ከወራሾቹ አንደ ለውርስ የሚከፍለው እዲ ያለበት እንደሆነ የውርስ ንብረት ክፍፍል ከመደረጉ በፉት የውርስ እዲ ሉቀነስ የሚገባ ስለመሆኑ በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 1014፤1090
No summary available.
ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካቾች፡-
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዖነበች ከሳዬ - ቀረቡ።
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የነገሩ አመጣጥ የውርስ ንብረት ክርክርን የሚመለከት ነው።ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን ተጠሪ ከሳሽ ሲሆኑ የአሁን አመልካቾች ደግሞ ተከሳሾች ነበሩ። የሥር ከሳሽ /የአሁን ተጠሪ/ መጋቢት 6 ቀን 2008 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ አቤቱታ ከሳሽ የሟች እናታቸው የወ/ሮ እልፍነሽ ሄይ ብቸኛ ወራሽ መሆናቸውን፣ የሟች አናታቸው የውርስ ሀብት በመ/ቁ. 97412 ተጣርቶ ግንቦት 26 ቀን 2007 ዓ/ም መጽደቁን፣ ሟች እናታቸው ከሟች አቶ ካሳዬ ደሳለኝ ጋር በትዲር አብረው የቆዩ በመሆናቸው የሟች አቶ ከሳዬ ድርሻ በወራሾቻቸው በኩል በመ/ቁ.
62253 ተጣርቶ የቀረበ መሆኑን፣ የሟቾቹን የውርስ ንብረት የውርስ አጣሪ ተሹሞ ያጣራ መሆኑንና በፍርድ ቤት መጽደቁን፣ ተከሳሾች ከጥቅምት 22 ቀን 2002 ዓ/ም እስከ ሀምላ 19 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ እንዱሁም ከግንቦት 1 ቀን 2005 እስከ ሚያዛያ 30 ቀን 2006 ዓ/ም ድረስ ከመኖሪያ ቤትና ወፍጮ በወር ብር 20,513 /ሃያ ሺህ አምስት መቶ አስራ ሶስት/ ለ31 ወር ሲሰበስቡ መቆየታቸውን፣ በአጠቃላይ ብር 20,513 X 31 ወር = 635,903 /ስድስት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ዖጠኝ መቶ ሶስት/ ብር መሰብሰቡን ገልጸው የከሳሽ ድርሻ ብር 211,967 /ሁለት መቶ አስራ አንድ ሺህ ዖጠኝ መቶ ስልሳ ሰባት ብር/ ከእነ ወለደ ተከሳሾች እንዱከፍለ እንዱሁም ለክርክሩ የወጣውን ወጪ እንዱተኩ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተከሳሾች ሚያዛያ 26 ቀን 2008 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የወፍጮ ቤት ገቢን በተመለከተ ሟች ከሞቱበት ከ2002 ዓ/ም ጀምሮ ወፍጮ ቤት እስከተከራየበት መስከረም 29 ቀን 2005 ዓ/ም ድረስ ያለው ብር ሲሰባሰብ ቢቆይም ከቤት ኪራይና የወፍጮ ቤት ኪራይ ከሚገኘው ገቢ ውስጥ ለመንግሥት የሚከፈል እዲ፣ የከሳሽ ወላጅ እናት በህይወት እያለ የወሰደትን ለቀለብና ለህክምና የወጣ በፍርድ ቤት የተወሰነውን ተቀንሶ ድርሻቸውን ብር 2,865.15 /ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ አምስት ብር ከአስራ አምስት ሳንቲም/ ስለሚደርሳቸው መውሰድ ይችላለ በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን የተመለከተው ፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን መርምሮ የቤት ኪራይ በተመለከተ በመዛገብ ላይ ግራ ቀኙ በተገኙበት የተጣራው ንብረት ውስጥ የቤት ኪራይ በአጠቃላይ ብር 435,430 /አራት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰላሳ/ ሲሆን ከዘህ ውስጥ በንብረት አስተዲዲሪዎች እጅ አለ የተባለው ብር 176,840 /አንድ መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ አርባ/ ሲሆን በተከሳሾች እጅ የሚገኘው ብር 258,590 /ሁለት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ዖጠና ብር/ መሆኑ ነው። የወፍጮ ቤት ገቢን በተመለከተ ከውርስ አጣሪ ሪፕርት ለመረዲት የተቻለው ጣልቃ ገብ የነበሩ የአሁን ከሳሽ እናት ያቀረቡት ገቢ ብር 618,750 /ስድስት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር/ ሲሆን በወቅቱ በውርስ አጣሪ መዛገብ ላይ ተጠሪዎች የነበሩ የአሁን ተከሳሾች በኩል የታመነ ነው የተባለው ብር 432,960.16 /አራት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ዖጠኝ መቶ ስልሳ ብር ከአስራ ስድስት ሳንቲም/ ነው። ከዘህ ገንዖብ ውስጥ በንብረት አስተዲዲሪዎች እጅ የነበረው ብር 133,860 /አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ብር/ ስለሆነ ተከሳሾች በውርስ አጣሪ ሪፕርት ላይ ያመኑት ገቢ ቢወሰድ እንኳን በውርስ አስተዲዲሪዎች እጅ የነበረው ሲቀነስ ብር 299,100 /ሁለት መቶ ዖጠና ዖጠኝ ሺህ አንድ መቶ ብር / ይሆናል። ስለዘህ ከቤት ኪራይ 258,590 /ሁለት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ዖጠና ብር/ እና ከወፍጮ ብር 299,100 /ሁለት መቶ ዖጠና ዖጠኝ ሺህ አንድ መቶ ብር / ሲደመር ብር 557,690 /አምስት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ዖጠና ብር/ ይሆናል። በውርስ አጣሪ ሪፕርት በወጪነት የተያዖው በጋራ ብር 7,051 /ሰባት ሺህ አምሳ አንድ ብር/ ሲሆን ይህ እዲ ለሶስት ሲካፈል ብር 2,350 /ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ ብር/ ይሆናል። ለከሳሽ አውራሽ ቀለብ ተብል የታሰበው ብር 7,890 /ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ዖጠና ብር/ ስለሆነ የከሳሽ ድርሻ ወጪ ብር 10,240 /አስር ሺህ ሁለት መቶ አርባ ብር/ ይሆናል። ይህ ወጪ ከከሳሽ ወጪ የሚተካ ይሆናል። ስለሆነም አጠቃላይ ገቢ ብር 557,690 /አምስት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ዖጠና ብር/ ለ3 ሲካፈል ብር 185,896.66 /አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ዖጠና ስድስት ብር ከስልሳ ስድስት ሳንቲም/ ሲሆን ከዘህ ውስጥ የከሳሽ ብር 10,240 /አስር ሺህ ሁለት መቶ አርባ ብር/ ሲቀነስ ብር 175,656.66 /አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከስልሳ ስድስት ሳንቲም/ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከውርስ አጣሪ ሪፕርት ተረድቷል። ስለዘህ ተከሳሾች ለከሳሽ በፍርድ ቤት ቀርቦ በፀደቀው የውርስ አጣሪ ሪፕርት መሰረት ብር 175,656.66 /አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር/ ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ሉከፍለ ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁን አመልካቾች ይህን ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን የይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይግባኛቸውን ሰርዜባቸዋል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ውሳኔውን ለማስለወጥ ሲሆን የአመልካቾች አቤቱታ ይዖትም በአጭሩ፡- የውርስ አጣሪ ሪፕርቱ ላይ በወጪነት /በእዲነት/ የተመዖገበውን ብር 185,455.25 /አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ አምስት ብር ከሃያ አምስት ሳንቲም/ ፍርድ ቤቱ በኮ/መ/ቁ. 62253 ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ/ም ያለማንም ነቀፊ እና ተቃውሞ አጽድቆት እያለ የሥር ፍርድ ቤት በወጪነት ሳይዛ ዛም ብል ማለፈ አግባብነት የላለው በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው።
ስለሆነም አመልካቾች የተጠሪ ድርሻ የሆነን ወጪ (እዲ) የምንወስድበት የህግ አግባብ የለም።በመሆኑም ለተጠሪ ሉከፈል የሚገባው የገንዖብ መጠን በፀደቀው የውርስ አጣሪ ሪፕርት መሰረት ከሚደርሳቸው የውርስ ድርሻ ብር 185,896.66 /አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ዖጠና ስድስት ብር ከስልሳ ስድስት ሳንቲም/ ላይ ወጪዎችን /እዲዎችን/ ተቀናሽ በማድረግ ነው። ስለሆነም ለተጠሪ ሉከፈላቸው የሚገባው የገንዖብ መጠን ብር 185,896.66 - ብር 61,818.21 - ብር 10,240 = 113,838.21 /አንድ መቶ አስራ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሃያ አንድ ሳንቲም/ ሆኖ እያለ ብር 175,656.66 ይከፈል መባለ አግባብነት የላለው ውሳኔ በመሆኑ እና ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ሥልጣን የላለው በመሆኑ ሉሻር የሚገባው ነው የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ የጉዲዩ አከራካሪ የሆነውን የውርስ ንብረት ለማቆየት አመልካቾች በውርስ አጣሪ በተራ ቁጥር 7 ላይ የተጠቀሰውን ወጪ ሳይቀንስ ወይም ሳይተቸው በማለፍ ይክፈለ ያለበት አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ይቅረብ ሲል ትዔዙዛ ሰጥቷል።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው በጠበቃቸው በኩል ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ/ም ባቀረቡት መልስ የአመልካቾች ክርክር ስላትን፣ ፍሬ ነገርን እና ማስረጃን የተመለከተ እንጂ የህግ ትርጉም ጥያቄ የሚያስነሳ ስላልሆነ ለሰበር ችልት ቀርቦ የሚታይበት የህግ አግባብ የለም። በውርስ አጣሪ ሪፕርቱ ተራ ቁጥር 7 ላይ ተጠቅሶ በፍርድ ቤትም የፀደቀውን እዲ ብር 185,455.25 በተመለከተ ዖጠኙ ባለጉዲዮች የደረሱበት እና ፍርድ ቤቱም ያፀደቀው ስምምነት በውርስ አጣሪው ሪፕርት ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የውርስ እዲውን እኩል ለመከፊፈል ነው። በዘሁ መሰረት ብር 185,455.25 እዲ ለዖጠኝ እኩል ሲካፈል ተጠሪ የሚደርስባቸው ብር 20,6006.00 /ሃያ ሺህ ስድስት መቶ ስድስት ብር/ እንጂ ብር 61,818.25 /ስልሳ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ስምንት ብር ከሃያ አምስት ሳንቲም/ አይደለም።
በሥር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር የአሁን ተጠሪ ሉከፈለኝ ይገባል ሲለ ያቀረቡት የውርስ ሀብት ገቢ ድርሻ መጠን በግልጽ የተቀመጠ ቢሆንም ከውርስ ሀብቱ እዲ ላይ በውርስ አጣሪው ሪፕርት መሰረት ሉከፍለት የሚገባ ያልከፈለት ወይም ቀድመው ያላቻቻለት የእዲ ድርሻ መኖሩን አመልካቾች ያቀረቡት ምንም ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም። በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 329 በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያልተነሳ አዱስ ክርክር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሉቀበል እንደማይችል ተቀምጧል።
ከብር 185,455.25 የውርስ እዲ ላይ ያልተከፈለ ወይም ያልተቻቻለ የተጠሪ የእዲ ድርሻ አለ የሚለው የአመልካቾች ክርክር ሥር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያልተነሳ አዱስ ክርክር ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያልተነሳ ክርክር በመሆኑ ደግሞ በይግባኝ ላይም ሆነ በሰበር ችልት ላቀርብ የሚችል አይደለም በማለት ተከራክረዋል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን በውርስ አጣሪ የተረጋገጠውና በፍርድ ቤት የፀደቀው የውርስ እዲ ከውርስ ንብረት ገቢ ላይ ሳይቀነስ ለአሁን ተጠሪ ድርሻቸው እንዱከፈል የተወሰነበት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው እንደሚከተለው ተመርምሯል። የአሁን አመልካቾች አባት፣ የተጠሪ እናት እንዱሁም ላላኛዋ የአመልካቾች አባት ሚስት ንብረት እንዱጣራ ተደርጎ በኮ/መ/ቁ. 62253 ግንቦት 28 ቀን 2006 ዓ/ም በተጻፈ ሪፕርት ለፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት መቅረቡን፣ ፍርድ ቤቱም የቀረበውን ሪፕርት በኮ/መ/ቁ. 62253 ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ/ም ማጽደቁን ተመልክተናል። የውርስ አጣሪው ባቀረበው ሪፕርት ተራ ቁጥር 7 ላይ ከጥቅምት 22/2002 እስከ ግንቦት 28/2006 ዓ/ም ድረስ ያለው ጠቅላላ ወጪ ብር 185,455.25 /አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ አራት መቶ አምሳ አምስት ብር ከሃያ አምስት ሳንቲም/ መሆኑ ተረጋግጧል። በወቅቱ በህይወት የነበሩት የአሁን ተጠሪ አውራሽ ይህን ወጪ እንደማይቃወሙ በመግለጽ መስማማታቸውን የውርስ አጣሪው ሪፕርት ያስረዲል። ይህም የውርስ እዲ በፍርድ ቤት መጽደቁ ግራ ቀኙን አላከራከረም። የአሁን ተጠሪ በዘህ ችልት ባቀረቡት ክርክር አራት ነጥቦችን ያነሱ ሲሆን የመጀመሪያው የአመልካቾች አቤቱታ የስላት ጉዲይ ስለሆነ ለሰበር ክርክር ብቁ አይደለም የሚል ነው። ይህንን ክርክር ስንመለከት የስላት ስህተትን መሰረት ያደረገ ክርክር አይደለም። ምክንያቱም የአመልካቾች ክርክር የታወቀና የተረጋገጠ የውርስ እዲ እያለ እዲው በድርሻ ልክ ሳይቀነስ ተጠሪ ከውርስ ንብረት የሚገኘውን ገቢ ብቻ ሉካፈለ አይችለም በማለት የሚከራከሩ በመሆናቸው ነው። ተጠሪ ለዘህ ችልት ያቀረቡት ላላኛው መከራከሪያ ነጥብ አመልካቾች ለሰበር ያቀረቡት አቤቱታ ፍሬ ነገርን የሚመለከት ስለሆነ ችልቱ ሉያየው አይገባም የሚል ነው። የአመልካቾች ክርክር ደግሞ የተረጋገጠና በፍርድ ቤት የፀደቀ የውርስ እዲ እያለ ተጠሪን የሚመለከተው የውርስ እዲው ድርሻ ሳይቀነስ ከውርስ ንብረት የተገኘውን ገቢ ድርሻ እንዱወስደ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚል ነው። የውርስ እዲዎች አከፊፈል ቅድም ተከተል በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 1014 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ በዛርዛር ተቀምጠዋል። እንዱሁም ከወራሾቹ አንደ ለውርስ የሚከፍለው እዲ ያለበት እንደሆነ እዲው በድርሻው ውስጥ ይታሰባል በማለት የፍትሕብሓር ህግ ቁጥር 1090 በግልጽ ይደነግጋል። ከእነዘህ ድንጋጌዎች የምንመለከተው የውርስ እዲ ካለ የውርስ ንብረት ክፍፍል ከመደረጉ በፉት የውርስ እዲ ሉቀነስ የሚገባ መሆኑን ነው። በተያዖው ጉዲይ አመልካቾች የውርስ እዲ ስላለ ከውርስ ንብረት ገቢ ላይ የሚደርሳቸው ድርሻ ላይ ተቀንሶ ለተጠሪ የሚገባቸው እንዱከፈል መደረግ ሲገባው አልተደረገም በማለት ያቀረቡት ቅሬታ ነጥብ እንደ ተጠሪ አባባል ፍሬ ነገርን የሚመለከት ክርክር ሳይሆን ከላይ እንደተገለጸው የህግ መሰረት ያለው ወይም የህግ ነጥብን የሚመለከት ክርክር ነው። ተጠሪ ለዘህ ሰበር ያቀረቡት ሶስተኛው የመከራከሪያ ነጥብ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችልት በኮ/መ/ቁ. 62253 ላይም ሆነ በውርስ አጣሪው ሪፕርት ላይ ተከራካሪ ወገን ሆነው የቀረቡት ግለሰቦች ብዙት በዘህ የሰበር ክርክር ላይ አመልካቾች እና ተጠሪ ሆነው የቀረቡትን ጨምሮ አንድ አመልካች፣ ሶስት ተጠሪዎች እና አምስት ጣልቃ ገቦች በአጠቃላይ ዖጠኝ ባለጉዲዮች ናቸው። በውርስ አጣሪ ሪፕርቱ ተራ ቁጥር 7 ላይ ተጠቅሶ በፍርድ ቤትም የፀደቀውን ብር 185,455.25 /አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ አራት መቶ አምሳ አምስት ብር ከሃያ አምስት ሳንቲም/ በተመለከተ ዖጠኝ ባለጉዲዮች የደረሱበት እና ፍርድ ቤቱም ያፀደቀው ስምምነት በውርስ አጣሪው ሪፕርት ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የውርስ እዲውን እኩል ለመከፊፈል ነው። በዘሁ መሰረት ብር 185,455.25 እዲ ለዖጠኝ እኩል ሲካፈል ለተጠሪ የሚደርሳቸው ድርሻ ብር 20,606.45 እንጂ ብር 61,818.45 አይደለም የሚል ነው። ይህንን መከራከሪያ ነጥብ ከውርስ አጣሪው ሪፕርት እና ሪፕርቱ ከፀደቀው ውሳኔ ላይ ተመለክተናል። የውርስ አጣሪው ንብረትን ሲያጣራ በአመልካችነት፣ በተጠሪነት እና በጣልቃ ገብነት የተመዖገቡት የሟች አቶ ካሳ ደሳለኝ ልጆች ሰባት ሲሆኑ ወ/ሮ እልፍነሽ ሄይ ማለትም የአሁን ተጠሪ አውራሽ እናት እና ወ/ሮ ገላዬ በጋሻው የሟች አቶ ካሳዬ ደሳለኝ ሚስቶች ነበሩ። ይህን መሰረት በማድረግ የውርስ አጣሪው የውርስ ንብረቱ በአመልካቾች አባት እና በሁለቱ ሚስቶች አስተዋፅኦ የተፈራ በመሆኑ እኩል ሶስት ቦታ እንዱካፈል በሪፕርቱ ተራ ቁጥር 8 ላይ አስተያየቱን የገለጸ መሆኑንና ይህም ፍርድ ቤት ቀርቦ ማጽደቁን ተመልክተናል። ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ንብረት ለሶስት እኩል የሚካፈል ከሆነ የውርስ እዲም ሶስት ቦታ እኩል ከሚካፈል ወጪ ለዖጠኝ የሚካፈልበት ህጋዊ መሰረት የለም። የአሁን ተጠሪ እንደሚለትም እዲው ለዖጠኝ እኩል እንዱካፈል ስለመስማማታቸው የውርስ አጣሪው ሪፕርት በፍጹም አያሳይም። ይልቁንም በውርስ አጣሪው ሪፕርት ላይ እያንዲንደ ወጪዎች በሙለ የሟች የውርስ ሀብት ጠብቆ ለማቆየት የተደረገ ስለመሆኑ የመደምደሚያ ሀሳብ ስለተደረሰ ተጠሪዎች የአሁን አመልካቾች/ ወጪ በማለት ያቀረቡት በሙለ ቢመዖገብ የሥር አመልካችም፣ 1ኛ ጣልቃ ገብ /የአሁን ተጠሪ እናትም/ እንደማይቃወሙ በመግለጽ መስማማታቸውን ነው። ስለሆነም የአሁን ተጠሪ የውርስ እዲው የሚካፈል ቢሆን እንኳን ለዖጠኝ ሰው ሉካፈል ይገባል በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
የተጠሪ የመጨረሻ መከራከሪያ ነጥብ የውርስ እዲ ስለመኖሩ አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት አንስተው አልተከራከሩም የሚል ነው። ከሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ እንደተመለከትነው የአሁን አመልካቾች በመልሳቸው ላይ የወፍጮ ቤት ገቢን በተመለከተ ሟች ከሞቱበት ከ2002 ዓ/ም ጀምሮ ወፍጮ ቤት እስከተከራየበት መስከረም 29 ቀን 2005 ዓ/ም ድረስ ያለው ብር ሲሰባሰብ ቢቆይም ከቤት ኪራይና የወፍጮ ቤት ኪራይ ከሚገኘው ገቢ ውስጥ ለመንግሥት የሚከፈል እዲ፣ የከሳሽ ወላጅ እናት በህይወት እያለ የወሰደትን ለቀለብና ለህክምና የወጣ በፍርድ ቤት የተወሰነውን ተቀንሶ ድርሻቸውን ብር 2,865.15 /ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ አምስት ብር ከአስራ አምስት ሳንቲም/ ስለሚደርሳቸው መውሰድ ይችላለ በማለት መከራከራቸውን ያሳያል። በዘህ ክርክር ላይ በግልጽ እንደተገለጸው የውርስ እዲ መኖሩን ነው። በመሆኑም አመልካቾች የውርስ እዲ እንደነበረ አንስተው አልተከራከሩም፣በዘህ ችልት አንስተው የተከራከሩት ክርክር ነው በማለት ተጠሪ ያቀረቡት ክርክር በሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ላይ የተመዖገበውን የአመልካቾችን ክርክር ይዖት ያገናዖበ ሆኖ አላገኘነውም።
ሲጠቃለልም የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችልት ተጠሪ የጠየቁትን የውርስ ንብረት ገቢን በተመለከተ የውርስ አጣሪውን ሪፕርት መሰረት በማድረግ የወሰነ ሲሆን ለዘህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነውን በውርስ አጣሪው ተጣርቶ ከቀረበ በኋላ በፍርድ ቤቱም የፀደቀውን የውርስ እዲ ሳይቀንስ ከውርስ ንብረት ላይ ከሚገኘው ገቢ ላይ ለተጠሪ ድርሻቸው እንዱከፈል የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም ይህ ውሳኔ በይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ስህተቱን ሳያርም ይግባኙን መሰረዘ ሲታይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ቀጥል ያለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 111280 በቀን 03/04/09 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 182802 በቀን 25/08/2009 ዓ/ም የሰጠው ትዔዙዛ በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 1/ መሰረት ተሻሽሎል።
የከሳሽ አውራሽ ወጪ ብር 10,240 /አስር ሺህ ሁለት መቶ አርባ ብር/ ከተጠሪ ድርሻ ላይ እንዱቀነስ ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
በውርስ አጣሪ ሪፕርት በተራ ቁጥር 7 ላይ የተገለጸው የውርስ እዲ ብር 185,455.25 በኮ/መ/ቁ. 62253 ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም የፀደቀው የውርስ ንብረት ክፍፍል ለሶስት እኩል እንዱካፈል በተወሰነው መሰረት እዲውም ለሶስት እኩል ተካፍል በሚደርሰው ድርሻ ልክ የአሁን ተጠሪ ብር 61,818.45 /ስልሳ አንድ ሺህ ስምንት መቶ አስራ ስምንት ብር ከአርባ አምስት ሳንቲም/ እዲቸው ነው ተብል ተወስኗል።
ለተጠሪ ሉከፈላቸው ይገባል ተብል ከተወሰነው ብር 175,656.66 /አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከስልሳ ስድስት ሳንቲም/ ላይ ብር 61,818.45 /ስልሳ አንድ ሺህ ስምንት መቶ አስራ ስምንት ብር ከአርባ አምስት ሳንቲም/ ተቀንሶ ብር 113,838.21 /አንድ መቶ አስራ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሃያ አንድ ሳንቲም/ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር አመልካቾች ለተጠሪ ሉከፍለ ይገባል ተብል ተወስኗል።
የዘህን ችልት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.