በሐሰት ማስረጃ የተሰጠ ፍርድ እንዱነሳ የሚቀርብ ጥያቄ በዲግም ዲኝነት ጥያቄ ቀርቦ ከሚስተናገድ በቀር መደበኛ(አዱስ) ክስ በማቅረብ ውሳኔው እንዱሻር የሚጠየቅበት የህግ አግባብ የላለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 6
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 29/9/2011 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች- በኬሚካል ኢንዲስትሪ ኮርፕሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፊብሪካ ነገረ ፈጅ ወዲጄ ማሞ ቀረቡ።
ተጠሪ- አቶ ይትባረክ ተካ፡- ቀረቡ።
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ ሰበር መዛገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የቀረበው አመልካች ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው። ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዖረዛርና በሰበር ሰሚው ችልት በኩል ላታይልኝ ይገባል የሚለውን ዲኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት በአመልካችና ተጠሪ መካከል የነበረው የስራ ክርክር በ5/6/2010 ዓ/ም በቃል ክርክር በተያዖው ቀጠሮ ቀን ግራ ቀኙ ባለመቅረባችን መዛገቡ ተዖግቶ እያለና መዛገቡ ተከፍቶ ክርክር የቀጠለ መሆኑ ሳይነገረኝ በላለሁበት የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ውሳኔው ተነስቶ ክርክር እንዲደርግ መወሰን ሲገባ አቤቱታዬን ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ሲሆን ከሳሽ የአሁን ተጠሪ ሲሆን ተከሳሽ የአሁን አመልካች ነው። የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ በሰጠው ውሳኔ ላይ የአሁን ተጠሪ ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች በላለበት የሰጠውን ውሳኔ የአሁን አመልካች በላለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ይነሳልኝ ሲል በማመልከቱ ነው። መልስ ሰጪ የአሁን አመልካች ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው አቤቱታ በ5/6/2010 ዓ/ም ለቃል ክርክር ለያዖው ቀጠሮ ግራ ቀኛችን ባለመቅረባችን መዛገቡ የተዖጋ ሲሆን ሳይነገረኝ በላለሁበት የሰጠው ውሳኔ መብቴን የሚጎዲ በመሆኑ በላለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ይነሳልኝ ሲል ጠይቋል። ይግባኝ ባይ የአሁን ተጠሪም ለቃል ክርክር እንዱቀርብ የተላከለት መጥሪያ የደረሰው መሆኑን አልካደም። የአፈጻጸም ክስ ቀርቦበት ከፈጸመልኝ በኃላ በላለሁበት የተሰጠብኝ ውሳኔ ይነሳልኝ ሲል ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የላለው በመሆኑ ውድቅ ይሁንልኝ በሚል መልስ ሰጥተዋል። የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ ለመ/ሰጪ ለቃል ክርክር እንዱቀርብ መጥሪያ ደርሶት በቃል ክርክር ጊዚ ሁለቱም ባለመቅረባቸው መዛገቡ የተዖጋ ሲሆን ይግባኝ ባይ መዛገቡ እንዱከፈትለት ምክንያቱን ገልጾ መዛገቡ ተከፍቶለት ክርክሩ እንዱቀጥል ያስፈቀደ ሲሆን መ/ሰጪም ይህንኑ መፈጸም ነበረበት። መ/ሰጪ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት እንዱፈጽም ክስ ቀርቦበት ለይግባኝ ባይ ከፈጸመ በኃላ በላለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ይነሳልኝ በማለት ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የላውም ሲል አቤቱታ ውድቅ አድርጓል።
የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል። መዛገቡም ተመርምሮ ለክርክር ምክንያት የሆነውን ጉዲይ በይግባኝ የተመለከተው የስር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች መጥሪያ ተልኮለት ሳይቀርብ የቀረ ቢሆንም የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ከይግባኝ ባይ ክርክር ጋር በመመርመር የወሰነ መሆን አለመሆኑን ከመሰረታዊ የክርክር አመራር ስነ ሥርዓት ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዲልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ሲል ተከራክሯል። አመልካችም ሚያዛያ 1 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲሆን፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልሱን እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ በሰጠው ውሳኔ መብቴ ተጎድቷል ሉታረምልኝ ይገባል ሲል ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቧል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ለግራ ቀኙ ክርክር እንዱያቀረቡ በተቀጠረበት ቀን ሁለቱም ባለመቅረባቸው መዛገቡ ተዖግቷል። የይግባኝ ቅሬታ የሚያቀርበው ሰው፣ የተወሰነበት ወገን ወይም ይግባኝ የሚባልበት ውሳኔ መብቴን ጎድቶታል የሚለው ወገን ሲሆን፣ በውሳኔው ተጠቃሚ የሆነው ወገን እንዱጸናለት የሚከራከር እንጂ ይግባኝ የሚጠይቅበት ሁኔታ አይኖርም። እንደዘሁም የይግባኝ መዛገብ የተዖጋ እንደሆነም መዛገቡ እንዱከፈትለት የሚጠይቀው ሰው፣ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ መብቴን ጎድቶታልና መዛገቡ ተንቀሳቅሶ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ይታረምልኝ የሚለው ወገን እንጂ በውሳኔ ተጠቃሚ የሆነው ወገን የተዖጋው መዛገብ እንዱከፈት የሚገደድበት አግባብ የለም። የተዖጋው መዛገብ ከተከፈተ በኋላ ላላው ወገን መዛገቡ መንቀሳቀሱን አውቆ ቀርቦ እንዱከራከሩ ላደረግ እንደሚገባ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ አንቀጽ 233 ድንጋጌ በተመሳሳይ ለይግባኝ ክርክር ጊዚም እንደነገሩ አግባብ መፈጸም አለበት። ይግባኝ የተባለበትን ውሳኔ የፈጸመ ተከራካሪ ወገን ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይግባኝ ቅሬታ ለማቅረብም ሆነ አቤቱታ ለማቅረብ የሚከለክለው የህግ ድንጋጌ የላለና የትኛውንም ወገን የሚጎዲም አይደለም።
ይህ ሆኖ እያለ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የህግ መሰረት በላለው ምክንያት ግራ ቀኙ ለክርክር በተቀጠረው ቀን ባለመቅረባቸው ተዖግቶ የነበረው መዛገብ በይግባኝ ባዩ አመልካችነት ሲከፈት መ/ሲጪ እንዱያውቀው ሳይደረግ በላለበት ውሳኔ መስጠቱ እና አመልካች በላለበት የተሰጠው ውሳኔ እንዱነሳለት ያቀረበውን አቤቱታ በቂ ባልሆነ ምክንያት ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው ብለናል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሚያዛያ 25 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ እና ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የአሁን አመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ባቀረበው የይግባኝ ቅሬታ ያስቀርባል በተባለው ጭብጥ የአሁን አመልካች ክርክሩን እንዱያቀርብ በማድረግ ካከራከረ በኋላ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰናል።
በዘህ መዛገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
የዘህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
ሰ/ኃ
ቀን 29/09/2011ዓ/ም ዳኞች፦ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ገ/ኢየሱስ ሙለነህ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- 1ኛ አቶ ወልዳ አቡቴ - አልቀረቡም።
2ኛ ወ/ሮ አዲነች ደላ - ቀረቡ።
መዛገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዘህ መዛገብ የተያዖው ጉዲይ የቤት ክርክር የሚመለከት ሲሆን የጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ የሆሳዔና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በስር አመልካች ከሳሽ 1ኛ ተጠሪ ተከሳሽ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል።አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዖት ባጭሩ፦ አንደኛ ተጠሪ የሀሰት ማስረጃ አቅርበው በ21/08/2006 ዓ/ም በተሰጠው ውሳኔ ከነበራቸው ይዜታ 48 ካ.ሜ ወስደዋል። ይሁንና 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት እና ለውሳኔ መሰረት የሆነው ማስረጃ የሐሰት መሆኑን በፍርድ ቤት ተረጋግጦ በወንጀል ተከሰው 4 ዓመት ከ5 ወር የተቀጡ በመሆኑ ፍርደ ተሽሮ የሰሩትን ቤት አፍርሰው ይዜታውን እንዱያስረክቧቸው እንዱሁም ካሣ ለመጠየቅም የመክሰስ መብት እንዱጠበቅላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
1ኛ ተጠሪ ክሱ ፍርድ ባገኘው ጉዲይ በድጋሚ የቀረበ መሆኑን፣ በወንጀል ጉዲይ የተሰጠው ፍርድ ከፍ/ህግ ግንኙነት የላለው በመሆኑ ውድቅ እንዱደረግ ሲያመለክቱ፤2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ለክርክሩ መሰረት የሆነው ይዜታ ጨምሮ 500 ካ.ሜ ከ1ኛ ተጠሪ የገዘ በመሆኑ ጣልቃ ገብተው እንዱከራከሩ ጠይቀው ፍርድ ቤቱም አቤቱታው ተቀብል የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆኑ አዝል።
በዘህ መልኩ ክርክሩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ይዜታ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ የገዘት በመሆኑ የአመልካች ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱሁም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት ይግባኝ ቅሬታ እና ሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እና ትዔዙዛ በመቃወም ለማሳረም ነው።
አመልካች በ23/03/2011 ዓ/ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርበው የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እና ትዔዙዛ እንዱሻር አመልክቷል። የአመልካች አቤቱታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልትም ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ያቀረበው ሲሆን ተጠሪዎች የበኩላቸውን መልስ በማቅረብ ውሳኔው እንዱጸና ጠይቀዋል። የመልስ መልስም ቀርቧል።
ከስር የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተገለፀው ይዖት ያለው ሲሆን እኛም በየደረጃው ጉዲዩን የተመለከቱት የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ፍርድ እና ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን ክርክሩን በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
እንደመረመርውም፦ ከመዛገቡ እንደተረዲነው የአመልካች መሰረታዊ የዲኝነት ጥያቄ በሐሰት ማስረጃ የተሰጠው ፍርድ እንዱነሳ የሚጠይቅ ነው። የስር ፍርድ ቤት የተጠየቀው ዲኝነት ባሕሪ እና ይዖት ሳያገናዛብ ይዜታው 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛተጠሪ በግዢ ያገኙት በመሆኑ ሉለቁ አይገባም በማለት መወሰኑን ያሳያል። አመልካች በስር ፍርድ ቤት ካቀረቡት ክስ መገንዖብ የተቻለው 2ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ተከራክረው ለተሰጠው ፍርድ መሰረት የሆነው ማስረጃ ሀሰተኛ ሰነድ ላይ የተመሰረተ ነው የሚል ነው። የስር ፍርድ ቤት ዲኝነት እንደገና እንዱታይ የቀረበ አቤቱታ መሆኑን ተገንዛቦ በዘሁ አግባብ ስላልቀረበ መዛገቡን መዛጋት ሲገባው በመደበኛ (አዱስ) ክስ በማስተናገድ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም። የ2ኛ ተጠሪ የመብት ጥያቄም በውሳኔ ተዖጋ በተባለው መዛገብ ህጋዊ ውጤት ከሚታይ በስተቀር በዘህ መዛገብ ጣልቃ ገብ በመሆን የሚከራከሩበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም። በመሆኑም አመልካች የዲግም ዲኝነት ጥያቄው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ6 መሰረት አቅርበው ከሚስተናገደ በስተቀር አዱስ ክስ በማቅረብ ውሳኔው እንዱሻር የሚጠይቁበት የሕግ አግባብ አይኖርም። የስር ፍርድ ቤትም ክሱ ውድቅ ማድረግ ሲገባው የአመልካች ክስ ተቀብል እንደ አዱስ ክስ ማስተናገደ፤ ይኸው ውሳኔ በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች መጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት መፈጸሙን የሚያሳይ በመሆኑ ሉሻር የሚገባው ነው። በዘህ ሁለ ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ የሆሳዔና ከተማ የመጀመርያ ደረጃ በመ/ በ20/04/2010 ዓ/ም፣ የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ17695 በ18/5/2010 ዓ/ም፣ እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ በመ/ቁ10056 በ09/1/2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጡት ፍርድ እና ትዔዙዛ ተሽሯል።
የአመልካች መሰረታዊ የዲኝነት ጥያቄ በዲግም ዲኝነት እንዱታይ የቀረበ ሁኖ ሳለ በአዱስ ክስ መስተናገደ በሕጉ አግባብ አይደለም በማለት ወስነናል።
አመልካች ይሁን 2ኛ ተጠሪ በልላ አግባብ መብታቸው ለማስከበር የሚያቀርቡት ክርክር ይህ ውሳኔ አያግዲቸውም ብለናል።
የዘህ ፍርድ ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪ እና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይተላለፍ።
መዛገቡ ተዖጋ ወደ መዛገብ ቤት ተመለሰ።
No topics extracted.