አንድ ቤት በዓዋጅ 47/67 መሰረት ከተወረሰ በኋላ የተወረሱ የድሬደዋ ከተማ አስ/ቀበላ ለመመለስ በወቅቱ ስልጣን የነበረዉ የከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር ቤቱ እንዱመለስ የወሰነው ዉሳኔ መኖሩን የሚያሳይ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ምትክ ቤት እንዱሰጥ መወሰኑ ብቻ የተወረሰ ቤት ይመለስ ማለት ስላለመሆኑ እና ወ/ሮ ስንደ ሳልቫቶር
No summary available.
ቀን - 30/09/2011 ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- የድሬዲዋ አስ/ቀበላ 03 ጽ/ቤት - አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ስንደ ሳልቫቶር - ቀርበዋል።
መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ ፍርድ መነሻ የሆነዉ ጉዲይ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን፤
ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የተጠሪ ክስ ይዖትም በአጭሩ፡- በድሬዲዋ ከተማ ቀበላ 03 ቁጥሩ 315 ሆኖ ንብረትነቱ የሟች እናቴ የወ/ሮ ለምለም ሞገስ የነበረዉ ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት በመንግስት የተወረሰ ሲሆን ቤቱ እንዱመለስላቸዉ ወላጅ እናቴ ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ በየደረጃዉ ላለ ጉዲዩ ለሚመለከታቸዉ አካላት ባመለከቱት መሰረት ተገቢዉ ማጣራት ተደርጎ ተፈቅድላቸዋል፤ አዋጁን የማስፈጸም ስልጣን ያለዉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በዉሳኔዉ መሰረት ቤቱን ለሟች እንዱያስረክቡ በተዋረድ ለሚገኙት አካላት ትዔዙዛ የሰጠ ቢሆንም ተከሳሽ ቤቱን የያዘትን ሰዎች አስለቅቆ አላስረከበም፣ ይልቁንም ቤቱን አከራይቶ ኪራይ እየሰበሰበ ይገኛል፤ በመሆኑም ተከሳሽ የኪራይ ዉለን አቋርጦ ቤቱን የያዘትን ሰዎች አስለቅቀዉ እንዱያስረክበኝ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ።
አመልካች ለክሱ በሰጠዉ መልስ፡- ቤቱ በአዋጅ ተወርሶ መንግስት የሚያስተዲድረዉ መሆኑን እና የተወረሰዉ ቤት እንዱመለስ ጥያቄ አቅርቦ ቤቱ እንዱመለስለት ስልጣን ባለዉ አካል የተወሰነለት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አቅርቦ ባለመብት መሆኑን ሳያረጋግጥ ከሳሽ ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዘህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና የቤቱን ማህደር ጨምሮ ላልች የተለያዩ ማስረጃዎችን አስቀርቦ ከመረመረ በኋላ የተጠሪ አዉራሽ ወ/ሮ ለምለም ሞገስ አከራካሪዉ ቤት በአዋጅ ከተወረሰባቸዉ በኋላ በወቅቱ ስልጣን ባለዉ አካል ላላ ቤት የላላቸዉ መሆኑ ተረጋግጦ ቤቱ የተመለሰላቸዉ መሆኑ መረጋገጡን ጠቅሶ አመልካች ተከራዮችን አስለቅቆ ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክብ በማለት ወስኗል። በአመልካች አቤቱታ መነሻነት ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ግራ ቀኝን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም ይህኑን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካች በቀን 05/03/2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የተወረሱ ቤቶችን የማስመለስ ስልጣን ያለዉ የከተማና ቤቶች ልማት ሚኒስቴር ብቻ እንጂ በስሩ የሚዋቀሩ የአስተዲደር እርከኖች ጭምር አለመሆኑን ሰበር ሰሚ ችልት ትርጉም የሰጠበት ከመሆኑም በላይ ስልጣን አላቸዉ እንኳ ቢባል የከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር የሐረርጌ ክ/ሀገር ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት የወሰነዉ በተወረሰዉ ቤት ምትክ ተለዋጭ ቤት እንዱሰጥ የሚል ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች የተወረሰ ቤት ለተጠሪ አዉራሽ እንዱመለስ እንደተወሰነ በማድረግ ተጠሪ ቤቱን እንዱረከቡ የሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑን ጠቅሶ ታርሞ ይወሰንለት ዖንድ ዲኝነት ጠይቋል። አቤቱታዉ ተመርምሮም ቤቱ ለተጠሪ አዉራሽ እንዱመለስ ሳይታዖዛ እና ይልቁም የተወሰነዉ ምትክ ቦታ እንዱሰጣቸዉ በሚል በሚመለከተዉ አካል የተሰጠዉን ዉሳኔ የስር ፍርድ ቤቶች የተረጎሙበትን አግባብ ግራ ቀኝ በተገኙበት አከራክሮ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት በቀን 22/04/2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም የሚልባቸዉን ምክንያቶች በመዖርዖር ፀንቶ እንዱወሰንለት ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካች በቀን 17/05/2011 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዖት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን፣ ይህ ችልትም መዛገቡን ለማስቀረብ በአጣሪ ችልት የተያዖዉን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መዛገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተወረሰ መሆኑ አላከራከረም። ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች ቤቱን እንዱያስረክቧቸዉ ለጠየቁት ዲኝነት መሰረት ያደረጉት ሟች እናታቸዉ ቤቱ እንዱመለስላቸዉ ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ ለሚመለከተዉ አካል ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ቤቱ እንዱመለስላቸዉ በስራና ቤቶች ሚኒስቴር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ እንዱመለስላቸዉ የወሰነ መሆኑን ግን በየደረጃዉ ያለ የከተማዉ መስተዲደር አካላት ቤቱን ሉያስረክቧቸዉ ፍቃደኛ አለመሆናቸዉን ሲሆን፤ አመልካች በበኩለ ቤቱ በመንግስት የተወረሰ እና ለሟች እንዱመለስ ስልጣን ባለዉ አካል የተሰጠ ዉሳኔ አለመኖሩን ገልፆ ይከራከራል። የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ቤቱ ከተወረሰ በኋላ ለተጠሪ አዉራሽ የተወሰነ መሆን አለመሆኑን በጭብጥነት ይዜ ግራ ቀኝ ካቀረቧቸዉ ማስረጃዎች በተጨማሪ ከድሬዲዋ አስተዲደር መሬት ልማት ቢሮ ቤቱን የሚመለከት ማህደር አስቀርቦ የመረመረ መሆኑን ተመልክተናል። ሚያዛያ 18/1977 ዓ.ም በድሬዲዋ ከተማ አጠቃላይ የከተማ ነዋሪዎች ማህበር ምክር ቤት ለከፍተኛ ከነማ ወኪል የተፃፈዉ ደብዲቤ አከራካሪዉ ቤትና ቦታ በሟች ወ/ሮ ለምለም ሞገስ ተመዛግቦ የሚገኝ መሆኑን፣ ከዘህ ቦታና ቤት በስተቀር በስማቸዉ ተመዛግቦ የሚገኝ በእርሱ ዖንድ አለመኖሩን መግለጹን፤
በመቀጠልም በቁጥር ለተቀፍፍ/2/1/78 በ25/04/1978 ዓ.ም የከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር የሐረርጌ ክ/ሀገር ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት በፃፈዉ ደብዲቤ የተጠሪ አዉራሽ ቤቱ እንዱመለስላቸዉ ማመልከታቸዉን ተከትል በቦታዉ ላይ በግንባር ተገኝቶ በመመልከት የቤቱ አሰራር ለድርጅት ሆኖ ያገኘዉ መሆኑን እና ከአዋጁ በፉትም በድርጅትነት ተይዜ የነበረ መሆኑን ማረጋገጡን፣ በዘህም ምክንያት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ምክር ቤቱ አጠቃላዩን ተረክቦ ምትክ ቤት ለተጠሪ አዉራሽ እንዱሰጣቸዉ ያስታወቀ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት መዛገብ መገንዖብ ይቻላል።
ይህም በግልጽ የሚያሳየዉ የተወረሱ ቤቶችን ለመመለስ በወቅቱ ስልጣን የነበረዉ የከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት ለሟች ለምለም ሞገስ (ለተጠሪ አዉራሽ) እንዱመለስ አለመወሰኑን፣ ይልቁንም ስልጣን ያለዉ የከተማ አስተዲደር ምትክ ቤት እንዱሰጣቸዉ መወሰኑን ነዉ።
ለሟች ምትክ ቤት ይሰጥ ማለት የተወረሰ ቤት ይመለስ ማለት እንዲልሆነ ግልጽ ነዉ። ይህ ሆኖ እያለ የስር ሁለቱ ፍርድ ቤቶች የተጠሪ አዉራሽ ላላ ቤት የላላቸዉ ስለመሆኑ ተረጋግጦ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት በወቅቱ ስልጣን በነበረዉ አካል ተመልሶላቸዋል በሚል ድምዲሜ ላይ ሲደርሱ ምንን መነሻ አድርገዉ እንደሆነ ግልጽ አይደለም።
ተከሳሽ በከሳሽ የቀረበበትን ክስ ክድ የተከራከረ እንደሆነ ከሳሽ ክሱን በማስረጃዎቹ የማስረዲት ግዳታ እንዲለበት በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 258(1) እና 259(1) ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች የምንገነዖበዉ ነዉ። ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ የሚደርሱበት ድምዲሜ የቀረቡትን ማስረጃዎች መሰረት ሉያደርግ እንደሚገባ እሙን ነዉ። የዲኝነት አሰጣጥ ስርዓት መሰረታዊ መርህም ነዉ። ከዘህ አንፃር ሲታይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት ከተወረሰ በኋላ ለአዉራሻቸዉ የተመለሰ መሆኑን የሚያሳይ ስልጣን ባለዉ አካል የተወሰነ ዉሳኔ መኖሩን የሚያሳይ ማስረጃ ተጠሪ ባላቀረቡበት ሁኔታ እና ፍርድ ቤት በተጨማሪነት ያቀረባቸዉ ማስረጃዎችም ቤቱ ከተወረሰ በኋላ ለአዉራሻቸዉ የተመለሰ መሆኑን የማያስረዲ ሆኖ እያለ አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ለተጠሪ ሉያስረክብ ይገባል በሚል በስር ሁለቱ ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 22/01/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት፣ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 05/02/2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ምትክ ቤት አስመልክቶ ተጠሪ መብቴን ለማስከበር የሚያቀርበው ጥያቄ ካለ በዘህ ውሳኔ ምክንያት አይታገድም።
በዘህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
ሳ/ፀ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.