No summary available.
ሚያዘያ 29 ቀን 2011 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- አቶ ኃይለገብርኤል አየለ - ጠበቃ ትዔግስት ላዔከ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፀሐይ አየለ - ጠበቃ ወይንሸት መንግስቱ ቀረቡ።
መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዛልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኗ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ ባቀረቡት የመቃወሚያ አቤቱታ ነው። ተጠሪ በአመልካች ላይ በአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ጳጉሜ 01 ቀን 2009 ዓ/ም ባቀረቡት ማመልከቻ፡- አመልካች ከሟች አቶ አየለ ግዙው ያለመወለዲቸውንና ምንም አይነት የደም ግንኙነት የላላቸው መሆኑን ገልፀው አመልካች የሟቹ ወራሽ ነኝ በማለት በሐሰት ያገኙት ማስረጃ እንዱሰረዛላቸው ይወሰን ዖንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ አመልካች ለተጠሪ መቃወሚያ በሰጡት መልስም ጉዲዩን ለማየት ፍርድ ቤቱ ስልጣን እንደላለው እና ወራሽነታቸውን በ1997 ዓ/ም አረጋግጠው ከ2002 ዓ/ም ጀምሮ ከተጠሪ ጋር በፍርድ ቤት ክርክር ላይ የነበሩ ሁኖ እያለ መቃወሚያው መቅረቡ በይርጋ በታገደ ጉዲይ መሆኑን የሚያሳዩ ነጥቦችን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሱ ሲሆን በፍሬ ነገሩ ላይም ተገቢ ነው ያለትን ክርክር አቅርበዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ለአመልካች በመ/ቁጥር 1463/97 ሐምል 14 ቀን 1997 ዓ/ም የሰጠውን የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዛልኝ ጥያቄ የማስተናገድ ስልጣን እንዲለው ገልጾ በዘህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን መቃወሚያ ያለፈው ሲሆን ይርጋውን በሚመለከት ግን አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 (1) እና 1000 (2) ድንጋጌዎች መሆናቸውን ከለየ በኋላ በእነዘህ ድንጋጌዎች መሰረት ጥያቄው በጊዚ ገደቡ ውስጥ ያልቀረበ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የተጠሪን መቃወሚያ በይርጋ የታገደ ነው በማለት መዛገቡን ዖግቶታል። ከዘህም በኃላ የአሁኗ ተጠሪ ይግባኛቸውን ለከተማው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሙለ በሙለ አፅንቶታል። ተጠሪ የሰበር አቤቱታቸውን ለከተማው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ እንዱከራከሩ ከተደረገ በኋላ ችልቱ ጉዲዩን መርምሮ የአሁኗ ተጠሪ የሟች ንብረት ስለመያዙቸው ገልፀው በተከራከሩበትና የአሁኑ አመልካችም ይህንኑ የተጠሪ ክርክር ባላስተባበለበት ሁኔታ በአመልካች የተነሳው የይርጋ ክርክር በተጠሪ ላይ ሉታሰብባቸው አይገባም ወደሚለው ድምዲሜ ደርሶ ተጠሪ በአመልካች የወራሽነት ማስረጃ ላይ መቃወሚያ ለማቅረብ ይርጋ አያግዲቸውም በማለት ወስኖ ፍሬ ነገሩን የስር ፍርድ ቤት አጣርቶ እንዱወሰን ጉዲዩን መልሶለታል። የአሁኑ ሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡- ከተጠሪ ጋር በተለያየ እርከን በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ሲከራከሩ የቆዩና ተጠሪም በአመልካች የወራሽነት ማስረጃ ውሳኔ ላይ መቃወሚያ ሳያቀርቡ ለረዥም አመታት በቆዩበት ሁኔታና ተጠሪ የሟችን የውርስ ንብረት ስለመያዙቸው በማስረጃ ሳይረጋገጥ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ድንጋጌ ተጠቅሶ መቃወሚያው በይርጋ የሚታገድ አይደለም ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም በዘህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበውም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነውን ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልጋቸው አበይት ነጥቦች ተጠሪ ያቀረቡት የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዛልኝ ጥያቄ በይርጋ ሉታገድ ይችላል ወይስ አይችልም? ከተባለስ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የይርጋ ጊዚ ምን ይህል ነው? የሚለት ሁነው ተገኝተዋል።
ከክርክሩ መገንዖብ የተቻለው ለመቃወሚያው አቤቱታ መነሻ የሆነው የአሁኑ አመልካች የሟች አቶ አየለ ግዙው ወራሽ ነኝ በማለት በመ/ቁጥር 1463/97 በ14/11/1997 ዓ/ም ያገኙት የወራሽነት ማስረጃ ሲሆን ተጠሪ ይህ ማስረጃ ከሕግ ውጪ የተገኘ ነው በማለት ማስረጃው እንዱሰረዛላቸው የመቃወሚያ አቤቱታ ያቀረቡት ጳጉሜ 01 ቀን 2009 ዓ/ም መሆኑን፣ ከዘህ በፉት ደግሞ አመልካችና ተጠሪ ከ2002 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2007 ዓ/ም ድረስ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች በክርክር ላይ የነበሩ መሆኑን፣ አመልካች የሟች አቶ አየለ ግዙው ልጅ ነኝ የሚል አቋም ያላቸው ቢሆንም ተጠሪ ደግሞ ይህንኑ በመቃወም አመልካች የሟቹ ልጅ አይደለም በማለት የሚከራከሩ በመሆኑ ግራ ቀኙ የአቶ አየለ ግዙው ተወላጆች ናቸው በማለት ከወዱሁ መደምደም የማይቻል መሆኑን፣ የከተማው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የተጠሪ መቃወሚያ በይርጋ ሉታገድ የሚችል አይደለም ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው ተጠሪ የሟቹን ንብረት መያዙቸውን አመልካች አላስተባበለም በሚል አቢይ ምክንያትና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 (1) ደንጋጌን በዋቢነት በመጥቀስ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በተያዖው ጉዲይ ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈጻሚነት ያለው አንደ የሕግ ማዔቀፍ በአዋጅ ቁጥር 361/95 እና ይህንኑ አዋጅ ባሻሻለው አዋጅ ቁጥር 408/96 የተዖረጋው ስርዓት ሲሆን በአዋጁ አንቀፅ 41 ድንጋጌ አግባብ የወራሽነት ማስረጃ፣ የሞግዘትነት ምስክር ወረቀት ማስረጃ የመስጠት የስረ ነገር ስልጣን ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች የተሰጠ መሆኑን በግልጽ ያሳያለ። የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች በወራሽነት ምስክር ወረቀትና በሞግዘትነት ስልጣን ላይ የማስረጃ ወረቀት ውሳኔ መስጠት የሚችለ መሆኑ በሕጉ ተመልክቷል። ከዘህም በላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት የተቃውሞ አቤቱታ የሚቀርበው በፍትሒ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ በተሰጠው የውሳኔ ትርጉም (አንቀፅ 3 ይመልክቷል) መሰረት ሉፈፀም የሚችል ውሳኔ ከተሰጠ እና ውሳኔው የክርክሩ ተካፊይ ያልሆነ ወገን መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑ ሲረጋገጥና አቤቱታው ውሳኔው ከመፈፀሙ በፉት ከቀረበ ነው። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 አይነተኛ አላማ ማስረጃው ትክክለኛነቱና ሕጋዊነቱ ተረጋግጦ በማስረጃነቱ (Declaratory Judgement) በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ሳይሆን ከላይ እንደተገለፀው ሉፈፀም በሚችል ውሳኔ የክርክሩ ተካፊይ ያልሆነ ወገን መብትና ጥቅምን ማስከበር ነው።
ከላይ እንደተገለጸው አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 41/1//ሸ/ በአዋጅ ቁጥር 408/1996 አንቀፅ 2/1/ እንደተሻሻለው የወራሽነት የምስክር ወረቀት ለማግኘት በሚቀርብ አቤቱታ ላይ የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ስልጣን እንዲላቸው የተደገገ ሲሆን ተቃውሞ የቀረበበት ውሳኔ የተሰጠውም በሕጉ በተደለደለው የዲኝነት ስልጣን መሰረት ነው። በልላም በኩል የተቃውሞ አቤቱታው ያስከተለው የሕግ እና የፍሬ ነገር ክርክር ይዖት ሲታይ ከወራሽነት የምስክር ወረቀቱ የዖለለ እንድምታ የላለው መሆኑ ከተረጋገጠ ማስረጃውን የሰጠው ፍርድ ቤት የማስረጃው ይሰረዛልን ጥያቄ ማስተናገድ ያለበት መሆኑን በመግለጽ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በቀረበው ጉዲይ ላይ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2(1) ድንጋጌ መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። በዘህ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የስረ ነገር ስልጣን ጥያቄን ለመወሰን መርህ የሆነው የክሱን ምክንያት ይዖት መመልከት አስፈላጊ መሆኑንና በዘህም መሰረት ከይዖቱ ውጭ የሆኑ ላልች የማያመሳስለ ሁኔታዎች መኖር ጉዲዮች በተመሳሳይ የስረ ነገር ስልጣን ስር ያርፊለ የሚል መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ መሆኑ ከተረጋገጠ ማስረጃውን የሰጠው ፍርድ ቤት የማስረጃው ይሰረዛልኝ ጥያቄን ማስተናገድ የሚገባው መሆኑን፣ ሆኖም የማስረጃው ይሰረዛልኝ ጥያቄ ከማስረጃው መሰረዛ ባለፈ በላልች ህጋዊ መብቶች ውጤት ላይ ሁለ አንድምታ ያለው፣ ማስረጃውን ለሰጠው ፍርድ ቤት ያልተሰጠውን ጉዲይ የሚመለከትና ላልች ሕጎች የሚነካ የፍሬ ነገር እና የሕግ ክርክር የሚመለከት መሆኑ ከተረጋገጠ ግን ማስረጃውን የሰጠው ፍርድ ቤት ማስረጃው ይሰረዛልኝ በሚል መነሻ ስልጣኑ ስር የማያወድቀውን ጉዲይ ሉመለከተው የማይገባ መሆኑን ችልቱ መወሰኑን ከውሳኔው ይዖትና መንፈስ የምንረዲው ጉዲይ ነው። ስለሆነም የወራሽነት የምስክር ወረቀትን በተመለከተ የሚቀርብ የተቃውሞ አቤቱታ የማስረጃውን ትክክለኛነት እና ህጋዊነት ከማረጋገጥ ያለፈ አንድምታ የላለው መሆኑ ከተረጋገጠ ብቻ ማስረጃውን በሰጠው ፍርድ ቤት የሚስተናገድ ይሆናል። የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዛልኝ ጥያቄ ማስረጃውን በሰጠው ፍርድ ቤት የሚስተናገድ ነው ከተባለ እና መቃወሚያው የሚቀርበውም ከላይ በተገለጸው አግባብ ከሆነ ክርክሩ የሚመራው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 359 ስር በተደነገገው አግባብ በመደበኛው የክርክር አመራር ስርዓት ነው።ከዘህ አንጻር ሲታይ መደበኛ ክርክር ላይ በሕጉ አግባብ የተነሳ የይርጋ መቃወሚያ ሲኖር ፍርድ ቤቱ ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን ድንጋጌን በመለየት በመቃወሚያው ላይ ተገቢው ብይን መስጠት ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244 እና 245 ድንጋጌዎች ይዖትና መንፈስ ያስገነዛባለ።
የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 ድንጋጌ ተፈፃሚነት የሚኖረው አንድ እውነተኛ የሆነ ወራሽ ትክክለኛው ወራሽ መሆኑ ታውቆለት ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው የውርሱን ንብረት በእጁ ያደረገው ሰው የውርሱን ንብረት እንዱለቅ ክስ በሚያቀርብበት ጊዚ ስለመሆኑ የድንጋጌው ይዖት በግልጽ ያሳያል። ነገር ግን በተያዖው ጉዲይ የተጠሪ ክስ የሟች አቶ አየለ ግዙው የውርስ ንብረት በአሁኑ አመልካች ስለተያዖ ይለቀቅልኝ የሚል ይዖት የላለው ሲሆን በአመልካች ላይ የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ የቀረበው አመልካች ከሟች አቶ አየለ ግዙው ጋር ምንም ዓይነት የተወላጅነት ግንኙነት ሳይኖራቸው አመልካች የሟቹ ልጅ ነኝ በማለት የወሰደት የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዛልኝ የሚል መሆኑን የክርክሩ ሂደት በግልጽ ያሳያል። በመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 ድንጋጌ ለዘህ ጉዲይ ተፈፃሚ ላደረግ የሚችልበት የሕግ አግባብ የለውም።
ተጠሪ በዘህ መልኩ ያቀረቡት አቤቱታ በምን ያሕል ጊዚ መቅረብ እንዲለበት በውርስ ሕጉ ድንጋጌዎች በግልጽ አልተመለከተም። የውርስ ሕጉ በዘህ ረገድ ክፍተት ካለበት ወደ ጠቅላላ ሕግ በመሄድ ለጉዲዩ እልባት መስጠት በሕግ አተረጓጎም መርህ /principles of legal interpretation/ የተፈቀደ ነው። በዘሁ መሰረትም ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሕጉ ጠቅላላ ስለውልች ከተደነገገው አንፃር መመልከት የግድ ይላል። በዘህ ክፍልም ግዳታዎች ከውል የተገኙ ባይሆንም በውል ሕግ ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት እንዲላቸው በቁጥር 1677/1/ ላይ ተመልክቷል። በውል ሕግ ደግሞ ዋናው የይርጋ ድንጋጌ በቁጥር 1845 ላይ የተመለከተው የ1ዐ ዓመት የይርጋ ጊዚ ነው። የይርጋ አቆጣጣር ጊዚ መነሻ ላሆን የሚችለው ጊዚም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1846 ድንጋጌ አግባብ ላታይ የሚችል ነው።
በተያዖው ጉዲይ ተጠሪ አመልካች ከሕግ ውጪ የወራሽነት ማስረጃ አግኝተዋል በማለት ማስረጃውን ለሰጠው ፍርድ ቤት ለአመልካች የሰጠውን የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰረዛ የመቃወሚያ አቤቱታ ያቀረቡት ጳጉሜ 01 ቀን 2009 ዓ.ም. ሲሆን አመልካች ይህንን ማስረጃ ያገኙ መሆኑን ያወቁት ደግሞ ከ2002 ዓ/ም ጀምሮ መሆኑን የክርክሩ ሂደት በግልፅ ያሳያል። አመልካች ያያዘት የወራሽነት ማስረጃ በፍርድ ቤት የተረጋገጠ በመሆኑ ሕጋዊ ውጤት የሚኖረው እንደመሆኑ መጠን ተጠሪ ይህ ማስረጃ ከሕግ ውጪ ለአመልካች መሰጠቱን ከአወቁበት ጊዚ ጀምሮ በ1ዐ ዓመት ጊዚ ውስጥ ተጠሪ አቤቱታውን የማቅረብ ግዳታ አለባቸው። ከዘህ አንጻር ሲታይ ተጠሪ ከ2002 ዓ/ም ጀምሮ ጉዲዩን የሚያውቁ በመሆኑ ከዘህ ጊዚ ጀምሮ በአስር አመት ጊዚ ውስጥ መቃወሚያውን ማቅረብ የሚችለ በመሆኑና የአስር አመት ጊዚ ሳያልፍ በ2009 ዓ/ም መቃወሚያቸውን ያቀረቡ በመሆኑ ክሱ በይርጋ የሚታገድበት አግባብ የለም።
ስለሆነም የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1ዐዐዐ ድንጋጌ ለውሳኔው ዋቢ ማድረጉ ተገቢ ባሆንም ክሱ በይርጋ የታገደ አይደለም በማለት የደረሰው ድምዲሜ ግን ከውጤት አንጻር የሚነቀፍ ባለመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት አልተቻለም።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሰኔ 05 ቀን 2010 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ከውጤት አንጻር በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
በሐሰት ለተገኘ የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዛልኝ ጥያቄ ተፈጻሚነት ያለው የይርጋ ጊዚ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1677 እና 1845 ድንጋጌዎች መሰረት የአስር አመት የይርጋ ጊዚ ነው ብለናል።
ተጠሪ ያቀረቡት የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዛልኝ መቃወሚያ በይርጋ ቀሪ አልሆነም ተብል ተወስኗል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መ/ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.