No summary available.
የመ/ቁ. 169030 ህዲር 30/2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡ 1.አቶ አሰፊ ሰቦቃ ጠበቃ አቶ ከበደ ቱፊ ቀርበዋል።
አቶ ታደሰ ሰቦቃ
ወ/ሮ ቀነኒ ሰቦቃ
ወ/ት ኩሜ ሰቦቃ ተጠሪዎች፡ 1.አቶ ከበደ ሰቦቃ ቀርበዋል።
አቶ ኩማ ሰቦቃ
ወ/ሮ አለሚ ሰቦቃ አልቀረቡም።
ወ/ሮ ደስታ ሰቦቃ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የገጠር እርሻ መሬት የውርስ ይገባኛል ክርክርን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁ/282886 ላይ ጥቅምት 19/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔን በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በሚል ለማስለወጥ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ እንዱህ ነው። የአሁን 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ከሳሽ፤ 1ኛ እና 4ኛ አመልካቾች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን በደቡብ ምዔራብ ሸዋ ዜን ዲዎ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዛገብ ላይ በክርክር ላይ እያለ ጉዲዩ በእርቅ ስምምነት ጨርሰው ስምምነቱን ለፍርድ ቤቱ አቅርበው በስምምነቱ መሰረት ውሳኔ ተሰጥቶ መዛገቡ ይዖጋል። ከዘህ በኋላ የአሁን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በእርቅ በተዖጋው መዛገብ ላይ በመቃወም በአመልካችነት ቀርበው መዛገቡ ተከፍቶ ጉዲዩ በክርክር ላይ እያለ የአሁን 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች በጣልቃ ገብነት በመቅረባቸው ፍርድ ቤቱ የክርክሩ አካል አድርጓቸው የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ በመስማት እንዱሁም ክርክር ስላልተነሳበት ይዜታ ጉዲይ ከሚመለከተው አስተዲደር ክፍል ተጣርቶ እንዱቀርብለት በማድረግ ውሳኔ ሰጥቷል።
በውሳኔውም ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት የውርስ ይዜታ በአጠቃላይ 16(አስራ ስድስት) ቀርጥ መሆኑን፤የአሁን አመልካቾች ወላጆቻቸው በህይወት እያለ ለእያንዲንዲቸው ሁለት ቀርጥ መሬት ተሰጥቷቸው ይዖው እየተጠቀሙበት ስለመሆኑ እንዱሁም የአሁን 3ኛ እና 4ኛ አመልካቾች ክርክር በቀረበበት ይዜታ ላይ ወላጆቻቸው እስከሞቱበት ድረስ በጥገኝነት ሲኖሩ የነበረ ለመሆኑ ከወረዲው መሬት አስተዲደር የተገለፀለት መሆኑን፤ የግራ ቀኙ የሰው ምስክሮችም የአሁን 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ወላጆቻቸው በህይወት እያለ ለእያንዲንዲቸው ሁለት ቀርጥ መሬት ተሰጥቷቸው ይዜታውን በእጃቸው አድርገው እየተጠቀሙበት ያለ መሆኑን፤ 3ኛ እና 4ኛ አመልካቾች በወረዲው መሬት አስተዲደር በተገለፀው አኳኋን በይዜታው ላይ ከወላጆቻቸው ጋር በጥገኝነት ይኖሩ የነበረ ለመሆኑ ያረጋገጡ መሆኑን በመጥቀስ 3ኛ እና 4ኛ አመልካቾች በይዜታው ላይ ጥገኛ በመሆናቸው፤ 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ደግሞ ቀድሞ በወላጆቻቸው በተሰጣቸው ሁለት ቀርጥ መሬት ላይ የቀዲሚነት መብት ያላቸው መሆኑን በምክንያትነት በመጥቀስ 3ኛ እና 4ኛ አመልካቾች በክልለ ገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 2(16) እና 5(5) እንዱሁም ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀፅ 3(13) መሰረት እያንዲንዲቸው አንድ ሄክታር (አራት ቀርጥ) እንዱወስደ፤ 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ቀድሞ ለእያንዲንዲቸው የተሰጣቸው ሁለት ቀርጥ መሬት ከአጠቃላይ የውርስ ይዜታው ውስጥ ከወጣ በኋላ ቀሪውን አራት ቀርጥ ለስምንቱም ወራሾች የሚከፊፈል ቢሆን በክልለ የገጠር መሬት አዋጅ መሰረት የመሬት መበጣጠስን የሚያስከትል በመሆኑ ግራ ቀኙ በጋራ ሉጠቀሙበት ይግባል ብሎል።
የአሁን ተጠሪዎች በዘሁ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለደቡብ ምዔራብ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የይግባኝ አቤቱታውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዝል።
በዘሁ ውሳኔ ላይ የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የክልለ ሰበር ችልት በበኩለ የግራ ቀኙን የሰበር ክርክር ከሰማ በኋላ ከላይ በተጠቀሰው የመዛገብ ቁጥር እና ቀን በዋለው ችልት ለአሁን 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ተሰጥቷል የተባለውን ስጦታ በተመለከተ በክልለ ገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ህግ መሰረት የሚፀና የስጦታ ውል ባይኖርም ከውርስ ሃብት ስጦታ ከተቀበለ በኋላ ከቀሪ የውርስ ሃብት ለመካፈል የጠየቁ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1066 መሰረት ስጦታውን ወደ ውርስ ሃብት ሉመልሱ ይገባል፤ 3ኛ እና 4ኛ አመልካቾችም የቅድሚያ መብት ያላችው መሆኑን ቢረጋገጥም በቀዲሚነት መብታቸው ሉደርሳቸው የሚገባው የድርሻ መጠን እንደውርስ ሃብቱ ስፊት እና ወራሾች ብዙት የሚወሰን እንጂ እያንዲንዲቸው አንድ ሄክታር እንዱያገኙ የክልለ ገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ደንብ የማያስገድድ መሆኑን በመጥቀስ እያንዲንዲቸው አንድ ቀርጥ መሬት በቀዲሚነት ሉደርሳቸው ይገባል፤የተቀረውን 14 ቀርጥ መሬት ስምንቱም ወራሾች እኩል ሉካፈለ ይገባል በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማሻሻል ወስኗል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካቾች ጥር 08/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ ሰበር ችልት ውሳኔ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ዖርዛረው በዘህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። የቅሬታው ፍሬ ቃልም በእርቅ ባለቀ እና በተፈፀመ ጉዲይ ላይ የስር ፍርድ ቤቶች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 እና 41 ቀላቅለው መወሰናቸው ከሥነ ሥርዓት ውጭ ነው፤ተጠሪዎች የራሳቸው የእርሻ መሬት ያላቸው ለመሆኑ እና በአውራሾቻችን መሬት ላይ በጥገኝነት የምንኖረው አመልካቾች ለመሆናችን በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጦ እያለ ይዜታውን እኩል እንድንካፈል መወሰኑ ከክልለ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 9 እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀፅ 10 ድንጋጌ ውጭ ከመሆኑም በላይ ይኸው ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁ/109776 ላይ የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም የተላለፈ በመሆኑ ውሳኔው ተሽሮ በይዜታው ላይ የቅድሚያ መብት አላችሁ ተብለን ለእያዲንዲችን አንድ ሄክታር መሬት ሉወሰንልን ይገባል የሚል ነው።
የቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በክልለ ሰበር ችልት በአሁን ተጠሪዎች የቀረበው ቅሬታ የአሁን አመልካቾች የውርስ ይዜታው ላይ ቀድሞ የተሰጣቸው መሬት እያላቸው በድጋሚ ከውርሱ ሉካፈለ አይገባም የሚል ሆኖ እያለ የክልለ ሰበር ችልት ከዘህ ጭብጥ ውጭ በመውጣት ስጦታውን አፍርሶ ሁለም ወራሾች እኩል ይካፈለ በማለት የወሰነበት አግባብ ለዘህ ሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ በመታዖዘ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
ተጠሪዎች መጋቢት 20/2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካቾች በወረዲው ፍርድ ቤት አቅርበዉ የነበረው ክርክር በእርቅ ስለማለቁ እንጂ በእርቁ መሰረት ለመፈፀሙ የተረጋገጠ ነገር ባለመኖሩ በጉዲዩ ላይ በመቃወም አመልካችነት ቀርበን መስተናገዲችን በአግባቡ ነው፤አመልካቾች ሂደቱ ከሥነ ሥርዓት ውጭ ነው ቢለም በምን አግባብ ከሥነ ሥርዓት ውጭ እንደሆነ ለይተው የገለፁት ነገር የለም በማለት በተቀረው የክልለ ሰበር ችልት በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠን ፍሬ ነገር መሰረት አድርጎ የወሰነ በመሆኑ የሚነቀፍበት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ሞግተዋል። አመልካቾችም በመልስ መልሳቸው የሰበር ቅሬታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም በማስቀረቢያው ነጥብ ሳይወሰን አጠቃላይ የክርክሩ ይዖት መርምሯል። በዘሁ መሰረት የክልለ ሰበር ችልት የጠቀሰው የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1066 ክርክር ለተነሳበት ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለው መሆኑን አለመሆኑ በቅድሚያ ላታይ የሚገባ ነጥብ ሆኖ ተገኝቷል።
የክልለ ሰበር ችልት የአሁን 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ከውርስ ሃብቱ ቀድሞ ስጦታ የተቀበለ ቢሆንም ከተቀረው ውርስ ለመካፈል የጠየቁ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ/1066 መሰረት ቀድሞ በስጦታ የተቀበለትን ይዜታ ወደ ውርስ መልስው ከላልች ወራሾች ጋር ሉካፈለ ይገባል በማለት ወስኗል።
በእርግጥ ከሟች ወደታች የሚቆጠሩ የጋራ ወራሾች ውስጥ መመለስ የለብህም ተብል ቀድሞ ከሟቹ ያገኘውን ችሮታ/ስጦታ/ ካልሆነ በቀር ስጦታ ተቀባዩ ውርሱን የሚቀበል ከሆነ ተቀብልት የነበረውን ንብረት ዋጋ ከውርሱ ውስጥ መልሶ ማግባት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1065 ይደነግጋል።
የዘህ ድንጋጌ መሰረታዊ ዓላማ የሟች ወደታች የሚቆጠሩ ወራሾች ሟች በህይወት እያለ ከውርስ ሃብቱ ቀድሞ ስጦታ የተቀበለ ቢሆንም በሟቹ የውርስ ሃብት ላይ ከሚኖራቸው ተነፃፃሪ መብት አኳያ ወራሾችን በተቻለ መጠን እኩል ማድረግ ስለመሆኑ ከድንጋጌው ይዖት እና መንፈስ መረዲት ይቻላል።
መሰረታዊ ዓላማው ይህ ቢሆንም ሉስተዋል የሚገባው ነጥብ ውርሱን የተቀበለው ወራሽ እንዱመልስ የሚገደደው በስጦታ የተቀበለውን ንብረት በዓይነት ሳይሆን የንብረቱን ግምት ነው። የንብረቱን ግምት መመለስ ሲባልም ወራሹ ቀድሞ በስጦታ የተቀበለው ንብረት ተገምቶ በውርስ ሀብት ክፍፍል ከተቀረው ንብረት ጋር ተደምሮ ወራሾቹ እኩል ድርሻ እንዱኖራቸው ይደረጋል ለማለት እንጅ ወራሹ የንብረቱን ግምት ይከፍላል ማለት እንዲልሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁ/1066 እስክ 1074 ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዖት መገንዖብ ይቻላል። ቀድሞ ከሟች ስጦታ የተቀበለ ወደታች የሚቆጠር ወራሽ ከላልች ስጦታ ካልተቀበለ ወራሾች የሚለየው አብይ ጉዲይ ስጦታ ተቀባዩ ከውርስ ንብረቱ ውስጥ በዓይነት የሚደርሰውን ቀድሞ የሚያውቅ ሲሆን ላልች ወራሾች ግን በንፅፅር የሚደርሳቸውን ድርሻ መጠን እንጂ በዓይነት የሚደርሳቸውን ንብረት የማያውቁ መሆኑ ነው። እናም በዘህ ድንጋጌ መሰረት ከውርስ ንብረት ስጦታ የተቀበለ ወራሽ የንብረቱ ዋጋ ወደ ውርሱ ለመመለስ ንብረቱ ሉገመት የሚችል ላሆን ይገባል ማለት ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት የውርስ ሀብት የገጠር እርሻ መሬት ሲሆን የአሁን 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ቀድመው በስጦታ ወስደዋል የተባለትም ይህንኑ የገጠር መሬት ይዜታን ነው።
እነዘህ አመልካቾች የተቀረውን የአውራሾቻቸውን የይዜታ ውርስ ለመቀበል ከፈለጉ በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1065 መሰረት ወደ ውርሱ ሉመልሱ የሚገደደት በስጦታ የተቀበለትን ይዜታ በዓይነት ሳይሆን የይዜታውን ግምት ዋጋን ነው። ሆኖም በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 40(3) የገጠርም ሆነ ከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሃብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዛብ ብቻ መሆኑን እና መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሓሮች፣ብሓረሰቦችና ሕዛቦች የጋራ ንብረት መሆኑ የተደነገገ በመሆኑ በዋጋ ሉገመት የሚችል አይደለም።
ከዘህ አኳያ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት ከታወጀ በኋላ ባለው የመሬት ስሪት መሰረት የፍ/ብ/ህ/ቁ/1065 እና ተከታዮቹ መሬትን በሚመለከት ተፈፃሚነት የለውም ማለት ይቻላል። ሆኖም ህገ መንግስቱ ከመታወጁ በፉት የነበሩት የሀገሪቱ ህጎች በህግ አግባብ ተፈፃሚነታቸው እስካልተሻረ ድረስ ከህገ መንግስቱ ጋር በተጣጣመ መልኩ ስራ ላይ ሉውለ በሚችለበት አኳኋን ሉተረጎም ይገባል። በዘሁ አግባብ መሬትን በተመለከተ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1065 ድንጋጌ ተፈፃሚ ላሆን የሚችለው ቀድሞ ከሟች ስጦታ የተቀበለ ወደታች የሚቆጠር ወራሽ ውርሱን ለመቀበል ፍቃደኛ ከሆነ ቀድሞ የተቀበለው የመሬት ይዜታ መጠን በአካባቢው የመሬት ልኬት ልማድ መሰረት ተለክቶ ከተቀረው የውርስ ይዜታ ላይ ከሚደርሰው ድርሻ ጋር እንዱጣጣም በማድረግ በሚል ሲተረጎም ነው። በዘህ ስላት መሰረት ወራሹ ቀድሞ በስጦታ የተቀበለው ይዜታ ከአጠቃላይ የውርስ ይዜታው ከሚደርሰው ድርሻ መጠን በታች ከሆነ ከተቀረው የውርስ ይዜታ ላይ የሚቀረውን መጠን ያክል እንዱካፈል፤ ስጦታው ከድርሻው በላይ ከሆነ ደግሞ ቀድሞ የተቀበለውን ስጦታ ብቻ ይዜ እንዱቆይ ይደረጋል ማለት ነው።
ጉዲዩ በዘህ መልኩ ሉቃኝ ሲገባ የክልለ ሰበር ችልት 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ቀድመው በስጦታ የተቀበለትን የእርሻ መሬት ወደ ውርሱ መልሰው ከላልች ወራሾች ጋር እንዱካፈለ መወሰኑ ለውሳኔው መሰረት ካደረገውን የፍ/ብ/ህ/ቁር 1065 ድንጋጌ መንፈስ ውጭ ከመሆኑም በላይ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስትን የመሬት ስሪት ባህሪን ያላገናዖበ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ከመሬት ጋር በተያያዖ የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1065 ድንጋጌ ተፈፃሚነት በይዜታ መጠን ልኬት ማቻቻል ነው ከተባለ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት የውርስ ይዜታ ክፍፍል በምን መልኩ ሉመራ ይገባል የሚለው ቀጥል ላታይ የሚገባው ነጥብ ነው።ይህንኑ ነጥብ በአግባቡ ለመፍታት በስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጡትን መነሻ ማድረግ ያስፈልጋል። በዘሁ መሰረት ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ በተመለከተው የወረዲው ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር በሰው እና በሰነድ ማስረጃዎች በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት የውርስ ይዜታ በጠቅላላው 16 ቀርጥ ሲሆን ወራሾች ደግሞ 8 መሆናቸውን፤የአሁን 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች የግራ ቀኙ ወላጆች በህይወት እያለ ለእያንዲንዲቸው ሁለት ቀርጥ መሬት የሰጧቸው መሆኑን፤ 3ኛ እና 4ኛ አመልካቾች ክርክር በተነሳበት ይዜታ ላይ በጥገኝነት ሲኖሩ የነበረ መሆኑን እና ላልች ወራሾች የራሳቸው ይዜታ ያላቸው መሆኑን ነው።
3ኛ እና 4ኛ አመልካቾች ክርክር በተነሳበት ይዜታ ላይ በጥገኝነት ሲኖሩ የነበረ ለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ እና በቀዲሚነት መብት ሉደርሳቸው የሚገባውም የድርሻ መጠን በክልለ ሰበር ችልት እንደተገለፀው ከውርስ ይዜታው ስፊት እና ወራሾች ብዙት አኳያ ታይቶ ሉወሰን የሚገባው በመሆኑ በክለለ ገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጁ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 9(2) እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀፅ 10(10) መሰረት እያንዲንዲቸው ሁለት ቀርጥ ሉደርሳቸው እንደሚገባቸው ታምኗል። የሚቀረው 12 ቀርጥ መሬት ለሁለም ወራሾች እኩል ሲካፈል ለ1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች የሚደርሳቸው የይዜታ መጠን ቀድሞ በስጦታ ከተቀበለት መጠን በታች በመሆኑ በስጦታ ያገኙትን የይዜታ መጠን ይዖው ሉቀጥለ ይገባል። ይኸው ከቀሪ የውርስ ይዜታ ላይ ሲነሳ የሚቀረው 8 ቀርጥ ሲሆን በተቀሩት ስድስት ወራሾች መካከል የሚካፈል ይሆናል።
በመሆኑም በዘሁ ስላት መሰረት 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች የግራ ቀኙ ወላጆች በህይወት እያለ እያንዲንዲቸው ያገኙትን ሁለት ቀርጥ መሬት ይዖው እንዱቆዩ፤ ለ3ኛ እና 4ኛ አመልካቾች ለእያንዲንዲቸው ሁለት ቀርጥ መሬት በቀዲሚነት መብት ተነስቶላቸው ቀሪውን ስምንት ቀርጥ 3ኛ እና 4ኛ አመልካቾች ከአሁን ተጠሪዎች ጋር እኩል እንዱካፈለ ማድረጉ ፍትሐዊ ሆኖ የተገኘ በመሆኑ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት ከታወጀ በኋላ ባለው የመሬት ስሪት መሰረት የፍ/ብ/ህ/ቁ/1065 መሬትን በሚመለከት ተፈፃሚ የሚሆነው ቀድሞ በስጦታ የተወሰደውን ይዜታ በዓይነት ወደ ውርስ ይዜታ እንዱመለስ በማድረግ ሳይሆን የይዜታውን መጠን በልኬት በመለየት መጠኑ ከአጠቃላይ የውርስ ይዜታው ውስጥ ለስጦታ ተቀባዩ ከሚደርሰው ድርሻ ላይ እንዱቀነስ በማድረግ ነው።
በውሳኔ ተራ ቁጥር አንድ ስር ከተገለፀው አኳያ የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁ/282886 ላይ ጥቅምት 19/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽል፡- 2.1. 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች (አቶ አሰፊ ሰቦቃ እና አቶ ታደሰ ሰቦቃ) የግራ ቀኙ ወላጆች በህይወት እያለ የሰጧቸውን እያንዲንዲቸው ሁለት ቀርጥ መሬት ይዖው እንዱጠቀሙበት፤
2.2. 3ኛ እና 4ኛ (ቀነኒ ሰቦቃ እና ኩሜ ሰቦቃ) ክርክር በተነሳበት ይዜታ ላይ ጥገኛ የቤተሰብ አባል በመሆናቸው እና የቅድሚያ መብት ያላቸው በመሆኑ እያንዲንዲቸው ከውርስ ይዜታው ሁለት ቀርጥ መሬት እንዱካፈለ፤እና 2.3. የተቀረውን ስምንት ቀርጥ መሬት 3ኛ እና 4ኛ አመልካቾች እንዱሁም የአሁን ተጠሪዎች በክልለ ገጠር መሬት ድልድል መመዖኛ መሰረት የመሬት መበጣጠስን የማያስከትል ከሆነ እኩል እንዱካፈለ፤ ካልሆነ በስምምነት በጋራ እንዱጠቀሙበት ተወስኗል።
ት ዔ ዙ ዛ
ውሳኔው መሻሻለን እንዱያውቅ የዘህ ፍርድ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ።
የዘህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.