No summary available.
መጋቢት 02 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ደጀኔ አያንሳ ኑረዱን ከድር ብርቅነሽ እሱባለው አመልካቾች፡- ---1. አቶ ወድወሰን ታደሰ ይስማ 2. ወ/ሮ ወይንሸት ደስታ አጠረዉ የላልችም ወኪል 2ኛ አመልካች ቀርበዋል 3. ወ/ሪት ጥሩነሽ በቀለ ስዩ ተጠሪ፡- የለም መዛገቡ ለዙሬ የተቀጠረው ለምርመራ ሆኖ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል ።
ኢትዮጵያዊ እናት እና አባት የሆኑት 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች በትዉልድ ኢትዮጵያዊ በዚግነት አሜሪካዊ የሆኑት የ2ኛ አመልካች እህት 3ኛ አመልካች የ1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ልጅ የሆነችዉን ተማሪ ኤፍራታ ወንደሰን ቤተሰብ ለልጅ የሚያደርገዉን ሁለ ከልጅነቷ ጀምሮ ካለችበት ሀገር ሆና ስትንከባከባት የነበረች እና በምትኖርበት ሀገርም ልጇ መሆኗን የተለያዩ ፍርሞችን መሙላቷን አንስተዉ በአመልካቾች መካከል የተደረገዉ የተማሪ ኤፍራታ ወንደሰን የጉዱፈቻ ስምምነት እንዱፀድቅላቸዉ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዉ ፍርድ ቤቱ በመዛገብ በ2/11/2011 በዋለዉ ችልት የዉጭ ሀገር ጉዱፈቻ በአዋጅ ቁጥር 1070/2010 የተከለከለ ነዉ በማለት አቤቱታዉን ባለመቀበል ትዔዙዛ ሰጥቷል። ይህን ትዔዙዛ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የይግባኝ ነባሩ የዉጭ ጉዱፈቻን በአዋጅ ቁጥር 1070/2010 መተካት ያስፈለገዉ ሕጉን ከብሓራዊ የሕፃናት ፕሉሲ ጋር ለማጣጣም ሆኖ ለሕጉ መሻሻል መሰረት የሆነዉ ፕሉሲ ይዖትም ኢትዮጵያዊያን ህፃናት የትዉልድ አከባቢያቸዉን ባህል፣ልማድ፣ወግ እና ማህበራዊ እሴቶችን ጠብቀዉ እንዱያድጉ የተቀረፀ ሲሆን ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን የዉጭ ሀገር ዚጎች እንደ ሀገሪቱ ዚጋ በኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ፣አስተዲደርዊ ጉዲዮች እንዱሳተፈ ህግ ወቶ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የዉጭ ሀገር ጉዱፈቻን የሚከለክል የህግ ማሻሻያ መደረጉ እና ይህ ክልከላ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን የዉጭ ሀገር ዚጎችን እንደማይመለከት በግልጽ አለመደንገጉ ዔገዲዉ እነሱንም የሚጨምር መሆኑን ያመላክታል በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ ሕግ ቁጥር 337 መሰረት በመዛገብ ላይ ታህሳስ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የተሰጠዉ ብይን መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነዉ በማለት በሰበር እንዱታረምላቸዉ አመልካቾች ጥር 14 ቀን 2012 ዓ.ም ጠይቀዋል።
አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ ይዖት በአጭሩ፥-ተጠቃሹ አዋጅ የከለከለዉ በአመልካቾች መካከል የተደረገዉ የጉዱፈቻ ዉል ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ዚጋ ለላላ ሀገር ዚጋ በጉዱፈቻ ሲሰጥ ሆኖ እያለ የጉዱፈቻ ዉል ሰጪዎች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ 2ኛ የጉዱፈቻ ዉል ሰጪ የጉዱፈቻ ዉል ተቀባይ ታላቅ እህት ሆኖ ባለዉ የመረዲዲት ባሕህል በጉዱፈቻ ልትወስዲት የፈለገችዉን ተማሪ ኤፍራታ ወንደሰን በእናት እና አባት ለልጅ መደረግ የሚገባዉን ሁለ እያደረገች አሁን እስካለችበት እድሜ የምትንከባከባት እና በምትኖርበት ሀገርም ልጄ በማለት ፍርማሉትዎችን አሟልታ የጉዱፈቻ ዉለን መፅደቅ ብቻ የምትጠባበቅ መሆኑን ገልፀዉ ያቀረቡት የጉዱፈቻ ዉል እንዱፀድቃላቸዉ ጠይቀዋል።የሰበር አጣሪ ችልቱም የጉድፈቻ ጥያቄ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑትን የዉጭ ሀገር ዚጎችን ያካትታል ወይስ አያካትትም የሚለዉን ከአዋጅ ቁጥር 1070/2010 እና ቤተሰብ ህጉ አላማ እና አተረጓገም አንፃር ለማጣራት መዛገቡ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ትዔዙዛ ሰቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና በዘህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ከላይ የተጠቀሰዉን የሚመስል ሲሆን ችልቱም መዛገቡን 3ኛ አመልካች የጉዱፈቻ ዉለን ለመቀበል አይችለም ተብል የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን /አለመሆኑን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር እንደሚከተለዉ መርምሯል።ጉዱፈቻ ከሥጋ መወለድ ዉጭ ወይንም የደም ትስስር ሳይኖር በህግ ልጅነት ወይንም የልጅ ቤተሰብ ግንኙነት የሚፈጠርበት ህጋዊ ተግባር (juridical act) ነዉ።ይህ ተግባር ጥንታዊ ሆኖ የተስፊፊዉ እና ብዘ ሀገሮች የህግ ሥርዓታቸዉ አካል ማድረግ የጀመሩት ከ2ኛ ዓለም ጦርነት ወዱህ ነዉ።በኢትዮጲያም የጉዱፈቻ ባህል በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍልች ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል።በጥንቱ ዖመን ጉዱፈቻ ይደረግ የነበረዉ ጉዱፈቻ አድራጊዉን በእርጅና ጊዚ ለመርዲት፣ወራሽ እንዱያገኝ ፣ዖሩ እንዱቀጥል፣ሴት ወይንም ወንድ ልጅ ለላላቸዉ ለመስጠት ወዖተ ሆኖ በአጠቃላይ ለጉዱፈቻ አዱራጊዉ ጥቅም ተብል የሚደረግ ነበር።በተፈጥሮ እና ሰዉ ሰራሽ ክስተቶች ምክንያት መፈናቀል እየበዙ ሲመጣ ወላጅ አልባ ለሆኑት እና ተጥል የተገኙ ህፃናትን ለመታደግ ጉዱፈቻ እዉነተኛ የቤተሰብ ተቋም እየሆነ መቷል።በዖመናዊዉ ሕግ የጉዱፈቻ ዓላማ የሕፃናት ደህንነትን (best interst of the child) በማስጠበቅ ሕፃናት በሥጋ ከወለዶቸዉ ቤተሰብ ዉጭ ተተኪ ቤተሰብ እንዱያገኙ ለማስቻል ነዉ።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እ. ኤ. አ ታህሳስ 20 ቀን 1989 ዓ.ም ፀድቆ መስከረም 2 ቀን 1990 ዓ.ም በሥራ ላይ የዋለዉ ኢትዮጵያም ተቀብላ ያፀደቀችዉ የሕፃናት መብት ኮንቬንሺን አንቀጽ 20 ላይ እንደተገለጸዉ ተዋዋይ ሀገሮች ከቤተሰባቸዉ ለተለዩ ሕፃናት አማራጭ እንክብካቤ የሚያገኙበት መንግስት ማዖጋጀት ያለበት መሆኑንና ከዘህ ዉስጥ ጉዱፈቻ አንደ መሆኑን አንቀጽ 20 የሚደነግግ ሲሆን በአንቀጽ 21(ለ) መሰረት የዉጭ ሀገር ጉዱፈቻ የሚፈቀደዉ ሕፃናት በሀገር ዉስጥ አማራጭ እንክብካቤ የሚያገኙበት ማዔከል የላለ እንደሆነ መሆኑን ያስረዲል።በሀገር ዉስጥ እና በዉጭ ሀገር የሚደረግ ጉዱፈቻ እኩል ጥበቃ የሚደረግላቸዉ መሆኑን፣ጉዱፈቻ ዉስጥ ተሳትፍ ያላቸዉ አካላት የማይገባ ጥቅም እንዲያገኙ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑና የሕጉን ዓላማ ለማራመድ በሀገሮች መካከል የሁለትዮሽ እና ላልች ስምምነቶች እንደሚደረጉ አንቀጽ 21(ሐ)፣(መ) እና (ሰ) ይደነግጋል።የአፍርካ ሕፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር አንቀጽ 24(ለ) የሕፃናት መብቶች ስምምነቶች በተቀበለ ወይንም ባፀደቁ ሀገራት መካከል የዉጪ ሀገር ጉዱፈቻ እንደመጨረሻ አማራጭ የሚደረግ መሆኑና አንቀጽ 24(ረ) ሥር ጉዱፈቻ የተደረገዉ የሕፃናት ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችለ ሥርዓቶችን መዖርጋት ግዳታ መሆኑን ያስረዲል።እነዘህ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸዉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ የሕግ አካል መሆናቸዉን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 9(4) ይደነግጋል።
የሕጻናት መንት ኮንቬንሽን በአዋጅ ቁጥር 11/1984 የጸደቀ ሲሆን የአፍሪካ ሕጻናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 283/1994 ጸድቋል። በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት ስምምነቶች የዉጭ ሀገር ጉዱፈቻ በሀገር ዉስጥ አማራጭ ሕፃናት ከወላጆቻቸዉ ዉጭ እንክብካቤ የሚያገኙበት መንገድ በማይኖርበት ወቅት የሚደረግ ሆኖ ሕፃናቱ ለተለያየ የሰበአዊ መብት ጥሰት እንዲይጋለጡ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ ያለበት መሆኑን ያስረዲለ።
መንግስት እጓለ ሙታን በጉዱፈቻ የሚያድጉበትን ሥርዓት እንደሚያመቻች ሕገ መንግስቱ አንቀጽ 36(5) ይደነግጋል።የቤተሰብ ሕጉን ለማሻሻል ካስፈለጉት ምክንያቶች ዉስጥ አንደ ለሕፃናት ደህንነት ቅድሚያ ለመስጠት መሆኑ ከተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 መግቢያ መገንዖብ ይቻላል።በዘህ አዋጅ አንቀጽ 194(3)(መ) መሰረት ጉዱፈቻ አድራጊዉ የዉጭ ሀገር ዚጋ ላሆን የሚችለዉ ሕፃኑ በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚያድግበት ሁኔታ አለመኖሩ ሲረጋገጥ ሆኖ አፈፃፀሙም በአንቀጽ 193 ሥር ተመላክቷል።የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ ለ17 ዓመታት በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ሚያዘያ 2009 ዓ/ም የወጣዉ የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዳሞክራሲያዊ ሪፐብላክ መንግስት የህፃናት ፕሉሲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ የሚገኙት ህፃናት በኢትዮጵያ ባህል፣በአከባቢያቸዉ ወግ ፣ልማድና በማህብረሰባዊ እሴት ታንፀዉ እንዱያድጉ ለማድረግ በአገር ዉስጥ ባለ አማራጭ የድጋፍ እና እንክብካቤ አገልግልቶች ማለትም በማህብረሰብ አቀፍ ድጋፍ እና እንክብካቤ፣በሀገር ዉስጥ ጉዱፈቻ፣በአደራ ቤተሰብ እና በመልሶ ማቀላቀል እና ማዋሀድ ፔሮግራሞች ብቻ እንዱደረግ ማድረግ ከዛርዛር ዓላማዎቹ ዉስጥ አንደ ነዉ።ፕሉሲዉ ዉስጥ እንደ ዋና ዋና ጉዲዮች ከተጠቀሱት መካከል በአስቸጋር ሁኔታ ዉስጥ ያለት ሕፃናት የሚደገፈበትን የሚመለከት ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸዉን ያጡ ተንከባካቢ የላላቸዉ ሕፃናት የቤተሰብ ፍቅር ፣ እንክብካቤ እና ጥበቃ አግኝተዉ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸዉ ተሟልተዉ እንዱያድጉ ለማድረግ የሚያስችለ እንክብካቤ የሀገር ዉስጥ ጉዱፈቻ፣የአደራ ቤተሰብ እና በማህብረሰብ አቀፍ ድጋፍ እና እንክብካቤ ፔሮግራሞችን በማስፊፊት ለሕይወታቸዉ ጠቃሚ የሆኑ የምክር አግልግልት ሰጪ ተቋማት እንዱስፊፈ እና ተደራሽ በማድረግ የኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ አገልግልቶችን በጥራት፣ በስፊት በወቅቱ እንዱደርሳቸዉ በማድረግ እንደየ ችግራቸዉ ዓይነት በማህበረሰቡ ያለ እሴቶችን በመቀመርና በማስፊፊት በሀገር ዉስጥ ባለ አመራጭ የድጋፍ እና እንክብካቤዎች ዘዳዎች ብቻ እንደሚደገፈ ተመላክቷል።ሀገር ዉስጥ ምርጫ ሲጠፊ ተፈቅድ የነበረዉ የዉጪ ሀገር ጉዱፈቻ ሙለ ለሙለ በማስቀረት ለችግሩ ሀገራዊ መፍትሓ ብቻ በመስጠት የፕሉሲ ምርጫ የተወሰደበት ዋናዉ ምክንያት የዉጭ ሀገር ጉዱፈቻ የተፈጥሮ ቤተሰብ ፍቅር እና እንክብካቤን የማይተካ ከመሆኑም በላይ የዘህ አማራጭ ተጠቃሚ የሆኑት ሕፃናት በማያዉቁት ቋንቋ፣ባህል እንዱያድጉ በመደረጋቸዉ ለማንነት ቀዉስ ፣ለስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ችግሮች ሲጋለጡ በመታየታቸዉ የዉጭ ሀገር ጉዱፈቻ ተመራጭ የድጋፍ እና እንክብካቤ ዚዳ እንዲልሆነ ፕሉሲዉ ያመለክታል።ፕሉሲውን ተግባራዊ ለማድረግ በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ ላይ ማሻሻያ እንደሚደረግ ተገጿል።የዉጭ ሀገር ጉዱፈቻን በሚመለከት የተሻሻለዉን የቤተሰብ ሕግ አንቀጾችን ማሻሻል ያስፈለገዉ በፕሉሲዉ እና በሕጉ መካከል የሚቃረኑ ሀሳቦች በመኖራቸዉ ሁለቱን ሰነድች ለማጣጣም መሆኑ ህጉ ሲወጣ ከተያዖዉ ቃለጉባኤ እና የተሻሻለዉን የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 193 እና 194(3)(መ)ን የሻረዉ አዋጅ ቁጥር 1070/2010 መቅድም (preamble) መረዲት ተችሎል።
የዉጭ ሀገር ዚግነት ያላቸዉ ትዉልደ ኢትዮጵያዊን በሚመለከት በተቀረፀዉ የዱያስፕራ ፕሉሲ በንግድ፣ቱሪዛም፣በዔዉቀት እና ቴክኖልጂ ሽግግር፣የዉጭ ምንዙሪን በማስገኘት ብልም በሀገር ገጽታ ግንባታ ረገድ ዱያስፕራዉ ትልቅ ሀገራዊ ኃላፉነት ተጥልበታል።የፕሉሲዉ ዓላማ በዉጭ ሀገር የሚኖሩት ኢትዮጵያዊ እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ ከትዉልድ ሀገሩ ጋር ያለዉን ትስስር በማጠናከር በልማት፣ሰላምና ዱሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጠንካራ ተሳታፉ ሆኖ ራሱን ጠቅሞ ትዉልድ ሀሩን በመጥቀም በጋራ ለማደግ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ነዉ።ፕሉሲዉን ለማስፈፀም ከወጡት ሕጎች ዉስጥም የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የዉጭ ዚጎችን በትዉልድ ሀገራቸዉ ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 270/1994 አንደ ሲሆን የሕጉ ዓላማ ተብል በአዋጁ መቅድም(preamble) እንዱሁም በቁጥር 3 ከተገለፀዉ መረዲት እንደሚቻለዉ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ከትዉልድ ሀገራቸዉ ጋር ያላቸዉ ግንኙነት እንዱጠነክር የሚፈልጉ በመሆኑ በዉጭ ዚጎች ላይ የተጣለት የመብት ገደቦች ለማላላት የተለያዩ መብቶች እና ጥቅማ ጥቅሞች ባለቤቶች በማድረግ ለትዉልድ ሀገራቸዉ እድገት እና ለወገኖቻቸዉ ኑሮ መሻሻል አስተዋጽኦ እንድያደርጉ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል።በዘሁ አዋጅ በቁጥር 5 ሥር የተጠቀሱት መብቶችም ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት፣ ሀገር ዉስጥ ለመቆየት እና ለመኖር የመግቢያ ቪዙ እና የመኖሪያ ፈቃድ የማይጠየቁ መሆኑ፣ያለ ሥራ ፈቃድ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተቀጥሮ መስራት፣የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት መሆን፣የዉጭ ሀገር ዚጎች ተጠቃሚ እንዲይሆኑ የሚገድቡ ህጎች፣አሰራር፣ልምድ ልዩነት ሳይደረግባቸዉ የኢኮኖሚ፣የማህበራዊ እና አስተዲዲራዊ ጥቅሞችን ማግኘት እንዱችለ እና እንደ ሀገር ዉስጥ ባለሀብት መቆጠር ከፈለጉ ለሀገር ዉስጥ ባለሀብት በተፈቀደ የኢንቬስትመንት መስኮች መሳተፍ እንደሚችለ ያስረዲል።በቁጥር 6 ሥር በመንግስት ደረጃ በሚደረግ ምርጫ መምረጥም ሆነ መመረጥ፣በሀገር መከላከያ፣የሀገር ደህንነት በዉጭ ጉዲይና መሰል የፕለትካ መሥሪያ ቤቶች በመደበኛነት ተቀጥሮ መሥራት እንደማይችለ ገደብ ተጥሎል።የባንክ ሥራ አዋጅን ለማሻሻል የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1159/2012 ህጉን ለማሻሻል ያስፈለገዉ የዉጭ ሀገር ዚግነት ያላቸዉ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን በባንኩ ዖርፍ እንዱሳተፈ እና የባለቤትነት ድርሻ እንዱኖራቸዉ ለማድረግ መሆኑን የአዋጁ መቅድም (preamble) ያስረዲል።የዱያስፕራ ፕሉሲን ለማስፈፀም እና የኢትዮጵያዊያን ዱያስፕራዎችን መብት እና ጥቅም ማስከበር ዓላማዉ ያደረገ የኢትዮጵያ ዱያስፕራ ኤጀንሲ በሚል ስያሜ የህግ ሰዉነት ያለዉ የፋዳራል መንግስት መሥሪያ ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 432/2011 ተቋቁሟል።
ሕግ አዉጭዉ የህፃናቱን ደህንነት አስጠብቅበታለሁ ብል የያዖዉ አቋም ሕዛብ በተወካዮቹ በኩል ያደረገዉ የፕሉሲ ምርጫ ከዱሞክራሲ መርህ አንፃርም ሆነ ከኢ/ፋ/ዱ/ሪ ሕገ መንግስት አዋጅ ቁጥር 1/1987 አንቀጽ 50(3) ድንጋጌ መሰረት በፋዳራል መንግስቱ ከፍተኛ የሥልጣን አካል የወጣ ሕግ በመሆኑ እንዱሁም ከሥልጣን ክፍፍል መርህ (principle of separation of power) አንፃርም የፍርድ ቤት ሥራ ህግ ማዉጣት ስላልሆነ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል የወጣዉ ሕግ መከበር ያለበት ሆኖ ህግ ሲወጣ ሁለንም ጉዲዮች እንዱገዙ አጠቃላይ(general) ባህርይ ስላለዉ ህጉ ሳይቀየር ለህጉ አዱስ ትርጉም በመስጠት በህጉ እና ተጨባጭ በሕብረተሰቡ ኑሮ መካከል ያለዉን ክፍተት በትርጉም በመሙላት ለቀረቡላቸዉ ጉዲዮች እልባት በመስጠት ህግ አዉጭዉን ማገዛ የፍርድ ቤቶች የሥራ ግዳታ ነዉ።በልላ በኩል ሕፃናትን አስመልክቶ የሚወሰደ ማንኛዉም እርምጃዎች የሕፃናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ እንዲለበት የኢ/ፋ/ዱ/ሪ ሕገ መንግስት አዋጅ ቁጥር 1/1987 አንቀጽ 36(2) የሚያስረዲ ሲሆን ይህ ችልትም አግባብነት ያላቸዉን ሕጎች በመመርመር የሕፃናት መብት እና ጥቅም ለማስከበር በቀደምትነት መርህ የሕፃናት ጥቅምና ደህነት (best interest of the child) ስለመሆኑ በመዛገብ ,35710 እና በላልች በርካታ መዙግብት አስገዲጅ ዉሳኔ ሰቷል።
ወደተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ የኢትዮጵያዊያን ዱያስፕራዎች ለሀገር እድገት እና ብልጽግና በሀገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ ሀገር ትልቅ ኃላፉነት የተጣለባቸዉ በሆነ ምክንያት ኢትዮጵያዊ ዚግነታቸዉን ቢያጡም ትዉልድ ሀገራቸዉ ኢትዮጵያ ስለሆነች እና ዚጎቿም ወገኖቻቸዉ ስለሆኑ ነዉ።በትዉልድ ሀገራቸዉም እንደ ዉጭ ዚጋ እንዲይታዩ ልዩ መብት እና ጥቅማ ጥቅሞች ተክብሮላቸዋል።ሕጉ መብቶቻቸዉን ዖርዛሮ በመቀጠል ገድብ ማስቀመጡ ዛርዛሩ ሙለ አለመሆኑን ማሳያ ነዉ።የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የዉጭ ዚጎች ከኢትዮጵያዊያን ዚጎች መብቶች ዉስጥ ጥቂቶቹ ስለተቀነሱባቸዉ ሙለ በሙለ እንደ ላላ የዉጭ ሀገር ዚጋ ማየት ተገቢ አይሆንም።በልላ በኩል ኢትዮጵያዊ ማንነት ያላቸዉን የዉጭ ዚጎች ትልቅ ሀገራዊ ኃላፍነት የተጣለባቸዉ የሀገርቷን ባህል፣ቋንቋ፣እሴት እንደማያዉቁ የዉጭ ሀገር ጉዱፈቻ አድራጊዎች በጉዱፈቻ የሚወስደትን ኢትዮጵያዊ ሕፃን የሀገሩን ባህል፣ወግ ፣ልማድና በማህብረሰቡ እሴት ታንፀዉ እንዲያድግ ተፅኖ በማድረግ፣ፍቅር በመንፈግ ለስነ-ልቦናዊና ማሕበራዊ ችግር ያግልጣቸዋል ብል በማሰብ የሥጋ ዖመድቻተዉን በጉዱፈቻ እንዲይወስደ መከልከል የተጣላባቸዉን ኃላፉነት ካለመረዲት የሚመነጭ ነዉ።ትዉልደ ኢትዩጵያዊያኑ እና በጉዱፈቻ የሚወሰደት ኢትዩጵያዊያን ሕፃናት የጋራ ባህል እና ማንነት ያላቸዉ ሆኖ በዚግነት ብቻ የሚለያዩ ስለሆኑ የህፃናቱ የቀደመ ማንነት በልላ አዱስ ማንነት ለመቀየር ፍላጎት ይኖራቸዋል ተብል አይታሰብም። በተያዖዉ ጉዲይ 3ኛ አመልካች በጉዱፈቻ ለመቀበል ለምትፈለገዉ ልጅ አክስት ስትሆን ምንም የህግ ግዳታ ሳይኖርባት በማህብረሰቡ ዉስጥ ባለዉ የመረዲዲት ባህል እናት እና አባት ለልጅ የሚያደርጉትን ሁለ እያደረገች እና እንደ ልጇ በምትኖርበት ሀገር ያስመዖገበች መሆኑን ከመዛገቡ መረዲት ተችሎል።3ኛ አመልካች እና በተማሪ ኤፍራታ ወንደሰን መካከል የደም ግንኙነት መኖሩ፣ሕጋዊ ግዳታ ሳይኖርባት ስትረዲት መቆየቷ በራሱ ለቆየዉ የመረዲዲት እሴታችን ያላትን ቦታ ማሳያ መሆኑ፣የሚጋሩት የጋራ ባሕል ያላቸዉ መሆኑ ለጉዱፈቻ ተደራጊዋ ከቤተሰዋ ጋር ከትዉልድ ሀገሯ የመዉጣት ያክል ሆኖ እያለ እና 3ኛ አመልካች የምትኖረዉ አሜርካ ሀገር ብዘ ትዉልደ ኢትዩጵያዊያን ያለበት መሆኑ ታዲጊዋን ኢትዩጵያዊ ማንነቷን ይዙ በመልካም ስብዔና ለማደግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩ መልካም አጋጣሚ ሆኖ እያለ የኢትዮጵያዊያን ዱያስፕራዎች በሀገር እድገት እና ብልጽግና እንዱሁም ለወገኖቻቸዉ ኑሮ መሻሻል ያላቸዉን ሚና ባለመገንዖብ የህጻኗን የደህነት ቀደምትነት መብት በመንፈግ በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ16/04/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ብይን እና የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ02/11/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሓ/ሥ/ሥ ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተዖጋዉን መዛገብ በማንቀሳቀስ 3ኛ አመልካች ተማሪ ኤፍራታ ወንደሰን በጉዱፈቻ ለማሳደግ የሚያስችላቸዉን መስፈርት ማሟላት አለማሟላታቸዉን በማጣራት ተገቢ ነዉ የሚለዉን ዉሳኔ ይሰጥ ዖንድ መዛገቡ በፍ/ብ/ሓ/ሥ/ሥ ህግ ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰንለታል።
የመዛገቡ ትክክለኛ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረስ።
መዛገቡ ዉሳኔ ስላገኘ ተዖግቷል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፍርማ አለበት።
ፊ/ዖ
No topics extracted.