በልጅ ቀለብ አወሳሰን ጊዚ የከፊዩን የተጣራ የገቢ መጠን በማጣራት ተገቢ ነው የሚባለው የቀለብ ገንዖብ መጠን መወሰን የሚገባው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ መንግስት በአንቀጽ 36(2)፣አዋጅ ቁጥር 213/1992 የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 113
No summary available.
ሰኔ 24 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- አቶ አቡበከር አህመድ መሐመድ - ተወካይ ወ/ሮ ሰዓዲ አብደላ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሳራ ሱፍያን አብደረህማን - ጠበቃ ሀኒፍ ይህደጎ - ቀረቡ።
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ከልጅ ቀለብ ጋር ተያይዜ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለዘህ ችልት ያቀረቡት ለአንድ ልጅ ቀለብ ከግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በየወሩ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ እንዱከፍለ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ24/08/2010 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ05/06/2011ዓ.ም. በፍርድ የጸናው ውሳኔ በከፉል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
ተጠሪዋ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ14/05/2010 ዓ.ም. ባቀረቡት ክስ ፍቺ እንዱወሰን እና አመልካቹ በሶስት የንግድ ፈቃድች በመሥራት በወር በአማካይ ብር 100,000/ አንድ መቶ ሺህ/ ገቢ የሚያገኙ መሆኑን ገልጸው በጋብቻው ለተወለደው የሶስት ወር ዔድሜ ላለው ልጃቸው በየወሩ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ ቀለብ እንዱከፍለ እንዱወሰን የጠየቁ ሲሆን አመልካቹ በበኩላቸው በ20/06/2010 ዓ.ም. በሰጡት መልስ የፍቺ ጥያቄውን የማይቃወሙ መሆኑን እና የወር ገቢያቸው ግን ተጠሪዋ እንደሚለት ሳይሆን በወር ከብር 5,000 /አምስት ሺህ/ የማይበልጥ መሆኑን ገልጸው በተጠሪዋ የቀረበው የተጋነነ የልጅ ቀለብ ጥያቄ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክረዋል።ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም በጊዚያዊነት የብር 4,000 /አራት ሺህ/ የልጅ ቀለብ ትዔዙዛ ከሰጠ በኋላ የአመልካቹ ገቢ ተጣርቶ እንዱቀርብ አድርጎ በሚመለከተው አካል የተገለጸውን የአመልካች ገቢ መጠን በአስረጂነት በመጥቀስ የፍቺ ውሳኔ በሰጠበት ቀን አመልካቹ ለአንድ ልጅ ቀለብ ከግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በየወሩ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ እንዱከፍለ ውሳኔ ሰጥቷል።በይግባኝ ሰሚው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍርድ የጸናው ይኸው ውሳኔ ሲሆን አመልካቹ ለዘህ ችልት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት ለቀለብ አወሳሰኑ መሰረት ያደረገው ከገቢዎች አስተዲደር ጽ/ቤት የተላከው ማስረጃ የአመልካቹን ጠቅላላ ገቢ እንጂ ልዩ ልዩ ተቀናሽ ወጪዎችን ያላገናዖበ ከመሆኑ አንጻር የቀለብ አወሳሰኑን አግባብነት ተጠሪዋ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዖንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ክርክሩ የተስተናገደበትን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዛገብ በማስቀረብ ጭምር አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለጉዲዩ ከተያዖው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዘህም መሰረት የልጅ ቀለብ አወሳሰን ጥንቃቄ የሚያስፈልገውና የሕፃናትን ደህንነትና ጥቅም የሚያረጋግጥ መሆን እንደሚገባው የሚታወቅ ሲሆን የሕፃናትን ጉዲይ በሚመለከት የሚወሰደ እርምጃዎች እና የሚሰጡ ውሣኔዎች በሙለ የሕፃናትን ጥቅም ተቀዲሚ ያደረጉ መሆን ያለባቸው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ መንግስት በአንቀጽ 36(2) ስር ይደነግጋል።በሕጻናት መብት አጠባበቅ እና አወሳሰን ረገድ አገሪቱ ያፀደቀቻቸው የአገሪቱ የሕግ አካል የሆኑ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችም ከግምት መግባት እንደሚገባቸው የሚያጠያይቅ አይደለም።ፍርድ ቤት ጋብቻ እንዱፈርስ ሲወስን ውሳኔ ሉያሳርፍባቸው ከሚገቡ ቀዲሚ ጉዲዮች መካከል አንደ የልጆች አስተዲደግ፣የትምህርት፣የጤና፣የቀለብ እና የአጠቃላይ አኗኗራቸው ጉዲይ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 213/1992 በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 113 (1) ስር የተመለከተ ሲሆን በቀለብ አወሳሰን ረገድም ውሳኔው በሚሰጥበት ጊዚ የነበረው የወላጆች የገቢ፣የዔድሜ፣የጤና እና የአኗኗር ሁኔታ፣እንዱሁም የልጆቹ ዔድሜ፣ጥቅማቸው እና ፍላጎታቸው ከግምት መግባት የሚገባቸው ስለመሆኑ በዘሁ አንቀጽ በንዐስ አንቀጽ (2) ስር ተመልክቷል።ከዘህም በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ በዘህ አንቀጽ መሰረት ስለልጆች አያያዛ እና አጠባበቅ የሚሰጠው ውሳኔ የሁኔታዎች መለዋወጥን ምክንያት በማድረግ በሚቀርብ ጥያቄ ሉሻሻል ወይም ሉለወጥ የሚችል ስለመሆኑም በዘሁ አንቀጽ በንዐስ አንቀጽ (3) ስር ተደንግጎ ይገኛል።
በተያዖው ጉዲይ የአመልካቹን ወርኃዊ የገቢ መጠን በተመለከተ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ክርክር ያቀረቡ ሲሆን ጉዲዩ የቀረበለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በቀለብ አወሳሰኑ ረገድ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት ያስችለው ዖንድ በደቡብ ወል ዜን የደሴ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የአመልካቹን የ2009 ዓ.ም. ዓመታዊ ገቢ አጣርቶ እንዱገልጽ በ14/07/2010 ዓ.ም. በሰጠው ትዔዙዛ መሰረት አመልካቹ የሂሳብ መዛገብ ያቀረቡ መሆኑን እና ዓመታዊ ገቢያቸው ብር 1,817,379.04 /አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ አስራ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ዖጠኝ ከዚሮ አራት ሳንቲም/ መሆኑን ገልጾ ጽ/ቤቱ በቁጥር አወ/አሰ/ክት/7213/2010 በ02/08/2010 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዲቤ ምላሽ ሰጥቷል።ፍርድ ቤቱ ከገቢዎች ጽ/ቤት በቀረበው ምላሽ ላይ የግራ ቀኙን የጽሁፍ አስተያየት ከተቀበለ በኋላ የቀለብ ውሳኔ የሰጠው በጽ/ቤቱ የተገለጸውን ዓመታዊ ገቢ ወደ ወርኃዊ ገቢ በመለወጥ አመልካቹ ብር 151,448 /አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ አርባ ስምንት/ ወርኃዊ ገቢ አላቸው በማለት መሆኑን ከዋናው መዛገብ ተመልክተናል።ይሁን እንጂ በደቡብ ወል ዜን የደሴ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የአመልካቹን ዓመታዊ ገቢ ከመግለጹ በቀር ይህ ዓመታዊ ገቢ ተገቢ ተቀናሾች ሁለ ታሳቢ ተደርገው ከግብር በኋላ የተገኘ የተጣራ ገቢ ስለመሆኑ ለይቶ ያልገለጸ መሆኑን ከስር መዛገብ ጋር ተያይዜ ከሚገኘው የደብዲቤው ይዖት እና ግራ ቀኙ በደብዲቤው ላይ በጽሁፍ ካቀረቡት አስተያየት ተገንዛበናል።የተጣራ መሆኑ ያልተረጋገጠን የገቢ መጠን መሰረት በማድረግ የሚሰጥ የቀለብ ውሳኔ ደግሞ የከፊዩን ትክክለኛ የመክፈል አቅም ያገናዖበ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም።በመሆኑም የቀለብ መጠኑ እንደገና ተጣርቶ እንዱወሰን ጉዲዩ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሉመለስ የሚገባው መሆኑን ተገንዛበናል።
በልላ በኩል የተጣራ ዓመታዊ ገቢያቸው ብር 154,235.43 /አንድ መቶ ሃምሳ አራት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ከአርባ ሶስት ሳምቲም/ መሆኑን እና የተጣራ ወርኃዊ ገቢያቸው ደግሞ ብር 12,860.45 /አስራ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ስድሳ ከአርባ አምስት ሳምቲም/ መሆኑን አመልካች ለዘህ ችልት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ላይ የገለጹ መሆኑን መሰረት በማድረግ ይህ ውሳኔ እስከተሰጠበት ጊዚ ድረስ የሚከፍለት በስር ፍርድ ቤት በተወሰነባቸው መጠን መሰረት መሆኑ እንደተጠቀበ ሆኖ ትክክለኛው የቀለብ መጠን በስር ፍርድ ቤት ተጣርቶ እስኪወሰን ድረስ አመልካቹ ከሐምል ወር 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የተጣራ ወርኃዊ ገቢዬ ነው በማለት የገለጹትን ገቢ አጋማሽ ብር 6,430.22 /ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ከሃያ ሁለት ሳንቲም/የልጅ ቀለብ እየከፈለ እንዱቆዩ ማድረጉ ተገቢ መሆኑን ተገንዛበናል። ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በከፉል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እና ሉሻሻል የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
አመልካቹ ለአንድ ልጅ ቀለብ ከግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በየወሩ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ እንዱከፍለ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ24/08/2010 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ05/06/2011ዓ.ም. በፍርድ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች የሚከፍለት ወርኃዊ የልጅ ቀለብ የገንዖብ መጠን ብር 10,000 /አስር ሺህ/ ነው በሚል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የአመልካቹን የተጣራ የገቢ መጠን አጣርቶ ተገቢ ነው የሚለውን የቀለብ ገንዖብ እንዱወስን ጉዲዩ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343 (1) መሰረት በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዱመለስ ወስነናል።
ይህ ውሳኔ እስከተሰጠበት ጊዚ ድረስ የሚከፍለት በስር ፍርድ ቤት በተወሰነባቸው መጠን መሰረት መሆኑ እንደተጠቀበ ሆኖ ትክክለኛው የቀለብ መጠን በስር ፍርድ ቤት ተጣርቶ እስኪወሰን ድረስ አመልካቹ ከሐምል ወር 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የተጣራ ወርኃዊ ገቢዬ ነው በማለት የገለጹትን ገቢ አጋማሽ ብር 6,430.22 /ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ከሃያ ሁለት ሳንቲም/ የልጅ ቀለብ እየከፈለ እንዱቆዩ ወስነናል።
በቀሪ ጉዲዮች ረገድ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል አልተነካም።
የውሳኔው ቅጂ ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዖንድ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣እንዱያውቀው ደግሞ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.