አንድ በዉጭ አገር የተሰጠ ፍርድ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ለማስፈጸም በኢትዮጵያ እና ፍርደን በሰጠዉ ፍርድ ቤት አገር መካከል ይህን አስመልክቶ የተደረገ ስምምነት (bilateral agreement) ባይኖርም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 458 ስር የተመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸዉ ከተረጋገጠ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ፍርደን ተቀብለዉ ማስፈጸም የሚችለ ስለመሆኑ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 456፣458
No summary available.
ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ ፍሬህይወት ገበየሁ ተጠሪ፡- አቶ ዖሪሁን ተፈራ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በውጪ ሀገር የተሰጠ ፍርድ የሚፈፀምበትን አግባብ የሚመለከት ነው። አመልካች ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በቀን 19/07/2009 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት የአፈፃፀም አቤቱታ የአሜሪካን የዱስትሪክት ፍ/ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረውን የባልና ሚስት ፍቺና ንብረት ክፍፍል ክርክር መርምሮ እንደ አውሮፒውያን አቆጣጠር በቀን 1/02/2013 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ መሰረት ተጠሪ እንዱፈፅሙ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱም የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ በውጪ ሀገር የተሰጠ ፍርድ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዱፈፀም ሉሟለ ከሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች አንደ እንዱፈፀም የተጠየቀውን ፍርድ የሰጠው ፍርድ ቤት የሚገኝበት ሀገር በኢትዮጵያ የተሰጠውን ፍርድ የሚፈፅም መሆኑ ሲረጋገጥ በመሆኑ ይህንኑ መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች የሚሰጡት ውሳኔ በአሜሪካን ፍርድ ቤቶች የሚፈፀሙ ስለመሆን አለመሆኑ እንዱሁም ይህንኑ በተመለከተ የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ስምምነት ስለመኖር አለመኖሩ ለፍ/ቤቱ እንዱገለፅ ለኢ.ፋ.ዱ.ሪ የውጪ ጉዲይ ሚኒስቴር በቀን 01/03/2010 ዓ.ም ትዔዙዛ ሰጥቶ በቀን 10/04/2010 ዓ.ም በተፃፈ ምላሽ በሁለቱ ሀገራት መካከል ፍርድን ለማስፈፀም የሚያስችል ስምምነት አለመኖሩ የተገለፀ በመሆኑና የኢትዮጵያ ፍርድችም በአሜሪካን ሀገር የማይፈፀሙ ስለመሆኑ በቀን 27/04/2010 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ የውጪ ጉዲይ ሚኒስቴር ስለተገለፀ አመልካች ያቀረቡት የፍርድ ይፈፀምልኝ አቤቱታን አልተቀበልኩትም በማለት መዛገቡን ዖግቶታል። በዘህ ውሳኔ ቅር የተሰኙት አመልካች ይግባኛቸውን ለፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቢያቀርቡም የይግባኝ አቤቱታቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
ለዘህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም እነዘህ በስር ፍርድ ቤት የተሰጡትን ውሳኔዎች ለማስለወጥ ነው። አመልካች በጠበቃቸው አማካኝነት ሐምል 18 ቀን 2010 ዓ.ም በተፃፈ 03 ገፅ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈፅመዋል ያሎቸውን ስህተቶች ዖርዛረው በማቅረብ እንዱታረሙላቸው ጠይቀዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዖት በአጭሩ የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት በሁለቱ ሀገሮች መካከል የአንደን ሀገር ፍርድ እንዳት እንደሚፈፀም የጋራ ስምምነት የለም ተብል ተረጋግጦ እያለ በተዖረጋለት ስርዓት ጉዲያችንን ሉያስተናግድ ሲገባ "የተለየ ስምምነት ከላለ…" የሚለውን ሀረግ በስህተት በመተርጎም ፍርደ ሉፈፀም አይገባም በማለት መወሰኑ ተገቢነት የላለው በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪው ተመርምሮ አመልካች በአሜሪካን ሀገር ፍ/ቤት የተሰጠዉን ዉሳኔ መሰረት አድርገው በኢትዮጵያ ፍ/ቤት ያቀረቡት የአፈፃፀም ክስ በሁለቱ ሀገራት መካከል ፍርድን ለማስፈፀም የሁለትዮሽ ስምምነት የለም ተብል ውድቅ የመደረጉን አግባብ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 256 እና ተከታዮቹ አንፃር ለማጣራት መዛገቡ ለሰበር ችልት ቀርቧል። በጉዲዩ ላይ አመልካች መልስ እንዱሰጥበት በጋዚጣም ጭምር ጥሪ ቢደረግለትም ላቀርብ ባለመቻለ መልስ የማቅረብ መብታቸው ታልፍ ክርክሩ በላለበት እንዱቀጥል ትዔዙዛ ተሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ከተያዖው ጭብጥና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ ይህ ጉዲይ በዉጭ አገር የተሰጠ ፍርድ የሚፈጸምበትን ሁኔታ የሚመለከት ነዉ። በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ የተመለከተው የፍርድ አፈጻጸም ጉዲይ በሁለት ዓብይት ምዔራፍች የተመለከተ ሲሆን፣ በምዔራፍ 1 ላይ የተመለከተው በኢትዮጵያ ግዙት ውስጥ የተሰጠን ፍርድ በማስፈፀም ረገድ ተፈጻሚነት ያላቸው ድንጋጌዎች ሲሆን፣ በምዔራፍ 2 (ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 456 እስከ 461 የተጠቀሱት ድንጋጌዎች) ደግሞ በውጭ ሀገር የተሰጠ ፍርድ ወይም ብይን የሚፈፀምበትን ሁኔታ የሚመለከቱ ናቸው። በዉጭ አገር የተሰጠን ፍርድ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ከማስፈጸም ጋር በተያያዖ መሰረቱ (principle) በህጉ አንቀጽ 456 ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ በዘህ አንቀጽ ንዐስ ቁጥር 1 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ‛በኢንተርናሲዮናል ስምምነት በተለየ እንዱፈጸም የሚደረግ ልዩ ህግ ከላለ በቀር ከኢትዮጵያ ዉጪ የተሰጠ የፍርድ ዉሳኔ ወይም ብይን የሚፈጸመዉ በዘህ ህግ በተመለከተዉ ድንጋጌ መሰረት ነዉ“ በማለት የሚያስቀምጥ ሲሆን፣ የድንጋጌዉ የእንግሉዛኛ ትርጉምም ‛Unless otherwise expressly provided by international law conventions, foreign judgments may not be executed in Ethiopia except in accordance with the provisions of this chapter“ በማለት ያስቀምጣል። የዉጭ አገር ፍርድ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ሉፈጸሙ የሚችለባቸዉ ሁኔታዎችም በህጉ አንቀጽ 458 ላይ ተመልክተዋል። እነዘህም ሁኔታዎች እንዱፈጸም የተጠየቀዉን ፍርድ የወሰነዉ ፍርድ ቤት የሚገኝበት አገር በኢትዮጵያ የተሰጠዉን ፍርድም የሚያስፈጽም መሆኑ ሲረጋገጥ፤ ፍርደ የተሰጠዉ በህግ በተቋቋመ ፍርድ ቤት መሆኑ ሲታወቅ፤ የፍርድ ባለዔዲዉ ቀርቦ መቃወሚያዉን ለማሰማት መብት የተሰጠዉ መሆኑ ሲረጋገጥ፤ ፍርደ የመጨረሻና ተፈፃሚነት ያለዉ መሆኑ ሲታወቅ እና የፍርደ መፈጸም ለህዛብ ሞራልና ጸጥታ ተቃራኒ ያለመሆኑ ሲታወቅ ስለመሆኑ በድንጋጌዉ ላይ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል።
ከእነዘህ ሁለ መገንዖብ የሚቻለዉ፣ በዉጭ አገር የተሰጠ ፍርድ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ሉፈጸም የሚችለዉ በመርህ ደረጃ በኢትዮጵያ እና ፍርደን በሰጠዉ ፍርድ ቤት አገር መካከል ይህን አስመልክቶ የተደረገ ስምምነት (bilateral agreement) መኖሩ ሲረጋገጥ ሲሆን፣ በልዩ ሁኔታ በህጉ አንቀጽ 458 ስር የተመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተዉ ሲገኙ ነዉ። በመሆኑም በህጉ አንቀጽ 458 የተመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸዉ ከተረጋገጠ ምንም እንኳ የዉጭ አገር ፍርድ የሚፈጸምበትን ሁኔታ በተመለከተ የተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት ባይኖርም፣ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ፍርደን ተቀብለዉ ማስፈጸም የሚችለ መሆኑን ነዉ። ስለሆነም በዉጭ አገር የተሰጠን ፍርድ እንዱያስፈጽም ዲኝነት የቀረበለት የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በቅድሚያ እንዱያጣራ የሚጠበቅበት ለአፈፃፀም የቀረበዉን ፍርድ በሰጠዉ ፍርድ ቤት አገር እና በኢትዮጵያ መካከል የፍርድ አፈፃፀምን አስመልክቶ የተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት መኖር አለመኖሩን፣ ስምምነት የላለ መሆኑ ከተረጋገጠ በህጉ አንቀጽ 458 ላይ የተመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎች የተሟለ መሆን አለመሆኑን ነዉ።
ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ፣ ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ፣ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች የቀረበዉን የአፈፃፀም ጥያቄ ዉድቅ ያደረገዉ፣ ከፍርድ አፈፃፀም ጋር በተያያዖ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካን ሀገር መካከል የተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት አለመኖሩንና በኢትዮጵያ የተሰጡ ፍርድች በአሜሪካ የማይፈጸሙ ስለመሆኑ የኢፋዱሪ የዉጭ ጉዲይ ሚኒስቴር ከጻፈለት ደብዲቤ ማረጋገጡን ነዉ። ይሁንና ከላይ እንደተገለጸዉ የሁለትዮሽ ስምምነት መኖር ብቸኛዉ ቅድመ ሁኔታ አይደለም። በመሆኑም የአሜሪካን አገር ፍርድ ቤቶች በኢትዮጵያ የተሰጡትን ፍርድች የሚፈጽሙ መሆን ያለመሆኑን ጨምሮ ላልች በህጉ አንቀጽ 458 ላይ የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች በተጨባጭ ማስረጃ ሉረጋገጡ የሚገባቸዉ ናቸዉ። የአሜሪካን አገር ፍርድ ቤቶች በኢትዮጵያ የሚሰጡትን ፍርድ የሚፈጽሙ መሆን ያለመሆኑና ላልች በህጉ የተመለከቱት ሁኔታዎች ፍርድ ቤቱ የአፈፃፀም አቤቱታዉን ተቀብል ለማስተናገድ ስልጣን ያለዉ መሆን ያለመሆኑን በመወሰን ረገድ ሉረጋገጡ የሚገቡ መሰረታዊ የፍሬ ነገር ጭብጦች በመሆናቸዉ እና ፍሬ ነገሩን ለማስረዲት ላቀርብ የሚገባዉ የማስረጃ ዓይነት በህግ ተለይቶ የተወሰነ እስካልሆነ ድረስ፣ ፍርድ ቤቱ ማናቸዉንም ማስረጃ በማስቀረብ እና በመመርመር እነዘህን ፍሬ ነገሮች የማረጋገጥ ኃላፉነት ይኖርበታል። ይህ በመሆኑም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት እነዘህን ፍሬ ነገሮች በዘህ መልኩ አጣርቶ መወሰን ሲገባዉ፣ ከኢፋዱሪ የዉጭ ጉዲይ ሚኒስቴር የቀረበዉን ደብዲቤ ብቻ መሰረት በማድረግ የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 14/06/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 30/08/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዖግቶ የነበረዉን መዛገብ በማንቀሳቀስ፣ የአሜሪካን አገር ፍርድ ቤቶች በኢትዮጵያ የተሰጠዉን ፍርድ የማስፈጸም ልምድ ያላቸዉ መሆን ያለመሆኑን ላልች በህጉ አንቀጽ 458 ላይ የተመለከቱትን ሁኔታዎች አመልካች በሚያቀርቡትና ስለጉዲዩ ማስረዲት የሚችል ማንኛዉንም ማስረጃ በማስቀረብ እና በመመርመር ተገቢ ነዉ የሚለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ መዛገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 343(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዘህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.