ፍ/ቤቶች ተከራካሪ ወገኖች በሚያቀርቡት ክስ ላይ ያቀረቡትን መቃወሚያ እና በክሱ መነሻነት የቀረበ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ካለ ራሱን ችል መፍትሓ ማግኘት ያለበት ክርክር ስለሆነ እነ አቶ ዮሐንስ ዖውዳ አበራ እና ከሳሽነት ክሱ ላይ ተገቢውን ሀተታ በማስፈር አግባብነት ያለውን ትዔዙዛ ወይም ብይን መስጠት የሚገባቸው ስለመሆኑ በተከራካሪዎች ለዲኝነት በቀረበ ጉዲይ ላይ ፍ/ቤቶች በራሳቸው አነሳሽነት ወይም በተከራካሪዎቹ በሚቀርብ መቃወሚያ መነሻነት የስረ ነገር ስልጣን የላላቸው መሆኑን ካረጋገጡ መዛገቡን የስረ ነገር ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ሉያስተላልፈ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 17(3) እና 91(5)፤ 182(3) ወ/ሮ ተናኜ ማንያህልሀል ላቀው
No summary available.
ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች፡ 1ኛ አቶ ዮሐንስ ዖውዳ አበራ 2ኛ ወ/ሮ አህላም መሐመድ አብደልአዘዛ ጠ. ገ/እግዘአብሄር ኪዲኔ-ቀረቡ።
3ኛ አቶ አራድም መብራቱ ወልደ 4ኛ አሕላም ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተጠሪ፡ ወ/ሮ ተናኜ ማንያህልሀል ላቀው - አልቀረቡም።
መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በተከሳሽ ከሳሽነት የቀረበ ክርክርን ይመለከታል። ክርክሩ በተጀመረበት የፋ/የመ/ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካቾች ተከሳሾች ነበሩ። ተጠሪ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት የተሻሻለ ክስ ከሐምል 1 ቀን 2008 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2009 ያልተከፈለ ውዛፍ የቤት ኪራይ ብር 480,000.00 (አራት መቶ ሰማንያ ሺ) ከ9% ወለድ ፣ ቤቱን እስኪያስረክቡ ድረስ የሚታሰብ ኪራይ እና መቀጮ ብር 10,000.00 (አስር ሺ) እንዱከፍለ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካቾች ባቀረቡት የመከላከያ መልስ ክሱ እስከቀረበበት ቀን ድረስ ወለድን ጨምሮ ዲኝነት የተጠየቀበት ጠቅላላ የገንዖብ መጠን ብር 512,400.00 (አምስት መቶ አስራ ሁለት ሺ አራት መቶ) ስለሆነ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የለውም በማለት መቃወሚያቸውን አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም የ1 ዓመት ወለድ በባለሞያ ተሰልቶ ውጤቱ እንዱቀርብ ትዔዙዛ የሰጠ ሲሆን ወለደ ብር 43,200.00 (አርባ ሶስት ሺ ሁለት መቶ) መሆኑን በማረጋገጥ መቀጮ እና ዋናውን ገንዖብ ጨምሮ ጠቅላላ ዲኝነቱ ብር 533,900.00( አምስት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺ ዖጠኝ መቶ) ስለሆነ ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን የስረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት መዛገቡን ዖግቶታል። አመልካቾች በጉዲዩ ለፋ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ሥ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት በመሰረዘ በዘሕ ችልት የሰበር አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዖት ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ብር 632,000.00 (ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺ) እንዱከፈላቸው በመሰረቱት ክስ መነሻነት አመልካቾች በተከሳሽ ከሳሽነት ብር 162,194.16 (አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ሺ አንድ መቶ ዖጠና አራት ብር ከ16/100) እንዱወሰንልን ዲኝነት የጠየቅን ሲሆን ፍ/ቤቱ አመልካቾች ያነሳነውን መቃወሚያ በመቀበል ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የለኝም በሚል ብይን ሲሰጥ ያቀረብነው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በዛምታ በመታለፈ ለችልቱ አቤቱታ ያቀረብን ቢሆንም የከፍተኛ ፍ/ቤቱ ይመልከተው በማለት በሰጠው ትዔዙዛ የተፈፀመውን የሕግ ስህተት በማረም የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ላይ አከራክሮ እንዱወስን ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
ጉዲዩ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን በዛምታ የማለፈን አግባብነት ከፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 182(3) አንፃር ለመመርመር ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልሳቸውን እንዱያቀርቡ ታዝል። ተጠሪም በመልሳቸው የአመልካቾች ዲኝነት በዛምታ የታለፈ እንጂ በድጋሜ የቀረበ ክስ ነው ተብል ውድቅ ባለመደረጉ የስር ፍ/ቤት ብይን ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል። አመልካቾች በመልስ መልሳቸው የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አንፃር መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን በስር ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ ከቀረቡ ክርክሮች፣ በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮች እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ዲኝነት የጠየቁበት የገንዖብ መጠን ከፍ/ቤቱ የስረ ነገር ስልጣን በላይ በመሆኑ አመልካቾች ባቀረቡት መቃወሚያ መሰረት ፍ/ቤቱ መዛገቡን በብይን ዖግቶታል። እንዱሁም በስር በነበረው ክርክር አመልካቾች የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርበው የነበረ መሆኑም ግራ ቀኙን አላከራከረም። የአመልካች ቅሬታ የስር ፍ/ቤት ያቀረቡትን መቃወሚያ ተቀብል የተጠሪን ክስ ቢሰርዖውም ያቀረብነውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በዛምታ ማለፈ እና አከራክሮ አለመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚል ነው። በመሰረቱ ፍ/ቤቶች በተከራካሪዎች የሚነሱ የክርክር ነጥቦች በአንድ ጭብጥ ተካተው ሉወሰኑ ከሚችለት በቀር ክርክሮቹን በአግባቡ መርምሮ የቀረቡትን ጭብጦች በየራሳቸው መወሰን እና ተገቢውን ሀተታ በማስፈር የብይን ወይም የፍርደ አካል ሉያደርጓቸው የሚገባ ስለመሆኑ ከፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 182(3) ድንጋጌ መገንዖብ ይቻላል። አመልካቾች በተጠሪ ክስ ላይ ያቀረቡት መቃወሚያ እና በክሱ መነሻነት ያቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ እራሱን ችል መፍትሓ ማግኘት ያለበት ክርክር ነው። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት አመልካቾች ያቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ አግባብነት ያለውን ትዔዙዛ ወይም ብይን አለመስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝንተነዋል።
ላላው በጉዲዩ መፍትሓ ማግኘት ያለበት ነጥብ አመልካቾች በቀረበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ የስር ፍ/ቤት አከራክሮ ሉወስን ይገባ ነበር በማለት የሚያነሱት መከራከሪያ ነው። በተከራካሪዎች ለዲኝነት በቀረበ ጉዲይ ላይ ፍ/ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ወይም በተከራካሪዎቹ በሚቀርብ መቃወሚያ መነሻነት የስረ ነገር ስልጣን የላለው መሆኑን ካረጋገጠ መዛገቡን የስረ ነገር ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ሉያስተላልፍ የሚገባ መሆኑ ከፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 17(3) እና 91(5) መገንዖብ ይቻላል። መዛገቡ ስልጣን ወዲለው ፍ/ቤት መተላለፍ አለበት ከተባለ የተላለፈለት ፍ/ቤት ጉዲዩን ከየት ጀምሮ መቀጠል አለበት የሚለውን መመልከቱ ተገቢ ነው። ስልጣን ወዲለው ፍ/ቤት በሚተላለፍ መዛገብ ውስጥ የግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ብቻ ተጠናቆ የክስ መሰማት ሂደቱ ካልተጀመረ መዛገብ የተላለፈለት ፍ/ቤት ጉዲዩን ከቆመበት መቀጠለ ችግር አይኖረውም። ነገር ግን ጉዲዩን ሲመለከተው የነበረው ፍ/ቤት የስረ ነገር ስልጣን የለኝም ያለው የጽሁፍ ክርክር ካበቃ በኃላ ከክስ መስማት ጀምሮ ያለ የክርክር ሂደቶችን ካደረገ በኃላ ከሆነ ከክስ መስማት ጀምሮ የተደረጉት ሂደቶች ስልጣን በላለው ፍ/ቤት የተደረጉ በመሆኑ ሂደቶቹ በተላለፈው መዛገብ ውስጥ ቢኖሩም መዛገቡ የተላለፈለት ፍ/ቤት ከክስ መስማት ጀምሮ ያለትን የክርክር ሂደቶች እንዲልተደረጉ በመቁጠር እንደገና ሂደቱን ከክስ መስማት ጀምሮ መቀጠል አለበት።
በዘህ መሰረት የፍደራል መ/ደ/ፍ ቤት ተጠሪዎች ክስ ሲያሻሽለ ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የላለው መሆኑን ሲያረጋግጥ እንዲለ መዛገቡን ስልጣን ወዲለው ፍ/ቤት እንዱተላለፍ ማድረግ ሲገባው ስልጣን የለኝም ካለ በኃላ መዛገቡን መዛጋቱ መሰረታዊ የስነ ስርዓት ሕግ ግድፈት የተፈፀመበት ነው።
የፍደራል መ/ደ/ፍ/ቤት የስነ ስረዓት ህጉን ተከትል መዛገቡን እንዲለ ስልጣን ወዲለው ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያስተላልፍ ኖሮ የአመልካቾች የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አብሮ የሚተላለፍ በመሆኑ ለቅሬታ ምክንያት የሆነውም ጉዲይ በዘያው እልባት ማግኘት ይችል ነበር።
አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት ያቀረብነው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ ፍ/ቤቱ አከራክሮ ውሳኔ ላሰጥ ይገባዋል የሚል ነው። ይሁን እንጂ ፍ/ቤቱ በቀረበው ክስ ላይ የስረ ነገር ስልጣን ስለላለው ከስነ ስርዓት ሕጉ ዋና አላማዎች መካከል አንደ ክርክሮች በአነስተኛ ወጪ በአጭር ጊዚ እና በተፊጠነ ሁኔታ ተጠቃለው መፍትሓ እንዱያገኙ ማስቻል ሲሆን፤ ይህም ትክክለኛ ፍትህ ላይ ለመድረስ አስፈላጊ ስለሆነ በስረ ነገር ስልጣኑ ስር ያለትን መርጦ የማየትና ከስረ ነገር ስልጣኑ በላይ የሆኑት ጉዲዮች ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ይቅረብ በማለት ትዔዙዛ መስጠት አይችልም። ምክንያቱም የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የቀረበ እንደሆነ የፍ/ቤቱ የስረ ነገር ስልጣን የሚወሰነው ከተከራካሪዎቹ አንደኛው ወገን ያቀረበው ከፍተኛ የገንዖብ መጠን መሰረት በማድረግ መሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 17(3) ተመላክቷል። በመሆኑም የአመልካቾች የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በከፍተኛ ፍ/ቤቱ ተጠሪ ካቀረቡት ክስ ጋር ተጠቃል ታይቶ ውሳኔ ሉያገኝ የሚገባው በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 27/09/2010 በዋለው ችልት የሰጠው እና በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 21/05/2011 በትዔዙዛ የፀናው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል። ተጠሪ ያቀረቡትን ክስ አከራክሮ ለመወሰን የስረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ብይን ፀንቷል።
የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የተጠሪ ክስ እና አመልካቾች ያቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ተጠቃል ውሳኔ እንዱያገኝ የመዛገብ የሆነውን መዛገብ ስልጣን ላለው የፋ/ከ/ፍ/ቤት ያስተላልፍ ብለናል። ከፍተኛ ፍ/ቤቱም የቀረበውን ክስ እንዱሁም የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ መርምሮ ተገቢ የመሰለውን ይወስን።
በዘህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
ት እ ዙ ዛ ውሳኔው እንዱታተም ለጥናትና ህግ ስራ ክፍል ይተላለፍ።
የውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.