አንድ ባለይዜታ አንድን ይዜታ በስጦታ አግኝቶ ለረጅም ዓመታት ይዜ በሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ዔዉቅና ሲጠቀምበት የነበረ መሆኑ ከተረጋገጠ በክልል ከተሞች ዉስጥ የተሟላ ሰነድ የላላቸዉና ሰነድ አልባ ይዜታዎችን በማጣራት የይዜታ ማረጋገጫ ሰነድ/ካርታ ለመስጠት ተሻሽል በወጣ መመሪያ ቁጥር 8/2007 መሰረት የመስተናገድ መብት ያለው ስለመሆኑ የይዜታ ማረጋገጫ ሰነድ/ካርታ ለመስጠት ተሻሽል የወጣ መመሪያ ቁጥር 8/2007 አንቀጽ 4(5)
No summary available.
ቀን - 28/09/2011 ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- ወ/ሮ ብርሃን ማለድ ተጠሪ፡- የባህር ዲር ከተማ ጣና ክ/ከተማ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ ፍርድ መነሻ የሆነዉ ጉዲይ የተጀመረዉ በባሕር ዲር ከተማ አስተዲደር ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የአመልካች ክስ ይዖትም በአጭሩ፡- በባሕር ዲር ከተማ ጣና ክ/ከተማ ክልል ዉስጥ በ1988 ዓ.ም በስጦታ ተሰጥቶኝ በእጄ አድርጌ ግብር እየከፈልኩ ለረጅም ዓመታት ብልኬት የማምረት ስራ እየሰራሁና ትንሽ መኖሪያ ቤትም በመስራት ስጠቀምበት የቆየሁ ሲሆን በነባር ይዜታነትም ቀበላዉ አረጋግጦ ጊዚያዊ የይዜታ ማረጋገጫ ተሰጥቶኛል፤ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ግብር እየከፈልኩ የንግድ ፍቃድ አዉጥቼ የብልኬት ስራ ስሰራ የቤ/ቁጥር D-247 በሚል ተሰጥቶኝ የዉሃ እና የቴላ አገልግልት ክፍያዎችን እየከፈልኩ እና ቦታዉን ህጋዊ አድርጌ በመያዚ በመመሪያ ቁጥር 8/2007 መሰረት የይዜታ ማረጋገጫ ከተሰጠኝ በኋላ ተከሳሽ ያለበቂ እና ህጋዊ ምክንያት በቀን 22/10/2009 ዓ.ም በፃፋዉ ደብዲቤ ይዜታዬን ማምከኑ መብቴን የሚጥስና ይዜታዬንም የሚያሳጣኝ በመሆኑ ማረጋገጫዉ ሉመክን አይገባም እንዱባልልኝ እንዱሁም ቋሚ የይዜታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰርቶ እንዱሰጠኝ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ።
ተጠሪ የመጀመሪያ መቃወሚያዎች ናቸዉ የሚላቸዉን ክርክሮች በማስቀደም ለክሱ በሰጠዉ መልስ፡- ከሳሽ መመሪያ ቁጥር 8/2007 ሰነድ አልባና የተሟላ ሰነድ የላላቸዉን ይዜታዎች በተመለከተ የወጣውን መስፈርት ባለማሟላታቸው አጣሪ ኮሚቴዉ ባለይዜታ አይደለም በማለት ያቀረበዉን የዉሳኔ ሃሳብ በመቃወም እስከ ከንቲባ ጽ/ቤት ቀርቦ ታይቶ ባለይዜታ አለመሆናቸዉ በመረጋገጡ የይዜታ ማረጋገጫ አልተሰጣቸዉም፤ አመራሩ አዱስ በመሆኑ በ2009 ዓ.ም የይዜታ ማረጋገጫ ለከሳሽ የሰጣቸዉ ቢሆንም በድጋሚ ማጣራት ተደርጎ ያላግባብ መሆኑ ተረጋግጦ ሰኔ 12 ቀን 2009 ዓ.ም እንዱመክን መደረጉን እና ይህም ተገቢ መሆኑን፤ ከሳሽ ያቀረቡት የስጦታ ዉልም ህጋዊ ባለመሆኑ በማስረጃነት የሚያገለግል አለመሆኑን፤ ባለ ይዜታዎቹ አቶ መለስ ካሴ እና ልጆቹ ትክና ካሳ ተከፍልአቸዉ ቦታዉን እንዱለቁ መደረጉን፤ ቦታዉ የመንግስትና የህዛብ በመሆኑ በቦታዉ ላይ ተሰራ የተባለዉ ቤትም ህገ ወጥ መሆኑን ጠቅሶ የቀረበበት ክስ ዉድቅ እንዱሆንለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዘህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ከሳሽ ቦታዉ በስጦታ የተሰጣቸዉ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አለማቅረባቸዉን እና ላልች ከሳሽ ያቀረቧቸዉ ሰነድችም ሰነድ የላላቸዉና ሰነድ አልባ ይዜታዎችን በማጣራት ህጋዊ የይዜታ ማረጋገጫ የሚሰጥበትን ሁኔታ በተመለከተ በመመሪያ ቁጥር 8/2007 አንቀጽ 4(5) ላይ የተመለከተዉን መስፈርት የሚያሟላ ማስረጃ ከሳሽ አለማቅረባቸዉ በመጥቀስ የቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለባህር ዲር ከተማ ነክ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡት ይግባኝ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ሰበር ሰሚዉ ችልትም መዛገቡን አስቀርቦ የግራ ቀኝ ክርክር ከሰማ በኋላ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም ይህኑን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካች በቀን 23/05/2011 ዓ.ም ተጽፍ በጠበቃቸዉ አማካይነት በቀረበ አምስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር በክልለ በየደረጃዉ ባለት ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚለባቸዉን ምክንያቶች በመዖርዖር ታርሞ ይወሰንላቸዉ ዖንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። አቤቱታዉ ተመርምሮም ቀደም ሲል በመ/ቁጥር 2847 ላይ የተሰጠዉ ዉሳኔ አሁን በተያዖዉ ጉዲይ ላይ ያለዉን ተፈፃሚነት እንዱሁም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከመመሪያ ቁጥር 8/2007 አንፃር አገናዛቦ ለመመርመር ሲባል ያስቀርባል በመባለም ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዖት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን፣ ይህ ችልትም መዛገቡን ለማስቀረብ የተያዖዉን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መዛገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
እንደመረመረዉም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቦታ ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ አመልካች ይዖዉ የሚገኙ ስለመሆኑ ተጠሪ ክድ አልተከራከረም። አመልካች በቦታዉ ላይ በሰሩት ቤት ቁጥር ላይ የንግድ ፍቃድ በማዉጣት የብልከት ማምረቻ ስራ ሲሰሩበት እንደነበረ ጠቅሰዉ አመልካች ያቀረቡት ክርክርም በተጠሪ አልተካደም። አመልካች በይዜታዉ ላይ የሰሩት ቤት ህገ ወጥ መሆኑን ጠቅሶ የሰጠዉ ማስጠንቀቂያ ሁከት ነዉ በሚል አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረቡትን የሁከት ይወገድልኝ ክስ መሰረት በማድረግ የባህር ዲር ከተማ አስተዲደር ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 2847 ላይ በቀን 01/03/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች በቦታዉ ላይ ግንባታ ያከናወኑት አግባብ ባለዉ የከተማ አስተዲደር አካል የግንባታ ፍቃድ ተሰጥቶአቸዉ መሆኑን አረጋግጦ ሁከት እንዱወገድ የሚል ዉሳኔ መስጠቱን ከመዛገቡ መረዲት ተችሎል። ፍርድ ቤቱ በዘህ መልኩ ለሰጠዉ ዉሳኔ መነሻዉ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሆኖ ለተሰጠዉ ዉሳኔ በምክንያትነት የተጠቀሰዉ አመልካች ቤቱን የገነቡት ስልጣን ያለዉ አካል በሰጣቸዉ የግንባታ ፍቃድ መሰረት መሆኑ እንጂ ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ ቦታ ላይ ህጋዊ ባለይዜታ መሆናቸዉ ተረጋግጦ ባለመሆኑ ለያዛነዉ ጉዲይ መነሻ የሆነዉ ክስ እንዲይቀርብ የሚከለክለዉ (resjudicata) ባይሆንም፣ ዉሳኔዉ አመልካች በቦታዉ ላይ ቤት የሰሩት በተጠሪ ዔዉቅና እና ፍቃድ ስለመሆኑ አረጋጋጭ ነዉ። ከዘህም አልፍ አመልካች ቦታዉን የያዘት በ1988 ዓ.ም አጎታቸዉ አቶ መለስ ካሴ ሰጥቷቸዉ ስለመሆኑ በሰዉ እና በሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ስጦታዉን አድርገዋል የተባለት ሰዉም በምስክርነት ቀርበዉ ቦታዉን ለአመልካች እንደሰጡ ማስረዲታቸዉን የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። ቦታዉን ሰጥተዋል የተባለት አቶ መለስ ካሴ ቦታዉን ለመንግስት አስረክበዉ ትክ ቦታ ለእርሳቸዉ እና ለቤተሰባቸዉ ተሰጥቷል የሚል ክርክር ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት አንስቶ የተከራከረ ቢሆንም ይህን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አላቀረበም።
ይህ ሁለ የሚያሳየዉ አመልካች ይዜታዉ ወደ ከተማ ከመጠቃለለ በፉት ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ ይዜታዉን በእጃቸዉ አድርጎ ሲጠቀሙበት እንደነበረ እና ቦታዉ በከተማ ስር ከገባ በኋላም ለረጅም ዓመታት በቤትና ቦታዉ ላይ የንግድ ፍቃድ በማዉጣት እና በከተማዉ ጉዲዩ ከሚመለከታቸዉ አካላት ዔዉቅና ተሰጥቶ የግንባታ ፍቃድ ሁለ በማዉጣት ቤት ሰርተዉ ሲጠቀሙበት የነበሩ መሆኑን ነዉ።
የሚመለከተዉ አካል በቦታዉ ላይ ጊዚያዊ የይዜታ ማረጋገጫ ለአመልካች ላሰጥ የቻለዉም ይህኑን እዉነታ ግምት ዉስጥ በማስገባት እንደሆነ ይታመናል። የይዜታ ማረጋገጫ የተሰጠዉ ሰዉ በይዜታ ማረጋገጫዉ ላይ በተመለከተዉ ንብረት ላይ የባለቤትነት/የባለይዜታነት መብት እንዲለዉ የሚገመት ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1195 ድንጋጌ ያስገነዛባል። ከዘህ የፍሬ ነገር ግምት ጀርባ ያለዉ መሰረተ ሃሳብም የሚመለከተዉ አካል የይዜታ ማረጋገጫ ማስረጃን ሲሰጥ በህግ የተዖረጋዉን ተገቢዉን ስርዓት ተከትል የይዜታ ማረጋገጫዉ ማስረጃ የተሰጠዉ ሰዉ በማስረጃዉ ላይ በተመለከተዉ ንብረት ላይ መብት ያለዉ መሆኑን በማረጋገጥ ነዉ ተብል ስለሚታመን ስለመሆኑ መገንዖቡ ተገቢ ነዉ።
የይዜታ ማረጋገጫዉ ማስረጃ የሰጠ አካል በህጉ አንቀጽ ማስረጃዉ የተሰጠዉ ያላግባብ መሆኑን ከተረዲ የባለለቤትነት/የይዜታ ማረጋገጫዉን የማምከን ስልጣን ያለዉ ቢሆንም፣ ማስረጃዉን ለማምከን የሚያስችል በቂ እና በህግ ተቀባይነት ያለዉ ምክንያት ሉኖረዉ እንደሚገባ በህጉ አንቀጽ 1196 ላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ መንፈስ የምንገነዖበዉ ነዉ።
የተያዖዉን ጉዲይ በተመለከተ ተጠሪ ለአመልካች ተሰጥቶ የነበረዉን ጊዚያዊ የይዜታ ማረጋገጫ ማምከን የቻለዉ አመልካች መመሪያ ቁጥር 8/2007 ሰነድ አልባና የተሟላ ሰነድ የላላቸዉን ይዜታዎች በተመለከተ የወጣዉን መስፈርት ባለማሟላታቸዉ እና የይዜታ ማረጋገጫዉን የሰጠዉ አመራርም አዱስ መሆናቸዉን ሲሆን፣ የስር የክልለ ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ዉድቅ በማድረግ ለሰጡት ዉሳኔ መሰረት ያደረጉን አመልካች ቦታዉ በስጦታ የተሰጣቸዉ መሆኑን እና በህግ አግባብ የያዘ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አለመቅረባቸዉን እና ይዜታዉ ህጋዊ እንዱሆን በመመሪያ ቁጥር 8/2007 አንቀጽ 4(5) ላይ የተመለከተዉን መስፈርት አመልካች አለመሟላታቸዉን ስለመሆኑ ተመልክተናል።
መመሪያ ቁጥር 8/2007 ዓ.ም በክልለ ከተሞች ዉስጥ የተሟላ ሰነድ የላላቸዉና ሰነድ አልባ ይዜታዎችን በማጣራት የይዜታ ማረጋገጫ ሰነድ/ካርታ ለመስጠት ተሻሽል የወጣ ነዉ። ይህ መመሪያ በክፍል ሁለት የተሟላ ሰነድ የላላቸዉና የሰነድ አልባ ይዜታዎች መለያ መስፈርቶችን ይደነግጋል።
ለዘህ ክርክር መነሻ የሆነዉ ይዜታ የገጠር የእርሻ መሬት የነበረ በመሆኑ ተፈፃሚነት ያለዉ ድንጋጌ በአንቀጽ 4(5) ላይ የተመለከተዉ ነዉ። ይህ ድንጋጌ ‛በአርሶ አደር የእርሻ መሬት ይዜታ ላይ ያልተሰራ ቤት ሆኖ ነገር ግን ከተማዉ ወይም ቀበላዉ በምሪት የተያዘ ህጋዊ ይዜታዎች ስለመሆናቸዉ ማረጋገጫ የሚሰጣቸዉ ሆነዉ ለሦስተኛ ወገን የተላለፈና የባህላዊ ግዥ ወይም ስጦታ ዉል ማስረጃ ማቅረብ የሚችለ እና ቤት የተሰራባቸዉ ይዜታዎች“ በማለት ይደነግጋል። አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ይዜታ ያገኙት ከመንግስት በምሪት ሳይሆን በስጦታ መሆኑን በመግለጽ ይከራከራለ። መሬቱን በስጦታ ከአጎታቸዉ ስለማግኘታቸዉ ባቀረቡት ማስረጃ አረጋግጠዋል። የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ይህን ስጦታ ዉድቅ ለማድረግ በምክንያትነት ከጠቀሰዉ ዉስጥ አንደ የስጦታ ዉለ በሚመለከተዉ የአስተዲደር አካል ዖንድ አለመመዛገቡን ነዉ። ይሁንና ከፍ ሲል የተመለከተዉ ድንጋጌ ‛የባህላዊ ግዥ ወይም ስጦታ“ በሚል ሲደነግግ ይዜታዉ የእርሻ መሬት ሲሆን አንድ ሰዉ በስጦታ የሰነድ አልባ ይዜታ መብት ያለዉ መሆኑን ለማስረዲት የገጠር መሬትን በስጦታ ለማስተላለፍ በሚመለከተዉ ህግ የተመለከተዉን ጥብቅ ድንጋጌ መከተል አስፈላጊ አለመሆኑን ለማስገንዖብ እንደሆነ መገንዖቡ ተገቢ ነዉ። ይህ የሆነበት ምክንያትም አንድ ሰዉ ይዜታዉ በገጠር ቀበላ ስር በነበረበት ወቅት ለረጅም ጊዚ ይዜ ሲጠቀምበት የነበረዉን መሬት ቦታዉ በከተማ ስር በመግባቱ ምክንያት እንዲይፈናቀል ጥበቃ ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ ይታመናል። ከመመሪያዉ አፈፃፀም ጋር በተያያዖ የሚሰጥ ትርጉምም ይህኑን ግምት ዉስጥ ያስገባ ላሆን ይገባል የሚል እምነት አለን።
በአጠቃላይ አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ይዜታ በስጦታ አግኝተዉ ለረጅም ዓመታት ይዖዉ በሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ዔዉቅና ሲጠቀሙበት የነበረዉ ይዜታ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ በመመሪያ ቁጥር 8/2007 መሰረትም ተጠቃሚ ሉሆኑ አይችለም በሚል በከተማዉ የከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በአብላጫ ድምፅ የፀናው ዉሳኔ በግራ ቀኝ ክርክር የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር እንዱሁም የመመሪያ ቁጥር 8/2007 አንቀጽ 4(5) ትክክለኛ አፈፃፀም ያላገናዖበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለን ተከታዩን ወስነናል።
የብህር ዲር ከተማ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 2945 በቀን 17/08/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ፣ የከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት 1041/2010 ዓ.ም በቀን 15/09/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዔዙዛ፤ እንዱሁም የአማ/ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 12/03/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤትና ይዜታ በተመለከተ ለአመልካች ተሰጥቶ የነበረው ጊዚያዊ የይዜታ ማረጋገጫ ማስረጃ ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም ከተጠሪ በተፃፈ ደብዲቤ መምከኑ በአግባቡ አይደለም ብለናል።
አመልካች ለክርክሩ መነሻ በሆነው ቤትና ይዜታ ላይ በክልለ ከተሞች ውስጥ የተሟላ ሰነድ የላላቸውና ሰነድ አልባ ይዜታዎችን በማጣራት የይዜታ ማረጋገጫ ሰነድ/ካርታ ለመስጠት ተሻሽል በወጣ መመሪያ ቁጥር 8/2007 መሰረት የመስተናገድ መብት አላቸው ብለናል።
ይህ ችልት በቀን 11/07/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው የእግድ ትዔዙዛ ተነስቷል።
በዘህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.