አንድ የእርቅ ስምምነት በፍርድ ቤት ተረጋግጦ ከተመዖገበ በኋላ ወ/ሮ ሙለ ወንድሙ ጥር 3ዐ/ 2ዐ11 ዓ.ም 79 ስምምነቱ የፀደቀበት መዛገብ ባለበት ሁኔታ የእርቅ ስምምነቱን ለማሰረዛ በልላ መዛገብ አዱስ ክስ ማቅረብ የሚቻልበት የህግ አግባብ የላለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 274፣277 እና እነ ወ/ሮ ዖመኗ ድንቁ 16. በፍርድ ቤት ከቀረበ ክርክር ጋር በተያያዖ ከአስተዲደር ክፍል የሚሰጥ መግለጫ እንደየአግባብነቱ ለፍርድ ቤቱ ከቀረቡት ላልች የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ይዖት ጋር ተገናዛቦ የሚወሰድ እንጂ በራሱ የመጨረሻ ማስረጃ አቶ ሲራጅ አባፍጊ እና እነ አቶ አባቦር አባጨብሳ
No summary available.
ጥር 3ዐ ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ተኸሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ /ዶ/ር/ ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች፡- ወ/ሮ ሙለ ወንድሙ ተወካይ ዖላለም አበበ 1ኛወ/ሮ ዖመኗ ድንቁ 2ኛ አቶ እንግዲሰው ክብረት የሁለም ተወካይ 2ኛ ተጠሪ ቀረቡ።
3ኛ አቶ ክብረት ባልቻ መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዘህ መዛገብ የተያዖው ጉዲይ የእርቅ ውል ስለማስፈረስ የቀረበ ክስ የሚመለከት ክርክር ሲሆን የጀመረው በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት የአሁን 1ኛ ተጠሪ በአመልካች እና ከ2ኛ-3ኛ በተጠቀሱ ተጠሪዎች በመዛገብ በ19/7/2010 ዓ.ም ባቀረቡት ክስ መነሻ ነው ። የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ባጭሩ በሥር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሣሽ የነበረ በዘህ መዛገብ 2ኛ ተጠሪ ሆኖ የተመዖገበው ባለቤታቸው መሆኑን ገልጸው፤ ባለቤታቸው ከወላጅ አባቱ በ500 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ቤትና ይዜታ በ26/9/1999 ዓ.ም በተደረገ የስጦታ ውል ያገኙት የጋራ ንብረት ያላቸው ሲሆን ፤ይኸው ቤት በማስያዛ ከባንክ ገንዖብ የተበደሩ መሆኑን ጠቅሰው 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ውል ሰጪ አመልካች ደግሞ ውልተቀባይ በመሆን በ3/6/2008 ዓ.ም ያደረጉት የእርቅ ውል የባልና ሚስት በሆነው ንብረት የተደረገ በመሆኑ የእርቅ ውል በልላቸው መብት የተደረገ በመሆኑ እንዱፈርስ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የሥር ተከሳሾች ያቀረቡት የመከላከያ መልስ እንደተመለከተው 2ኛ ተጠሪ የእርቅ ውል በጋራ ንብረት የተደረገ በመሆኑ ውለ ቢፈርስ እንደማይቃወም ሲገልጽ 3ኛ ተጠሪም የእርቅ ውል ላላ ሰው ንብረት የተደረገ እኔም ደካማ ሽማግላ በመሆኔ ውል ስለመደረጉ አላውቅም ብሎል። የአሁኑ አመልካች በበኩላቸው የአሁን 1ኛ ተጠሪ የእርቅ ስምምነት እንዱፈርስ ያቀረቡት ክስ ውድቅ መደረጉን፤ የስጦታ ውለ እንደሚያውቁት፤ የሶጦታ ውል መደረጉን ካወቁ በኃላ ክስ አቅርበው በአመልካች፤2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በ3/6/2008 ዓ.ም በተደረገው የእርቅ ስምምነት 2ኛ ተጠሪ 100 ካሬ ሜትር ብቻ ወስድ ላላው መሬት እንዱለቅ መስማማታቸውን ገልጸው የእርቅ ውለ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት መከራከራቸውን መዛገቡ ያሳያል።
በዘህ አግባብ ክርክሩ የቀረበለትን የአሰላ ወረዲ ፍርድ ቤትም የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ የእርቅ ስምምነቱ የ1ኛ ተጠሪ መብትና ጥቅም የሚጎዲ በጋብቻ ንብረት ላይ የተደረገ ነው በማለት ስምምነቱን በመሻር ወስኗል። የአሁኑ አመልካች ለአርሲ ዜን ከፍተኛ ፍርደ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቤቱታ አቅርበው ተቀባይነት አላገኘም ። በመቀጠልም አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱ የአመልካችን አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በማለት በትዔዙዛ መዛገቡን ዖግቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህ ውሳኔ በመቃወም ለማሳረም ነው።
አመልካች ሐምል 30/2010 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ አቅርበው የእርቅ ውለ የሚፈርስበት አንዲችም ሕጋዊ ምክንያት በላለበት ሁኔታ እንዱፈርስ መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑን ተደረገ የተባለው የስጦታ ውልም የጋራ ንብረት ባለተለየበት የተሰጠ በመሆኑ ሉሻር ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የአመልካችአቤቱታ የመረመረው አጣሪ ችልትም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዛገብ የተሰጠው ውሳኔ በፀናበት ሁኔታ በተመሳሳይ ጭብጥ ነገር ግን በልላ መ/ ውሳኔ የሰጠበት አግባብ ተጠሪዎች ባለበት ጉዲዩን ማጣራት ይቻል ዖንድ ለዘህ ችልት ያስቀርባል ተብሎል። ተጠሪዎችም ቀርበው በ14/02/2011 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበው የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱፃፍ አመልክቷል። የመልስ መልስም ቀርቧል።
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ፍርድና ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆን አለመሆኑን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ከ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጋር ያደረጉት የእርቅ ስምምነት በሕግ አግባብ የተደረገ በመሆኑ ሉፈርስ አይገባም በሚል ነው። ከዘህ በተያያዖም የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ አመልካች ባቀረቡት የአፈፃፀም መዛገብ ጣልቃ ገብተው በየደረጃው ክርክር ሲደረግ ቆይቶ በመ/ቁ253020 በ20/10/2010 ዓ.ም የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ አዱስ ክስ ሉያቀርቡ አይገባም የሚል ክርክርም ቀርቧል። ከሥር ፍርድ ቤት መዛገቡ መረዲት የተቻለው አመልካች፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በ03/06/2008 ዓ.ም የእርቅ ስምምነት አድርጓል ለዘህ እርቅ ውል መነሻ የሆነው ጉዲይ የአሁኑን 3ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረት የሆነውን ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤትና ይዜታ ለ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ከአመልካች እውቅና ውጭ ሰጥቷል በማለት ስጦታው ለማስፈረስ በወረዲ ፍርድ ቤት ክስ በማቅረባቸው ነው።አመልካች፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጉዲያቸው በእርቅ የቋጩ በመሆኑ የእርቅ ስምምነቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 277/1/ መሰረት ተመዛግቦ መዛገቡ ተዖግቷል። አመልካች በ03/06/2008 ዓ.ም በተደረገው የእርቅ ስምምነት መሰረት እንዱፈጸምላቸው የአፈፃፀም መዛገብ ከፍቷል። የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ አመልካች ያቀረቡት አፈፃፀም መብትና ጥቅሜ የሚነካ ነው በማለት የክርክሩ ተከፊይ ሆናለች።
ጉዲዩ መጀመሪያ የተመለከተው የወረዲው ፍርድ ቤት የእርቅ ስምምነቱ ፍርድ/ውሳኔ/ ስላልሆነ የአመልካች መቃወሚያ ተገቢነት የለውም በማለት ስምምነቱን በመሻር ቤቱ የ1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ነው በማለት የወሰነ ሲሆን አመልካች ይግባኝ ቢጠይቁም ተቀባይነት አላገኙም።
አመልካች የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራቀኙ ከአከራከረ በኋላ በመዛገብ ቁጥር 3770 በሆነው ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 277/1/ የተመዖገበ የእርቅ ውል የአፈጻጸም ክስ ምክንያት መሆኑ እየታወቀ የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ የተዖጋው መዛገብ የእርሷን መብት የሚጎዲ ከሆነ በዙ መዛገብ የእርቅ ውል እንዱሻር ከመጠየቅ በቀር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 ያቀረበችው መቃወሚያ ማስተናገድ የክርክር አመራር ሥርዓት ያልተከተለ የአመልካች መብት የሚያሳጣ ነው በማለት ውሳኔውን ሽሮ 1ኛ ተጠሪ አለኝ የምትለውን ህጋዊ መብት ካለ ልትጠይቅ እንደምትችል በትዔዙዛ ክፍለ አመላክቷል።
በክርክሩ ሂደት መገንዖብ የተቻለው አመልካች ከ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪ ያደረጉት የእርቅ ውል በፍርድ ቤት የተመዖገበ መሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በ20/01/2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ግልባጭ አረጋጋጭ ነው። የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ የእርቅ ስምምነቱ ለማሰረዛ አዱስ ክስ ማቅረቧን መዛገቡ ያመላክታል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በአፈፃፀም መዛገብ ጣልቃ መግባት ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ሽሯል ።
የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ በእርቅ ስምምነት የተዖጋው መዛገብ በመቃወም ያቀረቡት አቤቱታ ስለመኖሩ መዛገቡ አያሳይም። አመልካች፣ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ባደረጉት የእርቅ ስምምነት 2ኛ ተጠሪ 100 ካሬ ሜትር ብቻ ወስድ ቀሪው 400 ካሬ ሜትር እንዱመልስ የተዋዋለ መሆኑን ከቀረበው ክርክር ተገንዛበናል በመሰረቱ ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸው በእርቅ መቋጨት እንደሚችለ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 274 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ያስገነዛባለ። የእርቅ ስምምነቱ በፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 277/1/ መሰረት ተረጋግጣ ከተመዖገበ በእርቁ መሰረት እንዱፈጽም ፍ/ቤት ትዔዙዛ ላሰጥ እንደሚችል ላይ የተገለጸው ህግ 277/2/ በግልጽ ያመለክታል። ከዘህ የምንረዲው የእርቅ ስምምነት የአፈፃፀም ክስ ላቀርብበት የሚችል ህጋዊ ውጤት ያለው ተግባር መሆኑን ነው። በተያዖው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ አመልካች ፣2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ያደረጉት ስምምነት መነሻ በማድረግ የተዖጋው መዛገብ ከሚያንቀሳቅሱ በቀር አዱስ ክስ ማቅረባቸውን በሕጉ የተዖረጋው የሙግት አመራር ሥርዓት የተከተለ ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም አመልካች የእርቅ ስምምነት የፀደቀበት መዛገብ ላይ መቃወሚያ አቅርበው የስጦታ ውል ያለ መሆን አለመሆኑን አለ ከተባለም የጋራ ነው የተባለውን ንብረት 3ኛ ተጠሪ ብቻቸውን ሉሰጡ የሚችለበት ህጋዊ ምክንያት መኖር አለመኖሩን ተመርምሮ ከሚወሰን በቀር የአሁና 1ኛ ተጠሪ ክስ አቅርበው በየደረጃው ያለ ፍርድ ቤቶችም የክርክሩ ይዖትና ባሕሪ በአግባቡ ሳይገናዖቡ የእርቅ ስምምነቱ እንዱሻር መወሰናቸው በሕጉ የተዖረጋው የሙግት አመራር ሥርዓት ያልተከተለ መሰረታዊ የህግ ስሕተት ያለበት ነው ብለናል። የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ አመልካች፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በ3/6/2008 ዓ.ም ያደረጉት የእርቅ ስምምነት የፀደቀበት መዛገብ ከሚያንቀሳቅሱ በስተቀር አዱስ ክስ ማቅረብ የሚችለበት የህግ አግባብ የለም ብለናል። በዘህም ተከታዩን ወስነናል።
በኦሮሚያ ክልል የአሰላ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ በ14/06/2010 ዓ.ም፤ የአርሲ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ29/08/2010 ዓ.ም ፤ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ስሚ ችልት በመ/ቁ289813 በ03/11/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ እና ትዔዙዛ በድምፅ ብልጫ ተሽሯል።
የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ የእርቅ ስምምነት የፀደቀበት መዛገብ ባለበት ሁኔታ በልላ መዛገብ አዱስ ክስ ሉያቀርቡ አይገባም በማለት ወስኗል።
1ኛ ተጠሪ የእርቅ ስምምነት የፀደቀበት መዛገብ የማንቀሳቀስ መብታቸው ይህ ውሳኔ አያግዲቸውም ብለናል።
የዘህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
የውሳኔ ግልባጭ ተረጋግጦ ለሥር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ ብለናል።
ውሳኔው በ26/06/2011 ዓ.ም ተነበበ።
መዛገቡ ዖግተን ወደ ፍ/ቤት መልሰናል።
No topics extracted.