽፊን ለመስጠት የተዖጋጀ ጊዚያዊ ውል እንደሆነና በክሱ የተጠቀሰው አደጋ ከመድረሱ በፉት ይህ ጊዚያዊ ውል በቀን 12/12/2006ዓ.ም በተፈረመ ዋና ውል ስለተተካ አመልካች ለክሳቸዉ ጊዚያዊ ውለን መጠቀማቸዉ አግባብ አይደለም በሚል ተከራክሯል።አመልካች ከዘህ ጋር ተያይዜ ተጠሪ በቀን 12/12/2006ዓ.ም ተደረገ ያለውን የኢንሹራንስ ውል ስላልፈረምኩ አያስገድደኝም በሚል ተከራክረዋል።
በንግድ ሕግ ቁጥር 657/3 ስር እንደተደነገገው ጊዚያዊ የኢንሹራንስ ሽፊን ማረጋገጫ ማለት የኢንሹራንስ ፕሉሲው ወይም የፕሉሲዉ ተጨማሪ ጽሁፍ ከመፈረሙ በፉት ለጊዚዉ ማረጋገጫ መድን እንዱሆን የሚሰጥ ጽሁፍ(ሰነድ) ሲሆን ዓላማውም ኢንሹራንስ ሰጪውና እንሹራንስ ገቢው አንደ ለአንደ ግዳታ እንደገቡ የሚያሳይ ማረጋገጫ ሰነድ። ይህ ጊዚያዊ የኢንሹራንስ ሽፊን ማረጋገጫ በኢንሹራንስ ስራ ዖርፍ በሰፉው ጊዚያዊ የኢንሹራንስ ማረጋገጫ ሰነድ (Cover Note) ተብል የሚታወቅ ሲሆን ዋና (መደበኛ) የኢንሹራንስ ውል እና ፕሉሲ ማዖጋጀት የሚቻለውስለሚከፈለው አርቦን መጠን፣ስለአደጋ ተጋላጭነት ሁኔታና መንስኤዎች፣ስለማግሉያዎች፣ ስለካሳ መጠን በባለሙያ ጥናት ከተደረገ እና ተዋዋዮች ከተዲራደሩ በኋላ በሆነ ጊዚ እነዘህ ተግባራት እስከሚጠናቀቁ እና ዋናውውል እስከሚፈጸም ድረስ ኢንሹራንስ የሚገባለት ነገር ያለሽፊን እንዲይቀመጥ በሰነደ በግልጽ ለተመለከተው የተወሰነ ጊዚ ስለሚከፈል አርቦን መጠን እና በሰነደ በተገለጹት ምክንያቶች ዋናው የኢንሹራንስ ውል እስከሚፈረም ድረስ አደጋ በደረሰ ጊዚ ስለሚከፈል ካሳ ተገልጾ የሚሰጥ ጊዚያዊ የኢንሹራንስ ሽፊን ነው።
በተያዖው ጉዲይ ላይ ግራ ቀኝ በቀን 15/11/2006 ዓ.ም በውል ቁጥር ጂኤኤም/4/አርኤልሲአር/0001/14 በተዋዋለት የሰብል መድን ዋስትና ላይ በአመልካች የጥጥና ሰሉጥ ሰብል ላይ በእሳትና መብረቅ፣ በጎርፍ፣ በኃይለኛ ንፊስና ውርጭ፣ በረድ በቀላቀለ አውለ ንፊስ፣አቧራ በቀላቀለ አውል ንፊስ፣በአውል ንፊስ እና መጥለቅለቅ (በቀን ከ35ሚ.ሜ በላይ የሆነ ከፍተኛ ዛናብ) በሆኑ የአደጋ ምክንያቶች ከቀን 16/11/2006 እስከ 07/07/2007 ዓ/ም ድረስ ባለው ጊዚ ጉዲት ሲደርስ በጥጥ አዛእርት ላይ ለሚደርስ ጉዲት እስከ ብር 10,528,000.00 (በውለ መሰረት 25% የሚቀነስ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ) ካሳ ለመክፈል ተጠሪ ግዳታ መግባቱን ፣አመልካችም የዘህን 2.5% አርቦን ለመከፍል መስማማታቸውን፤
እንዱሁም ኢንሹራንስ የተገባላቸዉ ሰብልች በእርሻ ባለሙያ/ሰርቬየር ከተመረመረ (ከታየ) በኋላ ከላይ በዘህ ውል ሰንጠረዥ በተገለጸው መድን የተገባለት ንብረት/ጥቅም ማስተካከል እንደሚቻል ስምምነት ማድረጋቸዉን እና ይህም ውል ጊዚያዊ የመድን ውል እንደሆነና የሚያገለግለውም የመጨረሻው የመድን ውል እስከሚሰጥበት ጊዚ ድረስ ብቻ እንደሆነ በውለ ላይ በግልጽ ተመልክቶ ስምምነት መደረጉን ከውለ ሰነድ እና ጉዲዩን በመጀመሪያ ዲኝነት ስልጣን ያየው የግልግል ጉባኤ ከሰጠውውሳኔ ይዖት ተገንዛበናል።
እንዱሁም ተጠሪ አጥብቆ እንደሚከራከረው በቀን 15/11/2006ዓ.ም ውል ከተደረገ በኋላ በባለሙያ እንዱጣራ ተደርጎ ለክሱ መነሻ የሆነው አደጋ ከመድረሱ በፉት ጊዚያዊ ውለ ሉሻሻል እንደሚገባ እና አመልካች የጥጡን ተጨማሪ የአርቦን ክፍያ እንዱከፍለ ተጠይቀው ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ጊዚያዊ ውለ ተሰርዜ በቀን 12/12/2006ዓ/ም በተደረገ ዋና የኢንሹራንስ ውል መሰረት የአርቦን ክፍያውበቀድሞው መጠን እንዱቀጥል በዘህ ዋና ውል የጊዚያዊ ውለ ሰንጠረዥ ተሻሽል ሽፊን የተሰጣቸው የአደጋ ምክያቶች(ምንጮች) ደግሞ እሳት እና መብረቅ፣ጎርፍ፣በረድ የቀላቀለ አውለ ንፊስ እና ቁር/ውርጭ እንዱሆን መደረጉን በመግለጽ ለክርክሩ ተፈጻሚነት ያለው ይህ ዋናው የኢንሹራንስ ውል ነዉ በሚል ተከራክሯል።
እንደሚታወቀው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1711 ስር በግልጽ እንደተደነገገው ተዋዋይ ወገኖች ሕግ ከወሰናቸውና ከከለከላቸው ነገሮች በቀር የሚዋዋለበትን ጉዲይ እንደመሰላቸው የመወሰን መብት አላቸው።በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ወልች ደግሞ ባቋቋሟቸው ሰዎች መብትና ግዳታን ስለሚጥለ እንደሕግ ሆነው እንደሚያገለግለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1731/1 ስር በግልጽ ተደንግጓል። በተያዖው ጉዲይ ከዘህ በላይ እንደተመለከተው በግራ ቀኝ መካከል በቀን 15/11/2006 ዓ.ም የተደረገው የኢንሹራንስ ውል ጊዚያዊ የኢንሹራንስ ማረጋገጫ ሰነድ (Cover Note) እንደሆነና የሚያገለግለውም ዋናው(በሰነደ ላይ የመጨረሻ ተብል የተገለጸው)የኢንሹራንስ ውል እስከሚደረግ ብቻ እንደሆነ በሰነደ ላይ በግልጽ የተመለከተና በዘህ አግባብ በቀን 12/12/2006ዓ.ም በተጠሪ በተፈረመ ዋና የኢንሹራንስ ውል መተካቱን መረዲት ችለናል። ለክርክሩ መነሻ የሆነው አደጋ የደረሰው ደግሞ አመልካች በክሳቸው ላይ እንደገለጹት ከቀን 01/13/2006ዓ.ም እስከ ቀን 03/13/2006ዓ.ም ድረስ እና በቀን 25/01/2007ዓ.ም በእርሻ ቦታ አካባቢና በአጎራባች አገር በዖነበ ከባድ ዛናብ መጥለቅለቅ እና ጎርፍ ምክንያት ስለሆነ ዋናውውል ከተደረገ በኋላ የደረሰ አደጋ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ። እንዱህ አይነት የኢንሹራንስ ውል አደራረግና የመድን ሽፊን አሰጣጥ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 657/3 ስር የተፈቀደ ነው። በዘህ አግባብ ግራ ቀኝ የመጀመሪያዉን ውል ፈቅደው የተስማሙበት በመሆኑ ለግራ ቀኝ ክርክር እንደ ሕግ ሆኖ ሉያገለግል የሚገባው በቀን 15/11/2006 ዓ.ም የተደረገው ጊዚያዊ የኢንሹራንስ ውል ሳይሆን ይህንን ውል የተካው በቀን 12/12/2006ዓ.ም የተደረገውዋናው የኢንሹራንስ ውል እንደሆነ አረጋግጠናል።
እንዱሁም አመልካች ዋናውን ውል ስላልፈረምኩና ስምምነቴን ስላልገለጽኩ ይህ ውል አያስገድደኝም በሚል የተከራከሩ ቢሆንም ይህንን ፍሬ ነገር በግራ ቀኝ ማስረጃ የማረጋገጥ ስልጣን ያለው የግልግል ጉባኤ በማስረጃ እንዲረጋገጠው ተጠሪ የተሻሻለውን ተጨማሪ የአርቦን ክፍያ እንዱከፍለ አመልካችን ጠይቆ አመልካች ተጨማሪ የአርቦን ክፍያ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በጊዚያዊ የኢንሹራንስ ሽፊን ሰንጠረዥ ላይ ከተዖረዖሩት የአደጋ ምክንያቶችን መካከል የተወሰኑትን በመቀነስ በጊዚያዊ የኢንሹራንስ ሽፊን ዉለ ላይ የተገለጸዉ የአርቦን ክፍያ እየተከፈለ የኢንሹራንስ ሽፊኑ እንዱቀጥል ዋናውን ውል በመፈረም ተጠሪ ለአመልካች ማሳወቁን የግልግል ጉባኤው የቀረቡለትን ማስረጃዎች መርምሮና መዛኖ ማረጋገጡን በውሳኔው አስፍሯል። መድን ሰጭው በሚያዖጋጀውፕሉሲላይ እራሱ መፈረም እንዲለበት በንግድ ሕጉ ቁጥር 657 ላይ ከመመልከቱ በስተቀር መድን ገቢው መፈረም እንደሚገባው ያልተመለከተ በመሆኑ በውል ማቅረቢያ /offer/ ሰነደ ጊዚያዊ ውለ ከመደረጉ በፉት በነበረው ላይ አመልካች (ኢንሹራንስ ገቢው)ከፈረሙና በዋናው የኢንሱራንስ ዉልና ፕሉሲው ላይ ደግሞ ተጠሪ (ኢንሹራንሰ ሰጭው) ከፈረመ በሁለቱ መካከል የመድን ውል ስለመደረጉ በቂ አስረጂ በመሆኑ የኢንሹራንሲ ዉልን ልዩ ባህሪ ከግምት ማስገባት የሚገባ በመሆኑ አመልካች በቀን 12/12/2006 ዓ.ም የተደረገውን የኢንሹራንስ ውል ስላልፈረምኩ አያስገድደኝም በማለት ያቀረቡት ክርክር በግልግል ጉባኤ ተቀባይነት ማጣቱ የሚነቀፍ አይደለም።በመሆኑም ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለውውል በቀን 12/12/2006ዓ.ም የተደረገው የኢንሹራንስ ውል ነው ተብል በመወሰኑ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተገኘም።
በአመልካች የጥጥ ማሳ ላይ ጉዲት የደረሰው በኢንሹራንስ ውለ ሽፊን በተሰጠው የአደጋ ምክንያት ነው ወይስ አይደለም? በሚል የያዛነውን ጭብጥ እንደመረመርነው ከዘህ በላይ በተገለጸው መሰረት ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የኢንሹራንስ ውል በቀን 12/12/2006ዓ.ም መሆኑ ተረጋግጧል። በዘህ የኢንሹራንስ ውል መሰረት ሽፊን ያገኙት የአደጋ ምክንያቶች ደግሞ እሳት እና መብረቅ፣ጎርፍ፣በረድ የቀላቀለ አውለ ንፊስ እና ቁር/ውርጭ ብቻ ናቸው።አመልካች በጥጥ ሰብላቸው ላይ ጉዲት ያደረሱ ምክንያቶች ናቸውብለውበክሳቸው ከለጹት ውስጥ አንደ በከባድ ዛናብ የጥጥ ማሳው መጥለቅለቅና ሙለ በሙለ መውደም የሚለውነው። በውሃ መጥለቅለቅ የተከሰተ ጉዲት በመጀመሪያው ጊዚያዊ ሽፊን የኢንሹራንስ ውል ሽፊን የተሰጠው ቢሆንም በቀን 12/12/2006ዓ.ም በተደረገ ዋና የኢንሹራንስ ውል ግን ሽፊን የተሰጠው የአደጋ ምክንያት አይደለም። ስለሆነም ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው በቀን 12/12/2006 ዓ.ም የተደረገው የኢንሹራንስ ውል በመሆኑ አመልካች በውሃ መጥለቅለቅ የአደጋ ምክንያት መነሻ በጥጥ ማሳዬ ላይ ጉዲት ስለደረሰብኝ በሚል የጠየቁትን ካሳ ተጠሪ ሉከፍል አይገባም ተብል በግልግል ጉባኤው መወሰኑና ይሄዉ በይግባኝ ታይቶ መጽናቱ አግባብነት ያለው በመሆኑ ከዘህም አኳያ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ የመድን ሽፊኑን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ አልተቀበልንም።
ላላዉ የዘህን ችልት ምላሽ የሚሻ አከራካሪው ነጥብ አመልካች በጥጥ ማሳዉ ላይ ጉዲት አደረሰ ብለው የገለጹት ሁለተኛው የአደጋ ምክንያት ጎርፍ ሲሆን የግልግል ጉባኤውና ጉዲዩን በይግባኝ አይቶ የወሰነው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ደግሞ የተጠሪን ክርክር ተቀብለው ምንም እንኳን በጥጥ ሰብለ ላይ በጎርፍ ምክንያት ለሚደርስ ጉዲት ካሳ ለመክፈል በቀን 12/12/2006ዓ.ም በተደረገ ዋናዉ የኢንሹራንስ ዉል ሽፊን የተሰጠ ቢሆንም በዘህ ዉል ላይ ለጎርፍ በተሰጠዉ ትርጉም መሰረት በጎርፍ የደረሰ ጉዲት የለም በሚል አመልካች በዘህ የአደጋ ምክንያት መነሻ የጠየቁትንም ካሳ ተጠሪ ሉከፍል አይገባም በማለት ወስነዋል። ከዘህም አኳያ የተነሳዉን ክርክር እንደመረመርነው በጎርፍ ምክንያት በአመልካች የጥጥ ማሳ ላይ ለሚደርስ ጉዲት ተጠሪ የመድን ሽፊን መስጠቱ በቀን 12/12/2006ዓ.ም በተደረገ ዋናው የኢንሹራንስ ውል ላይ በግልጽ የተመለከተ ከመሆኑም በተጨማሪ ተጠሪም የካደው ጉዲይ አይደለም። በዘህ ረገድ ግራ ቀኙን ያከራከረው በኢንሹራንስ ፕሉሲው የትርጉም ክፍል ተራ ቁጥር 1 ስር ለ"ለጎርፍ" የተሰጠው ትርጉም ነው። የተሰጠው ትርጉም ይዖት የሚከተለውነው፡- Flood shall mean loss of or damage to the crop insured caused by the overflow of water from the normal confine of any natural or artificial water course(other than water thanks, apparatus or pipes) or lakes. Reservoir, canal or dam whether resulting from storm or tempest (as defined herein) or otherwise. ይህም ጎርፍ ማለት በተፈጥሮ ወይም በሰዉ ሰራሽ መንገድ ውሃ ከተገደበበት ስፍራ(የዉሃ ታንከር፣ ቧንቧ ወይም መሰል ቁስ( apparatus) ሳይጨምር) ከሀይቅ፣ ከማጠራቀሚያ( Reservoir)፣ ከውሃ ማስተላለፉያ (canal ) ወይም ከግድብ( dam ) በማእበል አማካኝነት( storm or tempest) ወይም በልላ ምክንያት ውሃ ሞልቶ በመፍሰስ ኢንሹራንስ በተገባለት ሰብል ላይ የሚያደርስ ጥፊት ወይም ጉዲት ነው የሚል የአማርኛ ቋንቋ ትርጉም ያለዉ ነው። ግራ ቀኝ ይህንን ትርጉም ተስማምተው የተቀበለት በኢንሹራንስ ፕሉሲው የትርጉም ክፍል ነው። በንግድ ሕግ ቁጥር 657/1 ስር እንደተደነገገው የኢንሹራንስ ውለ በኢንሹራንስ ውል ፕለሲ በሚባል ጽሁፍ መደገፍ ይገባዋል።ይህ ከላይ የተጠቀሰው "ጎርፍ" ለሚለው ቃል ትርጉም የሚሰጠውም ግራ ቀኝ በቀን 12/12/2006ዓ.ም ባደረጉት ዋና ውልም ሆነ በመጀመሪያው ጊዚያዊ የኢንሹራንስ ሽፊን ውል አካል አድርገው(የኢንሹራንስ ውልቹን አስደግፈው) የተስማሙበት የኢንሹራንስ ውል ፕሉሲ ሲሆን ግራ ቀኝም ይህንኑ አልተካካደም። በዘህ የኢንሹራንስ ፕሉስ ላይ የተመለከተው ነገር ግራ ቀኝ ተጨማሪ በሆነ ጽሁፍ በልላ አግባብ ካልተስማሙ በቀር ሉለወጥ እንደማይችል በንግድ ሕጉ አንቀጽ 657/2 ሥር ተደንግጓል።ከላይ በተገለጸው መሰረት በተጠቀሰው አግባብ ለጎርፍ ትርጉም የሚሰጠው የኢንሹራንስ ውል ፕሉስ ተጨማሪ በሆነ ጽሁፍ የተለወጠ ስለመሆኑ በግራ ቀኝ የቀረበ ክርክር የለም።
በተጨማሪም አመልካች ከዘህ ጋር አያይዖው እየተከራከሩ ያለት ውሃው ከቆመበት ከውስጣዊ ንቅናቄ ፈንቅል ካልወጣ ጎርፍ እንደማይባል በዖፈቀደ ትርጉም የሚወጣለት ሳይሆን ጎርፍ በዓለም ደረጃ የሚታወቀው በከባድ ዛናብ መነሻ የሚከሰት ክስተት ሆኖ እያለ ከእውነታው የወጣ ትርጉም መሰጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው በሚል ነው።በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1733 ስር ውለታዎች ግልጽ በሆኑ ጊዚ ግልጽ ሆኖ ከሚሰማው በመራቅ የተዋዋዮቹ ፈቃድ ምን እንደነበር ዳኞች ለመተርጎም እንደማይችለ በግልጽ ተደንግጓል። በተያዖውም ጉዲይ በንግድ ሕጉ ቁጥር 657(1 እና 2) መሰረት የኢንሹራንስ ፕለሲው የኢንሹራንስ ውለ አካል በመሆኑ በኢንሹራንስ ፕሉሲው ላይ የተመለከተው ቃል የኢንሹራንስ ውል ቃል ተደርጎ ሉወሰድ የሚገባ በመሆኑ፣ በፕሉሲው ላይ ግራ ቀኝ ከላይ በተመለከተው መሰረት ጎርፍ ለሚለዉ ቃል ጠባብ ትርጉም በመስጠት እስከተዋዋለና በዘህ አግባብ ለቃለ ጠባብ ትርጉም በመስጠት መዋዋልን የሚከለክል ሕግ ባለመኖሩ፣ በፕሉሲው ለጎርፍ የተሰጠው ትርጉም ግልጽ አይደለም በሚል በአመልካች የቀረበ ክርክር ባለመኖሩና የተሰጠውም ትርጉም ግልጽ በመሆኑ ጎርፍ በነባራዊው ዓለም በትርጉሙ በተጠቀሰው ሁኔታ ብቻ የሚከሰት አይደለም የሚል ክርክር በአመልካች በመነሳቱ ብቻ በግራ ቀኝ መካከል እንደ ሕግ የሚያገለግለዉ የውል ቃል በሰፉው እንዱተረጎም የሚያስችል የሕግ መሰረት የለም።
በመሆኑም ምንም እንኳን በጎርፍ አደጋ ኢንሹራንስ በተገባለት የጥጥ አዛእርት ላይ የሚከሰት ጉዲት በቀን 12/12/2006ዓ.ም በተደረገ የኢንሹራንስ ውል የመድን ሽፊን የተሰጠው የአደጋ ምክንያት ቢሆንም ግራ ቀኝ በኢንሹራንስ ፕሉሲው ላይ ለጎርፍ በሰጡት ትርጉም መሰረት በአመልካች የጥጥ አዛእርት ላይ ጉዲት ያደረሰው ጎርፍ በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ መንገድ ውሃ ከተገደበበት ስፍራ(የውሃ ታንከር፣ ቧንቧ ወይም መሰል ቁስ( apparatus) ሳይጨምር) ከሀይቅ፣ ከማጠራቀሚያ( Reservoir)፣ ከውሃ ማስተላለፉያ (canal ) ወይም ከግድብ( dam ) ላይ በማእበል አማካኝነት( storm or tempest) ወይም በልላ ምክንያት ውሃ ሞልቶ በመፍሰሱ ምክንያት የተከሰተ ጎርፍ አለመሆኑን ፍሬ ነገርን በማስረጃ አጣርቶና መዛኖ የማረጋገጥ ስልጣን ያለው የግልግል ጉባኤ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ መስጠቱና ይሄውውሳኔ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት መጽናቱ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/3 ስልጣን የተሰጠው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ እንዱያርም እንጂ ከማስረጃ ምዖና ጋር በተያየዖ የሚቀርቡለትን የፍሬ ነገር ስህተት እንዱያርም ባለመሆኑ አመልካች ጎርፍ ስለመከሰቱ በማስረጃ አስረድቻለሁ ሲለ ያቀረቡት ክርክር በኢንሹራንስ ፕሉሲው የተቀመጠውን የጎርፍ ትርጉም ያላገናዖብ ከመሆኑም በተጨማሪ ፍሬ ነገርን ከቀረበው ማስረጃ አንጻር መርምሮና መዛኖ የማረጋገጥ የዲኝነት ተግባር በዘህ ችልት ደረጃ ላታይ የሚችል አይደለም።እንዱሁም የማስረጃ ምዖና ስርዓትና መርህ ተከትል የግራ ቀኝን ማስረጃ ከመመዖን አንጻር የግልግል ጉባኤውም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጡት ውሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልፈጸሙም። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የግልግል ዲኝነት ጉባኤ በቀን 14/04/2010 ዓ.ም የሰጠውውሳኔ እና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 29/08/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት የግልግል ዲኝነት ጉባኤው የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት የሰጠውን የፍርድ ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል።
ግራ ቀኝ በዘህ ችልት ደራጃ ያወጡትን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
የውሳኔው ግልባጭ ለግራ ቀኝ ይሰጣቸዉ።
ውሳኔው ይታተም ዖንድ ግልባጩ ለፍርድ ቤቱ ጉዲዩ ለሚመለከተው ክፍል ይተላለፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.