አንድ የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ድርሻን መሰረት በማድረግ የቀረበ ሲሆን አመልካቹ በድርሻው ተመስርቶ ዲኝነት እስከጠየቀ ድረስ ከድርሻው ውጪ ያለውን ግምት መሰረት አድርጎ ዲኝነት እንዱከፍል የሚደረግበት የህግ አግባብ ስላለመኖሩ እና የውርስ ንብረቱ ጠቅላላ ግምት የፍርድ ቤቱን የስረ ነገር ስልጣን ለመወሰን የግድ የሚባልበት የሕግ መሰረት የላለ ስለመሆኑና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 14 ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 17 እና 225
No summary available.
ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ጽጌ ታደሰ - ጠበቃ ውቤ ጓዳ ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
ወ/ሮ አልማዛ ሳህላ ወኪል ግርማ ታደሰ ቀረቡ።
አቶ ሰይፈ ታደሰ
አቶ ግርማ ታደሰ - ቀረቡ።
አቶ ደረጀ ታደሰ - ወኪል ግርማ ታደሰ ቀረቡ።
አቶ ወንድወሰን ታደሰ
ወ/ሮ ዖውድነሽ ታደሰ አልቀረቡም።
አቶ አሳምነው ታደሰ
አቶ ብሩክ ታደሰ - ወኪል ግርማ ታደሰ ቀረቡ።
መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ከውርስ ድርሻ ክፍፍል ጥያቄ የተነሳውን የስረ ነገር ስልጣን ጉዲይ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪዎች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ ነው።
የአሁኑ አመልካች ጥቅምት 20 ቀን 2010 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ማመልከቻ ከውርስ በጠቅላላ የተገመተ ሃብት ሉተላለፍላቸው የሚገባውን ድርሻቸው ብር 274,333.00 (ሁለት መቶ ሰባ አራት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር) መሆኑን በመለየት ተጠሪዎች እንዱያካፍሎቸው ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። የዲኝነት ገንዖቡንም በዘሁ ገንዖብ መጠን በታሪፈ መሰረት ብር 5,593.33 ከፍለው ፊይለን ከአስከፈቱ እና ለችልቱ ከቀረበ በኋላ ችልቱ ክሳቸውን መርምሮ ከሳሽ ባቀረቡት የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ላይ ክፍያ የሚፈፀመው በውርሱ ቤት ወይም አክሲዮን ተገምቶ እና ተሽጦ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የክፍያ ውሳኔ የሚሰጠው በቴክኒካዊ መንገድ ለቤቱና ለአክሲዮኑ ስለሆነ ሉከፈል የሚገባው ዲኝነትም ሆነ ጉዲዩ ላቀርብበት የሚገባው ፍርድ ቤት የሚወስነው በንብረቱ ጠቅላላ ግምት በመመሰረት እና ሁለንም ንብረት ለማካፈል ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት እንጂ ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ላሆን እንደማይገባው ደምድሞ ፍርድ ቤቱ መዛገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 231(ለ) መሰረት ዖግቶታል። በዘህ ብይን የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ እንዱከራከሩ ከተደረገ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን ሙለ በሙለ አፅንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ዲኝነት በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡- ውርስ ተጣርቶ የወራሾች ድርሻ በተለየበት ሁኔታ አመልካች ድርሻቸውን ተጠሪዎች እንዱያካፍለ ያቀረቡት ክስ የውርስ ንብረቱን ጠቅላላ ግምት መሰረት በማድረግ የፍርድ ቤቱ የስረ ነገር ስልጣን የሚታይ ነው ተብል መወሰኑ ከዲኝነት አከፊፈል እና በዲኝነት ከሚጠየቅ መብት አንፃር ተገቢነት የላለው ነው የሚል ሲሆን አቤቱታቸው ተመርምሮም በዘህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪዎች ቀርበውም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም፡-የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት የአመልካቾችን ክስ መዛጋቱ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዛ ጉዲዩን እንደሚከተለው ተመልክቷል።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት ክስ ሲመሰርቱ ከውርስ ጠቅላላ የተገመተ ሃብት ድርሻቸውን ከላልች ወራሾች ይደርሰኛል ያለትን መጠኑን በግልጽ በመለየትና በመጥቀስ ሲሆን ዲኝነት የጠየቁትም ድርሻቸውን ተከሳሾች እንዱያካፍሎቸው ይወሰን ዖንድ የውርስ ቤትና አክሲዮን ግምት ከብር 4,000,000.00 (አራት ሚሉዮን ብር) በላይ መሆኑን ተጠሪዎች ገልፀው የሚከራከሩ መሆኑን ተገንዛበናል።
አመልካች የጠየቁት የውርስ ንብረት አይነቱንና ግምቱን ለይተው ድርሻቸው የሆነውንና ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር ) በታች የሆነውን ብር 274,333.00 (ሁለት መቶ ሰባ አራት ሺህ ሶስት መቶ ሰለሳ ሶስት ብር) እንዱከፈላቸው ይወሰን ዖንድ ነው። የተያዖውን ጉዲይ መሰረት ያደረገው የገንዖብ መጠን ሲታይ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ የማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለው የፋደራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 14(1(ሀ)) ድንጋጌ መረዲት የምንችለው ሲሆን አመልካች ከድርሻቸው ውጪ ያለውን ግምት መሰረት አድርገው ዲኝነት የሚጠይቁበት የሕግ አግባብም የለም። የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን መሰረት የሚያደርገው የጉዲዮችን ክብደትና ቅለት መሆኑ የሚታመን ቢሆንም ከሳሹ ከሚጠይቀው ዲኝነት ውጪ ያለው እና ከሳሹ ከሚጠይቀው ንብረት ጋር ተያያዥነት ያለው ንብረት ግምት ሁለ መሰረት ተደርጎ የፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን እንዱታይ የሚስገድድ የስነ ስርዓት ሕግ ድንጋጌ የለም። አመልካች ድርሻቸውን ለይተው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 225 መሰረት ተገቢውን ዲኝነት ከፍለው በድርሻቸው ላይ ክርክር ከሚያቀርቡ በስተቀር ፍርድ ቤቱ ውርሱ ሲጣራ የውርስ ንብረት ስለመሆኑ በተረጋገጠው ንብረት ላይ ላላ ክርክር የሚመራበት ሁኔታም የላለ ሲሆን ተጠሪዎቹም ቢሆኑ ክርክር የቀረበባቸው ንብረቶች የውርስ ሃብት አይደለም የሚል ክርክር ያቀረቡ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት አያሳይም። ከተጠሪዎች ውጪ ያለወገን መብት ቢኖር እንኳን አመልካች በድርሻቸው ተመስርተው ዲኝነት እስከጠየቁ ድረስ በሕጉ አግባብ የሚጠየቁበት ከሚኖር በስተቀር የንብረቱ ጠቅላላ ግምት የፍርድ ቤቱን የስረ ነገር ስልጣን ለመወሰን የግድ የሚልበት የሕግ መሰረት የለም።
ሲጠቃለልም አመልካች የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄውን ያቀረቡት ድርሻቸውን መሰረት በማድረግ በመሆኑና የተጠሪ ድርሻ ደግሞ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በታች በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 14፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 17 እና 225 እና ላልች የውርስ ህግ ድንጋጌዎች መሰረት ክሱን የማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤት የህግ መሰረት የላለውን መስፈርት በመጥቀስ ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት መዛገቡን መዛጋቱም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤትን የሕግ መሰረት የላለውን ብይን መቀበለ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል።
በዘህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በ21/02/2010 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ07/3/2011 ዓ/ም የጸናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ስልጣን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው ብለናል።
የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ክርክሩን ቀጥል በጉዲዩ ላይ ተገቢውን ዲኝነት እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል። ይጻፍ።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.