በባለመሬቱ ወይም በባለይዜታዉ ፈቃድ አትክልቶችን በልላ ሰው ይዜታ ላይ የተከለ ሰዉ ከባለይዜታው ጋር ባለው ስምምነት መሰረት የመሬቱ አላባ ተጠቃሚ እንደሆነና ከስምምነቱ ዉጪ አትክልቶቹ እንዱነሱ ሲደረግ ካሳ የሚገባው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 40(3 እና 4)፣የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1175፣1176
No summary available.
ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ አባዛናብ አባድማ -ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ አባተማም ሼህ ሽኩር - ቀረቡ።
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የገጠር መሬት አላባ ጉዲይ ሲሆን የተጀመረው በደቡብ ክልል በየም ልዩ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በዘህ ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ይዖት፡- አመልካች ምንም መብት ሳይኖራቸዉና የግል ንብረቴ የሆነዉን ባሕር ዙፍ ለጥቅም የደረሰዉን በጥቅምት ወር 2009 ዓ.ም መንጥሮ ለ3ኛ ወገን በመሸጥ ላይ ሳለ በሕግ ያስቆምኳቸዉ ሲሆን ቆርጠዉ የወሰደትና የሸጡብኝ የባሕር ዙፍ ምርት ጠቅላላ ዋጋዉ ብር 17,400 በመሆኑ ግምቱን ይክፈለኝ የሚል ነዉ።
አመልካች በበኩላቸዉ በሰጡት መልስ ክስ የቀረበብኝ የባህር ዙፍ ንብረት ይዜታ የእኔ እንጂ የተጠሪ ባለመሆኑ ክሱ ዉድቅ ተደርጎ ባቀረብኩት ማስረጃ መሰረት ይወሰንልኝ በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተዉ የየም ልዩ ወረዲ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃ ሰምቶ እንዱሁም የባህር ዙፈ ይዜታ የማን ነዉ የሚለዉ በወረዲዉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት በኩል ተጣርቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኃላ ይዜታዉ የአመልካች መሆኑ በመረጋገጡ ቆርጦ የወሰደዉንና የሸጠዉን ባህር ዙፍ ግምት ሉከፍል አይገባም በማለት የተጠሪን ክስ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። በዘህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ ተጠሪ ባቀረቡት ይግባኝ መነሻነት ጉዲዩን የተመለከተዉ የየም ልዩ ወረዲ ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ መርምሮ በ1997/98 ዓ.ም በነበረዉ የመጀመሪያ ደረጃ የመሬት ልኬት ወቅት ለተጠሪ ይዜታዉ ተለክቶ የይዜታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጥቶት የነበረ ሆኖ እያለ በ2006 ዓ.ም ልኬት ያለአግባብ በአመልካች መመዛገቡ ስለተረጋገጠ፤ ተጠሪ በባህር ዙፈ በጋራ ለመጠቀም ይዜታዉን ለአመልካች ሰጥቶ ባህር ዙፈን የተከለ መሆኑን ተጠሪ የተናገረዉን መሰረት በማድረግ የተቆረጠዉ ባህር ዙፍ የጋራ ነዉ በማለት ግምቱ በባለሙያ ተገምቶ እኩል ይከፊፈለ በማለት የስር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል። በዘህ ዉሳኔ አመልካች ቅር ተሰኝተዉ ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም። በመቀጠል አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻነት ጉዲዩን የተመለከተዉ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ዉሳኔዉን በማጽናት ወስኗል። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዘሁ ዉሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘታቸዉ ነው።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዖት፡- በክልለ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 110/99 አንቀጽ 12(1) መሰረት ጉዲዩ በቅድሚያ በቀበላ አስተዲደር የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ኮሚቴ በእርቅና ድርድር ሳይታይ መወሰኑ ተገቢ አይደለም። በዉሳኔዉ ይዜታዉ የተጠሪ ነዉ ብል ሲወሰን ለዉሳኔ መሰረት ያደረገዉ የወረዲዉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት በ1997/98 ዓ.ም መሬት ሲለካ ተጠሪ በስሙ ተለክቷል ብሎል። ነገር ግን በ2006 ዓ.ም የወረዲዉ መሬት በጅፑኤስ ዖመናዊ መሳሪያ ሲለካ በስሜ መለካቱን፤ ሲለካም ተጠሪ ተቃዉሞ እንዲላሰማ በጻፈዉ ደብዲቤ አረጋግጧል። ይዜታዉ የእኔ መሆኑን የሚያረጋግጥ የይዜታ ማረጋገጫ አቅርቤያለሁ። ተጠሪ የይዜታ ማረጋገጫ ሰነድ አቅርቦ ባላስረዲበት የተሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ባለመሆኑ ተሽሮ የወረዲዉ ፍ/ቤት ዉሳኔ ይጽናልኝ ሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ በዘህ ጉዲይ አከራካሪዉ ይዜታ ለአመልካች ከተሰጠዉ የይዜታ ማረጋገጫ አንጻር ሳይሆን የስር ፍ/ቤቶች በገመድ ልኬትና በኮምፑዩተር መመዛገብና አለመመዛገብ ላይ ትኩረት በማድረግ የተሰጡት ዉሳኔ አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራ ቀኙ መልስና የመልስ መልስ በጽሁፍ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ይዖት በስር ፍ/ቤት አመልካች በማስረጃነት ያቀረበዉ ሀሰተኛ ማስረጃ ነዉ። በወረዲ ደረጃ እስከ ቦታዉ ድረስ እንዱጣራ ሲደረግ አመልካች ምንም ዓይነት ይዜታ እንደላላቸዉ ተገልጿል። አመልካች ያቀረቡት ማስረጃ በድብቅ በሀሰት ተዖጋጅቶ የተሰጠ ነዉ። የባህር ዙፍ ንብረቱም በአያቴ ዖመን ተተክል አባቴ እየተጠቀመበት ቆይቶ ሲሞት በተራዬ መጠቀም ከጀመርኩ 40 ዓመት ያስቆጠረና የገበርኩበትን አመልካች ሳይመለከታቸዉ ያቀረቡት ክርክር ተገቢነት የላለዉ በመሆኑ ዉሳኔዉ ስህተት የለዉም ተብል ይወሰንልኝ የሚል ነዉ። አመልካች ባቀረቡት የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታቸዉን በሚያጠናክር መልኩ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን ከስር ፍ/ቤት ዉሳኔ እና ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ተብል ከተያዖዉ ጭብጥ ጋር በማገናዖብ መርምረናል።
መርምረን እንደተረዲነዉ በስር ፍ/ቤት ተጠሪ አመልካች ባህር ዙፈን ቆርጦ የሸጠበት መሆኑን ገልጾ ግምቱ ብር 17,400 እንዱከፍለዉ የጠየቀ ሲሆን አመልካች ባህር ዙፈ የራሱ መሆኑን በመግለጽ ግምት ሉከፍል እንደማይገባ በመግለጽ ተከራክሯል። ጉዲዩን በቅድሚያ የተመለከተዉ የወረዲ ፍ/ቤት በግራ ቀኙ የቀረቡ ማስረጃዎችንና የወረዲዉ እርሻና የተፈጥሮ ሀብት መሬት አስተዲደር ጽ/ቤት የጻፈዉን ደብዲቤ መርምሮ ይዜታዉ የተጠሪ የነበረ ቢሆንም በ1979 ዓ.ም ጀምሮ ለአመልካች ሰጥቶት አመልካች ባህር ዙፈን በእጁ ተክል ሲጠቀምና ግብር ሲከፈል መቆየቱ ተረጋግጧል በሚል የተጠሪን የባህር ዙፍ ግምት ጥያቄ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። የልዩ ወረዲዉ ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩለ ምንም እንኳ ይዜታዉ በ2006 ዓ.ም በተደረገዉ ልኬት በአመልካች ተመዛግቦ የተገኘ ቢሆንም በ1997/98 ዓ.ም በተደረገዉ ልኬት በተጠሪ ተመዛግቦ የሚታወቅ መሆኑን በመግለጽ ተጠሪ በሕግ አግባብ ይዜታዉ ሳይወሰድበት ለአመልካች ሉተላለፍ የሚችልበት አግባብ አለመኖሩን እንዱሁም ተጠሪ ለእኩል ለመጠቀም ለአመልካች መስጠቱን በቃል መግለጹን በመጥቀስ ይዜታዉ የተጠሪ ሆኖ አመልካች እኩል ለመጠቀም ባህር ዙፈን ያለማዉ ነዉ በሚል የባህር ዙፈ ግምት በባለሙያ ተገምቶ ግማሹን ለተጠሪ ይክፈል ሲል ወስኗል።
አመልካች አጥብቀዉ የሚከራከሩትም ሆነ አቤቱታዉ ለሰበር ያስቀርባል የተባለዉ አመልካች በ2006 ዓ.ም የይዜታ ማረጋገጫ ተሰጥቶት እያለ በ1997/98 ዓ.ም በነበረዉ ልኬት ወቅት በኮምፑዩተር መመዛገብ አለመመዛገቡ ላይ ትኩረት በመስጠት ይዜታዉ የተጠሪ ነዉ ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነዉ?
ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነዉ።
በመሰረቱ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(3) የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዛብ እንደሆነና መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሓሮች ብሓረሰቦችና ህዛቦች የጋራ ሀብት መሆኑ የተመለከተ ሲሆን አርሶ አደሮች በነጻ መሬት የማግኘትና ከመሬታቸዉ ያለመነቀል መብት ያላቸዉ መሆኑ በዘሁ አንቀጽ 4 ተደንግጎ ይገኛል።
በአዋጅ ቁጥር 456/97"ም" ቢሆን ባለይዜታ አርሶ አደር የመሬት ይዜታውን በስጦታም ሆነ በዉርስ ለቤተሰቡ አባል ካልሆነ ወይም በሕግ በተፈቀደዉ መሰረት ለተወሰነ ጊዚ በማከራየት ካልሆነ በቀር ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ አይችልም። በልላ በኩል የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1175 የባለመሬቱን ወይም የባለይዜታዉን ፈቃድ በመጣስ አትክልቶችን የተከለ ሰዉ በአትክልቶቹ ላይ ምንም ዓይነት መብት እንደላለዉና ካሳ መጠየቅ እንደማይችል የተመለከተ ሲሆን ቁጥር 1176 ደግሞ በባለመሬቱ ወይም በባለይዜታዉ ፈቃድ አትክልቶቹን የተከለ ሰዉ በስምምነታቸዉ መሰረት ተጠቃሚ እንደሆነና ከስምምነቱ ዉጪ እንዱነሱ ሲደረግ ካሳ እንደሚገባዉ ተደንግጓል።
በተያዖዉ ጉዲይ አመልካች ባህር ዙፍ የተተከለበትን ይዜታ በራሱ ስም በመያዛ እና በ2006 ዓ.ም ይዜታዉን በስሙ ከማስመዛገቡ በፉት ይዜታዉ በ1997/98 ዓ.ም በክልለ በነበረዉ የመሬት ልኬት ወቅት በተጠሪ ስም ተመዛግቦ የነበረ መሆኑንና ይዜታዉ በአመልካች እጅ ሉገባ የቻለዉ በግራ ቀኙ መካከል ባህር ዙፍ አመልካች እንዱያለማና ለእኩል ለመጠቀም በነበረ ስምምነት መሆኑን ማስረጃ ለመመዖንና ፍሬ ነገርን ለማረጋገጥ ስልጣን የተሰጣቸዉ የስር ፍ/ቤቶች አረጋግጠዋል። አመልካች በዘህ አግባብ በእጁ የገባዉን ይዜታ በስሙ በድብቅ ማስመዛገቡና የይዜታ ማረጋገጫ ማዉጣቱ፤ ይዜታዉ ከተጠሪ በሕግ አግባብ የተላለፈለት መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ ያለአግባብ የይዜታ ማረጋገጫ ስለተሰጠዉ ብቻ የተጠሪን ባለይዜታነት መብት አያስቀርም። እንዱሁም በሕግ አግባብ ካልሆነ በቀር የአስተዲደር አካለ ተጠሪን ከመሬት ይዜታዉ ከሕግ ዉጪ አፈናቀል ለአመልካች ይዜታ ማረጋገጫ ላሰጥ አይችልም። ስለሆነም የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንን በማረጋገጥ አመልካች በተጠሪ ይዜታ ላይ ለእኩል ለመጠቀም በነበረ ስምምነት ያለማዉን ባህር ዙፍ ለብቻዉ ቆርጦ መዉሰደን በማረጋገጥ የባህር ዙፈ ግምት በባለሙያ ተጣርቶ ግማሹ አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት የሰጠዉና በየደረጃዉ የጸናዉ ዉሳኔ የሚነቀፍበት በቂ ምክንያት አልተገኘም።
ሲጠቃለል የየም ልዩ ወረዲ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይዜታዉ የተጠሪ ሆኖ በአመልካች እጅ ሉገባና በ2006 ዓ.ም በስሙ አስመዛግቦ ባህር ዙፍ አልምቶ ቆርጦ ሉሸጥ የቻለዉ ከተጠሪ ጋር በነበራቸዉ ስምምነት መሆኑን በማረጋገጥ ያለአግባብ በአመልካች ስም መመዛቡ የተጠሪን ባለይዜታነት ሉያስቀር አይችልም በማለት ባህር ዙፈ ተገምቶ ግማሹን ግምት ለተጠሪ ይክፈል በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 40(3 እና 4)፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1175 እና ተከታዮችን ድንጋጌዎች ይዖትና መንፈስ ያገናዖበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አልተቻለም።
በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ. በየም ልዩ ወረዲ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሚያዘያ 04 ቀን 2010 ዓ.ም ተሰጥቶ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 09 ቀን 2010 ዓ.ም በተሰጠ ትዔዙዛ እና በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ.ም የተሰጠዉ ዉሳኔ የጸናዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ጸንቷል።
2ኛ. በስር ፍ/ቤት የተጀመረዉ አፈጻጸም ለጊዚዉ ታግድ እንዱቆይ ታሕሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም የተሰጠዉ የእግድ ትዔዙዛ ተነስቷል። ይጻፍ።
3ኛ. በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል። መዛገቡ ተዖግቷል፣ ወደ መዛገብ ቤት ተመላሽ ብለናል።
No topics extracted.