ተከራካሪ ወገኖች የሚያቀርቡትን ክርክር በቅን ልቦና እና እውነትነት ባለው ማስረጃ የማይከራከሩ በሆነ ጊዚ ፍ/ቤቶች የቀረበላቸው ነገር እውነት መሆኑን ባልተረደ እና ፍፁም ድብቅ በሆነባቸው ጊዚ እውነት ላይ ለመድረስ በሀሰተኛ ማስረጃ እና በሃሰተኛ ተከራካሪዎች ቅን ልቦና መጉደል ምክንያት እውነትን የያዘ ሰዎች ላይ ያልተገባ ፍርድ እንዲይሰጥ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ትክክለኛ ነው ያለትን ውሣኔ መስጠት ያለባቸው አቶ ምስጋናው አሰጌ እና እነ አቶ አይናዱስ አሰጌ ታህሳስ 22 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም. 10. የአፈፃፀም ችልት በፍርድ ባለመብትና በፍርድ ባለዔዲ መካከል አንድን ቤት በዓይነት ለመካፈል ስምምነት እንደላለ በማረጋገጥ በሐራጅ እንዱሸጥ ትዔዙዛ የሰጠ እና ግራቀኙም በቀረቡት ተጫራቾች ሐራጁ እንዱቀጥል በፊርማቸው አረጋግጠው ቤቱ የተሸጠ ከሆነ የሐራጁ የሽያጭ ሥርዓት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ወይም በማጭበርበር ተፈጽሟል ለማለት የሚያስችል የአቶ ተሾመ ጎርፋ ወራሽ መቅደስ ተሾመ እና ወ/ሮ ፈሰሰች ወንድማገኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 445
No summary available.
የሰ.መ.
የካቲት 29 ቀን 2011ዓ.ም ዳኞች፡- ሰለሞን አረዲ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- የአቶ ተሾመ ጎርፋ ወራሽ መቅደስ ተሾመ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፈሰሰች ወንድማገኝ ወራሽ ጣሰው ተሾመ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ አፈጻጸምን የሚመለከት ነው። በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ የፍርድ ባለመብት የአሁን አመልካች ደግሞ የፍርድ ባለዔዲ በመሆን ተከራክረዋል። የአሁን አመልካች ለስር አፈጻጸም ችልቱ ባቀረቡት አቤቱታ የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት በመጀመሪያው አማራጭ በዓይነት የማካፈል ስራ ሳይሰራ ንብረቱን በሐራጅ እንዱሸጥ ማድረጉ አግባብ ስላልሆነ የሀራጅ ሽያጩ ታግድ በዓይነት እንድንካፈል ትዔዙዛ ይሰጥላቸው ዖንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። አፈጻጸሙን የመራው ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ መርምሮ ፍ/ቤቱ ከሰጠው ውሳኔ እና ትዔዙዛ ውጪ እየተደረገ ያለ የአፈጻጸም ሂደት ስለመኖሩ የቀረበ ማስረጃ የላለ በመሆኑ ሐራጁ የሚታገድበት የሕግ አግባብ የለም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች ይህን ትዔዙዖ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት አቤቱታቸውውድቅ ተደርጓል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንትዔዙዛ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡- አመልካች እና ተጠሪ የውርስ ሐብት በሆነው ንብረት ላይ እኩል ድርሻና መብት አለን፤ ክፍፍለን በተመለከተ ወደ ላልች አማራጭ መሓድ የሚቻለው ፍርድ ያረፈበት ቤት መካፈል የማይችል ከሆነ ነው፤ ቤቱንማካፈል እየቻለ በሐራጅ ቢሸጥ የአመልካችን መብት ይጎዲል፤ የክፍለከተማው የይዜታ አስተዲደር የሽግግር ጊዚ አገልግልት ፔሮጀክት ጽ/ቤት በቀን 12/01/10 ዓ.ም ጽፍ በላከው ማስረጃ በመመሪያ ቁጥር 12/2006 መሰረት መካፈል የሚችል መሆኑን ገልጾ ሳለ በዘሁ አግባብ ክፍፍለ መፈጸም ሲገባው የመጨረሻውን አማራጭ በመጠቀም በሐራጅ እንዱሸጥ መደረጉ ተገቢ አይደለም፤ ቤቱ በሐራጅ ቢሸጥ ዋጋው በጣም አነስተኛ ስለሚሆን እና በቤቱ እንዲልገለገል የሚያደርገኝ በመሆኑ ቤቱ በሐራጅ መሸጡ ቀርቶ በዓይነት እንድካፈል ይወሰንልኝ የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ቤቱ መካፈል መቻል አለመቻለን በተመለከተ ከአፈጻጸም ዲይሬክቶሬቱ ለቀረበው ጥያቄ በመመሪያ ቁጥር 12/2006 መሰረት መካፈል ይችላል የሚለው ምላሽ ውጤቱ ባልታወቀበት ተጠቃሹ ቤት በጨረታ እንዱሸጥ መወሰኑ ዋናውን ውሳኔ ያገናዖበ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ፡- ቤቱን በዓይነት ለማካፈል የማይቻል መሆኑን የክፍለከተማው የሰነድ አልባ ይዜታዎች ዳስክ ቦታው ድረስ መሐንዱስ በመላክ አረጋግጧል፤ ቤቱን በዓይነት እኩል መካፈል የማይቻለው በአንድ በኩል ያለው ቤት በብረት እና በብልኬት በጥራት የተሰራ ትልቅ ቪላ ቤት ሲሆን በልላ አቅጣጫ ያለት ቤቶቸ ደግሞ በእንጨት እና በጭቃ የተሰሩ ያረጁና እየፈራረሱ ያለ ቤቶች በመሆናቸው ነው፤ ይህንኑ ለመግለጽም የሰነድ አልባ ይዜታዎች የተጠቀመው አገላለጽ ቤቶቹ የተሰሩበት ቁስ ወይም ማቴሪያል የሚል ነው፤ ቤቱ በዓይነት መካፈል የማይችል እና ግራቀኛችን በስምምነት መካፈል ያልቻልን በመሆኑ በሐራጅ እንዱሸጥ ታዝል፤ መመሪያ ቁጥር 12/2006 የይዜታ አሰጣጥ መመሪያ እንጂ የውርስ ሀብት የሆነ የቤት ክፍፍል መመሪያ አይደለም፤ ቤቱ በሐራጅ ከተሸጠበት ከነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በውሳኔው ለአመልካች እንዱከፈላቸው የተወሰነው 9 በመቶ ወለድ በተጠሪ ላይ እየቆጠረብኝ በመሆኑ አመልካች አላግባብ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። እኛም እንዱጣራ የተያዖውን አከራካሪውን ጭብጥ ከግራቀኙ ክርክር፤ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
አከራካሪ የሆነው ቤት ግማሽ ድርሻ የአቶ ተሾመ ጎርፋ መሆኑ እና ግማሹ ድርሻ ደግሞ የሟች ወ/ሮ ተናኜ ተሾመ በመሆኑ የሟች ወ/ሮ ተናኜ ተሾመ ግማሽ ድርሻ ወራሻቸው ለሆኑት የወ/ሮ ፈሰሰች ወንድማገኘሁ ድርሻ ነው በማለት የተወሰነ መሆኑን፤ በመዛገቡ ተከራካሪ የሆኑት አቶ ተሾመ ጎርፋ እና ወ/ሮ ፈሰሰች ወንድማገኘሁ ከዘህ ዓለም በሞት በመለየታቸው በአመልካች በኩል መቅደስ ተሾመ በተጠሪ በኩል ደግሞ ጣሰው ተሾመ ተተኪ ወራሽ በመሆን ክርክሩ የቀጠለ መሆኑን የሥር መዛገብ የሚያሳይ ሲሆን የአሁን አመልካች አፈጻጸሙን ለመራው ፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረቡት በመጀመሪያው አማራጭ መሰረት በዓይነት የማካፈል ስራ ሳይሰራ ቤቱ በሐራጅ እንዱሸጥ መደረጉ አግባብ ስላልሆነ የሐራጅ ሽያጩ ታግድ በዓይነት እንድንካፈል ይደረግልኝ በሚል ነው።
አመልካች በዘህ አግባብ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት ቤቱ በዓይነት መካፈል የሚችል መሆን አለመሆኑን ተጣርቶ እንዱቀርብለት ለክፍለከተማው የይዜታ አስተዲደር የሽግግር ጊዚ አገልግልት ፔሮጀክት ጽ/ቤት በሰጠው ትዔዙዛ መሰረት ተጠቃሹ አካል በቀን 12/01/10 ዓ.ም በጻፈው ምላሽ ካርታው ወጪ ያልሆነ ሰነድ ስለሆነ በሰነድ አልባ ዳስክ እንጂ በኛ በኩል ለማካፈል የማንችል መሆኑን እየገለጽን ነገርግን በመመሪያ ቁጥር 12/2006 መሰረት መካፈል የሚችል መሆኑን እንገልጻለን የሚል ምላሽ የሰጠ መሆኑን፤ ይህንኑ ምላሽ መነሻ በማድረግ የአፈጻጸም ዲይሬክቶሬቱ ክፍለከተማው የይዜታ አስተዲደር የሽግግር ጊዚ አገልግልት ፔሮጀክት ጽ/ቤት የሰነድ አልባ ፔሮጀክት ዳስክ ቤቱን በዓይነት እንዱያካፍል በማለት ትዔዙዛ የሰጠ መሆኑን፤ ትዔዙዘ የተላለፈለት የክፍለከተማው ሰነድ አልባ ዳስክም በቀን 21/06/2010 ለዲይሬክቶሬቱ በሰጠው ምላሽ ቦታው ድረስ በመገኘት ለመካፈል በተደረገው ጥረት መሰረት ቤቱን በዓይነት ለማካፈል የተሰራበት ቁስ / ማቴርያል / ስለሚለያይ ለማካፈል ተቸግረናል በማለት ምላሽ የሰጠ መሆኑን፤ የአፈጻጸም ዲይሬክቶሬም በግራቀኙ መካከል ስምምነት የላለ መሆኑን በመግለጽ ቤቱ በብር 32,1,279.13 የጨረታ መነሻ ዋጋ በሐራጅ እንዱሸጥ በማለት ትዔዙዛ የሰጠ መሆኑን፤ በዘሁ መሰረት አከራካሪው ቤት ለጨረታ የቀርበ እና አመልካች እና ተጠሪ በቀረቡት ተጫራቾች ጨረታው እንዱቀጥል በማለት በፊርማቸው አረጋግጠው ወ/ት ራሓል ሞገስ የተባለ ግለሰብ በብር 6,850,000 /ስድስት ሚልዬን ስምንት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር / ጨረታውን ያሸነፈ እና ገንዖቡን ገቢ ያደረጉ መሆኑን የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአፈጻጸም መዛገብ እና የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት የአፈጻጸም መዛገብ አስቀርበን በማየት መገንዖብ ችለናል።
በመሰረቱ የውርስ ሐብት ክፍያን በሚመለከት በተቻለ መጠን በዓይነት የሚከፊፈል ስለመሆኑ፤
በዓይነት መካፈል የማይችል ከሆነ እና በባለመብቶቹ መካከል ስምምነት ከታጣ ንብረቱ በሐራጅ ተሸጦ ክፍፍለ የሚፈጸም ስለመሆኑ የውርስ ክፍፍለን አስመልክቶ ከተደነገጉት የፍትሐብሕር ሕጉ ድንጋጌዎች መገንዖብ ይቻላል። በልላ በኩል የሽያጭ ሥርዓት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ወይም በማጭበርበር ተፈጽሟል በማለት እንዱፈርስ ወይም እንዱታገድ ማመልከቻ ማቅረብየሚቻል መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 445 ድንጋጌ ያስገነዛባል።
በያዛነው ጉዲይ አመልካች እና ተጠሪ የየራሳቸውን መስመር በመከተል የንብረቱ ባለቤቶች የነበሩት ተተኪ ወራሾች ሲሆኑ የክፍለከተማው የይዜታ አስተዲደር የሽግግር ጊዚ አገልግልት ፔሮጀክት ጽ/ቤት ካርታው ወጪ ያልሆነ ሰነድ ስለሆነ በሰነድ አልባ ዳስክ እንጂ በኛ በኩል ለማካፈል የማንችል መሆኑን እየገለጽን ነገርግን በመመሪያ ቁጥር 12/2006 መሰረት መካፈል የሚችል መሆኑን እንገልጻለን የሚል ምላሽ በመስጠቱ የአፈጻጸም ዲይሬክቶሬቱ ክፍለከተማው የይዜታ አስተዲደር የሽግግር ጊዚ አገልግልት ፔሮጀክት ጽ/ቤት የሰነድ አልባ ፔሮጀክት ዳስክ ቤቱን በዓይነት እንዱያካፍል በማለት ትዔዙዛ በሰጠው ትዔዙዛ መሰረት ተጠቃሹ አካል ቦታው ድረስ በመገኘት ለማካፈል በተደረገው ጥረት መሰረት ቤቱን በዓይነት ለማካፈል የተሰራበት ቁስ / ማቴርያል / ስለሚለያይ ለማካፈል የተቸገረ መሆኑን በመግለጽ ምላሽ ሰጥቷል። ይህንኑ ተከትል ቤቱን በዓይነት ለመካፈል በግራቀኙ መካከል ስምምነት የላለ በመሆኑ ቤቱ በሐራጅ እንዱሸጥ ትዔዙዛ ተሰጥቶ አመልካች እና ተጠሪ በቀረቡት ተጫራቾች ጨረታው እንዱቀጥል በማለት በፊርማቸው አረጋግጠው ወ/ት ራሓል ሞገስ የተባለ ግለሰብ በብር 6,850,000 /ስድስት ሚልዬን ስምንት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር / ጨረታውን አሸንፈው ገንዖቡን ገቢ አድርገዋል።
አመልካች ለዘህ ችልት ባቀረቡት ክርክር ክፍፍለን በተመለከተ ወደ ላልች አማራጭ መሓድ የሚቻለው ፍርድ ያረፈበት ቤት መካፈል የማይችል ከሆነ ነው፤ ቤቱ መካፈል እየቻለ በሐራጅ ቢሸጥ መብቴን ይጎዲል በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም የክፍለከተማው የይዜታ አስተዲደር የሽግግር ጊዚ አገልግልት ፔሮጀክት ጽ/ቤት ካርታው ወጪ ያልሆነ ሰነድ ስለሆነ በሰነድ አልባ ዳስክ እንጂ በኛ በኩል ለማካፈል የማንችል መሆኑን እየገለጽን ነገርግን በመመሪያ ቁጥር 12/2006 መሰረት መካፈል የሚችል መሆኑን እንገልጻለን የሚል ምላሽ የሰጠ ከመሆኑ አኳያ፤ ይህንኑ ምላሽ መነሻ በማድረግ የአፈጻጸም ዲይሬክቶሬቱ ክፍለከተማው የይዜታ አስተዲደር የሽግግር ጊዚ አገልግልት ፔሮጀክት ጽ/ቤት የሰነድ አልባ ፔሮጀክት ዳስክ ቤቱን በዓይነት እንዱያካፍል በማለት ትዔዙዛ የሰጠ ከመሆኑ አኳያ፤ ትዔዙዘ የተላለፈለት የክፍለ ከተማው ሰነድ አልባ ዳስክም ቦታው ድረስ በመገኘት ለመካፈል በተደረገው ጥረት መሰረት ቤቱን በዓይነት ለማካፈል የተሰራበት ቁስ / ማቴርያል / ስለሚለያይ ለማካፈል የተቸገረ መሆኑን በመግለጽ ምላሽ የሰጠ ከመሆኑ አኳያ እና የአፈጻጸም ዲይሬክቶሬቱም በግራቀኙ መካከል ስምምነት እንደላለ በማረጋገጥ ቤቱ በሐራጅ እንዱሸጥ ትዔዙዛ የሰጠ እና አመልካች እና ተጠሪ በቀረቡት ተጫራቾች ሐራጁ እንዱቀጥል በፊርማቸው አረጋግጠው ቤቱ በብር 6,850,000 /ስድስት ሚልዬን ስምንት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር / የተሸጠ ከመሆኑ እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 445 በተገለጸው አግባብ የሐራጁ የሽያጭ ሥርዓት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ወይም በማጭበርበር ተፈጽሟል ለማለት የሚያስችል ሁኔታ ያልተገኘ ከመሆኑ አኳያ የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በሰጡት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት አላገኘንበትም። በዘሀም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ሐምል 24 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ እና ይህንን ትዔዙዛ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሕዲር 10 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
No topics extracted.