የኮንደምኒየም ቤት እጣ ከጋብቻ በፉት ወጥቶ የኮንድሚኒየም ቤቱ የሽያጭ ውል የተፈረመው ወይም የተደረገው በጋብቻ ውስጥ በሆነበት ሁኔታ ለቤቱ የተከፈለው ገንዖብ ምንጭ የሆነው ወገን የግለ መሆኑን ካላስረዲ በስተቀር ቤቱ የአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረት ነው ልባል የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የላለ ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 255 ባለመገንዖብ ኢትዮጵያውያንን በጉዱፈቻ እንዲይወስደ መከልከል አግባብነት የላለው ስለመሆኑ የሕፃናት መብት ኮንቬንሺን አንቀጽ 20 ፤የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደህነት ቻርተር አንቀጽ 24(ለ)፣24(ረ) ፤ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 36(5)፤ አዋጅ ቁጥር 1070/2010 መቅድም (preamble)፤ ከተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 193፣ 194(3)(መ) ፤ የዉጭ ዚጎችን በትዉልድ ሀገራቸዉ ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 270/1994 አንቀፅ 5 እና 6
No summary available.
ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ፅጌ በንቲ - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- አቶ ተስፊዬ ታደሰ - ጠበቃ አቶ ይልማ በየነ ቀረቡ ።
መዛገቡ ተመርምሮ ቀጥል ያለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የነገሩ አመጣጥ የፍቺ ውጤትን የሚመለከት ነው ። ጉዲዩ የጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዲ ምድብ ችልት ነው ። የአሁን አመልካች ታህሳስ 5 ቀን 2005 ዓ/ም ያቀረቡት የክስ አቤቱታ ከተጠሪ ጋር የነበራቸው ጋብቻ ህዲር 19 ቀን 2005 ዓ/ም በተሰጠ ውሳኔ መፍረሱን ፣ ከተጠሪ ጋር በጋብቻ በነበሩ ጊዚ ያፈሩት የጋራ ንብረት የሆነው በየካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 13/14 ብሩህ ተስፊ ቁጥር 1 በሚባለው ሳይት ላይ የህንፃ ቁጥር B6/10 የኮንደሚኒየም ቤት ከየካ ክፍል ከተማ የቤቶች ማስተላለፍ ጽ/ቤት ጋር ህዲር 20 ቀን 2000 ዓ/ም በተደረገው የሽያጭ ውል መግዙታቸውን፣የቤቱ ካርታ በተጠሪ ስም የተሰጠውም በየካቲት 10 ቀን 2002 ዓ/ም መሆኑን ገልጸው በተጠሪ ስም የተመዖገበ ቢሆንም በጋብቻ ውስጥ የተፈራ በመሆኑ የጋራ ንብረት ነው ተብል እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል የአሁን ተጠሪም መጋቢት 23 ቀን 2005 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ የኮንደሚኒየሙን ቤት የተመዖገቡት ፣ እጣው የወጣው አጠቃላይ ክፍያውን አጠናቀው የከፈለት አመልካችና ተጠሪ ጋብቻቸውን ከመፈጸማቸው በፉት መሆኑን አመልካችና ተጠሪ ጋብቻ የፈጸሙት በህዲር 19 ቀን 2000 ዓ/ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት እንደሆነ ፣ ለኮንደሚኒየም ክፍያ የተከፈለው ግን ጠዋት መሆኑን ፣ ለዘህም አመልካች በቤቱ ባለቤትነት ሳይሆን በምስክርነት የፈረሙ መሆኑን ገልጸው የአመልካች ጥያቄ ውድቅ ይደረግ በማለት ተከራክሯል ።
ጉዲዩን የተመለከተው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዲ ምድብ ችልት የግራ ቀኙን ክርክርና የቀረቡትን የሰነድ ማስረጃዎችን ከመረመረ በኃላ የቤቱ እጣ የወጣው ጋብቻ ከመፈጸሙ በፉት ሲሆን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዛገብ በሰጣቸው ውሳኔዎች መሰረት ለኮንደሚኒየም ባለቤትነት ዋናው ጉዲይ እጣ መውጣቱ ነው ።
ስለዘህ ቤቱ የአሁን ተጠሪ የግል ሀብት ነው ሲል ወስኗል ። አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቧል ። ይግባኙ የቀረበለት የከፍተኛ ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ተቀብል የግራ ቀኙን ክርክር ካዲመጠ በኋላ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቶታል ።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ውሳኔውን ለማስቀየር ሲሆን አመልካች በጠበቃቸው በኩል ጥር 30 ቀን 2010 ዓ/ም የተጻፈ ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ይዖቱም በአጭሩ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ጋብቻ የተፈጸመው ህዲር 19 ቀን 2000 ዓ/ም ሲሆን የኮንደሚኒየም ቤቱን አስመልክቶ ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የየካ ክፍለ ከተማ የቤቶች ማስተላለፍ ጽ/ቤት ጋር የሽያጭ ውል የተፈራረመው ህዲር 20 ቀን 2000 ዓ/ም በጋብቻ ውስጥ ነው ። የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ብር 29‚087.10 /ሀያ ዖጠኝ ሺህ ሰማኒያ ሰባት ብር ከአስር ሳንቲም/ የተከፈለው በጋብቻ ውስጥ ነው ። ይህ ገንዖብ የተከፈለውም አመልካች በተበዲሪነት በፈረሙት የብድር ውል መሰረት ህዲር 19 ቀን 2000 ዓ/ም አመልካች እና ተጠሪ ሆነን ከወ/ሮ ትዔግስት ሐዋዛ በብድር ካገኘነው ብር 200‚000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ላይ ወጪ ተደርጎ ነው። የስር ፍርድ ቤቶች ቤቱ የጋራ አይደለም በማለት የወሰኑት የቤቱ ቅድመ ክፍያ የተፈጸመውና የሽያጭ ውለ የተደረገው በጋብቻ ውስጥ ቢሆንም የኮንድሚኒየም እጣው ለተጠሪ የደረሰው ከጋብቻ በፉት ነው በሚል ምክንያት ነው። እጣ መውጣት ለብቻው የቤት ባለቤት አያደርግም የቤት ባለቤትነት የሚገኘው በነፃ ሳይሆን በግዢ በመሆኑ እጣው የደረሰው ሰው ከሚመለከተው መንግስት አካል ጋር የሽያጭ ውል ተዋውል የሽያጩን ገንዖብ ካልከፈለ እድለ ከሚያመልጠው በቀር እጣው ብቻ ባለሀብት ሉያደርገው አይችልም ። በመሆኑም የቤቱ ባለቤት ለመሆኑም የቤቱ ባለቤት ለመሆን ዋናው ጉዲይ የሽያጭ ውለን ማድረግና ክፍያውን መፈጸም ነው። አሁን በተያዖው ጉዲይም የሽያጭ ውለ የተፈረመውና ክፍያ የተፈጸመው በጋብቻ ውስጥ በመሆኑ ቤቱ የጋራ ንብረት ነው።
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ቤቱ የጋራ አይደለም ብለው መወሰናቸው ስህተት ነው። የኮንድሚኒየም ቤቱን ከመንግስት ከተረከብን በኋላ በጋብቻው ውስጥ የልስን ስራ ተሰርቷል ፣ ቻክ ተደርጎ ቀለም ተቀብቷል ለመኝታ ቤት እና ለቫኞ ቤት ሁለት በሮች ተገጥመዋል ፣ ቫኞ ቤት እና ሽንት ቤት ሙለ እቃ ተሟልቶበት በሴራሚክ ተሰርቷል ፣ ለማዔድ ቤቱ ኪችን ካቢኔት ተስርቷል ፣ ላልች የማጠናቀቂያ ስራዎች ተሰርተዋል። ይህን የማጠናቀቂያ ስራ ለመስራትም ብር 80‚200 /ሰማኒያ ሺህ ሁለት መቶ ብር/ ወጪ ተደርጓል። ይህን ስራ ለመስራት ከባለሙያ ጋር የተደረገው ውል በማስረጃነት ለስር ፍርድ ቀርቧል። የቤቱ ወጪ የተሸፈነው አመልካችና ተጠሪ በጋራ በተበደርነው ብር 200‚000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ መሆኑን ክርክር እንዱሁም የጽሁፍ ማስረጃ አቅርቤ ምስክሮችን ዖርዛሬ እያለሁ የስር ፍርድ ቤቶች ግን በተለይም የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ለቤቱ መገኘት ያደረጉት አስተዋጽኦ የለም በማለት ቤቱ የጋራ አይደለም ማለታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ በዘህ ጉዲይ አመልካች የአካራካሪው የኮንደሚኒየም ውል የተፈረመው ፣ የቤት ሽያጭ ዋጋ የተከፈለውም በጋብቻ ውስጥ በጋራ በተፈረመ ብድር ነው በማለት ያቀረበችው ክርክር በስር ፍርድ ቤቶች የቤቱ እጣ የወጣው ከጋብቻ በፉት ነው በሚል ብቻ የሰበር መዛገብ ተጠቅሶ የመወሰኑን አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ይቅረብ ሲል ትዔዙዛ ሰጥቷል ።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው በጠበቃቸው በኩል የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ/ም የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቤቱታው ጊዚ ካለፈ በኋላ የቀረበ ነው የሚል ሲሆን አማራጭ መልስ ይዖትም በአጭሩ የኮንደሚኒየም እጣ ቅድመ ክፍያ እና የማጠቃለያ ክፍያ በሙለ የተፈጸመው ከጋብቻ በፉት ከግል ገንዖቤ ሲሆን አመልካች በኮንደሚኒየም የቤት ሽያጭ ዋጋ የተከፈለው በጋራ በተፈረመ የብድር ውል በተገኘ ገንዖብ ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ከእውነታው ውጪ ከመሆኑም በላይ በሀሰት የቀረበ ክርክር ነው ። አመልካች የኮንደሚኒየም ቤት ሙለ ክፍያ ከግል ገንዖቤ ከከፈልኩ በኋላ ያውም በማላዉቀዉ እና ባልፈረምኩት የብድር ዉል በተገኝ ገንዖብ ቤት ክፍያ እንደተፈጸመ ተደርጎ የቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም። የሰበር መዛገብ ዉሳኔ ከተያዖዉ ጉዲይ ጋር አግባብነት የለዉም። አመልካች በሽያጭ ዉል ላይ የፈረሙት የምስክርነት ነዉ የቤት እድሳትም የተከናወነዉ አመልካች እንደሚለት በብድር ገንዖብ ሳይሆን ተጠሪ አሜሪካ ሀገር ከሄድኩ በኋላ በላኩት ገንዖብ ሲሆን የቤቱ ጠቅላላ ዋጋ ብር 29‚087.10 /ሃያ ዖጠኝ ሺህ ሰማኒያ ሰባር ብር ከአስር ሳንቲም /ስለሆነ ብር/ 200‚000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የምትበደርበት ምክንያት የላለ ከመሆኑም በላይ እድሳቱም ቢሆን ለቤቱ ከተከፈለዉ ብር 29‚087.10 በላይ ብር 80‚000 ከቤቱ ዋጋ ከሶስት እጥፍ በላይ ወጭ አድርጌበታለሁ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ በሀሰት የቀረበ ከመሆኑም በላይ ሉታመን የማይችል በመሆኑ በዘህ በኩል የቀረበዉ አቤቱታ የህግ ክርክር ሳይሆን የፍሬ ነገር እና የማስረጃ በመሆኑ ለዘህ ሰበር ላቀርብ አይገባም። ሲጠቃለልም የስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ በአግባቡ ስለሆነ ሉጸና ይገባል የሚል ነዉ።
የአመልካች ጠበቃም ሚያዘያ 02 ቀን 2011 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የነገሩ አመጣጥ የክርክሩ ሂደት በአጭር ከላይ እንደተገለጸዉ ሲሆን ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉ የኮንድሚንየም ቤት የተጠሪ የግል ንብረት ነዉ ተብል በተሰጠዉ ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ ህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ወይስ አልተፈጸመበትም የሚል ጭብጥ ተይዜ ጉዲዩ እንደሚከተለዉ ተመርምሯል።
በቅድሚያ ግን በተጠሪ ጠበቃ ከሰበር አቤቱታ ጊዚ ማለፍ ጋር አያይዖዉ ያነሱትን መቃወሚያ በተመለከተ የአመልካች ጠበቃ በሰጡት የመልስ መልስ ጉዲዩ በልላ መዛገብ በስር ክርክር ካለዉ ጉዲይ ጋር የተያያዖ በመሆኑ አመልካች በቀረቡ ጊዚ የማንቀሳቀስ መብት ተጠብቆ ተዖግቷል።
በመሆኑም አመልካች በልላ መዛገብ ያለዉ ክርክር ማለትም የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ ችልት በኮ/መ/ቁ. 79982 የነበረዉ ክርክር ተጠናቆ በቀን 25/04/2011 ዓ/ም ዉሳኔ የተሰጠበት በመሆኑ ከዘህ መዛገብ ጋር ተያይዜ ቀድሞ በተሰጠዉ ትእዙዛ መሰረት ጉዲዩ ከቆመበት እንዱቀጥል ጥር 10 ቀን 2011 ዓ/ም አቤቱታ በመቅረቡ ነዉ በማለት ተከራክሯል። ከዘህ ጋር የተነሳዉ ክርክር ይህ ችልትም እንደተመለከተዉ ለቤቱ ግዢ እና ተጠሪን ወደ አሜሪካን አገር ለመሸኘት ተወስዶል ተብል አመልካች ተጠሪ እንዱከፍለ ተብል የቀረበ የብድር ገንዖብ ክስ ምክንያት ያደረገ ክርክር ቀደም ሲል እስከዘህ ሰበር ችልት ድረስ ደርሶ በሰበር መዛገብ ሚያዘያ 25 ቀን 2009 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የሚጣሩ ነጥቦች ተለይተዉ በስር ፍ/ቤት ቤት ተመልሷል። ጉዲዩ የተመለሰለት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ ችልት ጉዲዩን አጣርቶ በኮ/መ/ቁ. 79982 በቀን 25/04/2011 ዓ/ም ዉሳኔ መሰጠቱን ከተደረገዉ ክርክር ይዖት እንዱሁም ከዉሳኔዉ የተመለከትን በመሆኑም በዘህ ምክንያት ለዘህ ሰበር መነሻ የሆነዉ አቤቱታ ተዖግቶ መቆየቱን ለማረጋገጥ ተችሎል።
ስለዘህ ተጠሪ ከዘህ ጋር አያይዖዉ ያነሱትን ቅሬታ አግባብነት ያለዉ ሆኖ አላገኘነዉም።
በልላ በኩል ዋናዉን ጉዲይ በተመለከተ ከላይ በዛርዛር እንደተመለከተዉ በግራ ቀኙ መካከል ጋብቻ የተፈጸመዉና ለክርክሩ ምክንያት ለሆነዉ ቤት ክፍያ የተከፈለዉ ህዲር 19 ቀን 2000 ዓ/ም ነዉ።
ተጠሪ ይህንን ሳይክደ የሚከራከሩትን የኮንድሚንየም ቤት ገንዖብ ጠዋት ከተከፈለ በኃላ ጋብቻ ከሰአት በኃላ ተፈጽሟል የሚል ነዉ። በአንድ ቀን ዉስጥ በተለያየ ጊዚ የተለያየ ህጋዊ ድርጊት እንደተፈጸመና ይህም ልዩነት ልያመጣ እንደሚችል ተጠሪ ቢከራከሩም በስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ላይ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር የኮንደምንየም ቤቱ ክፍያ እና የቤቱ ሽያጭ ዉል የተፈጸመዉ ጋብቻ ዉስጥ መሆኑ ነዉ።የስር ፍ/ቤቶችም ዉሳኔያቸዉ ይህንን አምነዉ ተቀብለዋል።የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የኮንደምንያም ቤቱ የተጠሪ የግል ንብረት ነዉ በማለት ሉደመድም የቻለዉ እጣዉ ከጋብቻ በፉት የደረሰ በመሆኑ ነው የሚል ነው። የኮንደምኒየም ቤት እጣው ብቻ ከጋብቻ በፉት መድረስ ክፍያ ባልተፈጸመ ሁኔታ ተጠሪን ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉ ቤት ብቸኛ ባለመብት ሉያደርግ ይችላልን? የሚለዉን ምላሽ ሉያገኝ የሚገባዉ ነዉ። በዘህ ረገድ አመልካች ለዘህ ሰበር ችልት አቅርቦ የተከራከሩት ክርክር ይሁንታ የሚሰጠው ነዉ የሚል ነዉ። ምክንያቱም እጣ መዉጣት ለብቻዉ የቤት ባለቤት አያደርግም።
የኮንድምንየም ቤት ባለቤትነት የሚገኘዉ በነጻ ወይም እጣዉ በመዉጣቱ ብቻ ሳይሆን በግዢ በመሆኑ ገንዖቡ ሲከፈል ነው ። በተያዖው ጉዲይ ከላይ እንደተገለጸው ገንዖብ የተከፈለው በጋብቻ ውስጥ ነው።
ይህ የተከፈለው ገንዖብም በብድር የተገኘ መሆኑንና የብድር ውለንም አያይዖው ማቅረባቸው አመልካች አጥብቀው ተከራክረዋል ። ተጠሪ ለዘህ ችልት ባቀረቡት ክርክር ለኮንደሚኒየም ቤቱ የተከፈለው ገንዖብ የግላቸው ስለመሆኑ የተከራከሩ ቢሆንም ይህንን በስር ፍርድ ቤት በማስረጃ አላረጋገጡም ። በአንድ ክርክር ላይ መብትና ጥቅም አለኝ የሚል ተከራካሪ ወገን ይህንን የማስረዲት ሸክም የእራሱ ስለመሆኑ ከማስረጃ ህግ መርህ የምንገነዖበው ነው የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 255 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎችም ይህንን መርህ የሚያጠናክሩ ናቸው ። በፍትሐብሕር ክርክር አንድ መብት ወይም ግዳታ አለ ብል የሚከራከር ወገን መብቱ ወይም ግዳታው ስለመኖሩ የማስረዲት ሸክም ያለበት ስለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር መዛገብ አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል ። በመሆኑም ለክርክሩ ምክንያት ለሆነው ቤት የተከፈለው ገንዖብ ምንጭ የተጠሪ የግል መሆኑን ካላስረደ በስተቀር ቤቱ የተጠሪ የግል ነው ልባል የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም ።ከዘህ በተጨማሪ የአካራካሪው ኮንደሚኒየም ቤት የሸያጭ ውል የተፈረመው ወይም የተደረገው በጋብቻው ውስጥ ነው። የቤት ባለቤትነት ወይም የቤቱ ካርታ በተጠሪ ስም የተሰጠውም የካቲት 10 ቀን 2002 ዓ/ም ሲሆን ይህም አመልካችና ተጠሪ በጋብቻ ውስጥ አብረዉ እያለ ነው። እነዘህ ሁለ ተዲምረው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የጋራ ንብርት እንደሆነ አረጋጋጭ ናቸው።
በመጨረሻም የስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችን በአግባቡ ሳያጤኑ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ኮንደሚኒየም ቤት የተጠሪ የግል ንብረት ነው ሲለ የደረሱበት ድምዲሜ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ። በመሆኑም ቀጥል ያለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍ/መ/ቁ.103524 በቀን 28/02/07 ዓ/ም እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.163552 በቀን 20/4/2010 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ኮንደሚኒየም ቤት የአመልካችና የተጠሪ የጋራ ንብረት ነው ተብል ተወስኗል ።
የዘህን ችልት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
ጉዲዩ ስለተወሰነ መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.