የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት ከታወጀ በኋላ ባለው የመሬት ስሪት መሰረት የፍ/ብ/ህ/ቁ/1065 መሬትን በሚመለከት ተፈፃሚ የሚሆነው ቀድሞ በስጦታ የተወሰደን ይዜታ በዓይነት ወደ ውርስ ይዜታ እንዱመለስ በማድረግ ሳይሆን የይዜታውን መጠን በልኬት በመለየት መጠኑ ከአጠቃላይ የውርስ ይዜታው ውስጥ ለስጦታ ተቀባዩ ከሚደርሰው ድርሻ ላይ እንዱቀነስ እነ አቶ አሰፊ ሰቦቃ እና እነ አቶ ከበደ ሰቦቃ ህዲር 30/2012ዓ.ም 194 ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 40፤ የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1065፤ገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጁ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 9(2) እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀፅ 10(10 40. ለሕዛብ ጥቅም ሲባል የእርሻ መሬቱ የተወሰደበት ሰው ካሳም ሆነ ትክ መሬት ባለማግኘቱ በአስተዲደር አካል መፍትሄ ሳይሰጠው ለፍርድ ቤት አቤቱታውን ሲያቀርብ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አከራክሮ ዲኝነት ላሰጥበት የሚገባዉ ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 37፤ከአዋጅ ቁ/455/97 አንቀጽ 3/1/
No summary available.
ሰኔ 14 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሀይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ ተሾመ ድለንሴ ተጠሪዎች፡- 1.የቀርሳ ማሉማ ወረዲ ገጠር መ/ ባለስልጣን ጽ/ቤት 2. የቀርሳ ወርኮ ቀበላ ገ/ማ//ጽ/ቤት መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የገጠር መሬት ይዜታ ለህዛብ መንገድ ስራ በሚል ከአመልካች ላይ በመወሰደ ካሳና ትክ መሬት እንዱሰጠዉ አመልካች ያቀረበዉ የዲኝነት ጥያቄ የስር ወረዲ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁ/455/97 መሰረት የሚታይ እንጂ የፍርድ ቤት ስልጣን አይደለም በማለት የሰጠዉን ብይን የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የኦሮሚያ ክልል ሰበር ሰሚ ችልት በማጽናቱ ዉሳኔዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በሚል እንዱታረም አቤቱታ የቀረበበት ነዉ።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ለመንገድ በተወሰደዉ መሬት ምትክ ቦታ ወይም ካሳ ስላልተሰጠኝ በፍ/ቤት ይወሰንልኝ የሚል ሆኖ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ስለመቋቋሙ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ አግባብነት ከአዋጅ ቁ/ 455/97 አንጻር ለመመርመር በሚል ጭብጥ ተይዜ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ተድርጓል።በ1ኛ ተጠሪ በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ በአዋጅ ቁ/455/97 አንቀጽ 11/1/መሰረት ለአስተዲደር አካል ቅሬታ ቀርቦ ዉሳኔ ሳይሰጥ ለፍርድ ቤት መቅረቡ ተገቢ አለመሆኑንና ቅሬታ ሰሚ አስተዲደራዊ አካል አልተቋቋመም ቢባል እንኳን ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዚ አልፍበታል በሚል የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱጸና የተከራከረ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ በበኩለ ከአመልካች ይዜታ ላይ 110ሜ በ12ሜ የሆነ የእርሻ መሬት ለህዛብ መንገድ የተወሰደበት መሆኑን ገልጾ ቀበላዉ የወል መሬት የላለዉ በመሆኑ ትክ መሬት ሉሰጠዉ እንዲልቻለ እንዱሁም ለዘህ ተብል የተያዖ በጀት ባለመኖሩ ካሳም እንዲልተከፈለ ገልጾ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱጸና ጠይቋል።አመልካችም አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም እንዱጣራ የተያዖውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምረናል።
የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ የእርሻ መሬት ይዜታዉ ላይ ለህዛብ መንገድ ተብል የተወሰደዉን መሬት ትክ መሬት ወይም ካሳ እንዱከፈለዉ ለአስተዲደር አካላት አቤቱታ አቅርቦ ምላሽ በማጣቱ ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱሰጠዉ ዲኝነት የጠየቀ ስለመሆኑ መዛገቡ ያስረዲል። ተጠሪዎችም የአመልካች መሬት በከፉል ለህዛብ መንገድ ስራ መዋለን አልካደም። ነገር ግን በቅድሚያ በአሥተዲደሩ በተቋቋመ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ላታይ ይገባል የሚል መቃወሚያ አቅርበዋል።የስር ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ መሰረት አድርገዉ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን በዲኝነት የማየት ስልጣን የለዉም በማለት ዉሳኔ የሰጡ ስለመሆኑ መገንዖብ ተችሎል።
በመሰረቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት እና የተፈጥሮ ሀብት የባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዛብ ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 40/3/ ላይ ተደንግጓል። የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነጻ የማግኘትና ከመሬታቸዉ ያለመፈናቀል መብታቸዉ የተከበረ ስለመሆኑና አፈጻጸሙ በዛርዛር ህግ የሚወሰን መሆኑን አንቀጽ 40/4/ ላይ ተደንግጓል።ይህንኑ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ተከትል የወጣዉ የፋዳራል የገጠር መሬት አስተዲደር አዋጅ ቁ456/97 አንቀጽ 5/3/ እንዱሁም በስራ ላይ ያለዉ የኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁ/130/99 አንቀጽ 5/1 እና 5 ድንጋጌዎች እንደሚያስገነዛቡት በገጠር መሬት የመጠቀም የይዜታ መብት የሚገኘዉ በመንግስት በሚደረግ ድልድል፣በዉርስ ወይም በስጦታ ነዉ።ስለሆነም የገጠር መሬት ላይ የይዜታ መብት አለኝ የሚል ሰዉ ከእነዘህ በአንደኛዉ አግባብ ይዜታዉን ያገኘ እንደሆነ ያለገደብ መሬቱን የመጠቀም ፤በመሬቱ ላይ ያፈራዉን ንብረት የመሸጥ፣የመለወጥና የማስተላለፍ መብት እንዲለዉ እና ይህም መብት ሉቋረጥ የሚችለዉ መሬቱ ለበለጠ የህዛብ ጥቅም ሲፈለግ ስለመሆኑና ለዘህም ካሳ እና ትክ መሬት እንደሚሰጠዉ ትክ መሬት መስጠት ካልተቻለ መልሶ ማቋቋሚያ ካሳ እንደሚከፈለዉ አዋጅ ቁ/ 130/99 አንቀጽ 6/1፣10፣11እና 12 ድንጋጌዎች ይዖት ያሥገነዛባለ፡ ሕገ-መንግሥቱን መሰረት በማድረግ የወጣው ለሕዛብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዜታ የሚለቀቅበትን እና የንብረት ካሣ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/ 1997 አንቀጽ 2/1 ‘ካሣ’ ማለት የመሬት ይዜታውን እንዱለቅ ለሚወሰንበት ባለይዜታ በመሬቱ ላይ ለሰፈረው ንብረት በዓይነት ወይም በገንዖብ ወይም በሁለቱም የሚከፈል ክፍያ ነው በማለት ይደነግጋል። የአዋጁ አንቀጽ 11/1/ ተቃራኒ ንባብ የመሬት ነክ አቤቱታ ሰሚ አሥተዲደራዊ አካል በተቋቋመባቸው ከተሞች የካሣ መጠንን አስመልክቶ አቤቱታ የሚቀርበው በከተማው አሥተዲደር ለተቋቋመ የመሬት ነክ አቤቱታ ሰሚ አሥተዲደራዊ አካል መሆኑን ነገር ግን አቤቱታ ሰሚ አካል ባልተቋቋመባቸዉ የከተማ አስተዲደርና የገጠር መሬት አስመልክቶ ቅሬታዉን ለመደበኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚችል ያስገነዛባል።
በተያዖው ጉዲይ የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ አሥተዲደሩ ለሕዛብ ጥቅም ሲባል በወሰደው የእርሻ መሬት ይዜታ ላይ ካሳ ያልተከፈለዉ ወይም ትክ ቦታ ያልተሰጠዉ መሆኑን መሰረት አድርጎ ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን ከክርክሩ መገንዖብ እንደሚቻለዉ ከጅምሩም ካሳ ወይም ትክ መሬት ያልተሰጠዉ መሆኑና ለዘህም አስተዲደራዊ መፍትሄ ፍለጋ ያቀረበዉ አቤቱታ ምላሽ ያልተሰጠዉ መሆኑን ነዉ።በመሰረቱ ከአዋጅ ቁ/455/97 አንቀጽ 3/1/ላይ እንደተደነገገዉ የገጠር መሬት ሲሆን የወረዲዉ አስተዲደር መሬቱን ከማስለቀቁ በፉት ተገቢዉ ካሳ ስለመከፈለ የማረጋገጥ ግዳታ አለበት። በዘህ ጉዲይ ግን የአመልካች የእርሻ መሬት ለመንገድ ስራ መወሰደ በተጠሪዎች የታመነ ጉዲይ ሆኖ ካሳም ሆነ ትክ መሬት ለአመልካች ስለመሰጠቱ ክርክር ያልቀረበበት ሆኖ በአስተዲደር አካልም መፍትሄ ካልተሰጠዉ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ሲቀርብ የዲኝነት ስልጣን የለዉም የሚለዉ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 37 ላይ የተመለከተውን የዚጎች ፍትሕ የማግኘት መብታቸውን የሚጻረር ነው።
በመሆኑም በስር ፍርድ ቤት ዲኝነት የጠየቀበት ጉዲይ የገጠር መሬት ይዜታ ላይ በመሆኑ በህገ መንግስትና በአዋጅ ቁ/455/97 አንቀጽ 11/1/ ድንጋጌዎች ጋር ተገናዛቦ ሲታይ መደበኛዉ ፍርድ ቤት አከራክሮ ዲኝነት ላሰጥበት የሚገባዉ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የዲኝነት ስልጣን የለኝም በሚል የሰጠዉ ብይንና ይህንኑ በማጽናት የበላይ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስሀተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል ብለናል።በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።