ለአንድ ክስ መሻሻል ወይም ለክርክሩ መለወጥ ቀደም ሲል የቀረበን የክስ ምክንያት በልላ የክስ ምክንያት በመቀየር ለመሟገት ማቅረብ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራ ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዲ ነው በሚል ክስ እንዱሻሻል የሚፈቀድበት የህግ ምክንያት ስላለመኖሩ /በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 91/1/2/
No summary available.
ግንቦት29 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች-፡ ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች- አቶ ተጫነ ካሳ ተጠሪዎች- 1ኛ. አቶ ባህረ ሀፍቱ 2ኛ. አቶ ሀጎስ ሀፍቱ 3ኛ. አቶ ወርቁ አዱሱ መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዘህ መዛገብ የተያዖው ጉዲይ አቤቱታ ማሻሻልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁን አመልካች በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ በትግራይ ክልል ምዔራባዊ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐመራ ምድብ ችልት ባቀረቡት ክስ ነው።
የሥር ፍርድ ቤቶች መዛገብ ግልባጭ እንደሚያሳየው የአሁን አመልካች 3ኛ ተጠሪ ለሆኑት አቶ ወርቁ አዱሱ ከላልች ተጠሪዎች ጋር በአንድ የውል ሰነድ ገንዖብ ስለሰጠኋቸው በ3ኛ ተከሳሽነት አካትቼ ክሱን አሻሽዬ ላቅርብ በማለት አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም ክሱ እንዱሻሻል ፈቅዶል። ነገር ግን አመልካች በ28/03/2010 ዓ.ም የተሻሻለ ክስ ሲያቀርቡ በአጭር ስርዓት እንዱታይ ቀርቦ የነበረውን የብድር ክስ ምክንያት በመቀየር ያላግባብ የመበልፀግ ክስ አድርገው አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ አመልካች አሻሽለው ያቀረቡትን ክስ ባለመቀበል በቀደመው የክስ ምክንያት 3ኛ ተከሳሽን ጨምረው የተሻሻለውን ክስ እንዱያቀርቡ በ18/05/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት ትዔዙዛ ሰጥቶ ቀጠሮ ለውጧል። ነገር ግን አመልካች ክሱን በማሻሻል አቅርቤያለሁ ከዘህ ውጪ ማሻሻል አልችልም፤ በቀደመው ክስ ክርክርም አልቀጥልም በማለታቸው ይህን ተከትል ፍርድ ቤቱ በአመልካች ጉድለት ለቀጠሮው ምክንያት የሆነው ጉዲይ አልተፈፀመም በማለት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 199(2) መሰረት መዛገቡ እንዱዖጋ ብይን ሰጥቷል።
አመልካች ይህን በመቃወም ቅሬታቸውን ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የሰበር አቤቱታው ለዘህ ፍርድ ቤት የቀረበው በዘህ ነው።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ አመልካች ክሳቸውን አሻሽለው እንዱያቀርቡ በምክንያትነት የጠቀሱት ተከራካሪ ወገንን ጨምሮ ለማቅረብ መሆኑንና በዘህም መነሻ ከተፈቀደ በኋላ አመልካች በከሰሱበት ጉዲይ ከህግ የመነጨ መብት ያላቸው መሆኑን ለማሳየት ይረዲ ዖንድ በክስ ምክንያታቸው ላይ ለውጥ አድርገው ማቅረባቸው ሲታወቅ በሃገራችን የሙግት አመራር ስርዓት ፍርድ ቤቶች በእራሳቸው አነሳሽነት ከሚጫወቱት ሚና እና ፍትህ ከማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት አንጻር ታይቶ ጉዲዩ ሉስተናገድ ይገባል? ወይስ አስቀድሞ በተያዖው አቅጣጫ መሰረት አመልካች ፈጽመው ሉቀርቡ አልቻለም በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 199(2) መሰረት ጉዲዩ በጅምሩ ሉቋጭ ይገባል? የሚለውን ለይቶ ለመወሰን እንዱቻል ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል። በዘህ መሰረት ግራቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ ተለዋውጠዋል።
ከፍሲል ባጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። ለሰበር ችልቱ የተያዖውን ጭብጥ ቅሬታ ከቀረበበት ብይን እና ተገቢነት ካላቸው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማያያዛ እንደሚከተለው መርምረናል።
ከላይ እንደተገለፀው የሥር ፍርድ ቤት በአመልካች ጉድለት ለቀጠሮው ምክንያት የሆነው ጉዲይ አልተፈፀመም በማለት መዛገቡ እንዱዖጋ ብይን የሰጠው አስቀድሞ የቀረበው የብድር ክስ ምክንያት ሳይለወጥ 3ኛ ተከሳሽን ጨምረው የተሻሻለውን ክስ እንዱያቀርቡ ትዔዙዛ ሰጥቶ አመልካች በራሴ አሻሽዬ ካቀረብኩት ውጪ ክሱን ማሻሻል አልችልም በቀደመው ክስም ክርክሩን አልቀጥልም በማለታቸው ነው።
የዘህን ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚሻውም የሥር ፍርድ ቤት የተሻሻለውን ክስ ውድቅ ለማድረግ የሕግ መሰረት ነበረው? መዛገቡ መዖጋቱስ በአግባቡ ነው? አይደለም? የሚለት ናቸው።
ክሱ እንዱሻሻል በስር ፍርድ ቤት የተፈቀደበት ምክንያት 3ኛ ተጠሪ የሆኑት አቶ ወርቁ አዱሱ ከላልች ተጠሪዎች ጋር በአንድ የውል ሰነድ ገንዖብ ስለሰጠኋቸው በ3ኛ ተከሳሽነት አካትቼ ላቅርብ በማለት አመልካች አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም ስለተቀበለው መሆኑ በብይኑ ላይ ተመልክቷል።
ይህን ተከትል አመልካች ባቀረቡት የተሻሻለ አቤቱታ ግን የብድሩን ክስ ወደ ያላግባብ የመበልፀግ ክስ ቀይረው አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ በቀደመው የክስ ምክንያት ተከሳሽ ጨምረው የተሻሻለውን ክስ እንዱያቀርቡ ቢያዛም ከዘህ ውጪ ማሻሻል እንደማይችለ ገልፀዋል። ስለሆነም የክስ አቤቱታ ሲሻሻል ዲኝነት የተጠየቀበት የክሱ ምክንያት መለወጥ የሚቻል መሆን አለመሆኑን መመልከቱ ተገቢ ይሆናል።
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 91(1) እንደተደነገገው ፍርድ ከመስጠቱ በፉት በማናቸውም ጊዚ ወይም ፍ/ቤቱ ተገቢ ሆኖ ካገኘው ተከራካሪዎቹ ወገኖች ክሳቸውን እንዱያሻሽለና ክርክራቸውን እንዱለውጡ ሉፈቅድላቸው ይችላል። ስለሆነም የዘህ አይነት መብት ለተከራካሪዎቹ ወገኖች የሚሰጠው የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራው ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዲ ሆኖ በተገመተ ጊዚ ብቻ ነው።
የእንግሉዖኛው ቅጅ፡- ‛The court may at any time before judgment allow either party to alter or amend his pleading …………. and all such amendments shall be made as may be necessary for the purpose of determining the real questions in dispute“ በማለት ይደነግጋል።
ከድንጋጌው መገንዖብ እንደሚቻለው ተከራካሪው ክሱን ለማሻሻል ወይም ክርክሩን ለመለወጥ የሚችለው የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ክስ የቀረበበትን ጉዲይ ይበልጥ ግልጽ የሚያደርገው እንዱሁም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት አስፈላጊ መሆኑ በፍርድ ቤቱ ሲታመንበት ብቻ ነው። ስለሆነም የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ የሚፈቀድበት መሰረታዊ ማጠንጠኛ በግራ ቀኙ መካከል ያለውን ክርክር ለመወሰን አስፈላጊ የሚሆን (for the purpose of determining the real questions in dispute) መሆኑ ነው።
በተያዖው ጉዲይ አመልካች በቀደመው ክሳቸው ዲኝነት የጠየቁት የብድር ገንዖብ እንዱመለስላቸው ሲሆን ክሱን ለማሻሻል በምክንያትነት የጠቀሱትም 3ኛ ተጠሪ የሆኑት አቶ ወርቁ አዱሱ ከላልች ተጠሪዎች ጋር በአንድ የውል ሰነድ ገንዖብ ስለወሰደ በ3ኛ ተከሳሽነት ተካተው እንዱቀርቡ ለማድረግ ነው። ብድሩ ከተካደ በግራ ቀኙ መካከል አከራካሪ የሚሆነው ጉዲይ (the real questions in dispute) ብድር አለ?
ወይስ የለም? የሚለው ነው። ስለሆነም የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ይህን (የብድሩን ጉዲይ) ይበልጥ የሚያብራራው ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዲ ላሆን ይገባል። ነገር ግን አመልካች አሻሽለው ባቀረቡት ክስ የብድር ክስ ምክንያቱን በመቀየር ያላግባብ የመበልፀግ ክስ አድርገው አቅርበዋል። ይህ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራው ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዲ ነው የሚባልበት የህግ ምክንያት የለም።
በመሆኑም በሃገራችን የሙግት አመራር ስርዓት አቤቱታ የሚሻሻለው ጉዲዩን ይበልጥ ለማብራራት ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ሲሆን አመልካች የብድሩን የክስ ምክንያት ቀይረው ያላግባብ በመበልፀግ ክስ ለመሟገት መቅረባቸው በሥነ ስርዓት ህጉ የተዖረጋውን የማሻሻያ ሥርዓት የተከተለ ባለመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት የተሻሻለውን ክስ አለመቀበለ የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል ክሱን እንዱያሻሽል የተፈቀደለት ወገን ይህንኑ ካላቀረበ ክሱን የማሻሻል ወይም ሙግቱን የመለወጥ መብቱ እንደሚቀርና የዘህም ውጤት በቀደመው ክስ ክርክሩን መቀጠል መሆኑን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 91(2) ይዖት መገንዖብ ይቻላል። በተያዖው ጉዲይ አመልካች ክሱን በህጉ አግባብ ብቻ እንዱያሻሽለ ተጠይቀው አሻሽለው ካቀረቡት ውጪ ማሻሻል እንደማይችለና አስቀድመው ባቀረቡት ክስ ክርክሩን ለመቀጠል እንደማይፈልጉ መግለፃቸውን ተከትል ፍርድ ቤቱ በአመልካች ጉድለት መዛገቡን መዛጋቱ በሥነ ሥርዓቱ አግባብ ጉዲዩን መምራቱን ከሚያሳይ በቀር የህግ ስህተት ፈጽሟል የሚያሰኘው አይደለም።
የሰበር አጣሪ ችልቱ የጠቀሰው ላላው ምክንያት ፍርድ ቤቶች በራሳቸው አነሳሽነት የሚጫወቱት ሚና እና ፍትህ የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት ነው። ፍርድ ቤቶች በራሳቸው አነሳሽነት የሚጫወቱት ሚና ሉተገበር የሚችለው በሥነ ሥርዓት ህጉ አግባብ ሲሆን በህጉ በግልጽ ያልተደነገገ ሲሆን ተፈጥሯዊ የሆኑትን መርሆች (Principles of Natural Justice) መከተልም ተገቢ ነው።
የዳኞች ክርክር የመምራት ሚና በሥነ ሥርዓት ህጉና ተፈጥሯዊ የሆኑ መርሆችን በመከተል የተወሰነ በመሆኑ ጉዲዩን በዘህ ስርዓት መምራት ፍትህ የማግኘት መብትን የሚያረጋግጥ ነው ከሚባል በቀር መብቱን የሚጥስ ነው የሚባልበት ምክንያት የለም።
በአጠቃላይ የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በህጉ አግባብ በመምራት ብይን የሰጠ በመሆኑና የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህን መቀበላቸው የሚነቀፍ ባለመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
በትግራይ ክልል የምዔራብ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐመራ ምድብ ችልት በመ/ በ22/05/2010 ዓ.ም የሰጠው ብይን እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በ17/08/2010 ዓ.ም እና የክልለ ሰበር ችልት በመ/ በ25/10/2010 ዓ.ም የሰጡት ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ግራቀኙ ወገኖች በዘህ ፍ/ቤት ለተካሄደው ክርክር ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደመዛገብ ቤት ይመለስ።
እኛ ስማችን በተራ ቁጥር ሶስት እና አምስት ላይ የተጠቀስን ዳኞች በዘህ ጉዲይ የአብላጫ ድምጽ ከሰጠዉ ዉሳኔ በሚከተለዉ ምክንያት ተለይተን የልዩነት ሀሳብ አስቀምጠናል።
ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ግልባጭ መገንዖብ እንደሚቻለዉ የአሁን አመልካች (የሥር ከሳሽ) መጀመሪያ ባቀረበዉ ክስ የብድር ዉል መሰረት በማድረግ የአሁን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች (የሥር 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች) ገንዖብ እንዱከፍለት ዲኝነት መጠየቃቸዉን ነዉ። ነገር ግን የአሁን አመልካች ክስ ለማሻሻል ባቀረበዉ ጥያቄ የአሁን 3ኛ ተጠሪ (የሥር 3ኛ ተከሳሽ) ይህን ገንዖብ ከላልች ተጠሪዎች ጋር የመክፈል ኃላፉነት እንዲለበት በመግለጽ እሱን አካትቶ ክሳቸዉን አሻሽለዉ ለማቅረብ ጠይቋል። የሥር ፍ/ቤትም የአሁን አመልካች ክሳቸዉን ለማሻሻል ያቀረቡትን ጥያቄ በመቀበል የተሻሻለዉን ክስ እንዱያቀርቡ በ18/5/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ትዔዙዛ ፈቅድለት ነበር። ነገር ግን ፍ/ቤቱ የአሁን አመልካች የተሻሻለዉን ክስ ባቀረበ ጊዚ የተሻሻለዉ ክስ ከቀደመዉ ክስ ጋር አንድ ስላልሆነ ተቀባይነት የለዉም በማለት አመልካች ከፈለገ በቀደመዉ ክስ እንዱቀጥል ትዔዙዛ ሲሰጥ፣ አመልካቹ በቀደመዉ ክስ መቀጠል እንደማይፈልግ በመግለጹ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.199 (1) መሰረት መዛገቡን መዛጋቱን የዉሳኔዉ ግልባጭ ያሳያል። ይህ ችልት የአብላጫ ድምጽ በበኩለ አመልካች አሻሽል ያቀረበዉ ክስ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.91 (1) መሰረት ተቀባይነት የለዉም በማለት የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
እኛ ይህን ጉዲይ እንደመረመርነዉ የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች የብድር ዉል መሰረት በማድረግ ገንዖብ እንዱከፈለዉ የአሁን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ ያቀረበዉን ክስ አሻሽለዉ የአሁን 3ኛ ተጠሪን አካትተዉ ገንዖቡን ተጠሪዎች እንዱከፍለት ለመጠየቅ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.91 (1) መሰረት ያቀረበዉን ጥያቄ ተቀብል አመልካች የተሻሻለዉን ክስ እንዱያቀርብ ፈቅድለታል። የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠዉ ትዔዙዛ አመልካች ክሱን አሻሽል 3ኛ ተጠሪን አካትተዉ ገንዖብ እንዱከፈለዉ መጠየቅ እንደሚችል ከፈቀደ በኋላ ተሻሽል የቀረበዉ ክስ የክስ ምክንያት ከቀደመዉ ክስ ጋር አንድ ስላልሆነ ተቀባይነት የለዉም የሚልበት እና አንድ ጊዚ የፈቀደዉን መልሶ ትዔዙዘን በማንሳት የሚከለክልበት የህግ አግባብ የለም። የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች የተሻሻለዉን ክስ ማቅረብ እንደሚችል ከፈቀደለበት በኋላ በራሱ ተነሳሽነት ይህን ትዔዙዛ በማንሳት የተሻሻለዉን ክስ አልቀበልም በማለት የራሱን ትዔዙዛ ከሕግ ዉጭ መልሶ የሚሽርበት የሕግ አግባብ ሉኖር አይችልም። ስለዘህ የሥር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ክሱን ለማሻሻል ያቀረበዉን ምክንያት ተቀብል መጀመሪያ ያቀረበዉን ክስ እንዱተዉ እና የተሻሻለ ክስ እንዱቀርብ ትዔዙዛ ከሰጠ በኋላ ተሻሽል የቀረበዉን ክስ ባለመቀበል አመልካች ከፈለገ በመጀመሪያዉ ክስ እንዱቀጥል የሚያደርግበት የሕግ አግባብ የለም።
እንደሚታወቀዉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.91 (1) እንደሚደነግገዉ ‹‹ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት በማናቸዉም ጊዚ ወይም ፍርድ ቤቱ ተገቢ ሆኖ ካገኘዉ ተከራካሪዎቹ ወገኖች ክሳቸዉን እንዱያሻሽለና ክርክራቸዉን እንዱለዉጡ ሉፈቀድላቸዉ ይችላል። ስለሆነም የዘህ ዓይነት መብት ለተከራካሪዎቹ ወገኖች የሚሰጠዉ የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራ ወይም ትክክለኛ ፍትሕን ለመስጠት የሚረዲ ሆኖ በተገመተ ጊዚ ብቻ ነዉ። ይህንንም በሚፈቅድበት ፍርድ ቤቱ ተገቢ መስል የታየዉን ኪሳራ ለመወሰን ይችላል››። በማለት ይደነግጋል። አንድ ተከራካሪ ወገን ክስ ከቀረበ በኋላ ወሳኝ የዲኝነት ጥያቄ የቀረበት መሆኑን በሂደት የተገነዖብ እንደሆነ ክስ አሻሽል መብቱን መጠየቅ እንዱችል እድል የሚሰጥ ነዉ። በዘህ ድንጋጌ መሰረት የክስ ማሻሻል የማይፈቀድበት ሁኔታ አንደ የክስ ማሻሻል ጥያቄዉ የክርክሩን ጭብጥ ለመወሰን ምንም የማይጠቅም እንደሆነ ብቻ ነዉ። የዘህ ድንጋጌ እንግለዖኛዉ ቅጅ ‛The amendment of pleading shall not be allowed when the amendment is not necessary for the purpose of determining the real questions in dispute“ የሚል ነዉ። ይህ ማለት ፍ/ቤት ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ይረዲል ብል የሚገምት እንደሆነ ወይም የክርክሩን መሰረታዊ ጭብጥ ወይም ጥያቄ ለመወሰን የሚያስችል እንደሆነ አቤቱታ ማሻሻል መፍቀድ እንዲለበት የሚያመለክት ነዉ። እንዱሁም ይህ ድንጋጌ በክስ ማመልከቻ ላይ በሚፈጠረዉ ስህተት የተከራካሪ ወገኖች መሰረታዊ መብቶች እንዲይጎዲ ሕጉ ሰፉ ማዔቀፍ እንደዖረጋ የሚያሳይ ነዉ። ፍ/ቤት ደግሞ በዘህ አግባብ ክስ እንዱሻሻል ሲያደርግ የላላኛዉ ወገን መብት እንዲይጎዲ በቂ ነዉ ያለዉን ኪሳራ መወሰን እና ተሻሽል በቀረበዉ ክስ ላይ ተገቢ ክርክር እንዱያቀርብ እድል መስጠት አለበት። ከዘህ ዉጪ ግን አንድ ተከራካሪ ወገን ክሱን ለማሻሻል በቂ ምክንያት ያለዉ መሆኑን እየገለጸ፣ ሕጉም ደግሞ ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት ክስ ማሻሻል እንደሚቻል በግልጽ እያመለከተ፣ ይህን ድንጋጌ ከመጠን በላይ አጥብቦ በመተርጎም ክስ እንዲይሻሻል እና ተሻሽል የቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ የተከራካሪ ወገን ፍትህ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት እና መሰረታዊ መብቱን ማሳጣት የሚቻልበት አግባብ የለም።
በዘህ መሰረት አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች በዘህ ጉዲይ 3ኛ ተጠሪን ጨምሮ ተጠሪዎች ገንዖቡን እንዱከፍለት ለመጠየቅ ክሱን ለማሻሻል ያቀረበዉ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ከተፈቀደለት በኋላ የቀደመዉ ክስ አመልካች ገንዖብ እንዱከፈለዉ የጠየቀዉ የብድር ዉል መሰረት በማድረግ ሲሆን በተሻሻለዉ ክሰ ደግሞ ያለ አግባብ መበለጸግ መሰረት በማድረግ ስለጠየቀ፣ የተሻሻለዉ ክስ ከቀደመዉ ክስ ስለሚለይ ተቀባይነት የለዉም በማለት አመልካች ከፈለገ በቀደመዉ ክስ ክርክሩን እንዱቀጥል ሲጠየቅ፣ በመጀመሪያ ክስ ክርክሩን መቀጠል እንደማይፈልግ በመግለጹ ክሱን ዉድቅ ማድረጉን መገንዖብ ተችሎል። በዘህ ጉዲይ የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ የአሁን አመልካች ከተጠሪዎች አለኝ የሚለዉን ገንዖብ የሚያስመልስበት አግባብ ነዉ። አመልካች መጀመሪያ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ ክስ ሲያቀርብ የብድር ዉል እንደሆነ የጠቀሰ ቢሆንም 3ኛ ተጠሪን ወደ ክሱ በሚጨምርበት ጊዚ ደግሞ ያለ አግባብ መበልጸግ መሰረት በማድረግ እንደሆነ ተገልጿል። ስለዘህ አመልካች ከተጠሪዎች ሉከፍለኝ ይገባል የሚለዉን ገንዖብ መኖሩን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ የማረጋገጥ ኃላፉነት የእሱ ቢሆንም ይህን መብቱን ለመጠየቅ ግን መጀመሪያ ባቀረበዉ ክስ ላይ የተፈጠረዉን ስህተት በማረም በተሻሻለዉ ክስ ‹‹ያለ አግባብ መበልጸግ›› መሰረት በማድረግ መጠየቁ እና ተጠሪዎች ደግሞ በዘህ በተሻሻለዉ ክስ ተገቢዉን ክርክር የማቅረብ እና ክርክሩ ለዖገየበት ተገቢ የሆነ ኪሳራ የሚከፈላቸዉ ከተደረገ መብታቸዉ የሚጎዲበት አግባብ አይኖርም ማለት ነዉ። የአሁን አመልካች ለክርክር ምክንያት የሆነዉን ገንዖብ ተጠሪዎች እንዱከፍለት ለመጠየቅ በሚያስችለዉ አግባብ ክሱን አሻሽል እንዱያቀርብ ማድረግ ማለት ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዲ ወይም የክርክሩን ወሳኝ ጥያቄ ወይም ጭብጥ ለመወሰን የሚያስችል ጉዲይ ነዉ። ይህ ደግሞ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.91 (1) ሥር የተመለከተዉን መስፈርት የሚያሟላ ሆኖ እናገኛለን። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች ያቀረበዉን የተሻሻለዉን ክስ ተቀብል ተጠሪዎች ተገቢ ክርክራቸዉን እንዱያቀርቡና ተገቢ ኪሳራ እንዱከፈላቸዉ በማድረግ ግራ ቀኛቸዉን በሕጉ አግባብ የማከራከርና የመሰማት መብታቸዉን በማረጋገጥ አጣርቶ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ መስጠት ይገባቸዉ ነበር። ነገር ግን የሥር ፍ/ቤቶች ይህን ጉዲይ በዘህ አግባብ በማየት አመልካች ያቀረበዉን የተሻሻለዉን ክስ ተቀብል ግራ ቀኛቸዉን አከራክሮ ጉዲዩን አጣርቶ መወሰን ሲገባቸዉ ዉድቅ በማድረግ መዛገቡን መዛጋታቸዉ፣ አመልካች በኢ.ፋ.ዳ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37 መሰረት ፍትሕ የማግኘት መብቱን እና መሰረታዊ መብቱን የሚነፍግ እንዱሁም ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን የፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌን የሚጥስ ነዉ።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች በዘህ ጉዲይ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሮ የአሁን አመልካች ያቀረበዉ የተሻሻለዉ ክስ በመቀበል ለተጠሪዎች ተገቢ ኪሳራ ተቆርጦላቸዉና ክርክራቸዉን እንዱያቀርቡ በማድረግ ጉዲዩ ተጣርቶ ዉሳኔ እንዱሰጥበት ለሥር ፍ/ቤት መመለስ ነበረበት ብለን የአብላጫ ድምጽ ከሰጠዉ ዉሳኔ በመለየት የልዩነት ሀሳባችን አስቀምጠናል።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.