ግራቀኝ ተከራካሪ ወገኖች በሚያደርጉት ስምምነት መሰረት አለመግባባታቸውን በኢትዮጵያ መሰረታዊ ህግ (Substantive Law) እንዱሁም በውጪ ሃገር የሥነ-ሥርዓት ህግ መሰረት በሚቋቋም የግልግል ዲኝነት አካል በውጭ ሃገር ለመቋጨት በተስማሙት መሰረት አግሪኮም ኢንተርናሽናል ኩባንያ እና የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች የግልግል ጉባኤ የሰጠው ውሳኔ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ታይቶ እንዱታረም የሚቀርብ የሰበር ማመልከቻ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ የኢፋዳሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) እና በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 (በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 እንደተሻሻለ)፤ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 458(ሀ) እና 461(1)(ሀ) ኮርፕሬሽን
No summary available.
ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች- መዓዙ አሸናፉ ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች- አግሪኮም ኢንተርናሽናል ኩባንያ -ጠበቃ አለሙ ደነቀው ቀረቡ:: ተጠሪ- የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፕሬሽን-ጠበቆች ሜሮን ሰለሞን እና ዶ/ር ዖውድነህ በየነ ቀረቡ:: መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የስንዳ ግዢ ውልን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተደረገው ግራ ቀኙ እ.ኤ.አ ኖቨንበር 25/2011 ባደረጉት ስምምነት መሰረት አለመግባባታቸውን በኢትዮጵያ መሰረታዊ ህግ (Substantive Law) እንዱሁም በ Grain and Feeds Trading association (GAFTA) የሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 125 (GAFTA Rules NO. 125) መሰረት በሚቋቋም የግልግል ዲኝነት አካል በእንግሉዛ ሃገር ለመቋጨት በተስማሙት መሰረት ነው።
የአሁን ተጠሪ ለግልግል ጉባኤው ባቀረበው ክስ 200,000 ሜትሪክ ቶን ስንዳ ለማቅረብ አመልካች የውል ግዳታ ገብቶ ማቅረብ ባለመቻለ ጥቅምት 9/2005 ዓ.ም ማስጠንቀቂያ ሰጥቼ ውለን በማቋረጥ ላላ ግዢ ፈጽሜያለሁ፤ ስለሆነም በፈፀምኩት አዱስ ግዢ ምክንያት ለ 11,549,000.00 (አስራ አንድ ሚሉዮን አምስት መቶ አርባ ዖጠኝ ሺህ) የአሜሪካ ድላር ተጨማሪ ወጪ ተዲርጌያለሁ፤ ይህንኑ ገንዖብ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
አመልካች ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ ስንዳውን ለማቅረብ ያልቻልኩት ስንዳውን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን የባንክ የመተማመኛ ሰነድ (L/C) ተጠሪ አስተካክል በወቅቱ ለማቅረብ ባለመቻለ በራሱ ጥፊት ነው፤ የራሱን ግዳታ ባልተወጣበት ሁኔታ ውለን ለማቋረጥም ሆነ ኪሳራ ለመጠየቅ አይችልም፤ ከዘህም ላላ ውለ በሚተዲደርበት በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ተገቢው ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ተጠሪ ውለን ሉያቋርጥ አይችልም፤ ስለሆነም ካሳ እንድከፍል ሉጠይቀኝ አይችልም፤ ይህ የሚታለፍ ቢሆንና የደረሰ ጉዲት አለ ከተባለ ተጠሪ ሉጠይቅ የሚችለው ለ200,000 ሜትሪክ ቶን የዋጋ መጠን በተሰጠው የመልካም ሥራ አፈፃፀም ሰነድ (Performance Bond) ማለትም 5,855,000.00 (አምስት ሚሉዮን ስምንት መቶ ሃምሳ አምስት ሺህ) የአሜሪካን ድላር ብቻ ነው በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በዘህ መልኩ የቀረበለት የግልግል ጉባኤ ክርክርና ማስረጃውን መርምሮ ተጠሪ ውለን ያቋረጠው በአግባቡ ነው፤ ውለን ለማቋረጥ የተሰጠው ማስጠንቀቂያም የኢትዮጵያ ህግ የሚጠይቀውን የሚያሟላ ነው፤ እንዱሁም ተጠሪ የጠየቀውን የካሳ መጠን የማይከፍልበት ምክንያት የለም በማለት አመልካች ለተጠሪ 11,549,000.00 (አስራ አንድ ሚሉዮን አምስት መቶ አርባ ዖጠኝ ሺህ) የአሜሪካ ድላር እንዱከፍል የካቲት 20/2010 ዓ.ም ባሳለፈው ፍርድ ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካች መጋቢት 18/2010 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር ማመልከቻ ውሳኔው የተሰጠው በኢትዮጵያ ህግ ላይ ተመስርቶ መሆኑንና ውሳኔውም የመጨረሻና በሁለቱ ወገኖች ላይ ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ መደንገጉን፤ እንዱሁም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዛገብ ከሰጠው ውሳኔ አንጻር ጉዲዩን ተቀብል ለመዲኘት እንደሚችልና ህገመንግስታዊ ሥልጣን ያለው መሆኑን ጠቅሶ ማመልከቻውን አቅርቧል።
አመልካች በሰበር ማመልከቻው በ09/02/2005 ዓ.ም ተሰጠ የተባለው ማስጠንቀቂያ በ16/02/2005 ዓ.ም ከተጠሪ በተላከ መልዕክት የተነሳና የተሰረዖ በመሆኑ፤ ይህም ባይሆን ማስጠንቀቂያው የተሰጠው ተጠሪ የራሱን ግዳታ ሳይወጣና በቂ ጊዚም ሳይሰጥ የፍትሐብሕር ህጉንና የሰበር ውሳኔዎች ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች ሳያሟላ ስለሆነ በአግባቡ ባልተቋረጠ ውል ላይ ተመስርቶ አመልካች 11,5490,00.00 (አስራ አንድ ሺህ አምስት መቶ አርባ ዖጠኝ) የአሜሪካ ድላር እንዱከፍል የተሰጠው የግልግል ጉባኤ ውድቅ እንዱደረግ ጠይቋል። ይህ የሚታለፍ ከሆነም ለደረሰው ጉዲት መከፈል ያለበት ለ 200,000 ሜትሪክ ቶን ስንዳ ግራቀኙ ካደረጓቸው ውልች ተለይቶ በተሰጠው የፏርፍርማንስ ቦንድ ገንዖብ መጠን ማለትም 5,855,000.00 (አምስት ሚሉዮን ስምንት መቶ ሃምሳ አምስት ሺህ) የአሜሪካን ድላር ብቻ ነው ተብል እንዱወሰን አመልክቷል።
የሰበር ማመልከቻው በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ የግልግል ጉባኤው የሰጠው ውሳኔ ተዋዋይ ወገኖች ውለን በተናጠል ለመሰረዛ (Unilateral Cancillation of Contract) ስለሚችለበት አግባብ በሰበር መዛገብ ከተሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም አኳያ ተገቢነቱን መርምሮ ለመወሰን በሚል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል።
ተጠሪ መስከረም 22/2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የኢፋዳሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበውን ጉዲይ ለማየት ስልጣን የለውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና በፍሬነገሩም መልስ ሰጥቷል።
ተጠሪ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የላለው ስለመሆኑ ባቀረበው የመቃወሚያ ክርክር የግልግል ዲኝነቱ መቀመጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ባልሆነ የግልግል ዲኝነት የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ጉዲዩ እንዱታይ የሚቀርብበት የህግ መሰረትም ልምድም የለም፤
የግልግል ዲኝነቱ ውሳኔ እንደ ኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የመጨረሻ ውሳኔ ሆኖ እንዱቆጠር በተዋዋዮች መካከል የተደረገ ስምምነት ስለላለ ውሳኔውን በኢትዮጵያ ግዙት ውስጥ እንደተሰጠ ውሳኔ ቆጥሮ በመሰረታዊ የህግ ስህተት ስም ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ የሚደረግበት የህግ መሰረት የለም፤ ጉዲዩ በሰበር እንዱታይ የሚቀርብበት የህግ አግባብ የለም እንጂ አለ እንኳ ቢባል ላቀርብ ይገባ የነበረው የግልግል ዲኝነቱ ህጋዊ መቀመጫ ሆኖ በተመረጠውና በተዋዋይ ወገኖች ተቀባይነትን ባገኘው እ.ኤ.አ በ1996 በፀደቀው የዩናይትድ ኪንግደም የአርቢትሬሽን ህግ መሰረት ለለንደን የከፍተኛው ፍርድ ቤት የንግድ ችልት ብቻ ነበር፤ አመልካች የግልግል ዲኝነት አካለ የመጀመሪያ ጉባኤ (First Tier Tribunal) በሰጣቸው ውሳኔዎች ቅር በመሰኘት ከአንዳም ሁለት ጊዚ የይግባኝ አቤቱታውን ለለንደን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ንግድ ችልት አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበታል፤ አመልካች እ.ኤ.አ. በፋብሪዋሪ 27 ቀን 2018 በአምስት ዳኞች የተላለፈውን የ GAFTA የግልግል ዲኝነት የይግባኝ ጉባኤ የመጨረሻ ውሳኔ ቀሪ እንዱደረግ፣ እንዱሻር ወይም እንዲይፈፀም ለማድረግ አቤቱታውን ማቅረብ የነበረበት የግልግል ጉባኤው መቀመጫ ሀገር ህግ በሚፈቅደው መሰረት ሥልጣን ላለው ለለንደኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ንግድ ችልት ነበር፤
ስለሆነም ይህ የሰበር አቤቱታ ስልጣን ለላለው ፍ/ቤት የቀረበ በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል።
አመልካች በሰ/መ/ የተሰጠውን ውሳኔ በመጥቀስ አቤቱታውን ያቀረበ ቢሆንም በሁለቱ መዙግብት ክርክር ያስነሳው ጉዲይ፣ የውለ ሁኔታዎች እና የግልግል ጉባኤው መቀመጫ ፈጽሞ የተለያየ በመሆኑ በሰ/መ/ የተሰጠው ገዢ ትርጉም በዘህ መዛገብ ላይ ተፈጻሚ ላሆን አይገባም፤ ሰበር ችልቱ የመጨረሻና ይግባኝ የማይባልባቸው ናቸው የተባለ የግልግል ዲኝነት ውሳኔዎችን ተቀብል ማየት የሚችለው የመጨረሻውን የግልግል ዲኝነት ወሳኔ ያስተላለፈው የግልግል ዲኝነት አካል ህጋዊ መቀመጫ (Juridical or Legal Seat) በኢትዮጵያ ከሆነ ብቻ ነው፤ ከዘህም ላላ ተዋዋይ ወገኖች ውሳኔያቸውን የሚገዙው መሰረታዊ (የሥረ ነገር) ህግ (Substantive Law) የኢትዮጵያ ህግ በመሆኑና የኢትዮጵያ ህግ ሲተረጎም ደግሞ መሰረታዊ ስህተት ከተፈጸመበት ሉያቃና የሚችለው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ነው ከሚል ግንዙቤ የቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም፤ በግራቀኙ የተመረጠው መሰረታዊ ህግ የኢትዮጵያ ህግ ቢሆንም ክርክር ሂደቱን የሚገዙው የሥነ ሥርዓት ህግ ደግሞ የግልግል ዲኝነት አካለ (የ GAFTA የአርቢትሬሽን የሥነ ሥርዓት ህግ) ህጋዊ መቀመጫ ሀገር ህግ በመሆኑ ይህ ሰበር ችልት ‛መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል“ የተባለውን የግልግል ዲኝነት ጉባኤ ውሳኔ የማየት ሥልጣን የለውም። በተዋዋይ ወገኖች የአርብትሬሽን የሥነ ሥርዓት ህጎች የሚወሰኑትም ከፍርድ ቤቶች ጣልቃ ገብነት ለመራቅ ሲባል ነው። በልላም በኩል አመልካች በአቤቱታው የገለፀው ጥቅምት 9/2005 ዓ.ም የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ጥቅምት 16/2005 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ ተነስቷል? ወይስ አልተነሳም? የሚለው ክርክር ማስረጃን የሚመለከት በመሆኑና ውሳኔም የተሰጠው ማስረጃዎቹ ታይተው በመሆኑ በዘህ ረገድ የቀረበው ክርክር የህግ ክርክር አይደለም ለሰበር ችልቱ በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ላታይ የሚችል አይደለም ተብል ውድቅ ይደረግልን በማለት መቃወሚያውን አቅርቧል።
በውለ አንቀጽ 13 እንደተቀመጠው የመልካም ሥራ አፈጻፀም ዋስትናው የሚገባው የውለን ዋጋ 10% መሆኑን ስለሚደነግግ ይህ ሲሰላ 14,637,500.00 የአሜሪካ ድላር ይሆናል፤
አመልካች የ200,000 ሜትሪክ ቶን ስንዳ ዋጋን መሰረት በማድረግ ያስቀመጠው የዋስትና ገንዖብ መጠን የተሳሳተ እና የውል መሰረት የላለው ነው፤ ውለ የመልካም ሥራ አፈጻፀም ዋስትና (ቦንድ) መጠኑን ሲያስቀምጥ የዋሱን ኃላፉነት መጠን ለመገደብ እንጂ የጉዲቱን መጠን ለመገደብ እንደሆነ ያስቀመጠው ነገር የለም፤ ከቦንደ በላይ ጉዲት ቢደርስ ተጨማሪ ካሳ መጠየቅ አይቻልም የሚል መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ ነገርም የለም፤ በተጨማሪም በውለ አንቀጽ 17 ላይ liquidated damage የተቀመጠ ሲሆን ይህም በአንቀጽ 13 ላይ የተቀመጠው የጉዲት ካሳ የመልካም ሥራ አፈጻፀም ዋስትና ሰነድ የጉዲት መጠኑን በአጠቃላይ ለመገደብ የተቀመጠ እንዲልሆነ የሚያሳይ ነው። በአጠቃላይ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ የግልግል ጉባኤው ውሳኔ እንዱፀና በማለት ተከራክሯል።
አመልካች ጥቅምት 23/2011 ዓ.ም በተጻፈ የመልስ መልስ በመቃወሚያው ላይ የበኩለን ክርክር አቅርቧል። በዘህም መሰረት የጋፍታ የግልግል ጉባኤ (ቦርድ) የሰጠው ውሳኔ ጉዲዩ የሚዲኝበትን የኢትዮጵያ ህግ የጣሰ ነው በማለት የቀረበን ቅሬታ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 80 እና በአዋጅ ቁጥር 454/97 መሰረት ለማየት ሥልጣን ያለው ሰበር ሰሚው ችልት ነው፤ ሁለቱ ወገኖች ጉዲያቸውን በኢትዮጵያ መሰረታዊ ህግ (substantive law) መሰረት ለመገዙት ፈቃደኛነታቸውን በውል ከገለፁ የኢትዮጵያን ህግ አስመልክቶ ክርክር ቢነሳ ጉዲዩ ከሰበር ሰሚው ስልጣን ውጪ የሚሆንበት የህግ መሰረት የለም፤ ይህ ያልተገደበ የሰበር ስልጣን ፍርደ በየትም ቦታ ቢሰጥ ወይም ውሳኔ የሰጠው አካል የተከተለው ሥርዓት (Procedure) ምንም ይሁን የተሰጠው ውሳኔ የኢትዮጵያ የህግ መስፈርቶችን አያሟላም የሚል ጥያቄ ከተነሳ ውሳኔ የሚሰጠው በህግ ስልጣን የተሰጠው ሰበር ሰሚ ችልት ብቻ ነው፤ ተዋዋዮች በአንድ የግልግል ተቋም አማካኝነት በተወሰነ ሃገር ለመዲኘት ፈቃድ መስጠታቸው የግልግል ተቋሙ የሚመራበትን ሥርዓት (procedure) መቀበላቸውን ከሚያረጋግጥ በቀር መሰረታዊውን ህግ በተመለከተ ያላቸውን መብት ተነፍገዋል ማለት አይደለም። አመልካች በተለያዩ ጊዚያት ይግባኝ ሲያቀርብ የነበረው ለለንደኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው አሁንም በዘያው መሰረት ሉያቀርብ ይገባል ተብል በተጠሪ በኩል የቀረበውን ክርክር በተመለከተም ፍሬ ነገርን ወይም መሰረታዊ (የስረ ነገር) የህግ ስህተትን አስመልክቶ ለለንደን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረብነው አንዲችም ይግባኝ የለም፤ በርግጥ ጉዲዩ በግልግል ጉባኤ በመታየት ላይ እያለ ሁለት የሥነ ሥርዓት ጥያቄዎች ላይ በመመስረት አቤቱታ ለለንደን ፍርድ ቤት አቅርበናል፡- ይኸውም በመጀመሪያ ጉዲዩ ለግልግል ጉባኤ በቀረበበት ወቅት የአቤቱታ ማቅረቢያው ጊዚ አልፎል በማለት፣ ሁለተኛ ደግሞ ክርክሩ አልቆ ውሳኔውን ከመስማታችን በፉት ተዋዋይና ከሳሽ ወገን የነበረው የኢትዮጵያ እህል ንግድ ድርጅት አስቀድሞ ፈርሶ እያለ በፈረሰው ድርጅት ሥም ሲካሄድ የነበረው ክርክር እንደተካሄደ ሉቆጠር አይገባም በማለት የቀረበ የሥነ ሥርዓት ተቃውሞ ነው፤ የዘህ አይነት የሥነ ሥርዓት ተቃውሞ ደግሞ ክርክሩ የሚካሄድበትን ሥርዓት መሰረት በማድረግ በይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት መቅረቡ በአግባቡ ነው። ስለሆነም ተጠሪ ያቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ ላደረግ ይገባል ብሎል። ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተም አመልካች የቀደመ ክርክሩን በማጠናከር ውለ የተቋረጠው ያላግባብ ስለሆነ የግልግል ጉባኤው ውሳኔ ውድቅ እንዱደረግ፤ ይህ የሚታለፍ ከሆነም የካሳው መጠን በመልካም ሥራ አፈጻፀም ቦንደ ላይ የተቀመጠው የገንዖብ መጠን 5,855,000.00 (አምስት ሚሉዮን ስምንት መቶ ሃምሳ አምስት ሸህ) የአሜሪካን ድላር ነው ተብል እንዱወሰን ጠይቋል።
የጉዲዩ አመጣጥና የግራቀኙ የጽሁፍ ክርክር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያው ላይ ክርክራቸውን በቃል ሰምቷል። ጉዲዩንም የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
እንደመረመርነው በሰበር አጣሪ ችልቱ እንዱታይ የተያዖው ጭብጥ ፍሬ ጉዲዩን የተመለከተ ቢሆንም ከዘህ በፉት የችልቱን ምላሽ የሚጠይቀው ነጥብ የአሁን ተጠሪ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ተቀብል ለመወሰን ስልጣን የለውም በማለት ያቀረበው ክርክር ነው። ይህን ጭብጥ ለመመለስ ግራቀኙ በገቡት ስምምነት መሰረት ጉዲዩ በግልግል ጉባኤ ውሳኔ ያገኘበትን አግባብ እና የተሰጠውን ውሳኔ ተፈጥሮ፤ መሰል የአማራጭ ሙግት መፍቻ ዖዳዎችን በመጠቀም በሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ ለመደበኛ ፍርድ ቤቶች አቤቱታ የሚቀርብበትን ሁኔታ፤
እንዱሁም በሀገራችን የተዖረጋው የሰበር ስርዓት አላማና የህጉን ማእቀፍ መመልከቱ ተገቢ ነው።
ፍርድ ቤቶች የግልግል ዲኛ በመሾም፣ በመሻር፣ ጉዲይን ወደ ግልግል በመምራት እንዱሁም ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ ፍርደን ሉመረምሩ የሚችለበት ሁኔታ በህጉ ተደንግጓል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ ከአንቀጽ 350 እስከ 354 ስለ ይግባኝ፤ ከአንቀጽ 355 እስከ 356 ብይኑ ስለሚሻርበት እና ማመልከቻው ስለሚቀርብበት ሁኔታ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ፍርድ ቤቶች የግልግል ዲኝነቱ የተቋቋመበትን ዓላማ ማሳካቱና እና በህጉ አግባብ ጉዲዩን መርቶ መወሰኑን እንዱያረጋግጡ የሚያስችለ ናቸው። በአንፃሩ እነዘህ ድንጋጌዎች በውጪ ሀገራት የተሰጡ የግልግል ዲኝነቶችን በቀጥታ ይመለከታለ ባይባልም የሥነ ሥርዓት ህጉ ከአንቀጽ 456 እስከ 461 ድረስ ከውጪ አገር ስለሚመጡ የግልግል ውሳኔዎች አፈፃፀም ሂደትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ይዝል።
በልላ በኩለ በዓለም አቀፍ የግልግል ዲኝነት ያለው ልምድ እና የዲበረ የግልግል ዲኝነት ህግጋት ያላቸው የበርካታ ሀገራት ህጎች እንዱሁም አለምአቀፍ ስምምነቶች እንደሚያረጋግጡት የግልግል ዲኝነት ውሳኔዎች እንደመደበኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተቆጥረው የግልግል ውሳኔዎችን በፍርድ ውሳኔ ለማስቀረት (setting aside) ወይም ለማሰረዛ (annulment) አቤቱታ ላቀርብ የሚችለው በተዋዋይ ወገኖች መካከል ይኸው በስምምነት ሲደገፍ፣ ተዋዋይ ወገኖች በመረጡት የግልግል ዲኝነት የሥነ ሥርዓት ህግ (Institutional Arbitration Rule) ይኸው ሲደገፍ፣ እንዱሁም የግልግል ዲኝነቱ ህጋዊ መቀመጫ ሀገር (Juridical or Legal Seat) ህግ ይህንኑ የሚደግፍ ሲሆን ነው። በተያዖው ጉዲይ የግልግል ዲኝነቱ መቀመጫ በእንግሉዛ ሀገር መሆኑ እንዱሁም ግራቀኙ ባደረጉት ስምምነት ውስጥ የግልግል ዲኝነቱ ውሳኔ እንደ ኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሆኖ እንዱቆጠር የተደረገ ስምምነት አለመኖሩ አላከራከረም። የተመረጠው የግልግል ዲኝነት መቀመጫ ሀገር ህግም ቢሆን በግልግል ጉባኤው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ በዘያው ሀገር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤቱታ እንዱቀርብ የሚፈቅድ ነው። ስለሆነም የግልግል ጉባኤው ውሳኔ እንዱሻር/እንዱሻሻል አቤቱታው ለዘህ ፍርድ ቤት በቀጥታ የቀረበው ይህን የሚፈቅድ ህግ እንዱሁም የተዋዋይ ወገኖች ሥምምነት በላለበት ነው።
ከዘህ ጋር በተያያዖ አመልካች የግልግል ዲኝነት አካለ የመጀመሪያ ጉባኤ (First Tier Tribunal) በሰጣቸው ውሳኔዎች ቅር በመሰኘት ከአንዳም ሁለት ጊዚ የይግባኝ አቤቱታውን ለለንደን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ንግድ ችልት አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበታል፤ በመጨረሻው ውሳኔ ላይም ቅሬታው ላቀርብ የሚገባ በዘሁ አግባብ ነው በማለት ተጠሪ የተከራከረ ሲሆን አመልካች በሰጠው መልስ ሁለት ጊዚ የይግባኝ አቤቱታ ለለንደን የከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቦ እንደነበር ሳይክድ ያቀረበው ይግባኝ የስነ ሥርዓት ጉዲዮችን በተመለከተ ብቻ እንደነበርና ፍሬ ነገርን ወይም መሰረታዊ (የስረ ነገር) የህግ ስህተትን አስመልክቶ ለለንደን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ እንደላለ ተከራክሯል። እንደሚታወቀው በአንድ በተሰጠ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የማለት መብት መሰረታዊ መብት ሆኖ የሚቆጠር ሲሆን የይግባኝ መብቱ ዛርዛር አፈፃፀም ግን የሚወሰነው በሥነ ሥርዓት ህጎች ነው። ስህተቱ የሥነ ሥርዓትም ሆነ የፍሬ ነገር ቢሆን ሉሰማና ሉታረም የሚችለው ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ባለው የሥነ ሥርዓት ደንብ እየተመራ ነው።
ስለሆነም የግልግል ዲኝነቱ አካል የሚመራበት ሥነ ሥርዓት ላይ ግራ ቀኙ ስምምነት አድርገው በዘሁ አግባብ ሁለት ጊዚ የይግባኝ አቤቱታ ለለንደኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረቡ ባላከራከረበት ሁኔታ አመልካች ፍሬ ነገርን ወይም መሰረታዊ የህግ ስህተትን አስመልክቶ ለመደበኛው ፍርድ ቤት ያቀረብኩት ቅሬታ የለም በማለት ያቀረበው ክርክር የሥምምነታቸውን ይዖት እና ጉዲዩ የሚገዙበትን ህግና ልምድ የተከተለ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም።
ለዘህ ክርክራቸው መሰረት የሚያደርጉትም በሰ/መ/ የተሰጠውን አስገዲጅ ትርጉም እና የህገ መንግስቱን አንቀጽ 80 እንዱሁም የአዋጅ ቁጥር 454/97 ድንጋጌን ነው። በእርግጥ በኢትዮጵያ ሁኔታ በግልግል ጉባኤ የሚሰጥ የመጨረሻ ውሳኔ አስገዲጅና ይግባኝ የማይባልበት ስለመሆኑ በተከራካሪዎች ስምምነት የተደረገበት ቢሆን ጉዲዩ በሰበር ችልት ላታይ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለው ነጥብ አከራካሪ ሆኖ ይታያል። የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በጉዲዩ ላይ አስቀድሞ ሰጥቶት የነበረውን አስገዲጅ ትርጉም በፒናል ችልት በመለወጥ ትርጉም ሰጥቷል። በሰ/መ/ ብሓራዊ ማዔድን ኮርፕሬሽን ኃ/የተ/የግል ኩባንያ እና ዲኒ ድሪሉንግ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ መካከል በተደረገው ክርክር ሰበር ችልቱ የግልግል ውሳኔን የመጨረሻነት እንዱሁም በግልግል ዲኝነት አካላት የተሰጡ ውሳኔዎችን በተመለከተ ፍርድ ቤቶች ሉኖራቸው የሚገባውን ሚና አስመልክቶ አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶ ወስኗል። በዘህም መሰረት ‛…… አማራጭ የሙግት መፍቻ ዖዳዎች በኢትዮጵያ የህግ ስርዓት ውስጥ ተካተው የሚገኙ ሲሆን እነዘህን የሙግት መፍቻ ዖዳዎች ፍርድ ቤቶች የሚያበረታቱበት አጋጣሚ እንዲለ ሁለ የሚቆጣጠሩበት ሁኔታ መኖሩን…………፤ ከዘህ አኳያ አንድ ጉዲይ ለሰበር የመቅረቡ ሁኔታ በህገ መንግስቱ ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠ ሥልጣን በመሆኑ የሰበር ስርዓቱ ሉጫወተው ከተፈለገው ዐቢይ ዓላማ አንፃር ሲታይ ጉዲያቸው በግልግል ዲኝነት እንዱታይላቸው የተስማሙ ወገኖች የግልግል ዲኝነቱ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ነው በማለት ስለተስማሙ ብቻ ጉዲዩ በሰበር ሥርዓቱ እንዲይታይ ፍላጎት አሳይተዋል ተብል መሰረታዊውን የህግ ስህተት ላለማሳረም ምክንያት ላሆን የሚችል አይደለም….“ በማለት የኢፋዳሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ)፣ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10፣ እና አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት በማድረግ ወስኗል። ነገር ግን ላታይ የሚገባው ይህ ውሳኔ ለተያዖው ጉዲይ ያለው ተገቢነትና አስገዲጅነት ነው። ከውሳኔው መገንዖብ እንደሚቻለው በጉዲዩ ላይ በሰበር ችልቱ ውሳኔ የተሰጠው የግልግል ችልቱ መቀመጫ እዘሁ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ተከትል በመሆኑ አሁን በእጃችን ካለው ጉዲይ ጋር የተገናኘ አይደለም። በተያዖው ጉዲይ ግራቀኙ ባደረጉት የግዥ እና ሽያጭ ውል የግልግል ዲኝነት መቀመጫውን በእንግሉዛ ሀገር ለንደን ከተማ ያደረገ የግልግል ተቋም የመረጡ ሲሆን በ Grain and Feeds Trading association (GAFTA) የሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 125 (GAFTA Rules NO. 125) መሰረት ለመዲኛትም ተስማምተዋል። በሰ/መ/ የተሰጠው ውሳኔ ደግሞ ይህን መሰረት አድርጎ የተሰጠ ባለመሆኑ ከተያዖው ጉዲይ ጋር የሚገናኝ አይደለም። ተመሳሳይ የፍሬ ነገር ወይም የህግ ክርክሮች በላለበት ሁኔታ አስቀድሞ የተሰጠ የሰበር ውሳኔ በጉዲዩ ላይ ተፈፃሚ እንዱሆን የሚደረግበት የህግ አግባብ እንደላለም ከአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(4) ግልጽ ድንጋጌ መገንዖብ ይቻላል።
በልላ በኩል የሰበር አቤቱታ የቀረበበት የግልግል ጉባኤ ውሳኔ (APPEAL AWARD NO: 4496 & 4515) መግቢያ ላይ በተራ ቁጥር 1.4 ሥር የሚከተለው ተመልክቷል፡- ‛As the seat of the arbitration is in England and an Award subject to English procedural and Ethiopian substantive law, it therefore follows that it is an English Award for the purpose of recognition and enforcement under the terms of the 1958 New York Convention on the Recognition and Enforcement of Foreign Arbitral Awards“ የዘህ የአማርኛ ትርጉምም እንደሚከተለው ይነበባል፡- ‛የግልግል ዲኝነቱ መቀመጫ ቦታ እንግሉዛ ሀገር በመሆኑና የዲኝነቱ ሂደት የሚመራው በእንግሉዛ የሥነ ስርዓት ህግ፣ የውለን ይዖት በተመለከተ ግን ተፈፃሚው የኢትዮጵያ ህግ በመሆኑ፤ የግልግል ውሳኔው እንደ እንግሉዛ አገር ውሳኔ ተቆጥሮ ውሳኔው ዔውቅና የሚያገኘውና ተፈፃሚም የሚሆነው ከአንድ አገር ውጪ የተሰጠን ውሳኔ አፈፃፀም በተመለከተ በ1958 የወጣው የኒዮርክ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ነው“
ከዘህ የግልግል ጉባኤ ውሳኔ ይዖት መገንዖብ እንደሚቻለው የግልግል ውሳኔው ከአንድ አገር ውጪ የተሰጠ ውሳኔ (በእንግሉዛ) ተደርጎ የሚወሰድና ውሳኔው ዔውቅና የሚያገኘውና ተፈፃሚም የሚሆነው በ1958 የወጣው የኒዮርክ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን መሰረት ስለመሆኑ ነው። ስለሆነም ለሰበር ክርክሩ አወሳሰን ሲባል ይህ የግልግል ጉባኤው ውሳኔ ተፈጥሮና በ1958 የወጣው የኒዮርክ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን በሀገራችን የህግ ሥርዓት ያለውን ቦታ በአግባቡ መመርመር ይጠይቃል።
ከሀገር ውጪ የሚሰጡ የግልግል ውሳኔዎችን በሃገራት ውስጥ በማስፈፀም ረገድ እ.ኤ.አ በ1958 የወጣው ለግልግል ዲኝነት ውሳኔዎች ዔውቅና መስጠትና ማስፈፀምን የሚመለከት የኒውዮርክ ኮንቬንሽን (The New York Convention on the Recognition and Enforcement of Arbitral Awards) እንደ ትልቅ ስኬትና እመርታ ይወሰዲል። በርካታ የዖርፈ ተመራማሪዎች እንደሚመሰክሩለትም ከሁለም ሃገራት ፍላጎት ጋር በሚስማማ መልኩ የግልግል ውሳኔዎች በቀላለ የሚፈፀሙበትን መንገድ ዖርግቷል ተብል ይታመናል።
በሃገራችንም ከኢኮኖሚው እድገት ጋር ተያይዜ ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጦች እየተጠናከሩ በመሆኑና ግዘፍ ኩባንያዎች የገበያ አድማሳቸውን በማስፊት ወደ ሃገራችን በማቅናት መዋዔለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ በመሆኑ ይህን ዖላቂ ለማድረግ፤ በተለይም ኢትዮጵያ የዓለምአቀፈ የንግድ ማህበር (World Trade Organization) አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት አንደ መመዖኛ ተደርጎ የሚወሰድ በመሆኑ፤ እንዱሁም አለመግባባቶች በግልግል መቋጨታቸው ከሚኖረው ዖርፈ ብዘ ጠቀሜታ አንፃር ሃገራችን የኒውዮርኩን ኮንቬንሽን ለማጽደቅ በሂደት ላይ መሆኗ ይታወቃል።
በልላ በኩል ከውጪ ሀገር የሚመጡ የግልግል ውሳኔዎች የሚፈፀሙበት ራሱን የቻለ ሥርዓት በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ ከአንቀጽ 456 እስከ 461 ተደንግጎ ይገኛል።
በዘህ መልኩ በኒውዮርክ ስምምነት እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 461 መካከል የቃል በቃል መመሳሰል እንዳት ሉፈጠር ቻለ የሚለውን በአግባቡ ማየትም ያስፈልጋል። በኒውዮርክ ስምምነት እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ መካከል ላለው መመሳሰል በምክንያትነት የሚጠቀሰው የሥነሥርዓት ህጉ የወጣው የኒውዮርኩ ስምምነት በወጣ በጥቂት አመታት ውስጥ መሆኑ ነው። የሥነ ሥርዓት ህጉ እ.ኤ.አ በ08/10/1965 የወጣ ሲሆን የኒዮርክ ስምምነት ለፊርማ ክፍት የሆነው እ.ኤ.አ በ31/12/1958 ነው። ከዘህ በመነሳት ህግ አውጭው በውጪ ሃገራት የተሰጡ የግልግል ውሳኔዎችን ለማስፈፀም እንዱሁም አፈፃፀሙን ለመቃወም ሉጠቀሱ የሚችለ ምክንያቶችን ከኒዮርክ ስምምነት ሉወስድ መቻለ ይታመናል።
ስለሆነም በተያዖው ጉዲይ ግራቀኙ ያደረጉትን ስምምነት ተከትል የግልግል ጉባኤው የሰጠው ውሳኔ እንደ እንግሉዛ አገር ውሳኔ የተቆጠረ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ለማሳረም በሚል ለዘህ ፍርድ ቤት መቅረቡ ተገቢ ባይሆንም ውሳኔው ዔውቅና የሚያገኘውና ተፈፃሚም የሚሆነው ከአንድ አገር ውጪ የተሰጠን ውሳኔ አፈፃፀም በተመለከተ በ1958 በወጣው የኒዮርክ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን መሰረት በመሆኑ በዘህ አግባብ አቤቱታ ላቀርብና ሉስተናገድ አይገባም ማለት ግን አይሆንም።
በአጠቃላይ ግራቀኙ ወገኖች በ Grain and Feeds Trading association (GAFTA) የሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 125 (GAFTA Rules NO. 125) መሰረት በሚቋቋም የግልግል ዲኝነት አካል በእንግሉዛ ሃገር ክርክራቸውን ለመቋጨት የተስማሙ በመሆኑና የግልግል ዲኝነቱ ውሳኔ የተሰጠውም ይህን ስርዓት ተከትል በመሆኑ፤ አመልካቹም በግልግል ጉባኤው ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታውን በውል ስምምነታቸው እና በህግ በተዖረጋው ስርዓት መሰረት ለንደን ለሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅሬታውን በየጊዚው ያቀርብ እንደነበር የተረጋገጠ በመሆኑ፤
አመልካች አቤቱታውን ለዘህ ሰበር ችልት ለማቅረብ በዋቢነት በጠቀሰው የሰ/መ/ የተሰጠው የህግ ትርጉም የግልግል ጉባኤው መቀመጫ በተዋዋዮች በስምምነት ወይም ከህግ በተሰጠ ስልጣን በውጪ ሀገር እንዱሆን ተደርጎ በውጪ ሀገር የተሰጠ ፍርድን የሚመለከት ባለመሆኑ፤ እንዱሁም ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በኢፋዳሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) እና በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 (በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 እንደተሻሻለ) የተሰጠው መሰረታዊ የህግ ስህተትን የማረም ስልጣን የተያዖውን ጉዲይ የሚመለከት ባለመሆኑ አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል። ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
አመልካችና ተጠሪ እ.ኤ.አ ኖቨንበር 25/2011 ባደረጉት ስምምነት መሰረት አለመግባባታቸውን በ Grain and Feeds Trading association (GAFTA) የሥነ ሥርዓት ህግ 125 (GAFTA Rules NO. 125) መሰረት በሚቋቋም የግልግል ዲኝነት አካል በእንግሉዛ ሃገር ለመቋጨት በተስማሙት መሰረት የተቋቋመው ጉባኤ የሰጠው ውሳኔ (APPEAL AWARD NO: 4496 & 4515) በኢፋዳሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ታይቶ እንዱታረም የቀረበው የሰበር ማመልከቻ በግራቀኙ የተደረገውን ስምምነት እና ህጉን መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244(2)(ሀ) እና 245(2) መሰረት ወስነናል።
አመልካች ለዲኝነት ከከፈለው ብር 1,605,760.10 (አንድ ሚሉዮን ስድስት መቶ ሰምስት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ብር ከአስር ሳንቲም) ላይ በደንቡ መሰረት የሚቀነሰው ሂሳብ ከተቀነሰ በኋላ ቀሪው ገንዖብ ለአመልካች እንዱመለስ ብለናል። የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር ይህን ተከታትል ያስፈጽም።
ውሳኔው ሀምላ 5/2011 ዓ.ም በችልት ተነቧል።
በዘህ ችልት ስለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.