የሉዛ ዉል እንዱቋረጥ የተሰጠ አስተዲደራዊ ዉሳኔ ባልተሻረበት ሁኔታ በሉዛ ዉል የተያዖ መሬት ለማስለቀቅ የመሬት አስተዲደር አካል መሬቱን ለመረከብ እንዱቻለው የሚሰጠው ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር ነዉ ልባል የማይቻል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1149/3/፤የከተማ ቦታን በሉዛ ስለመያዛ አዋጅ ቁ/721/04 አንቀጽ 25
No summary available.
ጥር 27 ቀን 2011ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንደሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወ/ሮ ዖይነባ ሀሰን ተጠሪ፡- 1ኛ/የቢሸፍቱ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ኤጀንሲ 2ኛ/የኦሮሚያ የመሬት ልማትና ማ/ኤጀንሲ መዛገቡ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዘህ መዛገብ የቀረበዉ ጉዲይ በሉዛ ዉል የተያዖ መሬት ለማስለቀቅ በተጠሪዎች የተሰጠዉ ማስጠንቀቂያ የሐከት ተግባር ነዉ በሚል አመልካች ተጠሪዎች ላይ ያቀረበችዉ ክስ የሚመለከት ነዉ።የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የአሁኗ አመልካች ስትሆን ተጠሪዎች ተከሳሾች ናቸዉ።የአመልካች ክስ ይዖት ባጭሩ በቢሾፍቱ ከተማ ቀበላ 01 ክልል ዉስጥ 11,000ካ.ሜ ይዜታ ለሪል እስቴት ግንባታ የሚዉል በ27/05/2000ዓ.ም በተደረገ ዉል የተሰጣት ካርታ ቁ/28/29 የተመዖገበዉን በቦታዉ ላይ ሁለት ትልልቅ መጋዛን ተሰርቶበት እና ላልች የግንባታ እቃዎች ያለበትን ተጠሪዎች በ24/05/08 ዓ.ም እና በ26/05/08ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ በ7 ቀን ዉስጥ ንብረት በማንሳት ቦታዉን እንዱትለቅ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸዉ የሁከት ተግባር ነዉ በሚል ሁከት እንዱወገድ ዲኝነት የጠየቀች ሲሆን በተጠሪዎች በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ አመልካች በሉዛ ዉለ መሰረት ግንባታዉን በ6 ወር ጊዚ ዉስጥ ባለመጀመሯ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ ባለመፈጸሟ ካርታዉ እንዱሰረዛና መሬቱ ወደ መንግስት እንዱመለስ የተወሰነ ስለመሆኑና የአመልካች ይዜታ መብት የተቋረጠ ስለሆነ ክስ የማቅረብ መብት እንደላላት እንዱሁም የተጻፈዉ ደብዲቤም በሉዛ አዋጅና ደንብ እንዱሁም ተዙማጅነት ባላቸዉ መመሪያዎች መሰረት ለተከሳሾች የተሰጠ ስልጣን መሰረት ስለመሆኑ በመግለጽ ድርጊቱ የሁከት ተግባር ልባል አይችልም በማለት ተከራክረዋል።
ክርክሩን በመጀመሪያ የዲኝነት ስልጣን የተመለከተዉ የአደአ ወረዲ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በቦታዉ ላይ የተሰራዉ ግንባታ መጠን እና ዋጋ ግምት በባለሙያ ተጣርቶ እንዱቀርብ በማድረግ በቦታዉ ላይ ያለዉ ንብረትና ግንባታ ግምት ብር 2,233,875.00 ስለመሆኑና ይህም ካጠቃላይ ግንባታ አንጻር ሲሰላ 2.92% መሆኑን እንደሚያሳይና አመልካች ግንባታ አልጀመረችም በሚል የተሰጠዉ ማስጠንቀቂያ ተገቢ አይደለም በማለት ሁከት እንዱወገድ ዉሳኔ ሰጥቷል።ስር ተከሳሾች ይህንን ዉሳኔ በመቃወም ለምስራቅ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዉ ፍርድ ቤቱ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ክስ የቀረበበትን ይዜታ አመልካች በሉዛ ዉል መሰረት ያገኘች ስለመሆኑና በሉዛ ዉለ መሰረት በጊዚዉ ሳታለማ በመቅረቷበ12/07/2006 ዓ.ም በተደረገ ስብሰባ የሉዛ ዉለ እንዱቋረጥ እና ይዜታ ማረጋገጫ እንደተሰረዛ ተወስኖ በ23/10/06ዓ.ም እንደተገለጸላት የተረጋገጠ ስለመሆኑና መሬቱ እስካሁን በእጇ ላይ የቆየ ቢሆንም የሉዛ ዉለ ከተቋረጠ ቀን ጀምሮ መብት የላትም በማለት የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1140 እና 1149 ላይ የተደነገገዉን ምርኩዛ በማድረግ ስር ተከሳሾች መሬቱን ለማስለቀቅ የሰጡት ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር ነዉ ልባል አይገባም በማለት የወረዲ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ሽሯል።
አመልካች በበኩሎ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቅሬታ በማቅረቧ ፍርድ ቤቱም የግራቀኙን ክርክር ሰምቶ የሉዛ ዉለ በ2006 ዓ.ም የተሰረዖ ቢሆንም ይዜታዉ እስከ አሁን ድረስ በአመልካች እጅ ይገኛል በሚል ምክንያት የከፍተኛዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ በመሻር የወረዲ ፍርድ ቤት ዉሳኔ አጽንቷል።ተጠሪዎች ጉዲዩን ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በአቤቱታ አቅርበዉ ሰበር ችልቱም ጉዲዩ ላይ ግራቀኙን አከራክሮ በሉዛ አዋጅ ቁ/721/04 አንቀጽ 22 እና በደንብ ቁ/182/08 አንቀጽ 39/7 መሰረት በሉዛ ዉለ መሰረት ግንባታ ካልተጀመረ አስተዲደሩ መሬቱን መልሶ መዉሰድ እንደሚችል ስለመደንገጉ፣የአመልካች ዉል በ2006 ዓ.ም ከተሰረዖ ጊዚ ጀምሮ ንብረቷን ለማንሳት ከሁለት ዓመት በላይ ጊዚ እንደነበራት እንዱሁም የሉዛ ዉለ መሰረዛ የለበትም በሚል ለክልለ ኢንቨስትመንት ቦርድ አቤቱታ አቅርባ ከሆነም እግድ ከመጠየቅ ዉጪ የሉዛ ዉል መብት በተቋረጠበት ሁኔታ የአስተዲደር አካል ተግባር በፍ/ህግ አንቀጽ 1149/3/ መሰረት ተገቢ በመሆኑ ሁከት የለም በማለት ዉሳኔ ሰጥቷል።
ለዘህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዘህ ላይ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች በቦታዉ ላይ የሰራችዉ ግንባታ መጠን 2.92% መሆኑ በባለሙያ ተረጋግጦ በቀረበበት ሁኔታ የተጠሪዎች ድርጊት ሁከት አይደለም መባለ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ከፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1149 እና አዋጅ ቁ/721/04 እና ደንብ ቁ/182/08 ጋር በማገናዖብ ለመመርመር በሚል ጭብጥ ተይዜ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ተደርጓል።በተጠሪዎች በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ አመልካች በ29/08/2000ዓ.ም በተደረገ የሉዛ ዉል በከተማዉ ዉስጥ ዋና መንገድ ዲር ላይ 11,000ካ/ሜ መሬት ለሪል እስቴት ግንባታ መዉሰዶን ፣በአዋጅ ቁ/272/94 አንቀጽ 15/1 እንዱሁም 721/04 አንቀጽ 25/1/ሀ እና ደንብ ቁ/119/99 አንቀጽ 10/5 እንዱሁም 155/05ና ማሻሻያዉ ደንብ ቁ/182/08 መሰረት በተገቢዉ ጊዚ ዉስጥ ግንባታ ሳይገነቡና ወደ ስራ ሳይገቡ በመቅረታቸዉ መሬቱ ወደ መሬት ባንክ እንዱመለስ መወሰኑና ንብረታቸዉን እንዱያነሱ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ህጋዊ ተግባር ስለመሆኑ በመዖርዖር የሐከት ተግባር የለም በማለት ተከራክሯል።አመልካችም አቤቱታዋን በማጠናከር በጠበቃ አማካይነት የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥና የግራቀኙ ክርክር ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን እኛም አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገነዖብ መርመረናል።መዛገቡን መርምረን እንደተገነዖብነዉ አመልካች በ2000 ዓ.ም በተደረገ የሉዛ ዉል 11,000ካ.ሜ ይዜታ ከከተማዉ አስተዲደር መረከባቸዉና የይዜታ ማረጋገጫ ቁ.28/29 የተሰጣቸዉ ስለመሆኑ አላከራከረም።አመልካች በሉዛ ዉለና በህጉ መሰረት ግንባታ አላከናወኑም ለተገልጋዩ አላማ አልዋለም በሚል ምክንያት የሉዛ ዉለ እንዱቋረጥና የይዜታ ማረጋጫ ካርታ እንዱሰረዛ በ12/07/2006ዓ.ም በክልለ የሚመለከተዉ አካል ዉሳኔ መሰጠቱም በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ጉዲይ ነዉ።አመልካችም ይህንን ፍሬነገር በግልጽ ሳይክደ ለክልለ ኢንቨስትመንት ቦርድ አቤቱታ አቅርበዉ ዉሳኔ በመጠባበቅ ላይ ስለመሆናቸዉ ገልጸዉ ተከራክረዋል።አቤቱታ የቀረበለት የሉዛ ቦርድ የተለየ ዉሳኔ ስለመስጠቱ አመልካች አስረጂ አላቀረቡም።ስለሆነም የሉዛ ዉለ እንዱሰረዛ ና ይዜታዉ ወደ መሬት ባንክ እንዱገባ የተሰጠ አስተዲደራዊ ዉሳኔ ተከትል የከተማዉ አስተዲደር መሬቱን ለመረከብ ሲል በ24/05/08 እና በ26/05/08ዓ.ም የሰጠዉ ማስጠንቀቂያ የሐከት ተግባር ነዉ ልባል አይችልም በማለት የኦሮሚያ ክልል ሰበር ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ አግባብነት ከህጉ ጋር በማገንዖብ እንመለከታለን።
በመሰረቱ የአንድ ንብረት ባለይዜታ የሆነ ሰው ይዜታው ለመንጠቅ ወይም በይዜታው ላይ ሁከት ለመፍጠር የሚፈፀምን ማንኛውንም ድርጊት እንዱቆም ወይም ተገቢው መብት እንዱመለስለት ህጉ ከዖረጋቸው መንገድች አንደ የይዜታ ክስ /Possessory action/ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1149/1/ ድንጋጌ ያስገነዛባል። በዘህ ድንጋጌ መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ የሚቻለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ንብረት ላይ በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዜታ ሲኖረውና ይህንኑ ሁኔታ በኃይል ሲነጠቅ ወይም በይዜታዉ ስር ባለንብረት የመጠቀም መብቱ የሚያዉክ ተግባር ሲፈጸም ነው።
እንዱሁም የይዜታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዛ ምንም ዓይነት መብት የላለው ሰው ሲይዛ ስለመሆኑም ተጠቃሹ ድንጋጌ ያሣያል። በመሆኑም የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ አቅራቢ ማረጋገጥ ያለበት ንብረቱ በህግ አግባብ በይዜታው የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚው የኃይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጢር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ነው። ይህ የድንጋጌው መንፈስ የሚያስረዲው የሁከት ተግባር የሚኖረው ባለይዜታ የሆነው ሰው በይዜታው ሥር በሚገኘው ንብረት እንዲይገለገልበት ላላ ሰው ጣልቃ ገብቶበት መሰናክል ሲፈጥርበት ወይም ረብሻ ሲፈጥርበት መሆኑን ነው። የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1140 እና 1149 ድንጋጌዎች ይዖት የሚያሣዩትም ይህንኑ ነው። እነዘህ ድንጋጌዎች ከላይ ከተገለፀው ነጥብ በተጨማሪ የሚያስገነዛቡት ነጥብ የሁከት ይወገድልኝ ክስ አቅራቢ የተሻለ የይዜታ መብት ያለው ስለመሆኑ ማረጋገጥ ያለበት መሆኑን ነው።
በዘህ መዛገብ በተያዖዉ ጉዲይ አመልካች ክስ የቀረበበትን ይዜታ የመጠቀም መብት ያገኙት በ29/08/2000 ዓ.ም በተደረገ የሉዛ ዉል መነሻ ስለመሆኑና በሉዛ ዉል እና በህጉ አግባብ ተገቢዉን ግንባታ በወቅቱ አለማፈጸማቸዉ በሚመለከተዉ አካል ተረጋግጦ የሉዛ ዉለ እንዱሰረዛ እና መሬቱ ወደ መንግስት ይዜታ እንዱመለስ በ12/07/06ዓ.ም በሚመለከተዉ አካል ዉሳኔ ተሰጥቶ ያደረ ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬነገር ጉዲይ ነዉ።በስራ ላይ ባለዉ የከተማ ቦታን በሉዛ ስለመያዛ የሚደነግገዉ አዋጅ ቁ/721/04 አንቀጽ 25 መሰረት የሉዛ ዉል ስለምቋረጥበትና የሚያስከትለዉ ዉጤት በዛርዛር ተመልክቷል።ይህንን አስተዲደራዊ ዉሳኔ የሚቃወም ወገን ይግባኝ ስለሚያቀርብበት ስርዓትም በአዋጁ ላይ ተደንግጓል።አመልካች የሉዛ ዉለ መሰረዘን በመቃወም ለሚመለከተዉ አካል አቤቱታ አቅርበዉ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ስለመሆናቸዉ ከመግለጽ ዉጪ የተሰጠ አስተዲደራዊ ዉሳኔ ስለመኖሩ ያቀረቡት ማስረጃ የለም።ስለሆነም የሉዛ ዉለ እንዱቋረጥ በ12/07/2006 ዓ.ም የተሰጠዉ አስተዲደራዊ ዉሳኔ ባልተሻረበት ሁኔታ ተጠሪዎች መሬቱን ለመረከብ እንዱቻላቸዉ አመልካቿ ንብረታቸዉን እንዱያነሱ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸዉ በሉዛ አዋጁና ይህን ተከትል የወጡትን ማስፈጸሚያ ደንብና መመሪያ የተከተለ እና ድርጊታቸዉም በህግ የተሰጠ ስልጣን መሰረት ያደረገ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ከመሆኑ አኳያ በፍ/ብ ህግ አንቀጽ 1149/3/ ጋር ሲታይ የሁከት ተግባር ነዉ ልባል የማይቻል መሆኑን ያሥገነዛባል። ስለሆነም የክልለ ሰበር ችልት ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚባልበት ህጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
1ኛ/ የኦሮሚያ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/270624 በ29/08/2010 ዓ.ም የሰተዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/348/1/መሰረት ጸንቷል።
2ኛ/ በዘህ መዛገብ ላይ በ06/10/10 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ የእግድ ትእዙዛ ተነስተዋል።ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል ይመለስ።
No topics extracted.