በይግባኝ ደረጃ ግራ ቀኝ ወገኖች ለክርክር በተቀጠረበት ቀን ባለመቅረባቸው ተዖግቶ የነበረ መዛገብ በይግባኝ ባዩ አመልካችነት ሲከፈት መልስ ሰጪው እንዱያውቀው ሳይደረግ በላለበት ውሳኔ መስጠት እና መልስ ሰጪው በላለበት የተሰጠው ውሳኔ እንዱነሳለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በቂ ባልሆነ ምክንያት ውድቅ ማድረግ አግባብነት የላለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ አንቀጽ 233
No summary available.
ህዲር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፋ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡ አቶ ሲራጅ አባፎጊ ቀርበዋል።
ተጠሪዎች፡
አቶ አባቦር አባጨብሳ
አቶ ነዚፍ አባጨብሳ
ወ/ሮ ሙራዳ አባጨብሳ የቀረበ የለውም።
አቶ ኑሩ አባጨብሳ
አቶ መጫ አባጨብሳ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የገጠር መሬት ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ነው።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ/300663 ላይ ታህሳስ 15/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰቃ ወረዲ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማፅናት በሰጠው ትዕዛዝ ላይ በአሁን አመልካች የቀረበለትን የሰበር አቤቱታ ለሰበር ችልት ክርክር አያስቀርብም በማለት የሰጠው የመጨረሻ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ለማስለወጥ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ እንዱህ ነው። የአሁን አመልካች ታህሳስ 03/2009 ዓ.ም ፅፈው በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ በሰቃ ወረዲ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ መገኛ ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ውስጥ የተጠቀሰውን የገጠር መሬት ይዞታ ወላጅ እናታቸው ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1994 ዓ.ም ድረስ ተጠቅመውበት ሲሞቱ ተላልፎላቸው እስከ 2009 ዓ.ም ድረስ ግብር እየከፈለበት እና የተለያዩ አትክልቶችን ተክለው አልምተው በመጠቀም ላይ እያለ የአሁን 1ኛ ተጠሪ መስከረም 2009 ዓ.ም ወደ ይዞታው ገብተው በኃይል በመያዝ ቤት መስራት ሲጀምሩ ለቀበላ አመልክተው የጀመሩትን ግንባታ እንዱያቆሙ ቢነገራቸውም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገደው የጀመሩትን ግንባታ አፍርሰው ይዞታውን እንዱያስረክቧቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት የአሁን 1ኛ ተጠሪ ታህሳስ 12/2009 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ክርክር የተነሳበትን ይዞታ ለአሁን አመልካች እናት በኪራይ የሰጧቸው ከመሆኑ ውጭ ይዞታው የራሳቸው ለመሆኑ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆኑን በመግለፅ ልለቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የካቲት 17/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት የአሁን 1ኛ ተጠሪ ክርክር በተነሳበት ይዞታ ላይ የጀመሩትን ግንባታ አፍርሰው መሬቱን ለአመልካች እንዱያስረክቡ ወስኗል። በዚሁ ውሳኔ ላይ በአሁን 1ኛ ተጠሪ ይግባኝ የቀረበለት የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የይግባኝ ክርክር ከሰማ በኋላ ጉዲዩ እንደገና ተጣርቶ እንዱወሰን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 343(1) መሰረት በነጥብ መልሷል።
በዚሁ መነሻነት የወረዲው ፍርድ ቤት በታዘዘው መሰረት ጉዲዩን አጣርቶ ህዲር 28/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት በቀደመው ውሳኔ መሰረት ወስኗል። ከዚህ በኋላ ስላለው የክርክር ሂደት መዝገቡ የሚገልፀው ነገር ባይኖርም አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ጉዲዩ እስከዚህ ሰበር ችልት ደርሶ የፀና መሆኑን ገልፀዋል።
በዚሁ መሰረት አመልካች የአፈፃፀም መዝገብ ከፍተው ጉዲዩ በሂደት ላይ እንዲለ የአሁን ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተጠሪዎች በመቃወም አመልካችነት ይቀርባለ። የወረዲው ፍርድ ቤትም በመቃወም አቤቱታው ላይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ጥቅምት 28/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት ክርክር የተነሳበት ይዞታ በአቶ አባጨብሳ አባጎሹ ስም ግብር ሲገበርበት የነበረ ለመሆኑ እና በክልለ ገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 5(5) መሰረት ለአሁን 1ኛ ተጠሪ እና ስር ፍርድ ቤት የመቃወም አመልካቾች የተላለፈ መሆኑን አረጋግጫለሁ በማለት ቀድሞ የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ለአሁን ተጠሪዎች ወስኗል። ይህ ውሳኔ እስከ ክልለ ሰበር ችልት ድረስ የፀና ለመሆኑ ከመዝገቡ ይዘት እንዱሁም የሰበር አጣሪ ችልቱ አስቀርቦ ከመዝገብ ጋር ካያያዛቸው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔዎች ይዘት ለመገንዘብ ተችሎል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካች ጥር 20/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔና ትዕዛዝ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። ፍሬ ቃለም የአሁን ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያለት ተጠሪዎች በመቃወም አመልካችነት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ መጋቢት 17/2010 ዓ.ም በሰጡት የፅሁፍ መልስ ያቀረቧቸውን አምስት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን በመዘርዘር የወረዲው ፍርድ ቤት በመቃወሚያዎቹ ላይ ብይን ሳይሰጥ ያለፈ መሆኑን፤ ክርክር የተነሳበት ይዞታን በተመለከት በአስተዲደር ክፍል ተጣርቶ እንዱቀርብ የተሰጠው ትዕዛዝ እሳቸው በላለበት የአሁን ተጠሪዎች እና ሽማግላዎች በተገኙበት ብቻ በአንድ ወገን በቀረበ ማስረጃ ላይ ተንተርሶ የቀረበ ከመሆኑም በላይ በዚሁ ማስረጃ ላይ ተገቢውን ክርክር ለማቅረብ እድል ያልተሰጣቸው መሆኑን፤ ማስረጃውም ስለዚሁ ክርክር ስለተነሳበት ይዞታ ቀደም ሲል ከአንዳም ሶስት ጊዜ ተጣርቶ ከቀረበው የአስተዲደር ክፍል ሪፖርት ጋር የሚቃረን መሆኑን፤ የወረዲው ፍርድ ቤት እነዚህን ሁኔታዎች አልፎ ውሳኔ መስጠቱ እና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ሆነ የክልለ ሰበር ችልት ያለማረማቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ክርክር በተነሳበት ይዞታ ላይ ቤት ሰርተው ሲጠቀሙበት የነበረ ለመሆኑ ከወረዲው መሬት አስተዲዲር የቀረበው ማስረጃ እየገለፀ የስር ፍርድ ቤት ይህንን ማስረጃ አልፎ መሬቱ አይገባቸውም በማለት የወሰነበት አግባብ ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሐፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
ተጠሪዎች ወኪላቸው በሆኑት 2ኛ ተጠሪ በኩል መጋቢት 24/2011 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት መልስ አመልካች በስር ፍርድ ቤት አቅርቤ ብይን ሳይሰጥበት ታልፋል ብለው በዘረዘሯቸው መቃወሚያዎች ላይ ዝርዝር መልስ በመስጠት ክርክር የተነሳበት ይዞታ የቤተሰቦቻቸው በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች በበኩላቸው ሚያዝያ 25/2011 ዓ.ም በሰጡት የመልስ መልስ ተጠሪዎች በሰበር ማስቀረቢያ ነጥቡ ላይ የሰጡት መልስ ባለመኖሩ እንዲመኑ ተቆጥሮ በአቤቱታው መሰረት ሉወሰን ይገባል የሚል እና ቀድሞ ያቀረቡትን መከራከሪያ የሚያጠናክር ምክንያት በማከል ሞግተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም በማስቀረቢያ ነጥቡ ሳይወሰን ከሰበር ቅሬታው አኳያ በስር ፍርድ ቤቶች የነበረውን የክርክር አመራር ፈትሿል።
በዚሁ መሰረት የአሁን አመልካች በአሁን ከ2ኛ እስከ 5ኛ ባለት ተጠሪዎች በቀረበ የመቃወም አቤቱታ ላይ መጋቢት 17/2010 ዓ.ም በሰጡት መልስ በዝርዝር አምስት፤ በይዘት ደረጃ ደግሞ አራት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረባቸውን፤ እነዚህም 1ኛ/ የመቃወም አመልካቾቹ ከአሁን 1ኛ ተጠሪ ጋር በተለያየ ደረጃ ክርክር ሲደረግ ያውቁ የነበረ በመሆኑ የፍዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁ/56795 ላይ በሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም መሰረት ቀድመው የሚያውቁን ክርክር ውጤት ጠብቀው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 መሰረት መቃወሚያ ሉያቀርቡ አይችለም፤ 2ኛ/ የመቃወም አመልካቾቹ ከአቤቱታቸው ጋር ያቀረቧቸው የግብር ካርኒዎች የእነርሱን ስም የማይጠራ በመሆኑ እና ወራሽ ለመሆናቸውም ያቀረቡት ማስረጃ ባለመኖሩ መቃወሚያ ባቀረቡበት ጉዲይ ላይ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም፤ 3ኛ/ የመቃወም አመልካቾቹ በጉዲዩ ላይ መብት ወይም ጥቅም አላቸው ቢባል እንኳን ክርክር የተነሳበትን ይዞታ ከ12 ዓመት በፊት ከእናቴ ተላልፎልኝ ይዤ እየተገለገለኩበት ያለሁ በመሆኑ በክልለ መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀፅ 32 መሰረት ጥያቄያቸው በይርጋ ይታገዲል፤ 4ኛ/ አመልካቾች ይዞታው በውርስ ተላልፎልናል የሚለ ከሆነ ማንን እንደወረሱ እና አውራሻቸው መቼ እንደሞቱ በአቤቱታቸው ውስጥ አልጠቀሱም፤
ይህ መሆኑም አቤቱታው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 216 መሰረት ተሟልቶ ያልቀረበ እና አመልካች ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1000 አኳያ ማቅረብ የሚችለውን መከራከሪያ ያጣበበብኝ በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል መሆኑን የሰበር አጣሪ ችልቱ አስቀርቦ ከመዝገብ ካያያዘው ሰነድ ለመረዲት ተችሎል።
የቀረበው መቃወሚያ ይህ ሲሆን ጉዲዩን የተመለከተው የወረዲ ፍርድ ቤት የመቃወም አመልካቾች ዋናው ክርክር ሲካሄድ ያውቁ ነበር በማለት በቀረበው መቃወሚያ ላይ ብቻ ትዕዛዝ ሰጥቶ ስለ ላልቹ ምንም ሳይል ማለፉን ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ ለመገንዘብ ተችሎል።
አንድን ክርክር የሚሰማ ፍርድ ቤት በተከራካሪ ወገን በተለያየ የክርክር ደረጃ የሚቀርብለትን መከራከሪያ በተመለከተ ስለመቀበለም ሆነ ስላለመቀበለ ምክንያትን መሰረት ያደረገ ግልፅ ምላሽ ላሰጥ ይገባል። በተለይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በባህሪው ወደ ዋናው ክርክር መግባት ሳያስፈልግ የተጀመረውን ክርክር በመጀመሪያው የክርክር ምዕራፍ ላይ የማቋረጥ ውጤት ያለው በመሆኑ ጉዲዩን የሚያየው የዲኝነት አካል የቀረበውን መቃወሚያ ያልተቀበለበትን ግልፅ ምክንያት ሳያሰፍር ወደ ፍሬ ነገር ክርክር ሉሸጋገር እንደማይገባ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/244 እና 245 ደንጋጌዎች ይዘት እና መንፈስ መረዲት ይቻላል። ይህ ሳይፈፀም በዝምታ ታልፎ በፍሬ ነገር ላይ አከራክሮ መወሰን ተከራካሪዎችን አስፈላጊ ላልሆነ እንግልት እና ወጪ የሚዲርግ ጉልህ የሆነ የጉዲይ አመራር እና የሥነ ሥርዓት ግድፈት በመሆኑ ተቀባይነት አይኖረውም።
አሁን በቀረበው ጉዲይ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የወረዲው ፍርድ ቤት በአመልካች ከቀረበለት በርካታ መቃወሚያዎች ውስጥ በአንደ ላይ ብቻ ትዕዛዝ ሰጥቶ ላልቹን በዝምታ አልፎ በፍሬ ነገር ላይ ውሳኔ መስጠቱ እንዱሁም በየደረጃው ያለት ፍርድ ቤቶችም ይህንን ስህተት ሳያርሙ ማለፋቸው መሰረታዊ የፍትሐብሕር ጉዲይ የሙግት አመራር ሥነ ሥርዓት ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል ክርክር የተነሳበት ይዞታ በተመለከተ ተጣርቶ እንዱቀርብ በወረዲው ፍርድ ቤት በተለያየ ጊዜ በተሰጠ ትዕዛዝ መነሻነት የሰቃ ጮቆርሳ ወረዲ የገጠር መሬት አጠቃቀም ጽ/ቤት በቁጥር BUB/244/2010 ህዲር 19/2010 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ የአሁን አመልካች እናት ከ30 ዓመት በፊት ይዘው ቤት ሰርተውበት ሲጠቀሙበት ቆይተው እሳቸው ሲሞቱ ወደ አመልካች የተላለፈ መሆኑን፤ አመልካችም አትክልት ተክልበት የመንግስት ግብር እየገበረ ያለ እና ይዞታው በመንገድ ግንባታ ምክንያት በተነካ ጊዜም አመልካቹ ካሳ የተከፈለው መሆኑን የገለፀ ሲሆን ሰኔ 13/2010 ዓ.ም በሰጠው መልስ ደግሞ በይዞታው ላይ ላለፉ ሃምሳ ዓመታት ግብር ሲከፈል የነበረው በአቶ አባጨብሳ አባጎሹ ስም መሆኑን እና ክርክር በሚደረግበት ወቅትም ይዞታው በመቃወም አመልካቾች እጅ የነበረ ስለመሆኑ አጣርቶ ሪፖርት ማቅረቡን ለመረዲት ተችሎል።
እነዚህ በወራት ልዩነት ከአንድ አስተዲደር መስሪያ ቤት የተሰጡ ማረጋገጫዎች በይዘት ፍፁም ተቃራኒ ሲሆኑ ጉዲዩን በያዘው ፍርድ ቤት በምን መልኩ እንዱህ ዓይነት ማረጋገጫ ላሰጥ እንደቻለ እንኳን ለማጣራት የተወሰደ እርምጃ ስለመኖሩ መዝገቡ የሚገልፀው ነገር የለም።
በመሰረቱ በፍርድ ቤት ከቀረበ ክርክር ጋር በተያያዘ ከአስተዲደር ክፍል የሚሰጥ መግለጫ እንደየአግባብነቱ ለፍርድ ቤቱ ከቀረቡት ላልች የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ይዘት ጋር ተገናዝቦ የሚወሰድ እንጂ በራሱ የመጨረሻ ማስረጃ አይደለም። ከአስተዲደር ክፍል የሚሰጥ መግለጫ በራሱ የመጨረሻ ነው የሚባል ከሆነ በፍርድ ቤት ዲኝነት በተጠየቀበት ጉዲይ ላይ ወሳኙ ጉዲዩን የያዘው ፍርድ ቤት ሳይሆን አስተዲደር ክፍለ ይሆናል ማለት ነው። ይህ መሆኑ ደግሞ በህገ መንግስት በዲኝነት ሉያልቁ በሚችለ ጉዲዮች ላይ ለመደበኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን የዲኝነት ስልጣን ለላላ አካል አሳልፎ የመስጠት ውጤትን የሚያስከትል በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ከአስተዲደር ክፍል በሚቀርቡላቸው መግለጫዎች አቀባበል እና ምዘና ላይ ጥብቅ ጥንቃቄ ሉወስደ ይገባል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ የተስተዋለው ይኸው ከላይ የተጠቀሰው ስጋት ነው። መጀመሪያ ክርክር የተነሳበት ይዞታ የአሁን አመልካች ስለመሆኑ በምስክሮች አረጋግጫለሁ የሚል መግለጫ ሲቀረብ ለአመልካች ተወሰነ። በኋላ ላይ ደግሞ ይዞታው የመቃወም አመልካቾች አባት ለመሆኑ አጣርቻለሁ ሲባል ለተጠሪዎች ተወሰነ። እናም ጉዲዩን በትክክል ለመግለፅ ፍርድ ቤቱ በአስተዲደር ክፍል የተወሰነውን ውሳኔ ተቀብል መዘገበ ከሚባል በቀር በጉዲዩ ላይ የዲኝነት ውሳኔ ሰጥቷል ማለት አይቻልም።
በፍርድ ቤት ዲኝነት በተጠየቀበት ጉዲይ ላይ የአስተዲደር ክፍል እገዛ ካስፈለገም ተጣርቶ እንዱቀርብ የሚሰጠው ትዕዛዝ ከሞላ ጎደል አስተዲዲር ክፍለ ክርክር ከተነሳበት ጉዲይ ጋር በተያያዘ በእጁ የሚገኙ ሰነድች ላይ ብቻ ያተኮረ ላሆን ይገባል። ከዚህ ባለፈ አስተዲደር ክፍል በፍርድ ቤት በቀረበ ጉዲይ ላይ ምስክር ሰምቶ አልያም በቃለጉባኤ እያጣራ እንዱያቀርብ የሚሰጥ የውክልና ትዕዛዝ አግባብነት የለውም። አከራካሪው ነጥብ በምስክር የሚጣራ ከሆነ ምስክሮችን አስቀርቦ በሥ/ሥርዓት ህጉ መሰረት ምስክሮቹን ጠይቆና መርምሮ ማጥራት ያለበት ፍርድ ቤት እራሱ እንጂ ላላ አካል አይደለም።
እናም የስር የወረዲው ፍርድ ቤት አንድም በአስተዲደር ክፍለ በምስክር እና ቃለ ጉባኤ ተጣርቶ የቀረበለትን መግለጫ ሙለ በሙለ ከመቀበለም በላይ በተለያየ ጊዜ የቀረቡት መግለጫዎች ፍፁም ተቃራኒ በሆኑበት ሁኔታ ልዩነቱ እንዳት ሉፈጠር እንደቻለ በአግባቡ ሳያጣራ እና የቀረበለትን ሪፖርት ይዘት ከቀረቡት ላልች ማስረጃዎች ይዘት ጋር በተገቢው ሁኔታ ሳያገናዝብ አልፎ ከአስተዲደር ክፍል መግለጫ ጋር የሚለዋወጥ ውሳኔ መስጠቱ ህግን ያልተከተለ ብቻ ሳይሆን ፍትሕንም በእጅጉ የጎዲ መሰረታዊ የህግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ/300663 ላይ ታህሳስ 15/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰቃ ወረዲ ፍርድ ቤትን ውሳኔ ያፀናበትን ትዕዛዝ በማፅናት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የሰቃ ጮቆርሳ ወረዲ ፍርድ ቤት በውሳኔ የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ በአሁን አመልካች በአሁን ከ2ኛ እስከ 5ኛ ባለት ተጠሪዎች የመቃወም አቤቱታ ላይ መጋቢት 17/2010 ዓም ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ተገቢውን ብይን እንዱሰጥ ተወስኗል።
በውሳኔ ተራ ቁጥር ሁለት መሰረት በሚሰጥ ብይን የአሁን አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚታለፍ ቢሆን፡- 3.1 የወረዲው የገጠር መሬት አስተዲዲር ጽ/ቤት ክርክር ከተነሳበት ይዞታ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል ህዲር 19/2010 እና ሰኔ 13/2010 በሰጠው መግለጫ እርስ በራሱ የሚጋጭ መግለጫ የሰጠበትን ምክንያት በማጣራት፤
3.2 የወረዲው የገጠር መሬት አስተዲደር ክርክር የተነሳበትን ይዞታ በተመለከተ የተደራጀ ማህደር በእጁ ካለ ከማህደሩ በመመርመር ነባር ይዞታነቱ የማን እንደሆነ፣ በይዞታው ላይ አግባብነት ያለው የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማን ከመቼ ጀምሮ እንዲለው፤ ይህ ከላለ በይዞታው ላይ ግብር በማን ስምና ከመቼ ጀምሮ እየተከፈለ እንዲለ በአግባቡ ተጣርቶ እንዱቀርብለት በማዘዝ፤ እና 3.3. ከላይ በተመለከተው ሁኔታ ተጣርቶ የሚቀርብለትን ሪፖርት ቀድሞ በግራ ቀኙ ከተሰሙት ምስክሮች ቃል ጋር በማገናዘብ እንዱሁም ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስፈላጊ መስል የታየውን ተጨማሪ ምስክር በመስማት ወይም ማስረጃ በማስቀረብ ማስረጃዎቹን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ መርምሮ እና መዝኖ የመሰለውን እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 343(1) መሰረት መዝገቡ ይመለስለት።
የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.