አንድ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሥር ፍ/ቤት ውሳኔን በመሻር ጉዲዩ በድጋሚ እንዱታይ ነጥብ ለይቶ እስከመለሰ ድረስ የሥር ፍ/ቤቱ በበላይ ፍ/ቤቱ ትዔዙዛ ወይም መመሪያ መሰረት ግራ ቀኝ ተካራካሪ ወገኖችን በማከራከር ፣ በመስማት፣ ተገቢውን ጭብጥ በመመስረት እና በማስረጃ በማጣራት ዉሳኔ የመስጠት ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.246-249፣341(1)
No summary available.
ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡ …. ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡ …… . . አቶ ገ/መድህን መልከጻድቅ ፡- ጠበቃ አየለ ቦጋለ ቀርበዋል።
ተጠሪዎች፡ ………. . . 1. አቶ ቀነኒ ዱባባ ፡- የቀረበ የለም።
ይህ ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣የአሁን አመልካች ተከሳሽ፣የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ ከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.212821 ህዲር 11 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከቱ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪዎች) ባቀረቡት ክስ በከሳሾች እና በተከሳሽ መካከል ጥቅምት 3 ቀን 1980 ዓ.ም በተደረገ የወለድ አገድ ዉል በልደታ ክ/ከተማ ወረዲ 4 ክልል ዉስጥ የሚገኘዉን የቤት ቁጥር 752 የሆነዉን የከሳሾችን ቤት ከተከሳሾች ብር 20,000 (ሀያ ሺህ) ተቀብለን ቤቱን አስረክበን የተበደርን ሲሆን የብድሩ ጥቅምት 3 ቀን 1990 ዓ.ም ልንከፍል ተስማምተን ብሩን ተቀብለን ቤቱን ያስረከብን ሲሆን፣ ተከሳሽ ገንዖቡን ወስድ ቤቱን እንዱያስረክበን ብንጠይቀዉም ፈቃደኛ ስላልሆነ ገንዖቡን ተቀብለዉ፣ ቤቱን እንዱስረክበን፣ ቤቱን አከራይተን የሚናገኘዉን ጥቅም ብር 10,000 እንዱከፍለን በማለት ከሷል።
በዘህ ክስ ላይ ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ ከሳሽ ጥቅምት 3 ቀን 1990 ዓ.ም ጀምሮ ከ17 ዓመት በኋላ ስለሆነ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነዉ፤ በዉለ ላይ በተመለከተዉ መሰረት ከሳሾች ገንዖቡን በጊዚ ካልመለሱ ተከሳሽ ቤቱን ሸጠዉ ገንዖቡን መዉሰድ እንደሚችል ስለተስማማን በዘህ መሰረት ታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓ.ም ለአቶ መላኩ ዮሐንስ የሸጥኩኝ ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለዉም። ነገር ግን ፍ/ቤቱ ቤቱ ለከሳሾች ሉመለስ ይገባል የሚል ከሆነ ከሳሾች የወሰደትን የብድር ገንዖብ ብር 20,000 (ሀያ ሺህ) ከጥቅምት 3 ቀን 1980 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍለኝ በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ ከሳሾች ያቀረቡት ክስ በይርጋ የሚታገድ ነዉ በማለት ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። የሥር ከሳሾች በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በመ.ቁ.177014 በ18/8/2009 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ፍ/ቤት ከሳሾች ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ያለበት አግባብ ሕግን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ የሥር ዉሳኔ ዉሳኔ ተሽሯል በማለት በዋና ጉዲይ አከራክሮ እንዱወሰን በማለት ለሥር ፍ/ቤት መልሶታል።
ከዘህ በኋላ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን ድጋሚ በማየት በሰጠዉ ዉሳኔ በከሳሾች እና በተከሳሾች መካከል ጥቅምት 3 ቀን 1980 ዓ.ም የተደረገዉ የወለድ አገድ ዉል ሕጋዊ ዉጤት የላለዉ በመሆኑ ከሳሾች የተበደሩትን ብር 20,000 (ሀያ ሺህ) ለተከሳሽ በመክፈል ተከሳሽ ደግሞ የቤት ቁጥር 752 የሚታወቀዉን ለከሳሾች እንዱያስረክቡ በማለት ወስኗል። የሥር ተከሳሽ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የቀረበዉን ይግባኝ ዉድቅ በማድረግ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ በዘህ ትዔዙዛ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ታህሳስ 1 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዘህ ጉዲይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሥር ዉሳኔ በመሻር ግራ ቀኛቸዉን በዋኛዉ ጉዲይ አከራክሮ እንዱወሰን በመለሰለት መሰረት ፍ/ቤቱ ግራ ቀኛችንን በጉዲዩ ላይ አከራክሮ መወሰን ሲገባዉ ግራ ቀኛችንን ሳያከራክርና የቀረበዉን ማስረጃ ሳይመረምር የሰጠዉ ዉሳኔ የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት ትዔዙዛ (መመሪያ) እና የፍትሐብሕር ሥነሥርዓት ሕጉን ድንጋጌዎች የጣሰ ስለሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልኝ በማለት በዛርዛር ቅሬታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዘህ ጉዲይ የሰጠዉ ዉሳኔ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠዉ ፍርድ መሰረት ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 ድንጋጌ አፈጻጸም ከመሰማት መሰረታዊ መብት አንጻር ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ባዖዖዉ መጋቢት 16 ቀን 2011 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዖት በአጭሩ፡ የሥር ፍ/ቤቶች በዘህ ጉዲይ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ ዉሳኔዉ እንዱጸናልን ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብታችን እንዱጠበቅልን በማለት በዛርዛር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪዎች ያቀረቡትን ክስ በተመለከተ የአሁን አመልካች ያቀረበዉን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በመቀበል ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ በይርጋ የሚታገድ ነዉ በማለት መወሰኑን መዛገቡ ያሳያል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ የቀረበለትን ይግባኝ በመመርመር የሥር ፍ/ቤት የተጠሪዎችን ክስ በይርጋ ዉድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም በማለት በመሻር የሥር ፍ/ቤት በዋናዉ ጉዲይ ግራ ቀኛቸዉን አከራክሮ ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 (1) መሰረት የመለሰለት መሆኑን የሥር ዉሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዘህ አግባብ የተመለሰለትን ጉዲይ በመ.ቁ.228538 በ2/5/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ተጠሪዎች መዛገብ እንዱከፈትላቸዉ መጠየቃቸዉን በመግለጽ፣ ተጠሪዎች ለአመልካች መጥሪያ እንዱያደርሱ፣ መዛገቡን መርምሮ ለመስራት ለየካቲት 16 ቀን 2010 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። በዘህ መሰረት የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት የካቲት 16 ቀን 2010 ዓ.ም ዉሳኔ መስጠቱን የሥር ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። ይህ ማለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የበላይ ፍ/ቤት በሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረት ግራ ቀኛቸዉን ሳያከራክር ዉሳኔ መስጠቱን ያመለክታል።
እንደሚታወቀዉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 (1) እንደሚያመለክተዉ ‹‹ይግባኝ የተባለበትን ፍርድ ወይም ዉሳኔ የሰጠዉ ፍርድ ቤት ነገሩን የወሰነዉ ክርክር ዉስጥ ሳይገባ በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበለትን መቃወሚያ ብቻ መሰረት በማድረግ ሲሆንና ይህ ፍርድ ወይም ዉሳኔ በይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት የተለወጠ እንደሆነ ክርክሩ ወደ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዱመለስ በማድረግ መታየት የሚገባቸዉን ነጥቦች ለይቶ እንደገና እንዱታይ ለማዖዛ ይችላል›› በማለት ይደነግጋል። በዘህ አግባብ አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡትን ክስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በይርጋ ዉድቅ ያደረገ ቢሆንም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን በማየት የሥር ዉሳኔ በመሻር ግራ ቀኛቸዉን በዋናዉ ጉዲይ አከራክሮ ዉሳኔ እንዱሰጥበት የመለሰ መሆኑን መገንዖብ ተችሎል። ይህ ከሆነ ደግሞ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በዘህ የህግ ድንጋጌ መሰረት ዉሳኔ የሰጠ መሆኑን እና ዉሳኔዉም ሕግን የተከተለ መሆኑን ያስገነዛባል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 (1) መሰረት ዉሳኔ ለመስጠት በሕግ ስልጣን እስከተሰጠዉ እና በዘህ አግባብ የሥር ዉሳኔ በመሻር የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን ድጋሚ እንዱያይ ነጥብ ለይቶ እስከመለሰ ድረስ፣ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዘህ ዉሳኔ መሰረት የመፈጸም ኃላፉነት እንዲለበት የሚያከራክር አይሆንም። ይህ ማለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የበላይ ፍ/ቤት በሰጠዉ ትዔዙዛ ወይም መመሪያ መሰረት ግራ ቀኛቸዉን አከራክሮ ዉሳኔ የመስጠት ኃላፉነት አለበት።
ከዘህ መረዲት እንደሚቻለዉ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የበላይ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ግራ ቀኛቸዉን ማከራከር እንዲለበት ነዉ፣ ይህም ግራ ቀኛቸዉ ክርክራቸዉን እንዱያሰሙ እና ዋና የክርክር የመስማት ሂደት መከናወን እንዲለበት ያስገነዛባል። ፍ/ቤቱ በዋናዉ የክርክር መስማት ሂደት ደግሞ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.246-249 ድንጋጌዎች መሰረት ጭብጦችን መመስረት፣ ግራ ቀኛቸዉ ክሳቸዉን እና መልሳቸዉን ሲያቀርቡ የጠቀሱትን ማስረጃ እንዱያቀርቡ ማድረግና መመርመር፣ ፍርድ እና ዉሳኔ የመስጠት ተግባራትን ይፈጽማል ማለት ነዉ። ከዘህ አንጻር አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ መነሻ በማድረግ መዛገቡ የተንቀሳቀሰ መሆኑን ለተከራካሪ ወገኖች በማሳወቅ ዉሳኔ መስጠቱን እንጂ በዘህ አግባብ ግራ ቀኛቸዉ ክርክራቸዉን እንዱያሰሙ እና ዋናዉን የክርክር መስማት ሂደት ያካሂደበት ሁኔታ የለም። ፍ/ቤቱ በዘህ አግባብ አለመፈጸሙ ደግሞ ከፍ ሲል በተጠቀሱት የህግ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የበላይ ፍ/ቤት ከሰጠዉ ዉሳኔ የሚቃረን ስለሆነ የሕግ ድጋፍ የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የበላይ ፍ/ቤት ማለትም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ግራ ቀኛቸዉን ሳያከራክር፣ ሳይሰማቸዉ፣ ጭብጥ ሳይመሰርት እና በማስረጃ ሳያጣራ ዉሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀሪመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.228538 በ16/6/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.212821 ህዲር 11 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተዖጋዉን መዛገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሐተታዉ በተመለከተዉ መሰረት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር፣ ጭብጥ በመያዛ፣ ጉዲዩን በማስረጃ በማጣራት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.343 (1) መሰረት ተመልሶለታል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
የመ.ቁ.228538 ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይመለስ።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.