የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚ/ር አጥንቶ ስራ ላይ ባዋለው በነጥብ የስራ ምዖናና ደረጃ አወሳሰን ዖዳ/JEG/ የመንግስት ሰራተኞች ድልድል አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ለአንድ የሥራ መደብ የሚያስፈልገው የትምህርት ዛግጅት በግልጽ ተቀምጦ እያለ ተጨማሪ የትምሕርት ዓይነትን አካቶ ሰራተኞችን ማወዲደር የድልድል መመሪያውን የሚጥስ የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ እና አቶ ዋቅጋሪ ጥላሁን
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 24/10/2011 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ነ/ፈ ደነቀ ጉታ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ዋቅጋሪ ጥላሁን - ቀረቡ።
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ ሰበር መዛገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የቀረበው አመልካች መጋቢት 17 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፍደራል ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አስተዲደር ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 039/2011 ታህሳስ 25 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ እና የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው። ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዖረዛርና በሰበር ሰሚው ችልት በኩል ላታይልኝ ይገባል የሚለውን ዲኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤቶች የሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር ባጠናው የስራ ምዖናና ደረጃ አወሳሰን ዖዳ የመንግስት ሰራተኞች ድልድል አፈጻጸም መመሪያ መሰረት የአሁን ተጠሪ ባከራከረው የስራ መደብ ተፈላጊውን የትምህርት ዛግጁነት የማያሟላ መሆኑ ታውቆ እያለ የአመልካችን መ/ቤት ሥራና መብት በሚጥስ ሁኔታ ተጠሪ ተወዲድሮ ምደባ እንዱደረግ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከፋደራል ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አስተዲደር ፍ/ቤት ሲሆን ይግባኝ ባይ የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ቅሬታ መልስ ሰጪ የአሁን አመልካች በድልድል (JEG) አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ካለአግባብ የተሰጠኝ የስራ ምደባ ተገቢ ባለመሆኑ ጅማ ቅርንጫፍ በሚገኘው አቤቱታና ቅሬታ ማስተናገጃ ቡድን መሪ ደረጃ XIV ስራ መደብ ላይ ተወዲድሬ ምደባ ላገኝ ሲገባ እንዲልወዲደር መደረጉ ካለአግባብ በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ቅሬታውን አቅርቧል። መ/ሰጪም ይግባኝ ባይ ለጠየቀው የስራ መደብ የተቀመጠውን የትምህርት ዛግጁነት የማያሟላ በመሆኑ በስራ መደብ ላይ ለውድድር አልቀረበም።
በመሆኑም ቅሬታው ውድቅ ይሁንልኝ በሚል መልስ ሰጥተዋል። የፍደራል ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አስተዲደር ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 039/2011 ታህሳስ 25 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ ላከራከረው የስራ መደብ አቤቱታና ቅሬታ ማስተናገጃ ቡድን መሪ ደረጃ XIV ስራ መደብ በተዖጋጀው ፍርም 14 የስራ መዖርዛር ላይ በመ/ሰጪ መ/ቤት የድልድል አፈጻጸም (JEG) መመሪያ መሰረት በማድረግ ለስራ መደቡ የተጠየቀው የትምህርት ዛግጁነት፣ በማናጅመንት በህዛብ አስተዲደር፣ በሰው ሀብት ሥራ አመራር እና በሳይኮልጅ የመጀመሪያ ዱግሪ እና 8 ዓመት የስራ ልምድ ያለው ነው። ይግባኝ ባይ ያለው የትምህርት ዛግጅት በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዱግሪ ያለው መሆኑ ታውቋል፣ ላከራከረው የስራ መደብ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዱግሪ ያለው ሰው ብቁ መሆን አለመሆኑን አዱስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙያዊ አስተያየት እንዱሰጥ ተጠይቆ በስራ መደቡ የተሰጠውን ተግባር ለማከናወን እና አላማውን ለማስፈጸም የሚከለክል አለመሆኑን አንዱሁም ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አደረጃጀት ስራ ምዖናና ክፍያ ጥናት ክፍል የተሰጠው ማብራሪያ ላከራከረው የስራ መደብ በተዖጋጀው ፍርም 14 የስራ መዖርዛር ላይ ተጨማሪ የትምህርት ዓይነት የሚያስፈልግ ከሆነም በተቋሙ ጠያቂነት መተካት የሚቻል መሆኑን ገልጾ አቅርቧል። በመሆኑም በተጠቀሰው የትምህርት ዛግጁነት በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዱግሪ ባለመገለጹ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዱግሪ ያለው ሰው ባከራከረው የስራ መደብ ላይ እንዲይወዲደር መደረጉ ለጉዲዩ አግባብ ያለውን ነጥብና የስራ ምዖና ደረጃ አወሳሰን የመንግስት ሰራተኞች የስራ ድልድል መመሪያ መሰረታዊ መርህና ዓላማን ያላገናዖበና የሜሪቱን ስርዓት ያልተከተለ በመሆኑ አልተቀበልነውም፣ የመ/ሰጪ ውሳኔ ተሽሯል። ባከራከረው የስራ መደብ ላይ እንደገና ይ/ባይንም በማወዲደር ምደባ እንዱደረግ ሲል ወስኗል። መ/ሰጪ የአሁን አመልካች ለፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታ በመ/ መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ትእዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል ይግባኙን ሰርዜታል።
የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል። መዛገቡም ተመርምሮ በስር ፍ/ቤት የተጠሪ የትምህርት አይነት ኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ደረጃ ዱግሪ ለክርክር ምክንያት በሆነው የስራ መደብ ዛርዛር ውስጥ ባልተካተተበት እና ሲቪል ሰርቪስ ተጠይቆ ተጨማሪ የትምህርት ዓይነት የሚያስፈልግ ከሆነ በተቋሙ ጠያቂነት ማካተት እንደሚቻል ምላሽ በሰጠበት ሁኔታ እና በዘህ አግባብ እንዱካተት ባልተደረገበት የስር ፍ/ቤት የተጠሪ የትምህርት ዛግጅት ለአከራካሪው የስራ መደብ የሚጋብዖው መሆኑን አመልካችን አሳውቆ በ15 ቀን ውስጥ ‛በጄኢጂ“ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት በስራ መደቡ ላይ እንዱመደብ የወሰነበትን አግባብ ከፏብሉክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ሚ/ር በነጥብ የስራ ምዖናና ደረጃ አወሳሰን ዖዳ የመ/ሰ/ድ/አ/መ/ ግንቦት 2008 ዓ/ም ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ ሚያዛያ 25 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዲልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ሲል ተከራክሯል። አመልካችም ግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲሆን፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልሱን እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ከተያዖው ጭብጥ አንጻር መርምረናል። እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ባከራከረው የስራ መደብ አቤቱታና ቅሬታ ማስተናገጃ ቡድን መሪ ደረጃ XIV ላይ ተወዲድሮ ለመመደብ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አጥንቶ ስራ ላይ ባዋለው፣ በነጥብ የስራ ምዖናና ደረጃ አወሳሰን ዖዳ የመንግስት ሰራተኞች ድልድል አፈጻጸም መመሪያ መሰረት የሚያስፈልገው የትምህርት ዛግጁነት በማናጅመንት በህዛብ አስተዲደር፣ በሰው ሀብት ሥራ አመራር እና በሳይኮልጅ የመጀመሪያ ዱግሪ ያለው መሆኑ አላከራከረም። ባከራከረው የስራ መደብ በመመሪያው መሰረት ተወዲድሮ ለመመደብ በተዖጋጀው ፍርም 14 የስራ መዖርዛር ተፈላጊው የትምህርት ዛግጁነት በማናጅመንት በህዛብ አስተዲደር፣ በሰው ሀብት ሥራ አመራር እና በሳይኮልጅ የትምህርት ዓይነት ብቻ ተጠቅሶ የተቀመጠ ሲሆን ዛርዛሩ ተመሳሳይ ላላ የትምህርት ዓይነትን በሚጋብዛ መልኩ የተቀመጠ አይደለም። እነዘህ የተጠቀሱት የትምህርት ዓይነቶች ላከራከረው የስራ መደብ ተፈላጊው የትምህርት ዓይነቶች ሲሆኑ ጥናት ተደርጎ ለቦታው ትክክለኛው የትምህርት ዓይነቶች መሆናቸው ተለይቶ የተወሰደ ናቸው።
ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አደረጃጀት ስራ ምዖናና ክፍያ ጥናት ክፍልም በፍ/ቤት ጥያቄ የተሰጠው ማብራርያም መ/ቤቱ የአሁን አመልካች የሚጠይቅ ከሆነ በተጨማሪነት ለቦታው የሚያስፈልግ የትምህርት ዓይነት ካለ በጥናት የሚካተት መሆኑን የሚገልጽ ሲሆን የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ለቦታው በጥናት በወጣው መመሪያ መዖርዛሩ መሰረት ተፈላጊ የትምህርት ዓይነት ነው የሚል መልዕክት የለውም። ላላው በፍ/ቤት ጠያቂነት ከአዱስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቀረበውም ሙያዊ አስተያየት ሲሆን ላከራከረው የስራ መደብ ኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ሉሰራ እንደሚችል ሙያዊ አስተያየት መስጠቱ፣ ጥናት ተደርጎበት ላከራከረው የስራ መደብ ተፈላጊ የትምህርት ዓይነቶች ተብለው ተዖርዛረው የተቀመጠውን መመሪያ በመጣስ ተጨማሪ የትምህርት ዓይነት በፍ/ቤት እንዱጨመርበት ለመወሰን የሚያበቃ ምክንያት አይደለም። ይህ ሆኖ የአመልካች መ/ቤት የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር ተጠንቶ ስራ ላይ ከዋለው መመሪያ በግልጽ አስቀምጦ ካለው ውጪ ላከራከረው የስራ መደብ ተወዲድሮ ለመመደብ አስፈላጊ የሆነው የትምህርት ዛግጁነት በግልጽ ተዖርዛረው እያለና ትርጉም ባላስፈለገበትና ባላከራከሩበት ሁኔታ የአሁን አመልካች መ/ቤት ላላ ተጨማሪ የትምህርት ዓይነት እንደሚያስፈልገው ባልጠየቀበት በግልጽ በመመሪያው ከተዖረዖሩት ውጪ የትምህርት ዓይነት ኢኮኖሚክስ ተካቶ እንዱወዲደር መወሰኑ የፏብሉክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ሚኒስቴር በነጥብ የስራ ምዖናና ደረጃ አወሳሰን ዖዳ የመንግስት ሰራተኞች ድልድል አፈጻጸም መመሪያ የሚጥስ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
የፍደራል ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አስተዲደር ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 039/2011 ታህሳስ 25 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ እና የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአሁን ተጠሪ ላከራከረው የስራ መደብ አቤቱታና ቅሬታ ማስተናገጃ ቡድን መሪ ደረጃ XIV ላይ የአመልካች መ/ቤት ጂማ ቅርንጫፍ ተወዲድሮ ለመመደብ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አጥንቶ ስራ ላይ ባዋለው፣ በነጥብ የስራ ምዖናና ደረጃ አወሳሰን ዖዳ የመንግስት ሰራተኞች ድልድል አፈጻጸም መመሪያ መሰረት የትምህትር ዛግጁነት ስለማያሟላ በአመልካች መ/ቤት መከልከለ ተገቢ ነው ብለናል።
በዘህ መዛገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
በዘህ ላይ የተሰጠው የአፈጻጸም እግድ ተነስቷል። ይጻፍ።
የዘህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No specific laws extracted.
No topics extracted.