አንድን ክስ በመጀመሪያ መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ የተሰጠን ዉሳኔ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ከሻረው በኋላ የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ጉዲዩ ላይ ተገቢዉን እንዱወስን መመለስ ሲገባው ያን ሳያደርግ ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ራሱ የሚሰጠዉ ዉሳኔ ማስረጃን መዛኖ ፍሬ ነገርን ከማረጋገጥ ጋር በተያያዖ ሉፈጠር የሚችለዉን ስህተት ለማሳረም ይግባኝ የማቅረብ መብትን ከማስፊት አንፃር ታይቶ ተፈፃሚነት ሉኖረዉ የሚገባውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ አንቀፅ 341 ድንጋጌን ትክክለኛ አፈፃፀም ያልተከተለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ አንቀፅ 341
No summary available.
ቀን - 30/09/2011 ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ሙስጠፊ መሐመድ ተጠሪ፡- አቶ ናስር ኢሳ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ ፍርድ መነሻ የሆነዉ ጉዲይ የተጀመረዉ በሆሮ ወረዲ ዜን ፍርድ ቤት ሲሆን፣ አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የአመልካች ክስ ይዖትም በአጭሩ፡- አባቴ አቶ መሐመድ አባያሲን በሻምቡ ከተማ 01 እና 02 ቀበላ ዉስጥ ያለዉን ንብረቶቹን እንዱጠብቁ እና እንዱያከራዩ ለተከሳሽ ዉክልና ሰጥተዉ በ2004 ዓ.ም ከሞት የተለዩ ሲሆን፣ ከአባታችን ሞት በኋላም የአባቴ ወራሾች ለተከሳሽ ተመሳሳይ ዉክልና ሰጥተናል፤ ይሁንና ተከሳሽ የከተማዉን አስተዲደር በማሳሳት በሻምቡ ከተማ ቀበላ 02 ዉስጥ የሚገኘዉ እና አዋሳኞቹ በክሱ የተመለከተዉን እና በዉርስ የሚተላለፍልኝን ሁለት ክፍል የንግድ ቤት በስሙ በማድረግ እየተጠቀመበት የሚገኝ በመሆኑ ቤቱን እንዱያስረክበኝ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ።
ተጠሪ ለክሱ በሰጠዉ መልስ፡- ከሳሽ አባቱ ከሞተ ከ 9 ዓመት በኋላ የወራሽነት መብት አለኝ በሚል ያቀረበዉ ክስ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1000(1) መሰረት በይርጋ ይታገዲል የሚል የመጀመሪያ መቃወሚያ በማስቀደም ፍሬነገሩን በተመለከተም የከሳሽ አባት በህይወት እያለ ቤቱን ለባንክ አስይዖዉ የተበደሩትን ገንዖብ ባለመመለሳቸዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤቱን ለመሸጥ ያወጣዉን ጨረታ ተወዲድሬ ከባንክ የገዙሁት የግላ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የወረዲዉ ፍርድ ቤት ከግራ ቀኝ በዘህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የአመልካች አባት ከዘህ ዓለም በሞት ከተለዩበት ከ 8 ዓመት በኋላ አመልካች ያቀረበዉ ክስ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1000(1) መሰረት በይርጋ ቀሪ ነዉ በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለሆሮ ጉደሩ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን፣ ይግባኝ ሰሚዉ ችልት መዛገቡን አስቀርቦ ከመረመረ በኋላ ክሱ በይርጋ የማይታገድ መሆኑን ጠቅሶ የወረዲዉ ፍርድ ቤት በዘህ ረገድ የሰጠዉን ዉሳኔ የተቸ ሲሆን፣ በልላ በኩል ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ከባንክ ገዛቶ የያዖ ስለመሆኑ ተረጋግጧል በሚል የወረዲዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ በዉጤት ደረጃ በማጽናት ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ያቀረበዉ አቤቱታም ተቀባይነት አላገኘም።
አመልካች በቀን 23/12/2010 ዓ.ም ተዖጋጅቶ በቀረበ አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በሆሮ ወረዲ ፍርድ ቤት እንዱሁም በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በትዔዙዛ የፀናዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚልባቸዉን ምክንያቶች በመዖርዖር ታርሞ ይወሰንለት ዖንድ ዲኝነት ጠይቋል። አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለም ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል።
ከስር ጀምሮ የክርክሩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከላይ የተመለከተዉን ሲመስል፣ ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መዛገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። መዛገቡን መርምረን የወረዲዉ ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ዉድቅ በማድረግ ለሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ያደረገዉ ክሱ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1000(1) መሰረት በሦስት ዓመት ይርጋ የሚታገድ መሆኑን ነዉ።
ከላይ እንደተገለጸዉ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ክሱ በይርጋ የማይታገድ መሆኑን ጠቅሶ ግን የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉን ዉሳኔ በዉጤት ደረጃ ሉያፀና የቻለዉ የወረዲዉ ፍርድ ቤት ቤቱ የማን እንደሆነ የከተማዉን አስተዲደር ጠይቆ ያረጋገጠ በመሆኑ ጉዲዩን ወደ ስር ፍርድ መመለስ ላላስፈላጊ ወጪ እና ድካም ከሚዲርግ ዉጪ ላላ ፊይዲ የላለዉ መሆኑን ነዉ። በእኛ በኩል እንደተመለከትነዉ የወረዲዉ ፍርድ ቤት ከፍሬ ነገር ክርክር ጋር በተያያዖ በግራ ቀኝ የቀረቡትን ክርክሮች እና ማስረጃዎች ይዖት በዉሳኔዉ ያሰፈረ ቢሆንም የቀረቡትን የሰዉ ማስረጃዎች ከግራ ቀኝ ክርክር አንፃር በመመዖን እና በመመርመር የሰጠዉ ዉሳኔ የለም። የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 341 ክስን በመጀመሪያ መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ የተሰጠን ዉሳኔ ይግባኝ ሰሚዉ ሽሮ የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ጉዲዩ ላይ ተገቢዉን እንዱወስን ሉመልስ እንደሚገባ ይደነግጋል። የክርክሩን ፍሬ ነገር በተመለከተ ዉሳኔ መስጠት ማለት ደግሞ ማስረጃዎችን ማሰባሰብ ብቻ እንዲልሆነ እና የቀረቡትን ማስረጃዎች ከግራ ቀኝ ክርክር አንፃር በማገናዖብ፣ መርምሮ እና መዛኖ በፍሬ ነገር ረገድ ድምዲሜ ላይ መድረስን እንደሚያካትት ግልጽ ነዉ። የህጉ አንቀጽ 341 ድንጋጌ አፈፃፀም ማስረጃን መዛኖ ፍሬ ነገርን ከማረጋገጥ ጋር በተያያዖ ሉፈጠር የሚችለዉን ስህተት ለማሳረም ይግባኝ የማቅረብ መብትን ከማስፊት አንፃር ታይቶ ተፈፃሚነት ሉኖረዉ ይገባል።
ከዘህ አንፃር ሲታይ የሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወረዲዉ ፍርድ ቤት ክሱን በይርጋ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉን ዉሳኔ ማረሙ ተገቢ ሆኖ ግን ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተ የግራ ቀኝን ክርክር ከቀረቡት የተለያዩ ማስረጃዎች አንዱሁም እንዲስፈላጊነቱ ተጨማሪ ማስረጃም ካለ እንዱቀርብ በማድረግ መርምሮ እና መዛኖ ተገቢዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 341(1) መሰረት መመለስ ሲገባዉ ይህን ባለማድረግ ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተ የሰጠዉ ዉሳኔ የዘህን ድንጋጌ ትክክለኛ አፈፃፀም መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል።
በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
የሆሮ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 01/10/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፣ የሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 14/05/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፣ እንዱሁም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 28/09/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ ተሽረዋል።
የሆሮ ወረዲ ፍርድ ቤት የተዖጋዉን መዛገብ በማንቀሳቀስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ተጠሪ የያዖዉ ከአመልካች አባት እንዱሁም ከአመልካች በአደራ ነዉ ወይስ ከባንክ ገዛቶ ነዉ የሚለዉን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ማስረጃ እንዱሁም እንዲስፈላጊነቱ ተጨማሪ ማስረጃም ጭምር በማስቀረብ ከመረመረ በኋላ ተገቢዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት መዛገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 341(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዘህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.