አንድ የመድን ገቢ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር መድን የተገባለት ተሽከርካሪ ላይ አደጋ መድረሱን በተገባለት የመድን ዉልም ሆነ በሕግ የተመለከተዉን ለመድን ሰጭዉ አደጋን የማሳወቅ ቅድመ ሁኔታ በአግባቡ አሟልቶ እያለ መድን ሰጪው ለ3ኛ ወገን የከፈለውን ካሳ መድን ገቢው መልሶ ለመድን ሰጪው የሚከፍልበት አግባብ የላለ አቶ ሰለሞን በቀለ እና ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ አ.ማ
No summary available.
የካቲት 13 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ዳኞች፡ ….ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡ …… አቶ ሰለሞን በቀለ፡- ጠበቃ አቶ ዚና ደባሱ ቀርበዋል።
ተጠሪ፡ ………. ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ አ.ማ፡- የቀረበ የለም።
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣የአሁን አመልካች ተከሳሽ፣የአሁን ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ ሁኖ ሲከራከሩ ነበር።ይህ ጉዲይ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.214848 በ5/11/2010 ዓ.ም የሰጠዉን ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ባቀረቡት ክስ የተከሳሽ ንብረት የሆነዉ የሰላዲ ቁጥር ኮድ 2-A77230 አ.አ የሆነዉ ተሽከርካሪ ከከሳሽ የ3ኛ ወገን መድን ሽፊን የተሰጠዉ ሲሆን፣ ይህ ተሽከርካሪ በ16/11/2008 ዓ.ም በቂርቆስ ክ/ከተማ መስከረም ማዜሪያ አካባቢ የ3ኛ ወገን ንብረት የሆነዉን የሰላዲ ቁጥር ኮድ 2-A70206 አ.አ የሆነዉን ተሽከርካሪ ገጭቶ ጉዲት በማድረሱ ከሳሽ ብር 23,573.93 ለተጎጅዉ የከፈለ በመሆኑ፣ ተከሳሽ በመድን ዉለ መሰረት ጉዲት መድረሱን ለከሳሽ የማሳወቅ ግዳታዉን ያልተወጣ ስለሆነ፣ ይህን ገንዖብ ክሱ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር ተከሳሽ እንዱከፍለኝ እንዱወሰንልን በማለት ከሷል።
በዘህ ክስ ላይ ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ ከሳሽ የመድን ዉል መኖሩንና አደጋዉ መድረሱን በማመን ለፕሉስ ደብዲቤ የጻፈዉ በተከሳሽ አማካይነት አደጋ መድረሱን በማወቁ ነዉ፣ ተሽከርካሪዉ ወደ ተከሳሽ ስም መዙወሩን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ በከሳሽ እጅ መገኘቱ ነዉ፣ ለደረሰዉ አደጋ ኃላፉነቱ የከሳሽ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ ከሳሽ ለተከሳሽ ተሽከርካሪ በሰጠዉ የ3ኛ ወገን የመድን ዉል ተከሳሹ ተጠቃሚ በመሆኑ፣ በዉለ የተጣለበትን ቅድመ ሁኔታ ማለትም የደረሰዉን አደጋ ለከሳሽ የማሳወቅ ግዳታ የመወጣት ኃለፉነት አለበት፤ እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 799/05 አንቀጽ 17 [1] መሰረት የተመለከቱትን ቅድመ ሁኔታዎች መካከል አደጋን የማሳወቅ ግዳታ ነዉ። ተከሳሽ ፕሉስ የአደጋዉን ዛርዛር ሁኔታ ለከሳሽ እንዱገልጽ መጠየቃቸዉ አደጋ መድረሱን ከሳሽ እንዱያዉቅ የማድረግ ግዳታቸዉን ተወጥቷል ለማለት ስለማይቻል፤ ተከሳሽ በመድን ዉልም ሆነ በአዋጁ አደጋን የማሳወቅ ግዳታዉን ስላልተወጣ፣ ከሳሽ በሕግ የተጣለበትን አደጋ የደረሰበትን 3ኛ ወገን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመካስ ኃላፉነት ለመወጣት አደጋዉ ለደረሰበት 3ኛ ወገን የከፈለዉን ብር 23,573.93 ክስ ከቀረበበት ከ6/4/2010 ዓ.ም ጀምሮ ክፍያዉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ለከሳሽ እንዱከፍል፣ የተለያዩ ወጪዎችንም እንዱከፍል ወስኗል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በዘህ ጉዲይ የቀረበለትን ይግባኝ ዉድቅ በማድረግ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ ይህን ዉሳኔና ትዔዙዛ በመቃወም ለማሻር ነዉ።
የአሁን አመልካች ሐምል 13 ቀን 2010 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ ከተጠሪ የ3ኛ ወገን መድን ሽፊን የተሰጠዉ የአመልካች ንብረት የሆነዉ የሰላዲ ቁጥር ኮድ 2-A77230 አ.አ የሆነዉ ተሽከርካሪ የ3ኛ ወገን ንብረት በሆነዉ የሰላዲ ቁጥር ኮድ 2-A70206 አ.አ ተሽካርካሪ ላይ የግጭት አደጋ በማድረስ ጉዲት ያደረሰ መሆኑን በአመልካች ተሽከርካሪ ላይ አሽከርካሪ የነበረዉ አቶ ካሱ ወርድፊ አማካኝነት የግጭት አደጋ በ16/11/2008 ዓ.ም መድረሱን ወዱያዉኑ በወቅቱ ማሳወቁን ተጠሪ አምነዉ ተከራክሯል። ተጠሪዉ በዘህ መሰረት አደጋ መድረሱን የአመልካች ተሽከርካሪ ሾፋር በማሳወቃቸዉ አደጋዉ በደረሰ በአራተኛዉ ቀን በ20/11/2008 ዓ.ም በአዱስ አበባ ከተማ ለቂርቆስ ክ/ከተማ ፕሉስ መምሪያ በአመልካች አማካኝነት የግጭት አደጋዉ መመዛገቡን ማሳወቁንና ዛርዛር ሁኔታዉን እንዱያሳዉቀዉ ጥያቄዎችን ጽፎል። በዘህ መሰረት የፕሉስ መምሪያዉ በ20/11/2008 ዓ.ም የተጻፈ የትራፉክ አደጋ ሪፕርት መስጫ ፍርም ቅጽ ቁጥር 005/02 ለተጠሪ ያሳወቀበት ሰነድ በተጠሪ እንደማስረጃ የቀረበ ጉዲይ ነዉ። በመሆኑም የአሁን አመልካች በመድን ዉለም ሆነ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 17 [1] መሰረት አደጋን የማሳወቅ ግዳታ ተሰጥቶ እያለ የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች ይህን ግዳታዉን ስላልተወጣ የአሁን ተጠሪ ለ3ኛ ወገን የከፈለዉን የካሳ ገንዖብ እንዱከፍለዉ በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልን፣ ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብት እንዱጠበቅልኝ በማለት በዛርዛር አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ይህን ጉዲይ በማየት ፣በዘህ ጉዲይ አመልካች ተሽከርካሪዉ ያደረሰዉን የግጭት አደጋ በወቅቱ ለመድን ሰጪ ለሆነዉ ለተጠሪ አላሳወቀዉም ተብል ተጠሪ ያወጣዉን ወጪ ሉተካ ይገባል ተብል የመወሰኑን አግባብነት፣ ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ባዖዖዉ መሰረት መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዖት በአጭሩ፡ የአሁን አመልካች በመድን ዉለ እና ህግ የተመለከተዉ አደጋዉን ለመድን ሰጪ ለሆነዉ ለተጠሪ አደጋዉ በደረሰ በአስር ተከታታይ ቀናት የማሳወቅ ግዳታዉን ያልተወጡ መሆኑን የሥር ፍ/ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ ነዉ፤ ተጠሪ አደጋ መድረሱን ሉያዉቅ የቻለዉ ጉዲት የደረሰበት 3ኛ ወገን የካሳ ክፍያ እንዱፈጸምለት በጠየቀበት ወቅት ነዉ እንጂ አመልካች በተጠሪ ኩባንያ አደጋ ማሳወቂያ ቅፅ በመሙላት ያሳወቀዉ ነገር መኖሩን ያቀረበ ማስረጃ የለም። ስለዘህ የሥር ፍ/ቤቶች በዘህ ረገድ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ተብል የሚነቀፍ ባለመሆኑ፣ አመልካች ያቀረበዉ አቤቱታ ዉድቅ ሆኖ፣ የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔዎች እንዱጻናልን በማለት በዛርዛር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ የአሁን ተጠሪ የአመልካች ንብረት የሰላዲ ቁጥር ኮድ 2-A77230 አ.አ ለሆነዉ ተሽከርካሪ የ3ኛ ወገን መድን ሽፊን መስጠቱ ያልተካደ ፍሬ ነገር ነዉ። ይህ ተሽከርካሪ የ3ኛ ወገን ንብረት በሆነዉ የሰላዲ ቁጥር ኮድ 2-A70206 አ.አ ተሽካርካሪ ላይ የግጭት አደጋ በማድረስ ጉዲት ያደረሰ መሆኑን እና በዘህ ምክንያት የአሁን ተጠሪ በመድን ዉለ መሰረት ጉዲት ለደረሰበት 3ኛ ወገን ካሳ የከፈለ መሆኑ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነበር።
ይህን ተከትል የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክስ አመልካች በመድን ዉለ መሰረት ለተጠሪ አደጋ የማሳወቅ ግዳታዉን ስላልተወጣ ለ3ኛ ወገን የከፈልኩትን ብር 23,573.93 ከሕጋዊ ወለድ ጋር አመልካች እንዱከፍለኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል። አመልካች በበኩለ ባቀረበዉ ክርክር በዉለ መሰረት አደጋዉን ለተጠሪ የማሳወቅ ግዳታ ስለተወጣሁኝ ይህን ገንዖብ መክፈል የለብኝም በማለት ተከራክሯል። የሥር ፍ/ቤቶች ጉዲዩን በመመርመር በሰጡት ዉሳኔ አመልካች በዉለ እና በሕጉ አግባብ አደጋን የማሳወቅ ግዳታዉን ስላልተወጣ ተጠሪ በክሱ የጠቀሰዉን ገንዖብ ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፈለዉ ወስኗል።
እንግዱህ እነዘህ ጉዲዮች በሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ሲሆኑ በሕጉ አግባብ ሲታይ የአሁን አመልካች በመድን ዉለ እና ስለተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን የወጣ አዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 17 [1] መሰረት አደጋን የማሳውቅ ግዳታዉን አልተወጣም ተብል የተጠየቀዉን ገንዖብ ለተጠሪ እንዱከፈል የመወሰኑን አግባብነት መመርመሩ ተገቢ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 17 [1] ሥር እንደተመለከተዉ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካልኖረ በስተቀር መድን ተገቢዉ መድን የተገባለት ተሽከርካሪ አደጋ መድረሱን ወዱያዉኑ ወይም ቢዖጋይ በአስር ቀን ዉስጥ ለመድን ሰጭዉ ማስታወቅ አለበት። ከዘህ ድንጋጌ መገንዖብ እንደሚቻለዉ የ3ኛ ወገን መድን ዉል ገቢዉ መድን የተገባለት ተሽከርካሪ አደጋ ያደረሰ እንደሆነ አደጋ መድረሱን ለመድን ሰጭዉ በሕጉ በተመለከተዉ ጊዚ ዉስጥ የማሳወቅ ግዳታ የተጣለበት መሆኑን ነዉ። በመሆኑም አንድ የመድን ገቢዉ በዘህ ድንጋጌ መሰረት በሕግ የተጣለበትን ለመድን ሰጭዉ አደጋን የማሳወቅ ግዳታዉን ካልተወጣ በ3ኛ ወገን የመድን ዉል ተጠቃሚ ለመሆን በሕግ የተመለከተዉን ቅድመ ሁኔታ እንዲልተወጣ ስለሚያስቆጥረዉ መብቱን የሚያጣበት ሁኔታ ሉኖር እንደሚችል መገንዖብ ያስፈልጋል።
በዘህ አግባብ አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ በግራ ቀኛቸዉ መካከል በተደረገዉ የ3ኛ ወገን የመድን ዉል መሰረት አመልካች ለተጠሪ አደጋ የማሳወቅ ግዳታ እንደተጣለበት ያልተካደ ጉዲይ ነዉ።
የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክርክር የተሽከርካሪ አደጋ መድረሱን ለክፍለ ፕሉስም ሆነ ለተጠሪ ማሳወቁን ገልጾ ተከራክሯል። ተጠሪ በበኩለ ባቀረበዉ ክርክር በክሱ የተጠቀሰዉ ተሽከርካሪ አደጋ ማድረሱን ያወቅኩት የሶስተኛ ወገን ካሳ እንዱከፈለዉ ጥያቄ በማቅረቡ ነዉ እንጂ አመልካች አደጋዉን ለተጠሪ የማሳወቅ ግዳታዉን አልተወጣም በማለት ተከራክሯል።
በዘህ ረገድ ከሥር ፍ/ቤት መዛገብ መገንዖብ እንደሚቻለዉ የአመልካች ንብረት የሆነዉ ተሽከርካሪ በሶስተኛ ወገን ተሽከርካሪ ላይ የግጭት አደጋ ያደረሰዉ በ16/11/2008 ዓ.ም ሲሆን፣ የአሁን ተጠሪ ስለተሽከርካሪዉ ግጭት ጉዲይ ፕሉስ ዛርዛር መግለጫ እንዱሰጠዉ በ20/11/2008 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ የጠየቀ መሆኑን ነዉ። በዘህ መሰረት የቂርቆስ ክ/ከተማ ፕሉስ መምሪያ በቂ/ፕመ/11/1002/08 በ20/11/2008 ዓ.ም በጻፈዉ የትራፉክ አደጋ ሪፕርት መግለጫ ፍርም ቅጽ ቁጥር 005/02 የአመልካች ንብረት የሆነዉ ተሽከርካሪ ስላደረሰዉአደጋ ዛርዛር መግለጫ ለተጠሪ ማሳወቁን ማየት ይቻላል። ይህ ማለት ተጠሪ አደጋዉ እንደደረሰ በአራት ቀን ዉስጥ ስለአደጋዉ እንዱያዉቅ የተደረገ መሆኑን ነዉ።
የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክርክር ይህ ተሽከርካሪ አደጋ ማድረሱን ያወቅነዉ ጉዲት የደረሰበት ሶስተኛ ወገን ካሳ እንዱከፈለዉ ጥያቄ በማቅረቡ ነዉ ይባል እንጂ ይህ ሶስተኛ ወገን መቼ እንዲሳወቀዉ፣ አደጋዉን ያሳወቀበት ቅጽ እንደማስረጃ ማቅረቡን የሥር ፍ/ቤት መዛገብ የሚያሳየዉ ነገር የለም።
ተጠሪ ባቀረበዉ ክርክር አደጋ መድረሱን ማሳወቅ የሚቻለዉ በተጠሪ ኩባንያ በተዖጋጀዉ ቅጽ በመሙላት ብቻ ነዉ የሚል እስከሆነ ድረስ ስለአደጋዉ ማድረስ ላላ ወገን ያሳወቀዉ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ ማቅረቡን የሥር ዉሳኔ የሚያሳየዉ ነገር የለም። ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ መገንዖብ እንደሚቻለዉ የአሁን አመልካች ተቀጣሪ የሆነዉ አሽከርካሪ የነበረዉ አቶ ካሱ ወርድፊ ተሽከርካሪዉ ያደረሰዉን አደጋ ወዱያዉኑ ለክፍለ ፕሉስ ሪፕርት አድርጎ ማሳወቁን እና ፕሉስ ደግሞ ስለአደጋዉ ዛርዛር መግለጫ ለተጠሪ ማሳወቁን በፍሬ ነገር ደረጃ አረጋግጧል። ከፍ ሲል እንደተጠቀሰዉ የአሁን ተጠሪ በተሽከርካሪ ጉዲት የደረሰበት ሶስተኛ ወገን ስለአደጋዉ ለተጠሪ ያሳወቀዉ መሆኑን የሚያመለክት ማስረጃ በሥር ፍ/ቤት እስካላቀረበ ድረስ፣ ክርክሩን በማስረጃ የማስረዲት ኃላፉነቱን ተወጥቷል ለማለት ያዲግታል። ስለሆነም የአመልካች ንብረት የሆነዉ ተሽከርካሪ የ3ኛ ወገን ንብረት በሆነዉ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሰዉ የግጭት አደጋ ጉዲት ማድረሱን እና ለዘህ ተሽከርካሪ በተጠሪ ዖንድ የ3ኛ ወገን የመድን ዉል የተገባለት መሆኑን ለክፍለ ፕሉስ ያሳወቁ መሆኑን፣ በዘህ ሂደትም በተሽከርካሪዉ አደጋ ስለመድረሱ ተጠሪ እንዱያዉቅ የተደረገ መሆኑን መገንዖብ ይቻላል። የአሁን አመልካች በተቀጣሪዉ አሽከርካሪ በኩል ስለአደጋዉ መድረስና ተሽከርካሪ በተጠሪ ዖንድ የሶስተኛ ወገን የመድን ዉል የተገባለት መሆኑን ወዱያዉኑ ለክፍለ ፕሉስ ባያሳዉቀዉ እና አደጋዉ ስለመድረሱ ለተጠሪ እንዱታወቅ ባይድረግ ኖሮ፣ ይህ ተሽከርካሪ በተጠሪ ዖንድ የሶስተኛ ወገን የመድን ሽፊን ያለዉ መሆኑን ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሚሆን መገመት አያዲግትም።
በዘህ መሰረት የአመልካች ንብረት የሆነዉ ተሽከርካሪ በ3ኛ ወገን ተሽከርካሪ ላይ የግጭት አደጋ ያደረሰዉ በ16/11/2008 ዓ.ም ሲሆን፣ የአሁን አመልካች በዘህ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ በኩል ወዱያዉኑ ስለአደጋዉ ለክፍለ ፕሉስም ሆነ ለተጠሪ በማሳወቁ፣ ተጠሪ የክፍለ ፕሉስ ስለአደጋዉ ዛርዛር መግለጫ እንዱሰጠዉ ጠይቆ፣ ፕሉስ ደግሞ በ20/11/2008 ዓ.ም በተጻፈ የአደጋ ዛርዛር መግለጫ ለተጠሪ ማሳወቁን ከሥር መዛገብ መገንዖብ ይቻላል። ይህ ማለት ተጠሪ የአመልካች ንብረት የሆነዉ ተሽከርካሪ አደጋዉ እንደደረሰ በአራት ቀን ዉስጥ እንዱያዉቅና ስለአደጋዉ ዛርዛር መግለጫ ያገኘ መሆኑን ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ በመድን ዉለም ሆነ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ ሕግ መሰረት ስለአደጋዉ መድረስ ወዱያዉኑ ወይም ቢዖጋይ በአስር ቀን ዉስጥ ለተጠሪ እንዱታወቅ መደረግ አለበት የሚለዉ ጉዲይ መሟላቱን የሚያስገነዛብ ነዉ። የአሁን ተጠሪ አደጋዉ እንደደረሰ በአራት ቀን ዉስጥ ስለአደጋዉ ዛርዛር መግለጫ እስካወቀ ድረስ፣ በመድን ዉለም ሆነ በሕጉ የተቀመጠዉ የቅድመ ሁኔታ መሟላቱን ያሳያል። ተጠሪ ስለአደጋዉ መድረስ በዘህ አግባብ እንዱያዉቅ የተደረገና አደጋዉ መድረሱን አዉቆ ተገቢዉን ሁለ ለመፈጸም ወይም እርምጃ ለመዉሰድ የሚያችለዉ እስከሆነ ድረስ፣ በመድን ዉለም ሆነ በሕጉ የተቀመጠዉ ቅድመ ሁኔታ አልተሟላም በማለት የሚያቀርበዉ ክርክር የህግ ድጋፍ የለዉም።
ስለሆነም የአሁን ተጠሪ አደጋዉ እንደደረሰ በአራት ቀን ዉስጥ ስለአደጋዉ ዛርዛር መግለጫ እንዱያዉቅ የተደረገ እስከሆነ ድረስ፣ አመልካች በመድን ዉለም ሆነ በሕጉ የተመለከተዉን አደጋ የማሳወቅ ግዳታዉን አልተወጣም በማለት ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች በመድን ዉለም ሆነ በሕግ የተጣለበትን መድን ሰጭ ለሆነዉ ለተጠሪ አደጋን የማሳወቅ ግዳታዉን አልተወጣም በማለት ተጠሪዉ ለ3ኛ ወገን የከፈለዉን ገንዖብ መልሶ እንዱከፍለዉ የሰጡት ዉሳኔ በሕጉ አግባብ ሁኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን ተጠሪ የአመልካች ንብረት የሆነዉ ተሽከርካሪ በሶስተኛ ወገን ተሽከርካሪ ላይ የግጭት አደጋ ያደረሰ መሆኑን አደጋዉ እንደደረሰ በአራት ቀን ዉስጥ እንዱያዉቅ መደረጉ በማስረጃ ተረጋግጦ እና በመድን ዉለም ሆነ በሕጉ የተመለከተዉ አደጋን የማሳወቅ ቅድመ ሁኔታ ተሟልቶ እያለ፣ አመልካች አደጋን የማሳወቅ ግዳታዉን አልተወጣም በማለት ተጠሪዉ ለሶስተኛ ወገን የከፈለዉን ገንዖብ መልሶ እንዱከፍለዉ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.258901 በ19/7/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.214848 በ5/11/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 [1] መሰረት በአብላጫ ድምጽ ተሽሯል።
የአመልካች ንብረት ለሆነዉ ተሽከርካሪ በተገባለት የመድን ዉልም ሆነ በሕጉ የተመለከተዉን ለመድን ሰጭዉ አደጋን የማሰወቅ ቅድመ ሁኔታ በአግባቡ ተሟልቶ እያለ የአሁን ተጠሪ ለ3ኛ ወገን የከፈለዉን ካሳ አመልካች መልሶ ለተጠሪዉ የሚከፍልበት አግባብ የለም ብለናል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
የመ.ቁ.258901 የሆነዉ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችልት ይመለስ።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.