ከመደበኛ ፍ/ቤት ውጭ አንድን ጉዲይ የማየት የዲኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል ጉዲዩን ማየት እንደማይቻል ገልጾ ከመለሰው ጉዲዩን የማየት ስልጣን ለላላ አካል ተሰጥቷል የሚል ክርክር እስካልቀረበበት ድረስ መደበኛ ፍ/ቤቱ ይህን ጉዲይ ማየት አልችልም በሚል መመለስ የማይቻል ስለመሆኑ የፔራይቬታይዚሽን ኤጀንሲ በኤጀንሲው የሚታይ ጉዲይ አይደለም በሚል አረጋግጦ የመለሰው ጉዲይ በስልጣኑ ላይ ላላ ክርክር እስካልቀረበበት ድረሰ ፍ/ቤቶች ተቀብለው ማስተናገድ ያለባቸው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 37፣78(2) እና 79(1)
No summary available.
ጥቅምት 24/2012 ዓም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ኃይለ ነጋሽ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡-
ወ/ሪት ሰላማዊት ይልማ (9 ሰዎች) ተጠሪዎች፡-
የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር ቡታጅራ ቅርንጫፍ ነ/ፈጅ አቶ ሳመኑኤል ቀረቡ።
የቡታጅራ ከተማ አስተዲደር ጽ/ቤት ዐ/ህግ ቀረቡ።
መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዘህ መዛገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የዲኝነት የስረ ነገር ስልጣንን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የቡታጅራ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁን አመልካቾች የቀረበለትን ክስ በተመለከተ የተጠሪዎችን መልስ ከሰማ በኋላ በመ/ቁ/10273 ላይ ታህሳስ 26/2010 በዋለው ችልት ‛ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የለኝም“ በማለት የሰጠው ብይን በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ይግባኝ ችልት በፍ/ይ/መ/ ላይ የካቲት 07/2010 ዓ.ም በመፅናቱ እና የክልለ ሰበር ችልትም በሰ/መ/ቁ/10581 ላይ ሚያዛያ 26/2010 በዋለው ችልት ‛በጉዲይ ላይ የሰበር ስልጣን የለኝም“ በማለት የሰጠውን ትዔዙዛ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ እንዱህ ነው። የአሁን አመልካቾች ለቡታጅራ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክሰ አውራሻቸው አቶ ይልማ ሳህላ በህይወት እያለ በቡታጂራ ከተማ ቀበላ 04 ውስጥ በ1,275 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የንግድ ድርጅት ቤት የነበራቸው መሆኑን፤ በወቅቱ ድርጅቱን ባጋጠመው መጠነኛ የስራ መቀዙቀዛ ድርጅቱ ታድሶ በአዱስ መልክ ስራ እስኪጀምር ድርስ በመዖጋቱ በጊዚው የነበሩት የቀበላ ተመራጮች ያለአንዲች መመሪያ እና ትዔዙዛ እንዱሁም አዋጅ ከሚፈቅደው ውጭ ቤቱን ሰብረው ለወዙደሮች ቡና ቤት እንዱሰሩበት እንዲደረጉ፤ በዘሁ ምክንያት አውራሻቸው ቤቱ ያለአግባብ የተወሰደባቸው መሆኑን ገልፀው እንዱመለስላቸው ለተለያዩ አካላት አቤቱታ ሲያቀርቡ የቆዩ መሆኑን፤ ንብረቱ የአውራሻቸው ስለመሆኑ እና ያለአግባብ የተወሰደባቸው መሆኑንም በሚመለከተው አካል ተጣርቶ የተረጋገጠ ቢሆንም የያዘ አካላት ቤቱን ለቀው ንብረቱን ለባለሃብቱ ማስረከብ ሲገባቸው የአሁን 1ኛ ተጠሪ በምን አግባብ እንደያዖ ባልታወቀበት ሁኔታ ቤቱን ይዜ ያለአግባብ እየተገለገለበት ያለ መሆኑን፤ ይህንኑ ገልፀው ቤቱን እንዱያስረክባቸው ቢጠይቁም ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገድ ቤቱን እንዱያስረክባቸው እና ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በመያዘ የቀረባቸው ገቢ በወር በብር 1,000(አንድ ሺህ) ታስቦ ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና ተገቢ ነው ያለውን የፍሬ ነገር ክርክር በማቅረብ ቤቱን የተረከበው ከአሁን 2ኛ ተጠሪ መሆኑን ገልፆ በጣልቃ ገብነት ወደ ክርክሩ እንዱገባለት ጠይቋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት 2ኛ ተጠሪን በጣልቃገብነት የክርክሩ አካል አድርጎ መልስ ካሰጠ በኋላ ክርክር የተነሳበት ቤት በመንግስት እጅ ቆይቶ በአሁን 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ሐምል 12/1999 ዓ.ም የተላለፈ መሆኑን፤ ከዘህ ጊዚ በፉትም ሆነ በኋላ ቤቱ በመንግስት ቁጥጥር ስር ሆኖ ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጠውም በጊዚያዊነት ለመሆኑ እንዲረጋገጠ፤ በመንግስት እጅ ባለ ቤት ወይም ይዜታ ላይ በመንግስት እና በግለሰቦች መካከል የሚነሳን ክርክር የማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለው በአዋጅ ቁጥር 110/1987 እና 572/2000 መሰረት የፔራይቬታይዚሽን ኤጄንሲ እንጂ መደበኛ ፍርድ ቤት አለመሆኑን ጠቅሶ ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ሥልጣን የለኝም በማለት መዛገቡን ዖግቷል።
በዘሁ ብይን ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁጥር 337 መሰረት ሰርዝል። አመልካቾች ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ችልቱ ከተከራካሪ ወገኖች ውስጥ የአሁን 1ኛ ተጠሪ በፋዳራል መንግስት የተመዖገበ ተቋም በመሆኑ ጉዲዩ የፋዳራል ጉዲይ መሆኑን እና የክልለ ሰበር ችልት የሰበር ስልጣን ያለው በክልል ጉዲይ ላይ ብቻ መሆኑን በምክንያትነት በመጥቀስ የሰበር ስልጣን የለኝም ሲል መልሷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካቾች ጥር 22/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በዘህ ሰበር ችልት ሉታረም ይገባል ያለትን ነጥቦች ዖርዛረው አቅርበዋል። የአቤቱታው ፍሬ ቃልም ክርክር የተነሳበት ቤት የመንግስት ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ በላለበት፤ በአዋጅ፣ በመመሪያ በቀላጤ አልያም በትዔዙዛ ስለመወረሱም የቀረቡት ማስረጃዎች በአግባቡ ሳይመረመሩ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ክርክሩ ከመንግስት ጋር በመሆኑ የዲኝነት የስረ ነገር ስልጣን የለኝም ማለቱ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁ/37281 ላይ ከሰጠው አስገዲጅ ትርጉም አኳያ አግባብ አይደለም፤
የክልለ ሰበር ችልትም ከአሁን 1ኛ ተጠሪ የቀረበለት ክርክር ሳይኖር 1ኛ ተጠሪ በፋዳራል መንግስት የተመዖገበ ተቋም በመሆኑ ጉዲዩ የፋዳራል ጉዲይ ነው በሚል የሰበር ስልጣን የለኝም ማለቱ አግባብ አይደለም የሚል ነው።
በአመልካቾች የተጠየቀው ዲኝነት ያለአግባብ የተያዖብን ቤት ይለቀቅልን የሚል ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን የለንም ያለበት አግባብ ለዘህ ሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ በሰበር አጣሪ ችልት በመታዖዘ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ እንደቅደም ተከተላቸው ሰኔ 22 እና 21 ቀን 2011 ዓ.ም የተፃፈ አንድ አይነት ይዖት ያለው የተናጠል መልስ አቅርበዋል።
ፍሬ ቃለም አመልካቾች በዘሁ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁ/159230 ላይ የሰበር አቤቱታ አቅርበው ጊዚ ያለፈበት አቤቱታ ነው ተብል ውድቅ የተደረገባቸው በመሆኑ ድጋሚ አቤቱታ ሉያቀርቡ አይገባም፤
ክርክር የተነሳበት ቤት ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት እጅ(በአሁን 2ኛ ተጠሪ) የሚገኝ በመሆኑ እና እንደዘህ አይነት ክርክርን የማየት ስልጣን በአዋጅ ቁጥር 110/1987 መሰረት ለኢትዮጵያ ፔራይቬታይዚሽን ኤጄንሲ የተሰጠ በመሆኑ እና ይኸው ሰበር ችልትም በሰ/መ/ቁ/23608 ላይ ተመሳሳይ ትርጉም የሰጠ በመሆኑ የስር መደበኛ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን የለም ማለታቸው ተገቢ ነው፤ የክልለ ሰበር ችልትም የስረ ነገር ስልጣንን በተመለከተ ከተከራካሪዎች የሚነሳን ጥያቄ ሳይጠብቅ አይቶ ስልጣን የለኝ ማለቱ የሚነቀፍ አይደለም የሚል ነው።
አመልካቾች ሐምል 19/2011 ዓ.ም በሰጡት የመልስ መልስ ቀደም ሲል ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ጊዚው ያለፈበት ነው ተብል ውድቅ ቢደረግም በውሳኔው ላይ ጊዚ ያለፈበት አቤቱታ ቀርቦ እንዱታይ መጠየቅ የሚቻል ስለመሆኑ በመገለፁ ይኸው መነሻ ተደርጎ ጊዚ ያለፈበት አቤቱታ ቀርቦ እንዱታይ ማስፈቀጃ ቀርቦ በሰ/መ/ቁ/168197 ላይ በተፈቀደው መሰረት ይህ መዛገብ ሉከፈት የቻለ መሆኑን በመግለፅ በተቀረው ቀደም ሲል የቀረበው የሰበር አቤቱታ በማጠናከር ተከራክረዋል።
በግራ ቀኙ የቀረበው ክርክር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ጉዲዩን አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዖብ መርምሯል።
በመጀመሪያ አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታ ቀደም ሲል ቀርቦ ጊዚ ያለፈበት ነው ተብል ውድቅ ተደርጓል በሚል የቀረበውን መቃወሚያን አስመልክቶ በግራ ቀኙ የተጠቀሱትን መዙግብት ችልቱ አስቀርቦ ተመልክቷል። በዘሁ መሰረት በእርግጥም አመልካቾች በዘህ መዛገብ ላይ ያቀረቡትን አቤቱታ ቀደም ሲል በሰ/መ/ቁ/159230 ላይ አቅርበው አቤቱታው ጊዚ ያለፈበት መሆኑ ተረጋግጦ በህጉ አግባብ ጊዚ ያለፈበት የሰበር አቤቱታ ቀርቦ እንዱታይ ከሚጠየቅ በቀር በቀረበው አግባብ ላታይ አይገባም ተብል ውድቅ መደረጉን፤ በዘሁ ምክንያት አመልካቾች በሰ/መ/ቁ/168197 ላይ የማስፈቀጃ አቤቱታ አቅርበው ጥር 14/2011 ዓ.ም የተፈቀደ መሆኑን ለመገንዖብ ተችሎል። በመሆኑም በዘህ መዛገብ ላይ የቀረበው አቤቱታ የህግ ሥረዓቱን ጠብቆ የቀረበ በመሆኑ ከዘህ አኳያ በተጠሪዎች የቀረበውም መከራከሪያ ችልቱ አልተቀበለውም።
ዋናውን ጉዲይ በተመለከተ በመሰረቱ በፋዳራልም ሆነ በክልል የዲኝነት ስልጣን የመደበኛ ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 79(1) ይደነግጋል። የዲኝነት ስልጣን በመርህ ደረጃ የመደበኛ ፍርድ ቤቶች ቢሆንም ተለይተው በታወቁ ጉዲዮች ላይ በልዩ ህግ የዲኝነት ሥልጣን ለላላ አካል ላሰጥ የሚችል ለመሆኑ ከህገ መንግስቱ አንቀፅ 37 ድንጋጌ መገንዖብ ይቻላል። እናም ዲኝነትን በተመለከተ መሰረታዊ ስልጣኑ የመደበኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ መደበኛ ፍርድ ቤቶች ዲኝነት በተጠየቁበት ጉዲይ ላይ የስረ ነገር ስልጣን የለኝም ከማለታቸው በፉት ዲኝነት የተጠየቀበት ጉዲይ በልዩ ህግ ለላላ አካል የተሰጠ ለመሆኑ በተገቢው መንገድ አጣርተው ሉያረጋግጡ ይገባል። በዘህ መልኩ ሳይጣራ ስልጣን የለኝምበሚል የሚወሰድ እርምጃ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 37 የተረጋገጠውን ፍትህን የማግኘት መሰረታዊ መብትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት አይኖረውም።
አሁን በቀረበው ጉዲይ የአመልካቾች ጥያቄ ክርክር የተነሳበት ቤት ከአዋጅ ውጭ በወቅቱ በነበሩ የቀበላ ሹማምንት ትዔዙዛ ለወዙደሮች ተሰጥቶ የነበረ በመሆኑ እንዱመለስ በቀረበ አቤቱታ መነሻነት የቤቱ አያያዛ ህገ ወጥነት ቢረጋገጥም ሉመለስልን ሲገባ ለአሁን 1ኛ ተጠሪ የተላለፈ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ ሉያስረክበን ይገባል የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት በአሁን ተጠሪዎች በቀረበለት መቃወሚያ መሰረት ክርክር የተነሳበት ቤት በመንግስት እጅ የነበረ እና ለአሁን 1ኛ ተጠሪ በጊዚያዊነት በመንግስት ተላልፍ የተሰጠ በመሆኑ ጉዲዩ የማየት የስረ ነገረ ስልጣን ያለው የፔራይቬታይዚሽን ኤጀንሲ ነው ብሎል። በእርግጥ ከአዋጅ ቁጥር 47/1967 ውጭ በመመሪያ፣ በቀላጤ ወይም በትዔዙት የተወሰደ ንብረቶችን በሚመለከት የሚነሳ ክርክርን አይቶ የመወሰን የስረ ነገር ስልጣን የተሰጠው ለኢትዮጵያ ፔራይቬታይዚሽን ኤጄንሲ ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 110/1987 አንቀፅ 4(1) ድንጋጌ ያስገነዛባል።
ሆኖም ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም ከማለቱ በፉት ክርክር የተነሳበት ቤት/ንብረት/ በተመለከተ የተነሳው ጥያቄ በትክክል በኤጀንሲ ሥልጣን ስር የሚወድቅ ስለመሆኑ፤ ከሆነም በዘያ ረገድ የተደረገ ክርክር እና የተወሰደም አቋም ካለም ከግራ ቀኙ በሚቀርቡለት ክርክር እና ማስረጃ በተገቢው ሁኔታ ሉያጣራ ይገባል።
ይህ ችልም ይህንኑ መሰረት በማድረግ የክርክሩን አመጣጥ ከስረ መሰረቱ ፈትሿል። በዘሁ መሰረት ክርክር የተነሳበትን ቤት በተመለከተ የአሁን አመልካቾ ወላጅ አባት የሆኑት አቶ ይልማ ሳህላ ቤቱ እንዱመለስላችው በደርግ ዖመነ መንግስት ለሸዋ ክፍለ ሀገር ከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር አቤቱታ ያቀረቡ መሆኑን፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ጉዲዩን አጣርቶ እንዱያቀርብለት ለቡታጅራ ልዩ ከፍተኛ ከነማ ጽ/ቤት ጥቅምት 14/1981 ዓ.ም ትዔዙዛ መስጠቱን፤ ጽ/ቤቱ ጉዲዩ በቀበላ ፍርድ ሸንጎ እንዱጣራ ካደረገ በኋላ ሰኔ 24/1981 ዓ.ም ትዔዙዘ ለሰጠው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በሰጠው ምላሽ ክርክር የተነሳበት ቤት የአመልካቾ አባት ዖግተው በመሄዲቸው ምንክያት ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ በቀበላ የተያዖ ስለመሆኑ ማረጋገጡን ገልፆ መመሪያ እንዱሰጥበት መጠየቁ እና ከዘህ በኋላ የተሰጠ ውሳኔ አለመኖሩ ለመረዲት ተችሎል።
በልላ በኩል ይኸው ቤት እንዱመለስላቸው የአመልካቾች አባት ሐምል 29/1988 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ለፔራይቬታይዚሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጄንሲ ጥያቄ አቅርበው ኤጀንሲ መስከረም 12/1999 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቤቱ ከአዋጅ ውጭ በመመሪያ፣ በቀላጤ ለመወሰደ ወይም በአዋጅ ቁጥር 47/1967 አስፈፃሚ አካል ስለመፈቀደ የቀረበ ማስረጃ ባለመኖሩ ኤጀንሲው ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም በሚል ምክንያት መዛገቡን መዛጋቱን እና ይኸው ውሳኔ በይግባኝ በኤጀንሲ ስር ከአዋጅ ውጭ የተወሰደ ንብረቶች ማስፈፀሚያ ፔሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፉ ቀርቦ መስከረም 22/1999 ዓ.ም በምክንያት ተጠናክሮ የፀደቀ መሆኑን ከመዛገቡ ውስጥ ለመረዲት ተችሎል።
ከጉዲዩ አመጣጥ በግልፅ መረዲት እንደሚቻለው ክርክር የተነሳበት ቤት ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት እጅ የነበረ ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 47/1967 መሰረት ለመወረሱ የቀረበ ክርክርም ሆነ የቀረበ ማስረጃ የለም። እናም በአዋጅ ቁጥር 110/1987 መሰረት በዘህ መልኩ ከአዋጅ ውጭ በመመሪያ፣ በቃላጤ አልያም በቃል ትዔዙዛ የተወሰደ እና በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለትን ንብረቶች በተመለከተ የሚነሳን ክርክር ተቀብል የማየት የስረ ነገር ስልጣኑ የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዚሽን አጄንሲ ነው። ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ ኤጀንሲው የዲኝነት ስልጣን የለኝም ብል የመለሰበት አግባብ ግልፅ አይደለም።
ከዘሁ ጋር ተያይዜ ‛በልዩ ህግ የዲኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል የቀረበለትን የዲኝነት ጥያቄን አስመልክቶ ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት ቢመለስ እና ተመሳሳይ የዲኝነት ጥያቄ ለመደበኛ ፍርድ ቤት ቢቀርብ ውጤቱ ምን ይሆናል?“ የሚለውን ማየቱ ተገቢ ይሆናል።
ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት የዲኝነት ስልጣን የተሰጠው ለመደበኛ ፍርድ ቤቶች ብቻ ነው። መርሆው ይህ ቢሆንም ይህንኑ ስልጣን ለፍርድ ቤቶች የሰጠው ህገ መንግስት በልዩ ሁኔታ በህግ የዲኝነት ስልጣን ለላላ አካል ላሰጥ የሚችል ስለመሆኑ እውቅና የሰጠ በመሆኑ ይኸው የህገ መንግስቱ ድንጋጌ በፍርድ ቤቶች በአግባቡ ሉከበር ይገባል። ሆኖም ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጭ አንድን ጉዲይ የማየት በህግ የዲኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል በአንድም ይሁን በልላ ምክንያት ጉዲዩን አላይም ብል ከመለሰ የዲኝነት ተፈጥሮኣዊ ስልጣን የፍርድ ቤት በመሆኑ እና ፍትህ የማግኘት መብት በህገ መንግስቱ የተረጋገጠ በመሆኑ ጉዲዩን የማየት ስልጣን ለላላ የዲኝነት አካል ተሰጥቷል የሚል ክርክር እስካልቀረበ ድረስ መደበኛ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ መልኩ ጉዲዩን ሉመልስ አይገባም።
ከዘሁ ጋር በተያያዖ ይኸው ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁ/ 37964 ላይ ጥር 27/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የፔራይቬታይዚሽን ኤጀንሲ ስልጣን ሥር የሚወድቅ አይደለም በሚል በኤጀንሲው የተረጋገጠ ጉዲይን በተመለከተ ጉዲዩን የማየት ስልጣን ለላላ የዲኝነት አካል የተሰጠነው በሚል ክርክር እስካልቀረበ ድረስ ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ማስተናገድ የሚችለ ስለመሆኑ ትርጉም ተሰጥቷል።
በመሆኑም ጉዲዩ የማየት የስር ነገር የዲኝነት ስልጣን በልዩ ህግ የተሰጠው የፔራይቬታይዚሽን ኤጀንሲ ጉዲዩ ከቀረበለት ከ10 ዓመት በኋላ በኤጀንሲ ሥልጣን ስር አይወድቅም ብል የመለሰ ለመሆኑ ማስረጃ ቀርቦ መዛገብ ውስጥ እያለ እና ስልጣኑ ለላላ የዲኝነት አካል ተሰጥቷል በሚል በተከራካሪ ወገኖች የቀረበ ክርክር በላለበት ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበለት የቡታጅራ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ያለው የፔራይቬታይዚሽን ኤጀንሲ ነው ማለቱ የቀረበውን ማስረጃ እና የፍርድ ቤቶችን ተፈጥሮኣዊ ባህሪን ያላገናዖበ ነው። በዘሁ ጉዲይ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ስህተቱን ከዘህ አኳያ አይቶ ማረም ሲገባው አቤቱታውን መሰረዘ የአመልካቾን ፍትህ የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት የገፈፈ መሰረታዊ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
በመጨረሻም የክልለ ሰበር ችልት በቀረበው ጉዲይ ላይ የሰበር ስልጣን የለኝም ያለውን በተመለከተ በአመልካቾም እንደ አንድ የሰበር ቅሬታ የተነሳ በመሆኑ አንድ ነገር ማለቱ ተገቢ ይሆናል።
በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት የዲኝነትት ስልጣን በፋዳራል እና በክልል የተከፈለ ሲሆን የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የሰበር ስልጣን የተሰጣቸው በክልል ጉዲይ ላይ ብቻ ስለመሆኑ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 80(3(ለ)) ድንጋጌ ያስገነዛባል። የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ስልጣን በፋዳራል ጉዲዮች ላይ ስለመሆኑ እና ከዘህ ውስጥ አንደ በፋደራል መንግስት የተመዖገቡ ተቋማት የክርክር ተካፊይ በሚሆኑባቸው ጉዲዮች ስለመሆኑን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 5(6) ይደነግጋል።
በልላ በኩል የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በህግ በክልልች እስከሚቋቋሙ ድረስ የዲኝነት ስልጣናቸው እንደቅደም ተከተላቸው ለክልል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠ መሆኑን የህገ መንግስቱ አንቀፅ 78(2) እና 80(4 እና 5) ድንጋጌ ያስገነዛባል። የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፋዳራል ጉዲይ ላይ በይግባኝ አይቶ የሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ የሰበር አቤቱታ የሚቀርበው ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ስለመሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች መቋቋሚያ አዋጅ ቁር 25/1988 አንቀፅ 10(3) ይደነግጋል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ በፋዳራል መንግስት የተቋቋመ ድርጅት በመሆኑ ተቋሙ ተካፊይ የሚሆንበት የፍርድ ቤት ክርክር የፋዳራል ጉዲይ ይሆናል። በፋደራል ጉዲይ ላይ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ አይቶ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማፅናት የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ በመሆኑ ከላይ በተጠቀሰው የህግ መንግስቱ እና የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት የሰበር ስልጣን ያለው ይህ ችልት ነው። የዲኝነት የስረ ነገር ስልጣንን በተመለከተ ስልጣን ያለው መሆን ስላለመሆኑ የማረጋገጥ ቀዲሚ ኃላፉነት የፍርድ ቤቶች በመሆኑ የተከራካሪ ወገኖችን መቃወሚያ ወይም መከራከሪያ የሚጠብቅ አይደለም።
በመሆኑም የክልለ ሰበር ችልት በጉዲዩ ላይ የሰበር ስልጣን የለኝም ማለቱ ህጉን በአግባቡ በመተርጎም ተግባራዊ ያደረገ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት ምክንያት ባለመኖሩ ከዘህ አንፃር የቀረበውን የአመልካቾችን መከራከሪያ ችልቱ አልተቀበለውም።
ሲጠቃለል ይህንን ጉዲይ በተመለከተ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።