አንድ የግልግል ጉባኤ ከቤቶች የባለሀብትነት መብት ጋር የተያያዖ የመፊለም ክርክርን ተቀብል ዉሳኔ ለመስጠት የዲኝነት ስልጣን የላለው ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37 እና 78፤የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1731 ፣3325 ፣3329
No summary available.
ታህሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ዲኜ መላኩ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- ወ/ሮ ዲንሴ ጉርሙ - ጠበቃ አቶ ዲኛቸው ቱለ ቀርበዋል።
ተጠሪ፡- አቶ ተመስገን ደምሴ - ጠበቃ አቶ ብርሃኑ ታዬ ጋር ቀርበዋል።
ይህ መዛገብ የተቀጠረዉ ለምርመራ ሲሆን ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ለችልቱ ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.132562 ጥር 25 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዲዩ መነሻ ሲታይ በግልግል ጉባኤ ዳኞች ዖንድ የአሁን አመልካች የመቃወም አመልካች፣የአሁን ተጠሪ ደግሞ የመወቃወም ተጠሪ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ይህ ችልት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የመ.ቁ.110552 አስቀርቦ እንደተመለከተዉ፤ ይህ ጉዲይ የተጀመረዉ የአሁን ተጠሪ በሥር ተከሳሽ ዶ/ር አብነት ግርማይ ላይ ባቀረቡት ክስ መነሻነት ሲሆን፣ የክሱም ይዖት በአጭሩ፡በከሳሽ እና ተከሳሽ መካከል ሰኔ 23 ቀን 1997 ዓ.ም / June 30/2005 GC/ በተደረገዉ የኪራይ ዉል ተከሳሽ በአዱስ አበባ ከተማ በቦላ ክ/ከተማ በቀድሞ ወረዲ 17 ቀበላ 15 /በአሁኑ በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 4 አስተዲደር/ ክልል ዉስጥ የሚገኘዉን የቤት ቁጥር 414 የሆነዉን ሕንጻ ተከራይተዉ ሲጠቀሙበት ቆይተዉ የኪራይ ዉለ የተቋረጠ በመሆኑ ለቤቱ እድሳት ከሳሽ ያወጣዉን ወጪ እንዱከፍለኝ፣ ያልተከፈለዉን ዉዛፍ የኪራይ ክፍያ እንዱከፍለኝ፣ የመማር ማስተማሩ ሂደት በቤት ጥበት ምክንያት ተጎዲብኝ በማለቱ 5 ክፍል በከሳሽ ተሰርቶ ሲገለገልበት ከቆዩ በኋላ ነባሩን በር በብልኬት ዖግቶና አጥሩን አፍርሶ ላላ መዉጫ በር በመስራት የሚገለገልበት ያላስረከበዉን 5 ክፍል ቤት እንዱያስረክብ፣ በእነዘህ ክፍልች ላይ የኪራይ ክፍያ በገበያ ዋጋ እንዱከፍለኝ በማለት ከሷል። ተከሳሽ በበኩለ ባቀረበዉ መልስ አምስት ክፍል ቤቶችን በተመለከተ ከሳሽ የባለሀብትነት ማረጋገጫ ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ መብትና ጥቅም የለዉም፣ ተከሳሽ ቤቱን የሚመለከተዉ አካል በማስፈቀድ የሰራ ነዉ በማለት እና በላልች ነጥቦች ላይ መከላከያ ክርክራቸዉን አቅርቧል።
ከዘህ በኋላ የግልግል ጉባኤዉ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የሕንጻ ኪራይ ዉለን መሰረት በማድረግ የዉዛፍ ኪራይ ክፍያ፣ ለሕንጻዉ እድሳት እንዱሁም ወጪና ኪሳራ በተመለከተ ሉከፈል ይገባል ያለዉን ገንዖብ በመወሰን፣ ተከሳሽ በኪራይ ዉለ መሰረት ከተከራየዉ ዋናዉ ቤት ይዜታ ዉጭ ባለዉ ቦታ የተሰሩትን 5 ክፍልች በከሳሽ የተሰሩ መሆናቸዉን የሰዉ ምስክሮች ያረጋገጡ ስለሆነ ተከሰሽ በዉል የያዙቸዉንና በርክክብ ወቅት ያላስረከባቸዉን አምስት ክፍል ቤቶችን ከነአጥር ግቢዉ ለከሳሽ እንዱያስረክብ እና በላልች ጉዲዮች ላይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ሰጥቷል።
ከዘህ ዉሳኔ በኋላ የመቃወም አመልካች ወ/ሮ ዲንሴ ጉርሙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ አቅርቧል። የመቃወሚያ አቤቱታቸዉ ይዖት በአጭሩ፡ በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 4 ክልል ዉስጥ የሚገኝ በ950 ካ.ሜ ቦታ ስፊት ላይ ያረፈዉ ቤት በእነ ወ/ሮ አየለች ወርቁ ስም ተመዛግቦ ካርታ የተሰጠበትን የመቃወም አመልካች በሽያጭ ዉል ገዛተዉ የተላለፈላቸዉ እና የሉዛ ዉል ከቦላ ክ/ከተማ መሬት አስተዲደር ጽ/ቤት የፈጸሙበትን፣ እንዱሁም የቤቱን ስመ ሀብት ወደ አመልካች ለማዙወር በሂደት ላይ እያለሁ፣ ይህ ቤት እንደፍርድ ባለዔዲ ንብረት ተቆጥሮ የአፈጻጸም ትዔዙዜች የተሰጠበት ስለሆነ እነዘህ አምስት ክፍል ቤቶች የመቃወም አመልካች ንብረት ስለሆኑ የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዱሻርልኝ በማለት አመልክቷል።
በዘህ የመቃወሚያ ማመልከቻ ላይ ከሳሽ አቶ ተመስገን ደምሴ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና አማራጭ መልስ ያቀረቡ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወምያ በአጭሩ፡ የመቃወም አመልካች ወደ ክርክሩ ለመግባት መብትና ጥቅም የላቸዉም፣ ይህ ጉዲይ የግልግል ጉባኤ የሰጠዉ ዉሳኔ በይግባኝ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.110552 በ10/3/2008 ዓ.ም በሰጠዉ ፍርድ ጸንቷል፤ አመልካች በአፈጻጸም ላይ ጣልቃ ገብተዉ መብታቸዉን ማስከበር ነበረባቸዉ፣ የመቃወም አመልካች የዘህ ንብረት ባለሀብት ስለመሆናቸዉ ካርታ አላቀረቡም፣ አመልካች በዉል ገዛቻለሁ ያለት ቤት የቤት ቁጥር የለዉም፤ የመቃወም አመልካች አቤቱታ ዉሳኔ ከተሰጠበት ጉዲይ ጋር የሚገናኝ አይደለም ጉባኤዉ የመቃወም አቤቱታዉን አይቶ የመወሰን ስልጣን የለዉም፣ እንዱሁም በአማራጭ መልስ እንዲቀረቡ ተመልክቷል። ተከሳሽ ዶ/ር አብነት ግርማይ በወረዲዉ አስተዲደር በኩል መጥሪያና አቤቱታዉ በድርጅቱ ቤት ላይ ቢለጠፍም ባለመቅረባቸዉ ሳይከራከሩ ቀርተዋል።
በመቀጠል የግልግል ጉባኤዉ፣ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር፣ የቀረበዉን የሰነድ ማስረጃ በመመዖን፣ አስቀድመዉ የተሰሙትን የሰዉ ምስክሮች ቃል በመመርመር፣ በሰጠዉ ብይን ከሳሽ እነዘህን ቤቶች መስራታቸዉን በምስክሮች ቃል ያስረደ ሲሆን የመቃወም አመልካች ይህን የሚያስተባብል ማስረጃ ያላቀረቡ በመሆኑ የመቃወም አመልካች ክስ ባቀረቡት አምስት ክፍል ቤቶች ላይ በዉል ወይም በሕግ የተረጋገጠ መብትና ጥቅም የላቸዉም በማለት ከሳሽ ያቀረበዉን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በመቀበል አቤቱታቸዉን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.33 /2/ /3/ እና 244/2፣ መ/ መሰረት ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። የሥር የመቃወም አመልካች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ ምክንያቱን በማስቀመጥ የግልግል ጉባኤዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታዉ የቀረበዉ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ29/5/2009 ዓ.ም የተጻፈ አራት ገጽ አቤቱታ አቅርቧል። የአቤቱታዉ ይዖት በአጭሩ፡ ለክርክር ምክንያት የሆኑት በ950 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈት 5 ክፍል ቤቶች በእነ ወ/ሮ አየለች ወርቁ ስም የተመዖገበ እና በሽያጭ ለአመልካች የተላለፈ እንዱሁም አመልካች ከቦላ ክ/ከተማ መሬት አስተዲደር ጋር የሉዛ ዉል ፈጽመዋል። አመልካች ይህን ንብረት በእጃቸዉ አድርገዉ የሚቆጣጠሩ እና የሚያስተዲደሩ ሆኖ ሳለ የግልግል ጉባኤዉ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ንብረቱ የአሁን ተጠሪ ነዉ በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ እንዱታረምልን፣ የጠበቃ አበል ከወጪ ጋር እንዱወሰንልን በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት በዘህ ጉዲይ የሚጣራ ነጥብ አለ በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡ ባዖዖዉ መሰረት መጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም የተጻፈ አራት ገጽ መልስ አቅርቧል።
የመልሱም ይዖት በአጭሩ፡ በዘህ ጉዲይ የግልግል ጉባኤዉ የሰጠዉ ብይን እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠዉ ፍርድ ጉዲዩን በሕግ አግባብ አጣርተዉ የሰጡት ዉሳኔ እና የህግ ስህተት የላለባቸዉ ስለሆኑ አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ዉድቅ ተደርጎ የሥር ዉሳኔ እንዱጸናልኝ በማለት በዛርዛር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታቸዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም ‹‹የግልግል ጉባኤዉ ይህን ጉዲይ ተቀብል ግራ ቀኛቸዉን አከራክሮ የመወሰን ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም?›› የሚለዉን ነጥብ እንደጭብጥ በመያዛ እንደሚከተለዉ መርመሮታል። ይህ ችልት የሰበር አጣሪ ችልት በጉዲዩ ፍሬ ነገር ከያዖዉ ጭብጥ አስቀድሞ የስልጣን ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ያለበት ጉዲይ ሆኖ በመገኘቱ የስልጣን ጥያቄን እንደጭብጥ ለመያዛ ችሎል። ተከራካሪ ወገኖች ባያነሱትም የዲኝነት ጥያቄን የሚያይ ፍ/ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ጉዲዩን ለማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለዉ መሆኑን በራሱ አነሳሽነትም ቢሆን ማረጋገጥ እንደሚገባዉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.9 /2/ ሥር ተመልክቷል። ተከራካሪ ወገኖች ባያነሱትም ፍ/ቤት የስልጣን ጥያቄ በማንሳት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የላለዉ እንደሆነ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.244 /2፣ ሀ/ እና 245 /2/ መሰረት ክሱ ተቀባይነት የለዉም ብል መወሰን እንደሚገባዉ ተደንግጓል። ይህ ደግሞ ለግልግል ጉባኤዉም የሚሰራ በመሆኑ የስልጣን ጉዲይ ምላሽ የሚያስፈልገዉ ጉዲይ ነዉ።
በዘህ አግባብ እንደመረመርነዉ የግልግል ጉባኤዉ በከሳሽ አቶ ተመስገን ደምሴ እና በተከሳሽ ዶ/ር አብነት ግርማይ መካከል ያለዉን ክርክር ተቀብል ለመወሰን ስልጣን ያገኘዉ ሁለቱ ግለሰቦች ሰኔ 23 ቀን 1997 ዓ.ም / June 30/2005 GC/ ባደረጉት የሕንጻ ኪራይ ዉል መነሻነት መሆኑን ከሥር ዉሳኔዎች ግልባጭ መገንዖብ ይቻላል። የዘህ ዉል አንቀጽ 11 በአከራዩ እና ተከራዩ መካከል ከዉለ ጋር ተያይዜ የሚነሱትን ግጭቶች በስምምነት ለመፍታት፣ ይህ ካልተቻለ ጉዲዩ ግራ ቀኛቸዉ በሚመርጡት ገላጋይ ሽማግላዎች ታይቶ ዉሳኔ እንደሚሰጥበት መስማመታቸዉን ያመለክታል።
የሕንጻ ኪራይ ዉለ የተፈጻሚነት አድማስ ደግሞ በዉለ አንቀጽ 1 የተመለከተ እና የቤት ቁጥር 414 ሕንጻ ከነግቢ እና በጊዚያዊነት የተሰሩትን ተገጣጣሚ ግንባታዎችን እንደሚመለከት እና ይህን የሚያመክት አባሪም የዉለ አካል እንደሆነ ያሳያል። በዘህ ዉል የአከራይ እና የተከራይ መብትና ግዳታ በዛርዛር ተመልክቷል። በመሆኑም የግልግል ጉባኤዉ በዘህ ጉዲይ ስልጣን ሉኖረዉ የሚችለዉ በዉለ የተፈጻሚነት ወሰን ድረስ እንደሆነ የሚያከራክር አይደለም።
እንደሚታወቁ ተዋዋይ ወገኖች የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1678 ሥር የተመለከቱትን ሁኔታዎችን በማሟላት ዉል የተደረጉ እንደሆነ፣ በሕግ የተቋቋመዉ ዉል ዉለን ባቋቋሙት ተዋዋይ ወገኖች መካከል ሕግ እንደሆነ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1731 /1/ ሥር ተደንግጎ እናገኛለን። አንድ ዉል አስገዲጅነት የሚኖራዉ ዉለን ፈቅደዉና ተስማምተዉ በተዋዋለ ተዋዋይ ወገኖች ላይ እንጂ የዉለ አካል ባልሆኑት ሶስተኛ ወገኖች ላይ አስገዲጅነትም ሆነ ተፈጻሚነት እንደላለዉ መገንዖብ ያስፈልጋል።
ይህ ከሆነ ደግሞ የአሁን ተጠሪ እና የሥር ተከሳሽ ዶ/ር አብነት ግርማይ መካከል የተደረገዉ የኪራይ ዉል ተፈጻሚነት ዉለን ባደረጉት ተዋዋይ ወገኖች ብቻ ላይ ነዉ፤ በዘህ ዉል መነሻነት የሚነሳዉም አለመግባባት በግልግል ጉባኤዉ ታይቶ ዉሳኔ ላሰጥ የሚችለዉ በእነዘህ ሰዎች መካከል ብቻ ነዉ። በዘህ የኪራይ ዉል መሰረት የኪራይ ክፍያ፣ የቤቱ እድሳትና የጥገና ጉዲይ፣ ተከራይ በዉለ በግልጽ ተገልጾ የተረከበዉን ሕንጻ፣ ክፍልች እና ዔቃዎች ከማስረከብ ጋር የተያያዘትን ጉዲዮች የሚያጠቃልል እንደሆነ ማየት ይቻላል። እነዘህን ጉዲዮች በተመለከተ በአከራይ እና ተከራይ መካከል አለመግባባት የተነሳ እንደሆነ በዘህ ዉል አግባብ ሉፈታ እንደሚገባ ግልጽ ነዉ። እነዘህ ተዋዋይ ወገኖች በኪራይ ዉል ምክንያት በመካከላቸዉ የሚነሳዉን አለመግባበት በገላጋይ ሽማግላዎች እንዱታይላቸዉ መስማማታቸዉ ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3325 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት ተቀባይነት ያለዉ ጉዲይ ነዉ። በመሆኑም ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸዉ የሚነሳዉን አለመግባባት በሽምግልና ዲኝነት ለመጨረስ መስማማታቸዉ የሕጉን ዓላማ የተከተለ እንደሆነ የሚያከራክር አይደለም። ይሁን እንጂ የሽምግልና ዲኝነት ስልጣን በጠባቡ መተርጎም እንዲለበት የፍ/ብ/ሕ/ቁ.3329 ሥር ተደንግጎ እናገኛለን። ከእነዘህ የሕግ ድንጋጌዎች መገንዖብ እንደሚቻለዉ ተዋዋይ ወገኖች በምን አግባብ የገላጋይ ዳኞችን መምረጥ እንደሚችለም በዛርዛር ተመልክቷል። ስለሆነም በዘህ አግባብ የተቋቋመዉ የግልግል ጉባኤ ስልጣን ሉኖረዉ የሚችለዉ በዘህ አግባብ ተስማምተዉ ገላጋይ ዳኞችን መርጠዉ ስልጣን በሰጡት ወገኖች ብቻ ላይ እና በዘህ አግባብ እንዱታይላቸዉ በተስማሙበት ጉዲይ ወሰን ድረስ ብቻ እንደሆነ መገንዖብ ያስፈልጋል።
ከዘህ አንጻር አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች ባቀረቡት መቃወሚያ በከሳሽ እና በተከሳሽ በተደረገዉ ክርክር መነሻነት የተሰጠዉ ዉሳኔ መብቴን ይነካል፣ እነዘህ ለክርክር ምክንያት የሆኑት አምስት ክፍል ቤቶች የፍርድ ባለዔዲ የዶ/ር አብነት ግርማይ ንብረት ሳይሆኑ አመልካች በሽያጭ ዉል ከላልች ግለሰቦች ገዛተዉ የተላለፈላቸዉ እና የሉዛ ዉል የፈጸሙበት የግል ሀብታቸዉ እንደሆነ በመግለጽ ነዉ። የአሁን ተጠሪ በበኩላቸዉ ባቀረበዉ ክርክር እነዘህ ቤቶች የራሱ ንብረት መሆናቸዉንና ባለሀብት ተጠሪ እንደሆኑ ምስክሮች አረጋገጠዋል፣ አመልካች መብት እንደላላቸዉ በመግለጽ ነዉ። ከዘህ ክርክር መገንዖብ እንደሚቻለዉ ግራ ቀኛቸዉ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1204- 1206 ባለት ድንጋጌዎች አግባብ የባለሀብትነት መብት በተመለከተ የመፊለም ክርክር ማቅረባቸዉን የሚያመለክት እንደሆነ ነዉ። እንዱሁም ከጅምሩም በከሳሽ እና በተከሳሽ መካከል እነዘህን አምስት ክፍል ቤቶች በተመለከተ ሲካሄድ የነበረዉ የመፊለም ክርክር እንደነበር የቀደመዉ የግራ ቀኛቸዉ ክርክር፣ መቃወሚያ ያቀረበበት የግልግል ጉባኤዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ዉሳኔ የሚያስገነዛብ ጉዲይ ነዉ። ከፍ ሲል እንደተጠቀሰዉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በተደረገዉ ክርክር የግልግል ጉባኤዉም ሆነ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ዉሳኔ እንደሰጡ ቢገለጽም የዉሳኔያቸዉ ይዖት ሲታይ ግን ለክርክር ምክንያት የሆኑት አምስት ክፍል ቤቶች ማን እንደሰራቸዉ፣ ቤቶች የማን ንብረት እንደሆኑ የቀረቡትን የሰነድ ማስረጃዎች በመመዖን እንዱሁም አስቀድሞ የተሰሙትን የተጠሪን የሰዉ ምስክሮች በመመርመር የባለሀብትነት መብት ላይ ዉሳኔ እንደሰጡ የዉሳኔዎቹ ግልባጭ ያመለክታል።
ይህ ከሆነ ደግሞ ምላሽ የማግኘት ያለበት ጉዲይ የግልግል ጉባኤዉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተነሳዉን የአምስት ክፍል ቤቶችን የባለሀብትነት መብት ጋር የተያያዖ የመፊለም ክርክር ተቀብል ግራ ቀኛቸዉን አከራክሮ ዉሳኔ ለመስጠት የዉልም ሆነ የሕግ ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም?
የሚለዉ ነጥብ ነዉ። ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክስ ለክርክር ምክንያት የሆኑት አምስት ክፍል ቤቶችን በተመለከተ በኪራይ ዉለ እንደተሸፈኑ ሳይሆን የሥር ተከሳሽ እነዘህን ቤቶች አጥር ሰርተዉ ላላ በር ከፍተዉ በሕገ ወጥ መንገድ ሲገለገለበት እንደነበር እና የኪራይ ዋጋም ቢሆን በኪራይ ዉለ ላይ የተመለከተዉ ሳይሆን በገበያ ዋጋ በወር በብር 25 ሺህ ብር ታስቦ እንዱከፈላቸዉ መጠየቃቸዉን ያሳያል። የዘህ የዲኝነት ጥያቄ እንደሚያመለክተዉ እነዘህ ቤቶች በኪራይ ዉለ የተካተቱ ነበር ወይ? የሚለዉን ጥያቄ የሚያነሳ ነዉ። ከዘህም በላይ እነዘህን ቤቶች በተመለከተ በከሳሽ እና ተከሳሽ መካከል የመፊለም ክርክር መነሳቱን የዉሳኔዉ ግልባጭ ያመለክታል። ይህ በእንዱህ እንዲለ በአሁን ተጠሪ እና በሥር ተከሳሽ ዶ/ር አብነት ግርማይ መካከል የተደረገዉ የሕንጻ ኪራይ ዉል ተፈጻሚነት ያለዉ በእነዘሁ ተዋዋይ ወገኖች ላይ እንጂ የአሁን አመልካች ላይ እንዲልሆነ ግልጽ ነዉ።
ይህ ዉል የሚፈጥረዉ መብትና ግዳታ አመልካችን የማይመለከት እና ዉለን መነሻ ያደረገ አለመግባባት ቢከሰትም በገላጋይ ዳኞች እንዱፈታ ለማድረግ የሚገደደበት አግባብ አይኖርም። እንዱሁም የአሁን አመልካች እነዘህን የግልግል ዳኞች መርጠዉ ጉዲያቸዉ እንዱታይላቸዉ ስልጣን የሰጡት ነገር ባለመኖሩ የግልግል ጉባኤዉ የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ለመዲኘት የህግ ስልጣን የለዉም። ይህ ሲባል ግን የግልግል ጉባኤዉ የአመልካችን መቃወሚያ ከጅምሩ ስልጣን የለኝ በሚል ምክንያት ዉድቅ እንዱያደርግ ሳይሆን አመልካች ያቀረቡትን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ መሰረት በማድረግ አስቀድሞ እነዘህ አምስት ክፍል ቤቶችን በተመለከተ የባለሀብትነት መብት ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.360 /2/ መሰረት ተገቢዉን በመወሰን ነዉ። ይህ ማለት የግልግል ጉባኤዉ በኪራይ ዉል የተመለከቱትን ቤቶች የባለሀብትነትን መብት በተመለከተ የመፊለም ክርክርን ሰምቶ ዉሳኔ ለመስጠት ስልጣን እንደላለዉ በመገንዖብ በእነዘህ አምስት ክፍል ቤቶች ላይ አስቀድሞ የሰጠዉን ዉሳኔ ማንሳት ይገባዉ ነበር።
የአሁን አመልካች በበኩላቸዉ የራሴ ንብረት ናቸዉ የሚሎቸዉን እነዘህን ቤቶች በተመለከተ በገላጋይ ዳኞች እንዱታይላቸዉ የተስማሙት ነገር የለም፣ የመረጡትም የገላጋይ ዲኛ አለመኖሩን የሥር ዉሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። ይህ ከሆነ ደግሞ የአሁን አመልካች በኢ.ፋ.ዱ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37 እና 78 መሰረት ነጻና ገለልተኛ በሆነ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲያቸዉ ታይቶ ዉሳኔ እንዱሰጥበት ሕገ መንግስታዊ መብት አላቸዉ። ምክንያቱም በዘህ ጉዲይ ዉሳኔ የሰጠዉ የግልግል ጉባአዉ ለአመልካች ነጻና ገለልተኛ የዲኝነት አካል ነዉ ለማለት ስለማይቻል ነዉ። አመልካች በሕገ መንግስቱ የተጠበቀላቸዉ በሕግ በተቋቋመ ነጻና ገለልተኛ የዲኝነት አካል በሆነዉ የመደበኛ ፍ/ቤት የመዲኘት መብት የሚነፈጉበት አግባብ የለም።
በመሆኑም የግልግል ጉባኤዉ ለክርክር ምክንያት የሆኑትን አምስት ቤቶችን በተመለከተ የባለሀብትነትን የመፊለም ክርክር ሰምተዉ መወሰን ስልጣን እንደላለዉ በመገንዖብ አስቀድሞ በእነዘህ ቤቶች ላይ የሰጠዉን የዉሳኔ ክፍል በመሻር ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ጉዲይ ከፈለጉ ክርክራቸዉን ስልጣን ላለዉ ፍ/ቤት ማቅረብ እንደሚችለ በመጠቆም መወሰን ሲገባዉ፣ ባልተሰጠዉ ስልጣን እነዘህን አምስት ቤቶች በተመለከተ ማስረጃ በመመዖን ተጠሪ ባለሀብት ናቸዉ በማለት ዉሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሲሆን የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም በበኩለ ከስልጣን አንጻር ጉዲዩን በመመርመር የግልግል ጉባኤዉን ብይን ማረም ሲገባዉ ከዘህ ይልቅ የራሱን ዛርዛር ምክንያቶችን በማከል የሥር ብይን በማጽናት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ።
ሲጠቃለል የግልግል ጉባኤዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት የባለሀብትነት የመፊለም ዲኝነት ጥያቄን ተቀብል ግራ ቀኛቸዉን አከራክሮ የመወሰን ስልጣን ሳይኖረዉ ለክርክር ምክንያት የሆኑት አምስት ክፍል ቤቶች የአሁን ተጠሪ ንብረት ናቸዉ፣ አመልካች ግን መብትና ጥቅም የላቸዉም በማለት የሰጡት ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህን ዉሳኔ በማጽናት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የግልግል ጉባኤዉ እነዘህን አምስት ክፍል ቤቶች በተመለከተ ጥር 25 ቀን 2007 የሰጠዉ የዉሳኔ ክፍል እና መስከረም 4 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠዉ ብይን እና ይህን ብይን በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.132562 ጥር 25 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
የግልግል ጉባኤዉ ለክርክር ምክንያት የሆኑትን አምስት ክፍል ቤቶችን በተመለከተ የባለሀብትነት የመፊለም ክርክር ሰምቶ ለመወሰን ስልጣን የለዉም ብለናል።
የአሁን ተጠሪም ሆነ የአሁን አመልካች አሁን ለክርክር ምክንያት የሆኑትን እነዘህን አምስት ክፍል ቤቶች በተመለከተ ስልጣን ባለዉ ፍ/ቤት ክስ አቅርበዉ መብታቸዉን ከመጠየቅ ይህ ዉሳኔ የሚያግዲቸዉ አይሆንም ብለናል።
የግልግል ጉባአዉ ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት አምስት ክፍል ቤቶች ዉጭ በላልች ጉዲዮች ላይ የሰጠዉ የዉሳኔ ክፍል ጸንቷል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለግልግል ጉባኤዉ እና ለሥር ፍ/ቤት ይድረስ ብለናል።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
በ30/5/2009 ዓ.ም የተሰጠዉ የእግድ ትዔዙዛ በዘህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.