ከሳሽ ወገን ክስ በሚሰማበት ወቅት ያላቀረበው ማስረጃ መኖሩን በበቂ ምክንያት በማስደገፍ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ባገኘበት ሁኔታ ተከሳሽ የመከላከያ መልሱን እንዱያሻሽል የሚያቀርበውን ጥያቄ ውድቅ የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት እና በተሟላ መልስ ባልተከራከረበት ሁኔታ ተከሳሽ ከሳሽ ባቀረበው ሰነድ ላይ አስተያየቱን በጽሁፍ ብቻ ያቅርብ ብል የመደመጥ መብቱ ሉታለፍ የማይገባው ስለመሆኑ የፋዳራል ህገ መንግስት አንቀጽ 37 ፤ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ91፤137(1) ፣223፣256 ቢጋና ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
No summary available.
ቀን 30/09/2011 ዳኞች፡ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች፡ የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት-ነ/ፈጅ አሸናፉ ፉጣ ተጠሪ፡ ቢጋና ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር- አልቀረቡም ።
መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዘህ መዛገብ የተያዖው ጉዲይ የኮንስትራክሽን መስሪያዎች ኪራይ ውል የተመለከተ ሲሆን የጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ በኮ/መ/ቁ138392 ባቀረበው ክስ መነሻ ነው። የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እና ትእዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ጉዲይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ይዖት ባጭሩ፡- ከአመልካች ጋር ሰኔ እና ሐምል 2002 ዓ.ም በተደረገው ውል ዱኤስቢ3-ዱዚድ 0279 ባለ 305 የፈረስ ጉልበት ዱ 8ቢ0342ባለ 305የፈረስ ጉልበት በሰዓት ብር 1437.50 ለመክፈል በመስማማት የተከራየ ቢሆንም ክፍያው አጠቃልል ባለመክፈለ ብር 875,158.63 የ3 ዓመት ወለድ ታስቦ ብር 1,111,451.46 እንዱሁም ክስ ከተመሰረተበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ወለድ እንዱከፈለው እንዱወሰን ዲኝነት ጠይቋል።
አመልካች ባቀረበው መልስ፡- ክፍያ ለመጠየቅ የተጠሪ ተወካይ እና የአመልካች ኦፔሬተር የፈረሙት ሰነድ መቅረብ እንደሚገባ አዱስ አበባ ለተሰሩ ስራዎች ተገቢ ክፍያ መፈፀሙ አመልካች የሚያውቀው ላላ ክፍያ የላለ መሆኑን፣ ተጠሪ ክሱን ለማስረዲት ያዖጋጀው የጊዚ መቆጣጠሪያ ማጠቃልያ ራሱ ያዖጋጀው በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ2016 መሰረት ተቀባይነት እንደላለው፣ ከውለ በስተቀር ላላ ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ ውለ ስራ መሰራቱን አያሳይም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆን አመልክቷል።
በዘሁ መልኩ ክርክሩ የቀረበለትን ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ እንዱሁም በፍርድ ቤት ትእዙዛ የቀረበው ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች ለተጠሪ ያልከፈለው ገንዖብ መኖሩ ባቀረበው ማስረጃ አስረድቷል።ክሱ በተሰማበት ቀን ከሳሽ አለኝ የሚለውን የሰዓት መቆጣጠሪያ ቅጾች ከመግለጫ ጋር እንዱያቀርብ በ03/8/2006 ዓ.ም ታዜ ግንቦት 30 ቀን 2008 ዓ.ም አቅርቧል።አመልካች የቀረበው ማስረጃ በዋና መስሪያ ቤት የላለ በመሆኑ በሀሰት የተዖጋጀ ላሆን ስለሚችል እንዱመረመር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በፍረሲክ ተመርምሮ ውጤቱ የቀረበ ሲሆን በሰነደ ያለው ፊርማ ከአንድ በስተቀር በአመልካች ሰራተኞች መፈረሙን ተረጋግጧል።
አመልካች ማስረጃው በመጀመርያ ክርክር አልቀረበም የሚል መቃወሚያ ያቀረበ ቢሆንም በፍርድ ቤት ትእዙዛ የቀረበ በመሆኑ ክርክሩ ተገቢነት የለውም። አመልካች ያልከፈለው ዋና ገንዖብ ወለድ በድምር ብር 1,105,507.12 እንዱከፍል የነዲጅ በተመለከተ እንዱከፈለው ክሱ በሚሰማበት ጊዚ አልጠየቀም። በህጉ አግባብ የመከላከያ መልስ ለማሻሻል ጥያቄ ከሚቀርብ በስተቀር አዱስ ክርክር ማቅረብ አይቻልም በማለት ፍርድ ሰጥቷል። አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ቅሬታ ተቀባይነት ያላገኘ በመሆኑ ውሳኔው እና ትእዙዘ በመቃወም ለማሳረም ይህ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
ችልቱም ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ እንዱመች የከፍተኛ ፍርድ ቤት መ/ በ14/09/2011 ዓ.ም በሰጠው ትእዙዛ በማስቀረብ ተመልክቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተገለፀው ይዖት ያለው ሲሆን እኛም ግራ ቀኙ በጽሁፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔና ትእዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆን አለመሆኑን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መረዲት የተቻለው አመልካች እና ተጠሪ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ኪራይ ውል ማድረጋቸውን ያላከራከረ ቢሆንም ተጠሪ እንዱከፈለው ዲኝነት የጠየቀበት የገንዖብ መጠን በተመለከተ ግን ክርክር መነሳቱን መዛገቡ ያሳያል። አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው ለውሳኔ መሰረት የሆነውን የሰነድ ማሰረጃ ተጠሪ ክሱ ሲመሰርት አያይዜ ያላቀረበው ከመሆኑ አንፃር በክርክር ሂደት እንዱያቀርብ መፈቀደ ስነ ስርዓታዊ አይደለም በሚል ነው። ከዘህ በተጨማሪ አመልካች ቀሪ ክፍያ አለ የሚባል ቢሆን ስላቱ መሰራት ያለበት ባቀረበው ሰዓት ድምር ሳይሆን ውጤታማ የስራ ሰዓት ግምገማ መሰረት በማድረግ ነው የሚል ክርክር ማቅረቡን መዛገቡ ያመለክታል። ተጠሪ በበኩለ አመልካች ከክሱ በኋላ የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ላይ አስተያየቱን የሰጠ በመሆኑ የመከላከያ መልሱ ለማሻሻል ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ማጣቱ በአግባቡ ስለመሆኑ ቀሪ ክፍያ በተመለከተም በተደረገው ማጣራት ያልተከፈለ ገንዖብ መኖሩን ተረጋግጦ የተሰጠው ውሳኔ ሉነቀፍ አይገባም ብሎል።
በመሰረቱ መብት ለማስከበር ክስ የሚመሰርት ሰው ክሱን ለማስረዲት ይጠቅማል ያለውን ማስረጃ ዓይነት እና ዛርዛር ሁለ መጀመርያ ከሚያቀርበው ክስ ጋር አያይዜ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በእጁ የላለ ማስረጃዎች ካለ በፍርድ ቤት ትእዙዛ ማቅረብ እንዱቻል የሚገኙበት መስርያ ቤት (ስፍራ) ጭምር በመግልጽ ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ137(1) እና 223 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዖት እና መንፈስ ያስገነዛቡናል። የከሳሽ ወገን መጀመሪያ ያላቀረበው ማስረጃ ካለ በልዩ ሁኔታ በቂ ምክንያት መኖሩን በማስረዲት በፍርድ ቤት ፈቃድ ላቀርብ እንደሚችል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ137(2) እና 256 ጥምር ንባብ ያመለክታል። በልላ በኩል ፍርድ ቤት ማስረጃ በማስቀረብ የሚመረምርበት ስርአት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ145 እና 256 ተደንግጓል። በተያዖው ጉዲይ ተጠሪ ክስ በሚሰማበት ወቅት ያልቀረበ ሰነድ መኖሩን በመግለጽ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ማግኘቱን መዛገቡ ያሳያል። ተጠሪ ማስረጃ እንዱያቀረብ ከተፈቀደለት በኋላ አመልካች የመከላከያ መልስ ለማሻሻል ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉን መዛገቡ ያሳያል። ተጠሪ ክሱን ለማስረዲት ይጠቅመኛል ያለውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ክስ በመሰረተበት ቀን ያላቀረበበት በቂና ህጋዊ ምክንያት ምን እንደሆነ የስር ፍርድ ቤት በ3/8/2006 በሰጠው ትእዙዛ ግልጽ አላደረገም። ተጠሪ ክሱን ለማስረዲት በመጀመሪያ ቀጠሮ ያላቀረበው ማስረጃ በሂደት እንዱያቀርብ ከተፈቀደ አመልካችም የቀረበውን ማስረጃ አግባብነት እና ተአማኒነት ለመቃወም እንዱችል የመከላከያ መልሱ እንዱያሻሽል ሉፈቀድ ይገባ ነበር።
ምክንያቱም መጀመሪያ ያልቀረበው ማስረጃ ለውሳኔው መሰረት ከተደረገ አመልካችም ይህ ማስረጃ ተገቢ አለመሆኑን ለማሳየት ወይም ለመከላከል እኩል የመደመጥ መብት ሉነፈግ አይገባም። የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርክሩን የመራበት አግባብ በህጉ የተዖረጋውን ጥብቅ የክርክር አመራር ስርዓት የተከተለ ባይሆንም የተጠሪ ማስረጃ እንዱቀረብ በፈቀደበት ሁኔታ አመልካችም የበኩለን ማስተባብያ ለማቅረብ ይችል ዖንድ የመልስ ማሻሻል ጥያቄ ተቀባይነት ሉያገኝ ይገባል። አመልካች በተሟላ መልስ ባልተከራከረበት ሁኔታ ተጠሪ ባቀረበው ሰነድ ላይ አስተያየቱን በጽሁፍ ብቻ ያቅርብ ተብል የመደመጥ መብቱ ሉታለፍ አይገባም። ምክንያቱም ተጠሪ ያቀረበው አዱስ ማስረጃ የክርክሩ ይዖት እና ጭብጥ ሉለውጥ የሚችል በመሆኑ ነው።
የስር ፍርድ ቤት አመልካች በ23/10/2006 ዓ.ም ያቀረበው የመከላከያ መልስ የማሻሻል መሰረታዊ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ የፋዳራል ህገ መንግስት አንቀጽ 37 እና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ91 ያላገናዖበ ነው ብለናል በመሆኑም አመልካች የተሟላ ክርክር ለማቅረብ እንዱችል የመከላከያ መልሱ እንዱያሻሽል ሉፈቀድለት ይገባል ብለናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ138392 በ26/06/2010 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በይ/ብ/ይ/መ/ቁ156988 በ30/09/2010ዓ.ም የሰጠው ትእዙዛ ሽረናል።
አመልካች ያቀረበው የመከላከያ መልስ የማሻሻያ ጥያቄ ውድቅ መደረጉ በህጉ አግባብ አይደለም ብለናል።
አመልካች በተሟላ ሁኔታ ለመከራከር እንዱያስችለው መልሱን እንዱያሻሽል አዖናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተዖጋው የመ/ቁ138392 በማንቀሳቀስ አመልካች መልሱን ካሻሻለ በኋላ በፍርድ ይዖቱ እና መንፈስ እንዱጣሩ የተለዩ ነጥቦች መሰረት በማድረግ ክፍያ የተጠየቀው በውለ መሰረት ነው ወይስ አይደለም? የሚል መሰረታዊ ጭብጥ እና ተያያዥ ነጥቦች በግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ በማጣራት እንዱሁም አግባብነት ካለው ተቋም ተገቢ ነው ያለውን ማስረሰጃ በማሰባሰብ ወይም ባለሞያ በመመደብ በማጣራት ተገቢ ውሳኔ ይሰጥ ዖንድ ጉዲዩ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ343(1) በሚያዖው መሰረት መልሰንለታል።
የዘህ ፍርድ ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ።
መዛገቡ ሲሰራ ቆይቶ በ6/10/2011 ዓ.ም ተነበበ።
መዛገቡ ተዖጋ ወደ መዛገብ ቤት ተመለሰ።
No topics extracted.