የገጠር መሬት ባለይዜታዎች መካከል የሚደረግ ማንኛዉም የልዉዉጥ ዉል አግባብ ባለዉ የወረዲ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ በሀሰተኛ መረጃ ላይ መሰረት በማድረግ አስተዲደሩን በማሳሳት የተገኘ የይዜታ ደብተርና የተደረገው ምዛገባ ህጋዊ ዉጤት የማይኖረው እና በህግ ፉት በማይጸና ዉል የያዖ ወገን መሬቱን እንዱለቅ የሚደረግ ስለመሆኑ በአማራ ብ/ክ/መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁ/252/09 አንቀጽ 20/3/
No summary available.
መ/ቁ161676 የካቲት 25 ቀን 2011ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንደሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ መልካሙ አበራ ተጠሪ፡- ቄስ ዲምጤ በየነ መዛገቡ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዘህ መዛገብ የቀረበዉ ጉዲይ የገጠር መሬት ይዜታ የሚመለከት ነዉ።በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የአሁኑ ተጠሪ ሲሆን የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።የተጠሪ ክስ ይዖት ባጭሩ በስሙ የተመዖገበዉን አዋሳኙ እና መጠኑ በክሱ ዛርዛር የተገለጸዉን የእርሻ መሬት በህገወጥ ልዉዉጥ ምክንያት አመልካች ይዜ ስለሚገኝ እንዱለቅ እንዱወሰን የሚል ሲሆን በአመልካች በኩል የቀረበዉ ክርክር ልዉዉጥ የተደረገዉ ግንቦት 25 ቀን 2000ዓ.ም መሆኑንና ክሱ በ10ዓመት ይርጋ መታገድ ያለበት ስለመሆኑ እንዱሁም ተጠሪ በልዉዉጥ ዉል የወሰደዉን መሬት እየተጠቀመ ስለመሆኑ በመግለጽ ክሱ ዉድቅ እንዱደረግ የሚል ነዉ።
የግራቀኙን ክርከር በመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ስልጣን የተመለከተዉ የፍገራ ወረዲ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ምስክር ሰምቶ እና ከወረዲዉ መሬት አስተዲደር መረጃ አጣርቶ ክስ የቀረበበት መሬት ለተጠሪ የተደለደለ ስለመሆኑ፣በግራቀኙ መካካል የተደረገዉ የመሬት ልዉዉጥ ዉል በሚመለከተዉ የመሬት አስተዲደር አካል ያልተመዖገበ ስለመሆኑና አመልካች በሃሰተኛ መረጃ በዘህ መሬት ላይ ደብተር የተሰጠዉ ስለመሆኑ በማረጋገጥ የልዉዉጥ ዉል የተደረገዉ በ25/09/2000ዓ.ም በመሆኑና ክስ የቀረበዉ በ22/03/2010ዓ.ም በመሆኑ ዉል ከተደረገበት አንስቶ ክስ እስከቀረበበት ያለዉ ጊዚ 10ዓመት ያልሞላዉ ስለሆነ አመልካች ያቀረበዉ 10ዓመት ይርጋ ዉድቅ በማድረግ የልዉዉጥ ዉል በክልለ የገጠር መሬት አዋጅ ቁ/252/09 አንቀጽ 20/3/ መሰረት ያልተመዖገበ በመሆኑ ተፈጻሚነት የለዉም በማለት አመልካች በልዉዉጥ ምክንያት የያዖዉን የተጠሪ መሬት እንዱለቅ ዉሳኔ ሰጥቷል።አመልካች በዘህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እንደቅደም ተከተለ ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ክርክሩ ተቀባይነት አላገኘም።
ለዘህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዘህ ላይ ሲሆን የአመልካች ሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ክርክር ያስነሳዉ የይዜታ ቅይይር መደረጉ በተጠሪ ታምኖ ባለበት እንዱሁም ልዉዉጡ ያልተመዖገበ ቢሆንም ይህንን ደረጃ አልፍ የይዜታ ማረጋገጫ በተሰጠበት ሁኔታ ይዜታዉን አመልካች ይልቀቅ ተብል መወሰኑ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር እንዱቻል ጭብጥ ተይዜ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ታዝል።በተጠሪ በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ ባህላዊ ልዉዉጥ የተደረገ ቢሆንም አመልካች ሁለቱንም መሬት ይዜ አልሰጥም በማለቱ በሽማግላም ተጠይቆ እምቢተኛ በመሆኑ ልዉዉጡ ያልተመዖገበ በመሆኑ ቀሪ ሆኖ ወደነበሩበት እንዱመለሱ መወሰኑ ተገቢ ስለመሆኑ ተከራክሯል።አመልካችም አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን እኛም በሰበር አጣሪ የተያዖዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዖብ መርምረናል። መዛገቡን መርምረን እንደተገነዖብነዉ ለክርክር መነሻ የሆነዉ ጉዲይ በግራቀኙ መካከል የተደረገ የመሬት ልዉዉጥ ዉል ተፈጻሚነት በሚመለከት ነዉ።የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የተሰጠዉ ክስ የቀረበበት መሬት የተጠሪ ስለመሆኑ፣የመሬት ልዉዉጡ ያልተመዖገበ ስለመሆኑና አመልካች በሀሰተኛ መረጃ በዘሁ መሬት ደብተር ያገኘ መሆኑ በሚመለከተዉ የመሬት አስተዲደር አካል ስለተረጋገጠ አመልካች የተጠሪን መሬት እንዱለቅ ዉሳኔ መስጠቱን ነዉ።
በአማራ ብ/ክ/መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁ/252/09 አንቀጽ 20/3/ ላይ እንደተመለከተዉ የገጠር መሬት ባለይዜታዎች መካከል የሚደረግ ማንኛዉም የልዉዉጥ ዉል አግባብ ባለዉ የወረዲ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ መመዛገብ ያለበት ስለመሆኑ ነዉ።በዘህ መዛገብ በተያዖዉ ክርክር ከጅምሩም ተጠሪ ክስ ያቀረበዉ የልዉዉጥ ዉል መደረጉን ሳይክድ በህገወጥ የልዉዉጥ ዉል ምክንያት አመልካች የያዖዉን የተጠሪ መሬት እንዱለቅ እንዱወሰን ነዉ።ከዘህም ባሻገር አመልካች የራሱን መሬት ለተጠሪ ሳያስረክብ በለዉጥ ምክንያት የያዖዉንና የራሱን መሬት ድርቦ መያዘም በክርክሩ ሂደት የተገለጸ ነዉ።
ስለሆነም ዉለ ህገወጥ ነዉ ተፈጻሚነት የለዉም የሚለዉ የተጠሪ ክርክር ዉል መኖርን መነሻ ያደረገ ስለሚሆን ተጠሪ ዉለን አምኗል የሚለዉ የሰበር አጣሪ ችልት ጭብጥ የክርክር መነሻ ከመሆኑ አኳያ፣ይህም የልዉዉጥ ዉል በህጉ አግባብ ያልተፈጸመ ስለመሆኑ እንዱሁም አመልካች በዘህ ይዜታ ላይ ደብተር ያገኘዉ በሀሰተኛ መረጃ ላይ መሰረት በማድረግ አስተዲደሩን በማሳሳት ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት ከመሬት አስተዲደር አካል ጭምር በቀረበ ማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬጉዲይ በመሆኑ በሀሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተመዖገበ ደብተር መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ በክልለ የገጠር መሬት አዋጅ ቁ/252/09 አንቀጽ 34/5/መሰረት በሀሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ ፣ የተደረገ ምዛገባ ህጋዊ ውጤት ስለማይኖረው እና በህግ ፉት በማይፀና ውል የያዖውን የተጠሪ መሬት አመልካች እንዱለቅ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉ ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚባልበት ህጋዊ ምክንያት አላገኘንም።በዘሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/ በፍገራ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ/29546 ላይ በ12/06/2010 ዓ.ም የተሰጠዉ ፍርድ እና ይህንኑ በማጽናት የደቡብ ጎንደር ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/65196 ላይ በ01/10/2010ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/79074 ላይ በ12/11/2010ዓ.ም የሰጠዉ ትእዙዛ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/348/1 መሰረት ጸንቷል።
2ኛ/በዘህ ፍ/ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።